No summary available.
መጋቢት 06 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጏስ ወለደ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ኤሉያስ ዱጋ ጉዲይ የውብነሽ ማንደፍሮ ተጠሪ፡- የፋዳራል ዐቃቤ ሕግ የቀረበ የለም።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ወንጀል ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ አሻሽል በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። ክሱም በሁለት ምድብ የተከፈለ ሆኖ የ1ኛው ክስ ይዘትም ፡አመልካች በ1996 ዓ/ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 543/3/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በአሽከርካሪነት ሙያው የላላውን ሕይወትና ደህንነት የመጠበቅ ግዳታ እያለበት ጥር 2ዐ ቀን 2000 ዓ/ም ከቀኑ 11፡20 ሲሆን የሰላዲ ቅጥሩ 3-41980 አ.አ መኪና ይዞ ከቦላ አየር መንገድ ወደ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን አቅጣጫ እያሽከረከረ በቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 01 ልዩ ቦታው ቦላ ሚካኤል ከተባለ ቦታ ሲደርስ ግልፅ የሆነ ደንብ ተላልፍ ሰው በማይጫንበት አይሱዚ የጭነት መኪና የእቃ መጫኛ ላይ ተጭኖ የነበረውን ጋሻው ተሾመ የተባለውን ሰው ከመኪናው ላይ ጥል ሕይወቱ እንዱያልፍ በማድረጉ በቸልተኝነት የሰው መግደል ወንጀል ፈጽሟል የሚል ሲሆን 2ኛው ክስ ደግሞ ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ ከመኪናው ወድቆ ጉዲት የደረሰበትን ሰው አፊጣኝ ህክምና እንዱያገኝ ሳያደርግ ከወደቀበት ጥልት በመሄድ በአደጋ ላይ ያለን ሰው ባለመርዲቱ በ1996 ዓ/ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 575(2(ሀ)) ስር የተመለከተውን ተለልፎል የሚል ነው። የአሁኑ አመልካችም የክስ ማመልከቻው ደርሶት ክሱን እንዱረዲው ከተደረገ በኋላ ስለእምነት ክህደት ቃል ሲጠየቅ በክሱ ላይ ተቃውሞ የላለው መሆኑን ገልፆ የድርጊቱን አፈፃፀም በተመለከተ ግን የክህደት ቃለን ሰጥቷል። ዐቃቤ ሕግ በበኩለ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቦ አሰምቷል። ከዚህም በሁዋላ አመልካች የወንጀል ድርጊቶችን ስለመፈፀሙ አቃቤ ሕግ በማስረጃዎቹ ያስረዲበት መሆኑ በሥር ፍርድ ቤት ታምኖበት ይህንኑ እንዱያስተባብል ዕድል ተሰጥቶት አመልካች በልላ የመከላከያ ማስረጃ ያሰማ ሲሆን የሥር ፍ/ቤትም ጉዲዩን መርምሮ አመልካች በመከላከያ ማስረጃዎቹ የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን ያላስተባበለ መሆኑን በመጥቀስ በአቃቤ ሕግ በኩል ተጠቅሰው በቀረቡት ሁለቱም ድንጋጌዎች ስር ጥፊተኛ አድርጎ ወስኗል። ቅጣቱን በተመለከተም በ1ኛው ክስ በስድስት አመት እና በብር 10,000.00 በሁለተኛው ደግሞ በስድስት ወር ጽኑ እስራትና በብር 1000 በድምሩ በስድስት አመት ከስድስት ወር ፅኑ እስራትና በብር 11,000.00 (አስራ አንድ ሺህ ብር) አመልካች እንዱቀጣ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኘ ሰሚ ችልት ቢያቀርብም ይግባኙ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195/1/ መሰረት ተሰርዞበታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ሚያዚያ 29 ቀን 2002 ዓ/ም በተጻፈ አምስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፤ አመልካች የወንጀል ድርጊቶቹን ስለመፈፀሙ ዐቃቤ ሕግ በሕጉ አግባብ አላስረዲም፣ የመከላከያ ማስረጃው ውድቅ የተደረገው ያላግባብ ነው በማለት የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ እንዱሰረዝ ወይም ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ድንጋጌ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 543/2/ ነው ተብል የቅጣት ውሳኔው አመልካች የታሰረበትን ጊዜ በቂ በማድረግ እንዱወሰን ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች ጥፊተኛ ተብል መቀጣቱ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ የጽሐፍ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም አመልካች በ1ኛው ክስ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 543/3/ ስር ጥፊተኛ ተብል መቀጣቱ ባግበቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ በጭብጥነት የሚታይ ሆኖ አግኝቶታል። ይህንኑ ጭብጥ ምላሽ ከመስጠታችን በፉት ግን የአመልካች ጠበቃ አመልካች የወንጀል ድርጊቱን ፈፅሟል ተብል በስር ፍርድ ቤቶች የተደረሰው ድምዲሜ ከማስረጃ አረዲድና አፈፃፀም አንፃር ስህተት ያለበት ነው በማለት ያቀረቡትን ቅሬታ ከዚህ ሰበር ችልት ሥልጣን አንፃር ያለውን ተገቢነት ተመልክተናል። እንደሚታወቀው ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በኢ.ፋዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 1ዐ መሰረት የተሰጠው ስልጣን በማናቸው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖሩ ሲረጋገጥ ይህንኑ ማረም ነው። ከዚህ መገንዘብ የሚቻለውም የማስረጃ ምዘና ጉዲይ በሰበር ችልቱ ስልጣን ስር የማይወድቅ መሆኑን ነው። በተያዘው ጉዲይ የአመልካች ጠበቃ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የማስረጃ አረዲድና አፈፃጸም ግድፈት ተፈፅሟል፣ ይህም የወንጀል ሕጉን አንቀፅ 23/4/ የሚፃረር ነው በማለት በሰበር ማመልከቻው ላይ የዘረዘሩ ቢሆንም በዚህ ረገድ የቀረበው የቅሬታው አጠቃላይ ይዘት ሲታይ ግን የማስረጃ ምዘናን ጉዲይ የሚመለከት በመሆኑ በዚህ ሰበር ችልት ላታይ የሚገባው ሆኖ አላግኘነውም። በመሆኑም በዚህ ረገድ የቀረበው ቅሬታ የመሰረታዊ ሕግ ስህተት መመዘኛን የሚያሟላ ባለመሆኑ አልፈነዋል።
ወደዋናው ጭብጥ ስንመለስ አመልካች በ1ኛው ክስ ጥፊተኛ የተባለው እቃ በሚጫንበት መኪና ሰው ጭኖ ሲሄድ ሰው ውድቆ እንዱሞት አድርጓል፣ ይህም በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 543(3) ስር የተመለከተውን የወንጀል ማቋቋሚያ ነጥቦችን የሚያሟላ ነው በሚል ነው።
በሰበር ችልት ከላይ የተጠቀሰው አጠቃላይ የክርክሩ ሂደት አግባብ ካላቸው የወንጀል ሕግ ድንጋጌ እና የአመልካች ጠበቃና ተጠሪ ለዚህ ችልት በጽሐፍ ካቀረቡት ክርክር እንዱሁም የስር ፍርድ ቤትን ዋና መዝገብ በማስቀረብ ጉዲዩን ከሕጉ ጋር በማገናዘብ ተመልክቷል። በበታች ፍርድ ቤቶች ከተረጋገጠው ፍሬ ነገርና ከተወሰነው ውሣኔ አንፃርም አመልካችን በወንጀል ጥፊተኛ ለማለት በወንጀል ሕግ አንቀፅ 543/3/ የተጠቀሱት መስፈርቶች ተሟልተዋል? ወይስ አልተሟለም?
የሚለውን ነጥብ አጣርቷል። አመልካቹ በቸልተኝነት ሰው መግደል ወንጀል ፈፅሟል ተብል የተቀጣ በመሆኑ በሕጉ ቸልተኝነት የሚያቋቁሙ መስፈርቶች መሟላት አለመሟላታቸውን ተመልክቷል። ይህ ችልት በዋናነት የመረመረው የሕግ ነጥቡን ብቻ ቢሆንም የሕጉን አግባብነት በትክክል ለመመዘን በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች በቅደሚያ ማስቀመጥ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
ጉዲዩ በሥር ፍ/ቤት ሲታይ አመልካች የሰላዲ ቁጥር 3-41980 አ.አ መኪና ይዞ ከቦላ አየር መንገድ ወደ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን አቅጣጫ እያሽከረከረ በቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ ዐ1 ልዩ ቦታው ቦላ ሚካኤል ከተባለ በታ ሲደርስ የእቃ መጫኛ ላይ ተጭኖ የነበረውን ጋሻው ተሾመ የተባለውን ሰው ከመኪናው ላይ ወድቆ ሕይወቱ እንዱያልፍ ማድረጉ በክሱ ተገለጿል። ይሁን እንጂ መኪናው የእቃ መጫኛ ሆኖ እያለ ሟችን አመልካች ያሳፈረው ስለመሆኑ በአቃቤ ሕግ ማስረጃ ስለመነገሩ የስር ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ፍሬ ነገር የለም። በልላ አገላለጽ ሟችን አመልካች አሳፍሮት ሲጓዝ እንደነበር የሚያሳይ የፍሬ ነገር ድምዲሜ የለም። ይህ በፍርደ ሂደት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ሲሆን አመልካች ጥፊተኛ የተባለበትን ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ደግሞ ከዚህ ቀጥል እንመለከታለን።
በመሰረቱ አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለው ወንጀለን የሚያቋቁሙት ሕጋዊ፣ ግዙፊዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ መሆኑን በአዋጅ ቁጥር 414/1996 የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23/2/ በግልፅ ተደንግጓል። እንግዱህ አንድን ድርጊት ወንጀል ነው ብል ለመወሰን ሕጋዊ፣ ግዙፊዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች ተጣምረው መገኘት የግድ ይላል። ሕጋዊ ፍሬ ነገሮች የሚባለት ደግሞ ለጉዲዩ አግባብነት አለው ተብል የተጠቀሰውን ድንጋጌ ለማቋቋም ሙለ በሙለ መሟላት ያለባቸው ነጥቦች ሲሆን ግዙፊዊና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች የሚባለትን ደግሞ እንደየቅደምተከተላቸው ከድርጊት ማድረግ ወይም አለማድረግና ከሐሳብ ክፍል ጋር በሕጉ የተመለከቱትን ሁኔታዎች የሚመለከቱ ናቸው።
በተያዘው ጉዲይ ከላይ እንደተገለፀው አመልካች ሟች በመኪና ግጭት እንዱሞት ማድረጉ በፍሬ ነገር ደረጃ አመልካችን ሉያስጠይቅ የሚችለው በየትኛው ድንጋጌ ነው? የሚለው ነው።
አመልካቹ በዓቃቤ ሕግ ክስ የመሰረተበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 543/3/“ን“ በመተላለፍ ጋሻው ተሾመን ገድሎል በማለት ነው። በዚህ የሕግ ድንጋጌ አንድ ሰው ተጠያቂነት የሚከተልበት የላላ ሰውን ሕይወት ፣ጤንነት ወይም ደኀንነት የመጠበቅ የሙያ ወይም ላላ ግዳታ ያለበት እንደ ሕክሙና ባለሙያ ወይም አሽከርካሪ ያለ ሰው ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎችን የገደለ፣ ወይም ወንጀለን የፈፀመው ግልፅ የሆነ ደንብ /መመሪያን/ ተላልፍ እንደሆነ ወይም የሚያሰክሩ ወይም የሚያፈዙ ንጥረ ነገሮችን ወይም መጠጦችን በመውሰደ እራሱን ከኃላፉነት ነጻ በሚየወጣ ሁኔታ ውስጥ ካስገባ በኋላ በቸልተኝነት ሰው የገደለ እንደሆነ ስለመሆኑ በሕጉ ተመልክቷል።
የወንጀለ ማቋቋሚያ ነጥቦች ከላይ የተመለከቱት ሲሆኑ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች የተጠቀሰውን ሕግ የሚያቋቁሙ መሆን አለመሆናቸው ለማረጋገጥ ሕጉ ቸልተኝነት አለ የሚለው ምን ምን ሁኔታዎች ሲሟለ እንደሆነ መመልከቱ ተገቢነት ይኖረዋል።
በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 57 በግልፅ እንደሰፈረው ‛ለድርጊቱ ኃላፉ ላሆን የሚገባው ሰው አስቦ ወይም በቸልተኝነት አንድ ወንጀል ካላደረገ በቀር በወንጀል ጥፊተኛ አይሆንም’’ በአንፃሩ አንድ ሰው ‛የፈፀመው ድርጊት በሕግ የሚያስቀጣ ቢሆንም ምንም ጥፊት ሳያደርግ ወይም ከአቅም በላይ በሆነ ኃይል ምክንያት ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ ነገር የተፈፀመ ወይም የደረሰ ሆኖ ሲገኝ በወንጀል ሕግ ሉፈረድበት አይገባውም በማለት የወንጀል ሕጉ አንቀፅ 57/2/ ይደነግጋል። ከዚህ የሕጉ አጠቃላይ ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው በአንድ ድርጊት ምክንያት አንድን ሰው በወንጀል ጥፊተኛ ነው ለማለት ከሳሽ የሆነው ዓቃቤ ሕግ ድርጊቱ የተፈፀመው ሆነ ተብል ወይም በቸልተኝነት መሆኑን ማስረዲት የሚጠበቅበት መሆኑን ነው። ድርጊቱ ሆን ተብል ወይም በቸልተኝነት የተፈፀመ መሆኑ ማስረጃ ካላቀረበ ወይም ድርጊቱ ከአቅም በላይ ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ የተፈፀመ መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ በተከሣሽ በኩል ከቀረበ የተከሰሰውን ሰው በወንጀል ሕግ ጥፊተኛ ብል መፍረድ ከሕጉ መንፈስ ውጪ ነው። በወንጀል የተከሰሰ ሰው ቸልተኛ ነበር? ወይስ አልበረም? የሚለው ጥያቄ በወንጀል ሕጉ በአንቀፅ 59 የሰፈረውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ የሚወሰን ነው። የዚሁ አንቀፅ ንዐስ አንቀጽ አንድ አሁን ለተያዘው ጉዲይ ቀጥተኛ አግባብነት ያለው በመሆኑም የሕጉን ይዘት እንዲለ ማስቀመጡ ጠቃሚ ነው። ይኸው፡ማንም ሰው በቸልተኝነት የወንጀል ተግባር አድርጓል የሚባለው፡ሀ) ድርጊቱ በወንጀል ሕግ የሚያስቀጣ ውጤት ሉያስከትል እንደሚችል እያወቀ አይደርስም በሚል ግምት ወይም ባለመማዛዘን፣ ወይም ለ) ድርጊቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ውጤት ሉያስከትል እንደሚችል ማወቅ እያለበት ወይም እያቻለ ባለመገመት ወይም ባለማሰብ ድርጊቱን የፈፀመ እንደሆነ ነው።
በዚህ ድንጋጌ መሰረት አንድ ሰው በቸልተኝነት ወንጀል ፈፅሟል የሚባለው ውጤቱን እያወቀ ውጤቱ አይደርስም ከሚል መነሻ ድርጊቱን የፈፀመ እንደሆነ ወይም ደግሞ የወንጀል ውጤት የሚያስከትል መሆኑን ባያውቅም ውጤቱን ማወቅ ነበረበት ወይም ጥረት ቢያደርግ ውጤቱን ማወቅ ይችል ነበር ማለት ሲቻል ነው። በመሆኑም ቸልተኝነት አለ ለማለት ሕጉ የሚጠቀምበት ዋነኛ መስፈርት የተከሰሰው ሰው በድርጉቱና በውጠቱ መካከል ያለውን ግንኙነት አስመልክቶ ያለው ወይም ሉኖረው የሚገባው ግንዛቤ ነው። ድርጊቱን የፈፀመው ሰው የነበረው ዕውቀትና ግንዛቤ ወይም ሉኖረው የሚባው ዕውቀትና ግንዛቤ የሚመዘነው የሰውዬው ዕድሜ፣ ያለው የኑሮ ልምድ ፣ የትምህርት ደረጃው፣ ሥራውና የማህበራዊ ኑሮ ደረጃውን ግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነም የሕጉ አንቀፅ 59/1/ ይደነግጋል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች የሚከራከረው ሟችን ለእቃ ጭነት በሚያገለግለው መኪና እያወቀ ያልጫነው መሆኑንና ተሳፍሮ ያለ መሆኑንም ማወቅ ይችል የነበረ ስለመሆኑ አቃቤ በፍሬ ነገር ደረጃ ያላረጋገጠው መሆኑን በመጥቀስ ሲሆን ይህ ያለመረጋገጡ ደግሞ ደንብ ቁጥር 279/1956 አንቀጽ 46/1/ ስር የተመለከተውን ጥሷል ለማለት አያስችልም በማለት ነው።
ይሁን እንጂ ሟች አመልካች ሲያሽከረክር በነበረው የአይሱዚ መኪና ተገጭቶ ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ጉዲይ ሲሆን ይህ ድርጊት አመልካችን በወንጀል ሕግ አንቀጽ 543/3/ መሰረት ሉያስጠይቅ የሚችለው በአሽከርካሪነት ስራው ማድረግ የነበረበትን ጥንቃቄ ሳያደርግ ቀርቶ በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 59/1/ የተገለፀውን ያሟላና የትራፉክ ደንቡን መጣሱ የተረጋገጠ የሆነ እንደሆነ ነው።
በመሆኑንም በክርክሩ ሂደት አመልካች ሟችን በአይሱዚ መኪና በአንቀጽ 543/3/ ሥር ስለቸልተኝነት የተመለከተውን መመዘኛ በሚያሟላ መልኩ የጫነው መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ አመልካች በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 543/3/ ሥር ጥፊተኛ ልባል የሚችልበትን የሕግ አግባብ አላገኘንም። ይልቁንም በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠው ጉዲይ አመልካች በአሽከርካሪነት ስራው ማድረግ የነበረበትን ጥንቃቄ ሳያደርግ ቆርቶ ሟችን በመግጨት ለሕልፈት የዲረገው መሆኑን ሲሆን ይህም በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 543/2/ ሥር ተጠያቂነት የሚያሰከትል ነው።
ስለሆነም አመልካች በበታች ፍርድ ቤቶች በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 543/3/ ሥር ጥፊተኛ የተባለው ባለተረጋገጠ ፍሬ ነገር በመሆኑ በዚህ ረገድ የተሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስለአገኘን አመልካች ጥፊተኛ የተባለበትን ድንጋጌ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/113/2/ መሰረት በመለወጥ ድርጊቱ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 543/2/ ሥር የሚሸፈንና የሚያስጠይቅ ነው ብለናል።
ላላው አመልካች በሥር ፍርድ ቤቶች ጥፊተኛ የተባለው የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 575/2/ሀ/ ሥር ሲሆን አመልካች በአሽከርካሪነት ሥራው ማድረግ የነበረበትን ጥንቃቄ ሳያደርግ ቀርቶ ሟችን ከገጨ በኋላ እርዲታ ሳያደርግለት መሸሹ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ሥልጣን ባላቸው የሥር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ በመሆኑ በዚህ ረገድ በተሰጠው ውሳኔ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አላገኘንበትም ።
ከላይ እንደተገለጸው በ1ኛ ክስ ላይ አመልካች ጥፊተኛ ልባል የሚገባው ድንገጌ መለወጥ ያለበት መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ከዚሁ ተያይዞ መታየት ያለበት በዚህ ረገድ ሉጣል የሚገባው የቅጣት መጠን ነው። አመልካች ሉቀጣ የሚገባው በዚህ ችልት ጥፊተኛ በተባለበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 543/2/ መሰረት ነው። በዚህ ድንጋጌ ጥፊተኛ የተባለ ሰው ሉቀጣ የሚገባው ከአንድ ዓመት እስከ አምስት ዓመት ሉደረስ በሚችል ቀላል እስራት እና ከሦስት ሺህ እስከ ስድስት ሺህ ብር ሉደርስ በሚችል መቀጮ ነው። ቅጣት ደግሞ ሉጣል የሚገባው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 88/2/ ሥር የተመለከቱትን ነጥቦችን በማመዛዘን ነው። እኛም አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ያስመዘገባቸውን የቅጣት ማቅላያ ምክንያቶች (ሪኮርድ የላለበትና የቤተሰብ አስተዲዲሪ መሆኑን) ከድርጊቱ አፈጻጸምና ከቅጣት ዓላማ እንዱሁም ተደራራቢ ወንጀልች ተፈጽመው ሲገኙ ቅጣት ከሚጣልበት አግባብ (ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 184/1/ለ/ ) ጋር በበገናዘብ ጉዲዩን ተመልክተናል።
በመሆኑም አመልካች በሁለቱም ጉዲዮች ሉቀጣ የሚገባው የእስራት መጠን በጠቅላላው አራት አመት ቀላል እስራት ሆኖ የገንዘብ መቀጮው ደግሞ ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 90 ይዘትና መንፈስ አንጻር ሲታይ በድምሩ ብር 7000.00 (ሰባት ሺህ) ላሆን የሚገባ ሆኖ አግኝተናል። ሲጠቃለልም ከላይ በተመለከቱት ሕጋዊ ምክንያቶች በጉዲዩ ላይ በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ሉሻሻል የሚገበው ሆኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲት 03 ቀን 2003 ዓ/ም ተሰጥቶ በፍደራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ መጋቢት 29 ቀን 2002 ዓ/ም የፀናው ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195(2(ለ-2)) መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካች በ1996 ዓ/ም በወጣው የወንጀል ህግ አንቀጽ 543(2) እና 575(2(ሀ)) ሥር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች የተላለፈ ጥፊተኛ ነው በማለት በጉዲዩ ላይ የታሰረው ጊዜ የሚታሰብለት ሆኖ በጠቅላላው በአራት አመት ቀላል እስራትና በብር 7000.00 (ሰባት ሺህ) እንዱቀጣ በማለት ወስነናል።
በዚህ ችልት ተሻሽል በተወሰነው ውሳኔ መሰረት ቅጣቱን ተከታትል እንዱያስፈጽም ለማረሚያ ቤቱ ትዕዛዝ ይድረሰው ብለናል። መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
እ/ብ
No topics extracted.