No summary available.
መጋቢት 10 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡-
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰምተናል።
ጉዲዩ ለሰበር ችልት የቀረበው የከፍተኛው ፍርድ ቤት በአንደኛ አመልካችና በሁለተኛ አመልካች እያንዲንዲቸው ለመኪናው ሉከፈል የሚገባ የነበረውን የቀረጥና የታክስ ግምት ብር 332‚005.19 (ሶስት መቶ ሰላሣ ሁለት ሺህ አምስት ብር ከአሥራ ዘጠኝ ሣንቲም) እንዱቀጣ የመወሰነን ህጋዊነትና አግባብነት ለማጣራት ተብል ነው። አመልካቾች ፍርድ ቤቱ በሁለታችን ላይ የጣለው የገንዘብ ቅጣት ለመኪናው ሉከፈል የሚገባውን ቀረጥና ታክስ እጥፍ በመሆኑ አዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 73ን የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ተከራክረዋል።
ተጠሪ አመልካቾች ወንጀል በመፈፀማቸው ጥፊተኛ ሆነው ተገኝተዋል። ስለዚህ ቅጣት የሚወሰነው በአንዲንዲቸው ላይ በመሆኑና የበታች ፍርድ ቤቶች በእያንዲንዲቸው ላይ በህጉ የተመለከተውን ዝቅተኛ የገንዘብ ቅጣት እያንዲንዲቸው እንዱከፍለ የተሰጠው ውሣኔ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩን ስንመረምረው አመልካች በወንጀል ህግ ቁጥር 32/1/ሀ እና አዋጅ ቁጥር 60/89 እንደተሻሻለ አንቀጽ 73(1) በመተላለፍ ወንጀል የፈፀሙ ጥፊተኞች መሆናቸውን ተረድተናል። አመልካቾች ጥፊተኛ የተባለበት ድንጋጌ በእስራትና በገንዘብ መቀጮ በጣምራ የሚያስቀጣ ወንጀል ነው። ቅጣት የሚወሰነው የእያንዲንደን ጥፊተኛ ግላዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነና ወንጀልና የወንጀል ቅጣት ግላዊ መሆናቸውንና ከአንደ ወደ ላላው የማይተላለፍ መሆኑ በወንጀል ህግ አንቀጽ 41 ከተደነገገው መሰረታዊ መርህ ለመረዲት የሚቻል ሲሆን የበታች ፍርድ ቤቶችም የገንዘብ መቀጮ የወሰኑት በአንደኛ አመልካች ላይ ያለትን የቅጣት ማክበጃና ማቅለያ ምክንያቶችና በህጉ የተቀመጠውን ዝቅተኛ የገንዘብ መቀጮ መነሻ በማድረግና በማገናዘብ ነው። የበታች ፍርድ ቤቶች በሁለተኛ አመልካች ላይ የገንዘብ መቀጮ የወሰኑት በሁለተኛው አመልካች ላይ ያለ የቅጣት ማክበጃና ማቅለያ ምክንያቶችን መነሻ በማድረግና በማገናዘብ ነው፡ ስለሆነም እያንዲንዲቸው ጥፊተኛ ሆነው የተገኙበት የህግ ድንጋጌ በወቅቱ ከጠበቃ ማሩ ባዘዘው ጋር ቀረቡ ለመንግሥት ይከፈል የነበረውን ቀረጥና ታክስ ገንዘብ መነሻ በማድረግ ፍርድ ቤቱ ሉወሰን የሚችል መሆኑን የሚደነግግ ነው።
ወንጀል በመፈፀሙ የሚወሰነው የገንዘብ ቅጣት በወንጀል ሕጉ የቅጣት አወሳሰን መርሆችን መሰረት በማድረግ የሚወሰን ነው። በወንጀል ጥፊተኛ በተባለ ሰዎች ላይ የሚጣለው የገንዘብ መቀጮ በፍታብሓር መንግሥት ሣይከፈለው የቀረበን ቀረጥና ታክስ በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍል ለማድረግ ከሚቀርብ ክስና ከሚሰጥ ውሳኔ በእጅጉ የተለየ ነው። ስለዚህ የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካቾች እያንዲንዲቸው ለመኪናው ይከፈል የነበረውን ቀረጥና ታክስ መከፈል ያለበት ገንዘብ ለፈፀሙት ወንጀል በመቀጫነት እንዱከፍለ የሰጡት ውሣኔ የወንጀል ህጉን መሰረታዊ የቅጣት አወሳሰን መርሆች የተከተለና መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት በመሆኑ በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195(2)(ለ-2) መሰረት አጽንተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፋዳራል የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጡት ፍርድና ውሣኔ ፀንቷል።
ፍርደ የፀና መሆኑን አውቆ እንዱያስፈጽም ለሚመለከተው ክፍል የውሣኔው ግልባጭ ይተላለፍ ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.