No summary available.
ሚያዝያ 19 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አነዚር ኢብራሂም - አልቀረቡም ተጠሪ፡- የቤ/ጉ/ክ/ሥ/ፀ/ሙስና ኮሚሽን ዐ/ሕግ አቶ አብዮት አልቦሮ ቀረቡ መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ሲሆን መርምረን የሚከተለውን ትዕዛዝ ሰጥተናል።
አመልካች በሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪው ደግሞ ከሳሽ ነበር። የሥር ከሳሽም በአመልካች (በሥር ተከሳሽ) ሁለት ክሶችን አቅርቧል። 1ኛ ክስ ተከሳሹ ቀደም ሲል በክልለ የሥራ አመራር ተቋም ሀላፉ የነበረ ሲሆን ከዚሁ ከተጠቀሰው ተቋም ወደ ክልለ አቅም ግንባታ ቢሮ ከተዛወረ በኋላ የሥራ አመራር ተቋም በጀት በሆነው በስልክ መስመር 4789 በህገ ወጥ መንገድ ተጠቅሞ ብር 4,674.32 የመንግሥት ገንዘብ ወጪ ሆኖ እንዱባክን በማድረጉ በሥልጣን ያለአግባብ በመገልገል በወ/ህ/ቁ 407/1ሐ/ የተመለከተውን ተላልፎል የሚል ሲሆን፤ 2ኛ ክስ ደግሞ ተከሳሹ በሥራ አመራር ተቋም ሥራ አስኪያጅ ሆኖ በሚሰራበት ወቅት በሥራ አጋጣሚ በትውስት በእጁ የገቡትን የመንግስት ንብረቶች እንዱመልስ በተደጋጋሚ ተጠይቆ ጠፍተውብኛል በማለት ያለአግባብ በንብረቶቹ ለመጠቀም አስቦ የሰወራቸው በመሆኑ በወ/ህ/ቁ/አ 413 (1ለ) የተደነገገውን የመሰወርና የወውሰድ ወንጀል ፈጽሟል የሚል ነው።
ተከሳሹም ፍ/ቤት ቀርቦ የእምነት ክህደት ቃለን ሲጠየቅ ወንጀለን አለመፈፀሙንና ጥፊተኛ አለመሆኑን ክድ በመከራከሩ የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት የከሳሽ ማስረጃዎችን ከሰማ በኋላ በወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ 141 መሰረት ተከሳሹን በብይን በነፃ አሰናብቷል።
በተከሣሹ በነፃ መለቀቅ ቅር የተሰኘው የሥር ከሳሽም ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ይግባኝ ሰሚው ችልት በወ/ይ/መ/ በቀን 24/02/2002 ዓ.ም በዋለው ችልት በአብላጫ ድምፅ በሰጠው ትዕዛዝ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 195(1) መሰረት የይግባኝ ባዩን ይግባኝ ባለመቀበል አሰናብቷል። ይሁን እንጂ አነስተኛው ድምፅ መልስ ሰጪው በሥር ፍ/ቤት ሳይከላከል በነፃ መሰናበቱ ያለአግባብ በመሆኑ መከላከል አለበት ብሎል።
የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የወንጀል ይግባኝ ሰሚው ችልት በአብላጫ ድምጽ የከፍተኛውን ፍ/ቤት ብይን በማጽናቱ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት የአሁኑ ተጠሪ ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታውን ያቀረበ ሲሆን ችልቱም በመ/ በቀን 19/11/2002 ዓ.ም በዋለው ችልት በአብላጫ ድምፅ በሰጠው ፍርድ ከሳሽ (ይግባኝ ባይ) በሁለቱም ክሶች አስረድቶ እያለ አልተመሰከረበትም በሚል በነፃ መለቀቁ ያለአግባብ ነው በማለት በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 142(1) መሰረት እንዱከላከል ወስኗል። የሰበር ችልት አነስተኛው ድምጽ ደግሞ ተጠሪው (የሥር ተከሳሽ) ሉከላከል አይገባም ብሎል።
በክልለ ሰበር ሰሚው ችልት ፍርድ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል ያለው የአሁን አመልካችም ሐምል 30 ቀን 2002 ዓ.ም በተጻፈ ቅሬታ በቀረቡብኝ ሁለት ክሶች የተጠሪ ምስክሮች የወንጀለን ድርጊት አለመፈፀሜን በሚገባ በማረጋገጥ መስክረው እያለ የክልለ ሰበር ሰሚው ችልት በአብላጫ ድምጽ በሰጠው ፍርድ እንዱከላከል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ስህተቱ ታርሞ የአብላጫው ድምጽ ፍርድ ተሽሮና አነስተኛው ድምጽ መካላከል የለበትም ያለው ፀንቶልኝ በነፃ እንድሰናበት ይወሰንልኝ ብሎል።
ለዚህ የሰበር ቅሬታ ተጠሪው በቁጥር 01/2003 በቀን 02/05/2003 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት የለውም። ምክንያቱም አንድ ተከሳሽ ወይም ይግባኝ ባይ ወይም የሰበር አቤቱታ አቅራቢ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 184(መ) እና 195 መሰረት የጥፊተኛነት ወይም የቅጣት ውሣኔ ባልተሰጠበት ይግባኝም ሆነ የሰበር አቤቱታ ማቅረብ አይችልም። አመልካች የሚያነሣቸው ነጥቦች በመከላከያ ማስረጃዎች የሚረጋገጡ እንጂ በሰበር አቤቱታው ባቀረበው ሁኔታ የሚታመንበትና ተቀባይነት የሚያገኝበት አይደለም። በሁለቱም ክሶች ተጠሪ ባቀረባቸው የሰውና የጽሁፍ ማስረጃዎች ከተገቢው ጥርጣሬ በላይ የተመሰከረበት በመሆኑ የሥር ሰበር ሰሚው ችልት በአብላጫ ድምጽ የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያልተፈፀመበት ነው በማለት ተከራክሯል።
አመልካች ተጠሪው ለሰበር ችልት ለሰጠው መልስ የመልስ መልስ በማቅረብ ክርክሩን አጠናክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከዚህ በላይ እንደተጠቀሰው የቀረበ ሲሆን እኛም ይህ ሰበር ችልት ጉዲዩን የመመርመር ሥልጣን አለው ወይስ የለውም የሚለውን ጭብጥ ይዘን እንደሚከተለው መርምረናል።
ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10(2) ሆነ በኢ/ፋ/ዱ/ሪ/ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3) ሀ መሰረት የፋ/ጠ/ፍ/ቤት መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበትን ማንኛውንም የመጨረሻ ውሳኔ ለማረም በሰበር ችልት የማየት ሥልጣን ያለው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህ በተያዘው ጉዲይ ግን በሥር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚው ችልት አመልካች የቀረቡበትን ክሶች ይከላከል መባለ በጉዲዩ የመጨረሻ ውሳኔ ተሰጥቶበታል የሚያሰኝ አይደለም።
ስለሆነም የሰበር አቤቱታው ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ለመቅረብ ብቁ ባለመሆኑ ውድቅ አድርገን መዝገቡን ዘግተን ወደ መዝገብ ቤት ተመላሽ እንዱሆን ብለናል።
No topics extracted.