No summary available.
ሐምል 29 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፉሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ይግባኝ ችልት የሰጡት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። የክርክሩ መነሻ ተጠሪ አመልካቾች የወንጀል ህግ አንቀጽ 34 ንዐስ አንቀጽ 15 የአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 26 ንዐስ አንቀጽ 2/ሀ/ እና አንቀጽ 41 ንዐስ አንቀጽ 1ን በመተላለፍ አምድሁን ጠቅላላ ንግድ ኃላፉነቱ የግል ማህበር ብቸኛ አስመጭና አከፊፊይ የሆነበትንና ኮሪያ አገር ያለው ኦርዮን ኮርፕሬሽን የንግድ ድርጅት የሚጠቀምበትን ‛ORIQN“ የሚል የንግድ ምልክት ያለበትን 639 ካርቶን ማስቲካዎች በአዱስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበላ 16/17 የቤት ቁጥር 479 አከማችቶ የተገኘ በመሆኑ ህጋዊ ጥበቃ የተሰጠውን የንግድ ምልክት በማስመሰል ተጠቃሚውን ለማሳሳት የሚናችል ዕቃ የመያዝና የመሸጥ ወንጀል ፈጽመዋል በማለት ያቀረበው ክስ ነው።
አመልካቾች የወንጀል ተግባር አልፈፀምንም በማለት በመከራከራቸው ተጠሪ ‛ORION“ የሚለው የንግድ ምልክት በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት የተመዘገበ መሆኑና አምድሁን ጠቅላላ ንግድ ሀላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ብቸኛ አስመጭና አከፊፊይ መሆኑንና አመልካቾች ይዘው የተገኙት ማስቲካ ‛ORION“ ከሚለው ማስቲካ ጋር ተመሳሳይነት ያለው መሆኑን ያስረደልኛል በማለት የጽሐፍና የሰው ማስረጃ አቅርቧል። አመልካቾች የመከላከያ ማስረጃ እንዱያቀርብ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቶ አመልካቾች ORIQN የሚለው ማስቲካ ህብረተሰቡ ለይቶ የሚያውቀውና መሳሳትና መሳከር የማይፈጥር መሆኑን ያስረደልናል በማለት የሰው ምስክሮች አቅርበው አስመስክረዋል እንደዚሁም ማስቲካውን ከቻይና አገር በባንክ በኩል በተከፈተ ላተር ኦፍ ክሬዱት ዋጋ ከፍለው ማስገባታቸውና የጉምሩክ ቀረጥና ፍርማሉቲ አሟልተው ወደ አገር ውስጥ ያስገቡ መሆኑን ያሳያለ ያለቸውን የሰነድ ማስረጃዎችን በመከላከያ ማስረጃነት አቅርበዋል። የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ ከመረመረና ከመከሩ በኋላ አመልካቾች በአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 41 ንጉስ አንቀጽ 1ን በመተላለፍ ህጋዊ ጥበቃ ባለው የንግድ ምልክት ላይ ወንጀል የፈፀሙ ናቸው በማለት የጥፊተኝነት ውሣኔ ሰጥቷል። የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ከሰማ በኋላ አንደኛ አመልካች በብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ መቀጮ እንዱቀጣ ወስኗል።
ሁለተኛው አመልካች በአምስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጣ የወሰነ ሲሆን አመልካቾች ይዘው የተገኙት 639 ካርቶን ማስቲካና 23,000 ፕኬት ማስቲካ ወደ ገበያ እንዲይሰራጩ ይወገደ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካቾች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን የጥፊተኝነት ውሣኔ አጽንቶታል። አመልካቾች ሰኔ 7 ቀን 2003 ዓ.ም በፃፈው የሰበር አቤቱታ የንግድ ምልክቱ አላግባብ ጥቅም ላይ ውልበታል የተባለው ድርጅትና በአገር ውስጥ ያለው ብቸኛ አከፊፊይ ‛ORION“ የሚለውን የንግድ ምልክት በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ያስመዘገቡት አዋጅ ቁጥር 501/98 ከመውጣቱ በፉት ነው። ይህንን የንግድ ምልክት አዋጅ ቁጥር 501/98 ወጥቶ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ በአዋጅ አንቀጽ 46 ንዐስ አንቀጽ 1 በሚደነግገው መሰረት ከአሥራ ስምንት ወራት ውስጥ አላስመዘገቡም። የግል ተበዲይ በአዋጅ በተደነገገው መሰረት ሳያስመዘግቡ ለአራት ዓመት ያህል ከቆዩ በኋላ ህጋዊ ጥበቃ የተሰጠው የንግድ ምልክታችንን አላግባብ ተጠቅመዋል በማለት ክስ ለማቅረብ የሚችለበት ሁኔታ የለው። ስለሆነም ‛ORION“ የሚለው የንግድ ምልክት አዋጅ ቁጥር 501/98 ከመውጣቱ በፉት መመዝገቡ የአዋጁን አንቀጽ 46 ንዐስ አንቀጽ 1፣ አንቀጽ 48 እና አንቀጽ 29 አንቀጽ 2 መሥፈርት የሚያሟላና ሶስተኛ ወገኖች በሃላፉነት የማያስጠይቅና ውጤት የላለው ሆኖ እያለ በወንጀል ጥፊተኛ ተብለን መቀጣታችን መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። በልላ በኩል አመልካቾች ለማጭበርበርና ተጠቃሚውን ለማሳሳት ሆነ ብለንና አስበን የፈፀምነው ተግባር የለም። ስለዚህ ማስቲካ ከቻይና አገር በማስገባታችን በወንጀል የሚያስጠይቀን አይደለም እንጅ በወንጀል የምንጠየቅ ከሆነም በቸልተኝነት መሆን ሲገባው ሆነ ብለንና አስበን እንደፈፀምን ተቆጥሮ ጥፊተኛ ተብለን መቀጣታችን መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልን በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪ ሐምል 15 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በሰጠው መልስ ORION የሚለው የንግድ ምልክት የተመዘገበና ህጋዊ ጥበቃ የተሰጠው መሆኑን በአዋጅ ቁጥር 320/95 ሥልጣን የተሰጠው የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት በጽሐፍ አረጋግጧል። አመልካቾች ተጠቃሚውን የሚያሳስትና የማይሳክር እንደዚሁም በአገር ውስጥ የተመዘገበና ህጋዊ ጥበቃ የላለው QRIQN የሚል የንግድ ምልክት የለው ማስቲካ በአገር ውስጥ ሚያሰራው ተገኝተዋል። አመልካቾች QRIQN የሚለውን ማስቲካ ከቻይና አገር በባንክ በተከፈተ ላተር ኦፍ ክሬዱት የውጭ ምንዛሬ ተፈቅድላቸው ከፍለው ማስመጣታቸውና ማስቲካውን የጉምሩክ ቀረጥና ፍርማሉቲ አሟልተው ወደ አገር ውስጥ ማስገባታቸው አድራጏታቸው ወንጀል መሆኑን የሚያስቀረው ባለመሆኑ የአመልካቾች ክርክር የህግ መሰረት የለውም። የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የጽሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካቾች በአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 42 ንዐስ አንቀጽ 1ን በመተላለፍ ህጋዊ ጥበቃ በተሰጠው የንግድ ምልክት ላይ ወንጀል የፈፀሙ ጥፊተኛ ናቸው በማለት የሰጡት የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል። ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን አንደኛ አመልካችና ሁለተኛ አመልካች በወንጀል ተጠያቂ የሚሆኑባቸው የወንጀል ህግ መርሆዎች የየራሳቸው ልዩ ባህሪያት ያላቸው በመሆኑ በዚሁ አንፃር ጉዲዩን ማየቱ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
አዋጅ ቁጥር 501/98 በህግ ወለድ ሰዎች ላይ የወንጀል ሀላፉነትና ተጠያቂነትን የሚደነግግ የህግ ማዕቀፍ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ አከራካሪ በመሆኑ በመጀመሪያ የከፍተኛው ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት በሁለተኛው አመልካች ላይ የሰጡት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ተገቢነትን ማየቱ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። አንድ ሰው ወንጀል ፈጽሟል ተብል ተጠያቂ የሚሆነው የግዙፍ ተግባር የህግና የሃሳብ ሁኔታ ተሟልተው ሲገኙ እንደሆነ በኢ.ፋ.ዳ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 23 ንዐስ አንቀጽ 2 ይደነግጋል። ሁለተኛ አመልካች የተከሰሱትና ጥፊተኛ የተባለት በአዋጅ ቁጥር 501/98 ህጋዊ እውቅናና ጥበቃ የተሰጠውን የንግድ ምልክት የሚጏዲ ተጠቃሚውን የሚያሳስትና የሚያሳክር ተግባር ሆን ብለውና አስበው ፈጽመዋል ተብለው እንደሆነ ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ተገንዝበናል። ሁለተኛውን አመልካች በአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 41 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌን በመተላለፍ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ በመጀመሪያ ‛ORIQN“ የሚል የንግድ ምልክት ያላቸውንና በኮሪያ አገር የሚመረቱ ምርቶች ብቸኛ አስመጭ ነኝ የሚለው ‛አምደሁን ጠቅላላ ንግድ ሃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ‛ORION“ የሚለው የንግድ ምልክት የአዋጅ ቁጥር 501/98 ህጋዊ ጥበቃና እውቅና ለማግኘት የሚያስችለውን የህግ ሁኔታ /ህጋዊ መስፈርት/ ያሟላ ለመሆኑ ተጠሪ በቂ ማስረጃ በማቅረብ የማስረዲት ግዳታና ሃላፉነቱን ተወጥቷል ወይስ አልተወጣም የሚለውን ነጥብ ማየት አስፈላጊ ነው።
ይህንን ነጥብ ለማጣራት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትን መዝገብ አስቀርበናል።
የኢትዮጵያ አአምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ከፃፈው የሰነድ ማስረጃ እንደተረዲነው ጽ/ቤቱ ORION የሚለውን የንግድ ምልክት ለመመዝገብ የቀረበውን አቤቱታ በአዱስ ዘመንና በሄራልድ ጋዜጣ አውጥቶ ተቃዋሚ ባለመቅረቡ የንግድ ምልክቱን መጋቢት 12 ቀን 1998 ዓ.ም በመመዝገብ የምዝገባ ሰርተፉኬት ሰጥቷል። ጽ/ቤቱ በሰጠው የምዝገባ ሰርተፍኬት የንግድ ምልክቱ እስከ መጋቢት 11 ቀን 2004 ዓ.ም ህጋዊ ጥበቃ እንደሚኖረው የሚገልጽ ቢሆንም ORION የሚለው የንግድ ምልክት ከተመዘገበ በኋላ አዋጅ ቁጥር 501/98ን ህግ አውጭው በማወጅ፣ አዋጁ ከሰኔ 3ዐ ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ ውሎል። በአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 46 ንዐስ አንቀጽ 1 ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፉት የተቀመጡ የንግድ ምልክቶች ይህ አዋጅ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በአስራ አምስት ወራት ጊዜ ውስጥ መመዘገብ ይኖርባቸዋል በሚል መንገድ በመደንገድ አዋጁ ከመውጣቱ በፉት የንግድ ምልክት ለኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት አቅርበው በማስመዝገብ የባለሃብትነት ሰርተፉኬት አግኝተው የነበሩ ሰዎች አዋጁ ወጥቶ ሥራ ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባለት አሥራ አምስት ወራት የማስመዝገብ ግዳታና ሃላፉነት እንዲለባቸው ይደነግጋል።
ይህ የአዋጁ ድንጋጌ ፈቃጅነት ያለው የህግ ድንጋጌ ያለመሆኑን ከድንጋጌው አቀራረጽ፣ መንፈስና ዓላማ ለመገንዘብ ይቻላል። በተለይም የአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 46 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ የእንግሉዝኛው ቅጅ ‛Trade marks deposited before the entry into force of this proclamation shall be submitted for registration with in eighteen month beginning from the entry in to force of this proclamation“ በሚል መንገድ የተቀረፀና የተደነገገ መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል። አዋጅ ቁጥር 501/98 ከመውጣቱ በፉት የንግድ ምልክት ያስመዘገበ ማናቸውም ሰው ህግ አውጭው በአዋጁ የሰጠውን ጥበቃና ከለላ ለማግኘትና አዋጁን መሰረት በማድረግ የመብት ጥያቄ ለማቅረብ በመጀመሪያ ህግ አውጭው በአዋጅ ቁጥር 501/98 የደነገጋቸውን አስገዲጅ የህግ ድንጋጌዎች በመፈፀም ህጋዊ ሁኔታዎችን አሟልተው መገኘት አለባቸው። ህግ አውጭው በአዋጅ ቁጥር 501/98 አስገዲጅነት ባለው ሁኔታ የደነገጋቸው ድንጋጌዎች በአዋጁ መሰረት መብታቸው እንዱከበርላቸው የሚጠይቁ የህግ ወይም የተፈጥሮ ሰዎች ብቻ ሳይሆን አዋጁን የማስፈፀም ሥልጣንና ሀላፉነት በተሰጠው የመንግስት አካል ማለትም የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ላይ ገዥነትና አስገዲጅነት ያላቸው ናቸው። ይኸም በመሆኑ የአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 46 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ ጽ/ቤቱ ለግል ተበዲይ ለስድስት ዓመት ህጋዊ ጥበቃ እንዲለው በመግለጽ አዋጁ ከመውጣቱ በፉት ሰቶት በነበረው የምዝገባ ሰርተፍኬት ላይ የበላይነትና ገዥነት ያለውና የግል ተበዲይ የንግድ ምልክቱን አዋጁ ወጥቶ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ በአሥራ ስምንት ወራት ውስጥ እንደገና እንዱያስመዘግብ የሚያስገድድ ድንጋጌ ነው።
በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ የግል ተበዲይ የንግድ ምልክቱን አዋጅ ቁጥር 501/98 ከመውጣቱ በፉት ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ከመጋቢት 12 ቀን 1998 ዓ.ም እስከ መጋቢት 11 ቀን 2004 ዓ.ም የሚያገለግል የምዝገባ ሰርተፍኬት ተሰጥቶት የነበረ መሆኑን የሚያስረደ የሰነድ ማስረጃዎች አቅርቧል። ከዚህ ውጭ ተጠሪ በአዋጁ ቁጥር 501/98 ህጋዊ ጥበቃና ከለላ ለማግኘት ህግ አውጭው በአዋጁ አንቀጽ 46 ንዐስ አንቀጽ 1 የተደነገገውን አስገዲጅ መሥፈርት ያሟላና በአዋጅ ቀጥር 501/98 አንቀጽ 45 እና አንቀጽ 16 የተደነገጉትን ህጋዊ ሥርዓቶች በማሟላት በአስራ ስምንት ወራት ውስጥ የተመዘገበ መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ አላቀረበም። ይኸም በመሆኑ የግል ተበዲይ አምደሁን ጠቅላላ ንግድ ሃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በኢትዮጵያ ግዛት ብቸኛ አስመጭና አከፊፊይ ነኝ የሚለው ‛ORION“ የሚለው የንግድ ምልክት በአዋጅ ቁጥር 501/98 ህጋዊ ጥበቃና ከለላ ለማግኘት ህጋዊ ሁኔታዎችን ያሟላ መሆኑን ተጠሪ በበቂ ማስረጃ አላረጋገጠም። ሁለተኛውን አመልካች በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ አስፈላጊ የሆነው ህጋዊ ሁኔታ ማለትም ከአዋጅ ቁጥር 502/98 በፉት የነበረው ምዝገባና ሰርተፍኬት አዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 46 ንዐስ አንቀጽ 1 በአስገዲጅነት በደነገገው የጊዜ ገደብ ማለትም አዋጁ ወጥቶ ሥራ ላይ መዋል ከጀመረበት ቀን አንስቶ በአስራ ስምንት ወራት ውስጥ የንግድ ምልክቱን ያስመዘገበ መሆኑ በበቂ ማስረጃ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ሶስተኛ ወገኖችን በአዋጅ ቁጥር 501/98 ለንግድ ምልክቱ የተሰጠውን ህጋዊ እውቅና እና ጥበቃ በመተላለፍ የወንጀል ድርጊት ፈጽመዋል ብል ለመክሰስም ሆነ በወንጀል ጥፊተኛ ብል ለመቅጣት አይቻልም። በመሆኑም ሁለተኛ አመልካች በወንጀል ህግ አንቀጽ 23 ንዐስ አንቀጽ 2 በሚደነግገውና ወንጀል ለማቋቋም አስፈላጊ በመሆናቸው ከሚዘረዝራቸው አስፈላጊ ጉዲዮች ሁለተኛ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 46 ንዐስ አንቀጽ 1 የተደነገገውን አስገዲጅ መስፈርት ያሟላና ህጋዊ ጥበቃ የተሰጠው የንግድ ምልክትን የሚጥስ ግዙፍ ተግባር የፈፀመ መሆኑን ተጠሪ የማስረዲት ሸክሙን ሳይወጣ የግል ተበዲይ አዋጅ ቁጥር 501/98 ከመውጣቱ በፉት የንግድ ምልክቱ መመዝገቡን ብቻ በመመልከት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ በዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 1 የተደነገገውን አስገዲጅ መስፈርት ያላሟላና ህጋዊ ጥበቃ የተሰጠውን የንግድ ምልክት የሚጥስ ግዙፍ ተግባር የፈፀመ መሆኑን ተጠሪ የማስረዲት ሸክሙን ሳይወጣ የግል ተበዲይ አዋጅ ቁጥር 501/98 ከመውጣቱ በፉት የንግድ ምልክቱ መመዝገቡን ብቻ በመመልከት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ የአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 46 ንዐስ አንቀጽ 1 አስገዲጅ የህግ ድንጋጌ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 23 ንዐስ አንቀጽ 2 እና የወንጀል ህግ አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 2ን የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ የገለጽነው ምክንያት እንደተጠበቀ ሆኖ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በአንደኛ አመልካች ላይ አዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 41 ንዐስ አንቀጸ 1 የተደነገገውን በመተላለፍ የወንጀል ድርጊት ፈጽሟል በማለት የወሰኑት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ የሚያስነሳው የህግ ጥያቄ አለ። ይኸውም የህግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት በሁለም የወንጀል ድርጊቶች ተጠያቂና ሀላፉ እንደማይሆን የወንጀል ህግ አንቀጽ 34 ንዐስ አንቀጽ 1 ‛በህግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት የመንግስት አስተዲደር አካላትን ሳይጨምር በህግ በግልጽ በተደነገገ ጊዜ በዋና ወንጀል አድራጊነት፣ አነሳሽነት ወይም በአባሪነት በወንጀል ሉቀጣ ይችላል“ የማለት የህግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት በወንጀል ተጠያቂ የሚሆነው ይህንኑ የሚደነግግ ግልጽ የህግ ድንጋጌ በሚኖርበት ጊዜ ብቻ እንደሆነ ገዥነት ያለውን መርህ በግልጽ ያስቀመጠ በመሆኑ ነው።
ህግ አውጭው በወንጀል ህጉ ወይም በላልች የህግ ማዕቀፍች ለምሳላ በወንጀል ህጉና በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ በወንጀልነት የተፈረጀው አድራጏት የህግ ሰውነት በተሰጠው ድርጅት የተፈፀመ ሲሆን የህግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት በወንጀል የሚጠየቅ ስለመሆኑ በግልጽ የሚደነግግ ድንጋጌ በማወጅ ህግ ወለድ ሰዎች በወንጀል ተጠያቂና ሀላፉ የሚሆኑበትን ሥርዓት እንደሚዘረጋ አግባብነት ያላቸውን የህግ ማዕቀፍች ይዘትና አቀራረጽ በማየት ለመረዲት ይቻላል።
በያዝነው ጉዲይ በአዋጅ ቁጥር 501/98 የተደነገገውን የተላለፈ የንግድ ህግ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች የወንጀል ተጠያቂና ሃላፉ የሚሆኑ መሆኑን የሚደነግግ ግልጽ የህግ ድንጋጌ የለም።
ተጠሪ የአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 41 ንዐስ አንቀጽ 1 ‛ማንኛውም ሰው“ የሚለው አገላለጽ የተፈጥሮ ሰውና የህግ ሰውነት ያላቸውን ድርጅቶች የሚያካትት ስለሆነ አንደኛ አመልካች በወንጀል መጠየቁ ተገቢነው በማለት ያቀረበው ክርክር በወንጀል ህግ አንቀጽ 34 ንዐስ አንቀጽ 1 የተደነገገውን መሰረታዊ መርህ ያላገናዘበ ሆኖ አግኝተነዋል።
በአጠቃላይ አንደኛ አመልካች ላይ የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ የወንጀል ህግ አንቀጽ 34 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረታዊ መርህን የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ በዝርዝር በገለጽናቸው የህግ ምክንያቶች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በአመልካቾች ላይ የሰጡት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በአመልካቾች ላይ የሰጡት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀጽ 2/ለ/1 መሰረት ሙለ በሙለ ተሽሯል።
ሁለተኛ አመልካች ከተከሰሰበት ወንጀል በነፃ የተሰናበተ በመሆኑ ከእስር እንዱለቀው ለማረሚያ ቤት ይፃፍ።
አንደኛ አመልካችና ሁለተኛ አመልካች የወንጀል ሃላፉነትና ተጠያቂነት የላለባቸው በመሆኑ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት አንደኛ አመልካች ከቻይና አገር ያስገባው 639 ካርቶንና 23,000 ፒኬት QRIQN የሚል የንግድ ምልክት ያለው ማስቲካ እንዱወገድ የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የተያዘውና አመልካቾች ከቻይና አገር ያስገቡት ማስቲካ እንዱለቀቅ ወስነናል።
ይኸ ውሣኔ መብቴ ተጥሷል የሚል ወገን ህጋዊ ሁኔታዎችን በማሟላት ህጋዊ ጥበቃና ከለላ እንዱሰጠው ጥያቄ ከማቅረብ የሚገደብ አይደለም በማለት ወስነናል።
በትውስት የመጣው መዝገብ ይመለስ ነው።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.