No summary available.
ጥር 9 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ሐንካራ ሐርቃ ሃያሞ ተጠሪ፡- የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ህግ መርዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
የሰበር አቤቱታው የአሁኑ አመልካች በወንጀል የተከሰሱበትን ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ ባለቤት ሆኖ መገኘት ጉዲይ በሚመለከት በይግባኝ ደረጃ ቀርቦለት የተመለከተው የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰጠው የጥፊተኛነት ፍርድ እና የቅጣት ውሣኔ ላይ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ተብል የቀረበውን ክርክር በመጨረሻ ያየው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በመ/ በ22/10/2002 የጥፊተኛነቱም ሆነ የቅጣት ውሣኔው እንዱሁም የንብረት መወረስ ውሣኔው በአግባቡ ስለሆነ ፀንቷል በሚል የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በሚል በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10(3) መሰረት የቀረበ ነው።
የአመልካች ጠበቃ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው የሚለባቸውን ምክንያቶች ሐምል 19 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ዘርዝረው አቅርበዋል።
የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ ጉዲዩ ለሰበር ችልት የሚያስቀርብ ነው በመባለ ማመልከቻው ለተጠሪው ተልኮ ቀርቦ መልስ እንዱሰጥበት ተደርጓል።
የአሁኑ ተጠሪ በ08/03/2003 ጽፍ ባቀረበው መልስ በዚህ ጉዲይ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤትም ሆነ ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ምንም አይነት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም። አመልካች ለሰበር ባቀረቡት ማመልከቻ ላይ በሥር ፍ/ቤት የህግ ስህተት ተፈጽሟል ብለው የገለጿቸው ምክንያቶች ስለማስረጃ ምዘናና ከጥፊተኛነቱ ውሣኔ በኋላ ስላለ ጥቃቅን ፍሬ ነገሮች የሚመለከቱ እንጅ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለመኖሩ የሚያስረደ አይደለም። የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት እንዱህ አይነት የማስረጃ እና የፍሬ ነገር ክርክሮችን በሕጉ የማየት ስልጣን የለውም በማለት የሰበር አቤቱታው ውድቅ ሆኖ በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም ተብል እንዱፀና ጠይቋል።
በአመልካች ጠበቃ በኩልም የመልስ መልስ መቅረቡን መዝገቡ ያሳያል።
ይህ ችልትም የአሁኑ አመልካች በወንጀል ሕግ አንቀጽ 419 ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ በእጃቸው ገብቶ ተገኝቷል ተብለው በወንጀል የተከሰሱባቸውን ጉዲዮች በሚመለከት በሥር ፍ/ቤት ታይቶ በአመልካች ላይ የተሰጠው የጥፊተኛነትም ሆነ የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት መሆን አለመሆኑን ሲመረምር መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ለማለት የሚያስችል ምክንያት የለም። በተለይ ቅጣቱን በተመለከተ የአሁኑ አመልካች በመንግሥት ሥራ ላይ ሆነው ከብር 182 የወር ደመወዝ ተነስተው በጭማሪና በዕድገት ብር 928 የወር ደመወዝ ላይ ደርሰው በዚህ መጠነኛ ደመወዝ ራሣቸውን ሲያስተዲድሩ እንደቆዩና ባለቤታቸውም ላላ ህጋዊ ገቢ እንዲልነበራቸው እየተገለፀ ምንጩ ያልታወቀ በሚሉዮን የሚቆጠር ገንዘብ በእጃቸው ገብቶ መገኘቱና ከፍተኛ ግምት ያለው ንብረት ባለቤት ሆነው መገኘታቸው ነገሩን ከባድ ስለሚያደርገው በዚሁ በሕጉ ልዩ ክፍል ከተደነገገው እስከ አምስት አመት ከሚደርሰው የጽኑ እስራት ቅጣት በአራት አመት ጽኑ እሥራት እንዱቀጡ መወሰኑ ያለአግባብ ቅጣቱ ከብድባቸዋል ልባል የሚችል አይደለም። በመሆኑም ተከታዩ ውሣኔ ተሰጥቷል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.