No summary available.
ሐምል 14 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሤ አመልካች፡- ወ/ሮ ውልታ ደሳለኝ - ጠበቃ ግርማ ሚደቅሣ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የኦሮሚያ የስነ ምግባርና ፀረ - ሙስና ኮሚሽን ዐ/ሕግ ማንደፍሮ ናታአ ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የዋስትና አቤቱታ ሲሆን የቀረበው በፉንፉኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች በክልለ የስነ ምግባርና ፀረ - ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ሕግ በሙስና ወንጀል ከላልች 11 ሰዎች ጋር በተከሰሱበት መዝገብ በካንሰር በሽታ መታመማቸውን ገልፀው ውጪ አገር ሂደው ለመታከም ዋስትና እንዱፈቀድላቸው ያቀረቡት ጥያቄ በተከሰሱበት ወንጀል ዋስትና አይፈቀድም በማለት የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር የቀረበ ነው።
አሁን የቀረበው ቅሬታ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከላይ እንደተመለከተው በመወሰኑ እና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደዚሁም ሰበር ሰሚ ችልት አመልካች ያቀረቡትን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የዞኑን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ በማፅናታቸው ሲሆን በቀን 15-9-2003 ዓ.ም በ3 ገፅ የቀረበ የቅሬታ ፍሬ ሃሣብ ባደረብኝ የጉበት ካንሰር በሽታ በአገር ውስጥና ውጪ ስታከም የቆየሁ መሆኑ እየታወቀ፣ በተሰጠኝ በሐኪሞች ቦርድ መሰረት ውጪ አገር ሄጄ እንድታከም ተወስኖ እያለ በቁጥጥር ሥር በመሆኔ መሄድ ያልቻልኩ መሆኑ እየታወቀ፣ በጤንነት ምክንያት ችልት ቀርቤ መከራከር ያልቻልኩ በመሆኑ፣ ዋስትና ያስከላክላል በማለት የተጠቀሰብኝ አንቀፅ የሕክምና እድል የማግኘት መብቴን የማይነፍገኝ እንጂ የሚነፍገኝ ቢሆን እንኳን የአዋጁ ድንጋጌ ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 21 እና 15 እንደዚሁም አንቀፅ 9 ጋር ታይቶ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ትዕዛዝ ተሽሮ ውጪ አገር ሄጄ መታከም እንድችል እንዱፈቀድልኝ የሚል ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ ቀርቦ በቀን 02-10-2003 ዓ.ም በ4 ገፅ የሰጠው የመልስ ፍሬ ሃሣብ አመልካች ዋስትና የተከለከለት የተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ዋስትና የማይፈቅድ በመሆኑ፣ በበታች ፍርድ ቤቶች ያቀረቡት ጥያቄ የዋስትና ጥያቄ እንጂ ሕክምና የማግኘት መብት ባለመሆኑ ሁለቱ ጥያቄዎች ደግሞ መቅረብ ያለባቸው በተለያዩ ሁኔታዎች በመሆኑ አሁን የቀረበው ጥያቄ ተገቢነት የለውም፣ የበታች ፍርድ ቤቶችም ውሣኔ የሰጡት የቀረበው የዋስትና ጥያቄ ተቀባይነት አለው? ወይስ የለውም? በሚለው ነጥብ ላይ በመሆኑ አሁን እየተነሳ ያለው በህይወት የመኖር መብት ጋር ተያይዞ የሕገ-መንግስቱን አንቀጽ በመጥቀስ የቀረበው ከጉዲዩ ጋር ተያያዥነት የለውም፣ የቀረበው ጉዲይ ከሕገ መንግስቱ ጋር ተያያዥነት አለው ቢባል እንኳ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ሕገ-መንግስት አንቀጽ 19 ለተከሰሱ ሰዎች በመርህ ደረጃ የዋስትና መብት የሚፈቅድ ቢሆንም በልዩ ሁኔታ ግን ዜጏች እንደ ወንጀለ ሁኔታ ዋስትና ሉከለከለ እንደሚችለ የሚደነግግ በመሆኑ የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት የላለው በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ እንዱፀና በማለት ተከራክሯል።
በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የክርክር ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመርነውም የቀርበው አቤቱታ የዋስትና መብትን መሰረት ያደረገ ነው?
ወይስ የህክምና የማግኝት መብቱን ነው? በሁለቱ ጉዲይ መከተል የሚገባው ሥርዓት አንድ ነው?
ወይስ አይደለም? የሚለት ጭብጦች ተይዞ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁ መሰረት የሙስና ወንጀል እየታየ ያለበት ችልት ቀርቦ የነበረው አቤቱታ አመልካች በካንሰር በሽታ እየታመሙ መሆናቸውን ገልፀው የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ውጪ አገር ሂደው ለመታከም እንዱቻለ በሚል የቀረበ ሲሆን ችልቱም ሰጥቶት የነበረው ትዕዛዝ ዋስትናን በተመለከተ የተሰሱበት ወንጀል ዋስትና አያስጠብቅም። ሕክምናን በተመለከተ ግን በፕሉስ ክትትል ሥር ሆነው ለመታከም የሚያግድ ነገር የለም በሚል ነበር። ይሄ የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ እስከ ክልለ ሰበር ችልት ቀርቦ ፀድቋል።
አሁን ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የቀረበው ቅሬታ ‛…. የተከሰስሽበት የወ.መ.ሕ.ቁ. 407/2/ በአዋጅ ቁ. 434/1997 አንቀጽ 4/1/ መሰረት የዋስትና መብት አይፈቅድም በሚል ምክንያት የውጭ አገር የህክምና ጥያቄን በትእዛዝ እና ውሣኔ ውድቅ አድርገውብኛል።“ በሚል ነው። ከዞኑ ፍርድ ቤት ጀምሮ ሲጠየቅ የነበረውን የዋስትና ጥያቄ በተመለከተ አመልካች የተከሰሱበት የወንጀለኛ መቀጫ ሕግ አንቀጽ 407/2/ን ስንመለከት ከ7 ዓመት ፅኑ እስራት እስከ 15 ዓመት ፅኑ እስራት ሉያስቀጣ የሚችል አንቀጽ በመሆኑና አመልካች በካንሰር በሽታ መታመማቸው በራሱ ከተሻሸለው የፀረ-ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁ. 434/97 አንቀጽ 4/1/ አኳያ ሲታይ ለዋስትና ጉዲይ ከግምት የሚገባበት አግባብ የለም። ምክንያቱም በዚህ አዋጅ አመልካች የተከሰሱበት አንቀጽ ከ10 ዓመት በላይ ሉያስቀጣ በሚችል ወንጀል ከሆነ በዋስትና መልቀቅ እንደማይቻል ይደነግጋል።
በልላ በኩል የተሰጠው ትዕዛዝ ወይም ደግሞ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ መደረጉ የአመልካችን ሕከምና የማግኘት መብት ብልም በህይወት የመኖር ሕገ-መንግሥታዊ መብቷን ተቀባይነት አሳጥቷል ወይ? የሚለውን ነጥብ ስንመለከት በመጀመሪያ ደረጃ በሕግ ጥላ ሥር ያለ ተከሣሽ የመታከም መብት የማይገደብበትና ከዚህ አኳያ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግሥት የተቀመጡት መሰረታዊ መብቶች እንደ ማንኛውም ዜጋ የሚከበርላቸው ስለመሆኑ በሕገ መንግሥቱና አገሪቷ ካፀደቀቻቸው አለም አቀፍ የሰበአዊ መብት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። የበታች ፍርድ ቤቶች የዋስትናውን ጥያቄ ውድቅ ሲያደርጉ በላልች ሕጎች የተመለከቱትን የመታከም መብቷን ውድቅ ያላደረጉና አሁንም ቢሆን ጉዲዩ የሚመለከታቸውን አካላትን የመጠየቅ መብታቸውን የሚነካባቸው ባለመሆኑ አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ የተከሰሱበት ወንጀል ዋስትናን አያስጠብቅም በማለት ያቀረብኩትን የመታከም መብቴን ውድቅ አድርገውብኛል በማለት ያቀረቡት አቤቱታ አግባብነት የለውም ብለናል።
በመሆኑም አመልካች በበታች ፍርድ ቤት አቅርበውት የነበረው አቤቱታ የዋስትና ጥያቄ የነበረ በመሆኑ ፍርድ ቤቶች የተከሰሱበት ወንጀል ዋስትና ይከለክላል በማለት የሰጡት ውሣኔ በአግባቡ በመሆኑና ጉዲዩን የሚመለከተውን አካል በመጠየቅ የመታከም መብታቸውን የሚነካ ባለመሆኑ የቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት የለውም ብለናል። የበታች ፍርድ ቤቶችም ከላይ በተመለከተው መሰረት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ሰህተት ያለበት ሆኖ አልተገኘም።
በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
129766 በቀን 05-09-2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመዝ.ቁ.
122550 በቀን 02-9-2003 ዓ.ም በዋለው ችልት እና በፉንፉኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝ.ቁ. 03345 በቀን 08-7-2003 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጡት ውሣኔ በአዋጅ ቁ. 434/97 አንቀጽ 4/1/ እና በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 75/2/ መሰረት ፀንቷል።
No topics extracted.