No summary available.
ሐምል 28 ቀን 2003ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ተስፊዬ ተሾመ - ጠበቃ ሲሳይ ኃይለ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የፍደራል ዓቃቤ ሕግ - ማርታ በቀለ ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የወንጀል ክስ ሲሆን በፋ/ከፍተኛ ፍርድ በተጠሪ ቀርቦ የነበረው የክስ ይዘት ተከሣሽ/የአሁን አመልካች በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፋ.ደ.ሪ የወንጀል ሕግ ቁ.692(1) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ የማይገባውን ብልፅግና ለራሱ ወይም ለላላ ሰው ለማሰገኘት አስቦ የግል ተበዲይ ወይንሸት ወርቁ የከባድ መኪና ካምፑዮ እንደተሸጠለት በወ/ሮ አልማዝ ከበደ የከባድና ቀላል መኪና ዕቃ መለዋወጫ ሱቅ ውስጥ አስቀምጣ እንዲለ ተከሣሽ ወደ ሱቁ ውስጥ የሰላዲ ቁጥሩ ኮድ 2.35215 አ.አ በሆነ መኪና እያሽከረከረ በመምጣቱ መጀመሪያውኑም ከግል ተበዲይ ጋር የከባድ መኪና ካምፑዮ በብር 45,000 ለመግዛት ከመስማማቱ በኋላ ብር ላምጣ ብል መሄደን እንጂ የግል ተበዲይ ከላይ የተመለከተውን ዕቃ ውሰድ ሳትለው ወ/ሮ አልማዝም የግል ተበዲይ የታለች ብላ ስትጠይቀው ከኋላዬ ናት ከፉትና ኋላ ሆነን ነው የመጣነው በማለት አሳሳች ነገር በመናገር የከባድ መኪና ካምፑዮን ይዞት በነበረው መኪና ውስጥ ጭኖ በመጥፊቱ በፈፀመው የማታለል ወንጀል ተከሷል የሚል ነው።
በቀረበው ክስ ላይ አመልካች በመካድ የተከራከረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ማስረጃ በመስማት ክሱ በቀረበበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ ሥር ጥፊተኛ ነው በማለት በመወሰን የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት በመቀበል በአንድ ዓመት ከስድስት ወር የእስራት ቅጣት እንዱቀጣ በማለት ወሰኗል። አመልካች በተሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሣኔ በማፅናት ውሣኔ ሰጥቷል።
አሁን የቀረበው አቤቱታ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን አመልካች በጠበቃቸው በኩል መጋቢት 12 ቀን 2003ዓ.ም የተፃፈ የቅሬታ ፍሬ ሃሣብ ዋናው የወንጀል ማቋቋሚያ ፍሬ ነገር የሆነው የተከለከለ የወንጀል ድርጊት ስላልተሟላ ድርጊቱ የማያስከስስ በመሆኑ፣ ዓ/ሕግ ያቀረባቸው የሰው ምስክሮች አመልካች ከጥርጣሬ ውጭ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመ ስለመሆኑ የማያረጋግጡ በመሆኑ፣ አመልካች በሥር ፍርድ ቤቶች ያቀረባቸው የሰውና ሰነድ ማስረጃዎችን በአግባቡ ያልተመለከቱት በመሆኑ እና አመልካች በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.143(2) እና በሕገ-መንግስቱ በተሰጠኝ የመከላከል መብት መሰረት ያቀረብኩትን ተጨማሪ ማስረጃ ያለመቀበላቸው ያለአግባብ በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤት የፈፀሙት መሰረታዊ የህግ ስህተት ታርሞ አመልካች በነፃ እንዱሰናበት የሚል ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ ቀርቦ መልስ የሰጠ ሲሆን በቀን 22/9/2003 ዓ.ም በ3 ገፅ የተፃፈ የመልስ ፍሬ ሃሣብ አመልካች የፈፀማቸው ተግባር ሕጉ የተረጋገጠው ፍሬ ነገር ስንመለከት በወንጀል ሕጉ የተቀመጠውን የወንጀል አላፉነቱን የሚያቋቁሙትን ተግባራት የሚያሟላ በመሆኑ፣በዓቃቤ ህግ የቀረቡት ማስረጃዎች የተፈፀመውን ወንጀል በአግባቡ ያረጋገጡ በመሆኑና አመልካች በመከላከያ ምስክሮቹ ያላስተባበለ በመሆኑ እና ተጨማሪ የማስረጃ ጥያቄ በተመለከተ የመከላከልን መብት በተመለከተ ቀድሞ በመከላከያዎች ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሰ ባለመሆኑ እና ፍርድ ቤቱ የተጠየቀው ተጨማሪ ማስረጃ ነገሩን ለማዘግየት ሣይሆን ለፍትሕ አሰጣጡ አስፈላጊ ነው ብል ሲያምን የሚፈቅድ በመሆኑ በባሕርይው ፍቃጅ እንጂ አስገዲጅ ባለመሆኑ የቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል። የአመልካች የመልስ መልስ ቀርቧል።
በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የክርክር ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደተመረመረውም በመጀመሪያ ደረጃ የቀረቡት የዓቃቤ ሕግ ማስረጃዎች በበቂ ሁኔታ ተፈፀመ የተባለው ወንጀል ስለመፈፀሙ አላስረደም እና አመልካች ያቀረባቸው ማስረጃዎች በአግባቡ አልታየልኝም የሚለትን ነጥቦች ስንመለከት ማስረጃን መመዘን ጉዲዩን በመጀመርያ የተመለከተው እና በይግባኝ የያዘው የፍርድ ቤት ሥልጣን በመሆኑ እና የዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ሥልጣን በኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 80(3)(ሀ) እና በአዋጅ ቁ.25/88 አንቀጽ 1ዐ መሰረት መሰረታዊ የሕግ ስህተት ሲፈፀም ማቃናት በመሆኑ በፍሬ ነገር ረገድ የበታች ፍርድ ቤቶች የደረሱበትን መደምደሚያ መቀበለ አግባብነት ያለው ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁ መሰረት መታየት ያለባቸው አመልካች የጠየቀው ተጨማሪ ማስረጃ መታለፍ እና በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠው ነጥቦች አመልካች ጥፊተኛ የተባለውን የወንጀል ኃላፉነት ስለ ማቋቋሙ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለት ጭብጦች ተይዘው ይሄ ጉዲይ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
የመጀመረያውን ጭብጥ በተመለከተ ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት የችልት ሂደት ከመዝገቡ መረዲት እንደተቻለው አመልካች የሰውና የሰነድ መከላከያ ምስክሮችን /ማስረጃዎቹን/ ካጠናቀቀ በኋላ የካቲት 26 ቀን 2002ዓ.ም በዋለው ችልት የተጨማሪ የባለሙያ ምስክር የጠየቁ መሆኑ ተመዝግቦ የማስረጃው ዝርዝርና ምን እንደሚያስረደለት ሲያቀርብ ለትክክለኛ ፍትሕ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ይታያል በማለት መዝገቡ ለውሣኔ የተቀጠረ መሆኑ፣ ለውሣኔ በተቀጠረበት መጋቢት 2ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በዋለው ችልት የተከሣሽ ጠበቃ በቀን 10/7/2002 ዓ.ም በተፃፈ ተጨማሪ የባለሙያ ምስክር የተጠየቀ መሆኑ ተገልፆ አስፈላጊ ሲሆን የሚታዘዝ መሆኑ ተገልጾ አሁንም መዝገቡ ለውሣኔ የተቀጠረ መሆኑን፣ በቀጠሮው ሚያዝያ 18 ቀን 2ዐዐ2ዓ.ም በተመሣሣይ መልኩ የተቀጠረ መሆኑን በመጨረሻውም ለአሁኑ ቅሬታ ምክንያት የሆነው ፍርድ መሰጠቱን መመልከት ይቻላል። በዚሁ በስተመጨረሻ በተሰጠው ፍርድም የተጨማሪ ማስረጃ ጉዲይ የተነሣ ሲሆን ከሂደቱ ፍርድ ቤት ያለፈው መሆኑን ተረድተናል በማለት ተመልክቷል። ከዚህ አጠቃላይ ሂደት መገንዘብ የሚችለው መጀመሪያውኑ የተጨማሪው ማስረጃ የመራለት ችልት ወደ ፉት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ትዕዛዝ ይሰጥበታል በማለት ሲቀጥር መቆየቱ እና በመጨረሻም ፍርድ የሰጠው ችልት የተጨማሪ ማስረጃ ጉዲይ በማንሣት እንደታለፈ ይቆጠራል ማለቱ ጉዲዩን የተመለከተውና የቀረበውን ጥያቄ ያለመቀበለን ያመለክታል።
ፍርድ ቤቱ የተጨማሪ ማስረጃን ጥያቄ አልተቀበለውም የሚል መደምደሚያ ላይ ከተደረሰ የታለፈበትን አግባብ ወይም መታለፈ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ነጥብ መመልከት ተገቢ ይሆናል። ተጨማሪ ማስረጃ የተጠየቀው የባለሙያ ምስክርነት ሲሆን በወቅቱ የያዝኩት መኪና የከባድ መኪና ካምፑዮ መጫን የማይችል ስለመሆኑ ያረጋግጣል በማለት ነው።ተጠሪ የሙለ አመልካች ይዞት የነበረው የቤት መኪና የከባድ መኪና ካምፑዮ መጫን መቻለ ወይም ያለመቻለ በጭብጥነት ያልተያዘ ጉዲይ በመሆኑ እና መሸከም እንደሚችል ለማንም ሰው ግልፅ በመሆኑ የተለየ የባለሙያ ምስክርነት የማያስፈልገው በመሆኑ ቢታለፍ በአግባቡ ነው በማለት ተከራክሯል። ችልቱም የግራቀኙን ክርክር ሲመለከተው አጠቃላይ ክርክሩና የምስክር ሂደቱ አመልካች ከግል ተበዲይና ከዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ጋር የተባለውን የከባድ መኪና ካምፑዮ በእጅ ለማስገባት የተጠቀመባቸውን ስልቶች ወይም ዘዳዎች ላይ ያተከረ እንጂ የመኪናው ዓይነት እና በተለይም አመልካች ይዘውት የመጡት መኪና ዝርዝር ይዘት ወይም የመሸከም አቅም በተመለከተ ጭብጥ ተይዞ በስፊት የተኬደበት አይደለም። ይሄ ከሆነ ደግሞ ቀድሞ በጭብጥነት ያልተያዘ ጉዲይ ከመሆኑም በላይ ከወ/መ/ሕግ ቁ.143(2) ሥር እንደተመለከተው ተጨማሪ ማስረጃ ፍርድ ቤቱ ለትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ ተገቢ ነው ብል ሲያምን እንጅ አስገዲጅ ካለመሆኑ ጋር ተደምሮ ሲታይ መታለፈ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል የሚያሰኝ ሆኖ አልተገኘም። በዚህ መሰረት አመልካች በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ስርዓት ህግ እና በህገ መንግስቱ የተሰጡትን መከላከያ ማስረጃ በማቅረብ የመከላከል መብቱን የተጠቀመበት በመሆኑ እና ተጨማሪ ማስረጃ መቀበል ደግሞ አስገዲጅ ሣይሆን ፍርድ ቤቱ ለፍትሕ አሰጣጥ አስፈላጊ ነው ብል ሲያምን የሚሰጥ /የሚፈቀድ/ በመሆኑ በመታለፍ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል የሚያሰኝ ነገር የለም ብለናል።
ወደ ሁለተኛው ጭብጥ ስንመለስ የተረጋገጠው ፍሬ-ነገር አመልካች ጥፊተኛ ተብል የተቀጣበትን የወንጀል ህግ ኃላፉነት ሉያቋቁም ስለመቻለ መመልከት ተገቢ ነው። በዚሁ መሰረት የግል ተበዲይና አመልካች በደላላ ከተገናኙ በኋላ የከባድ መኪናውን ካምፑዮን ያስቀመጠችበት ድረስ በማምጣት የግል ተበዲይ ለአመልካች ካሣየችውና ዋጋውን ከተነጋገሩ በኋላ አመልካች ገንዘቡን ይዤ እመጣለሁ በማለት ሲሄድ ተበዲይም እስከዚያ የግል ጉዲይ ቦታ ለመድረስ እንደወጣች፣ አመልካች ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ተመልሶ የመጣ መሆኑ፣ የዓቃቤ ሕግ ምሥክሮች የግል ተበዲይስ ብለው ሲጠይቁት ከኋላዬ ነች አብረን ነው የመጣነው፣ ፒርክ ለማድረግ መኪና እያዞረች ነው፣ የመኪና ማቆሚያ ቦታ እየፈለገች ነው፣ እስከዚያ ይጫን ፣ይዘን እንጥፊ በማለት የተለያዩ የማሣመኛ ቃላቶችን በመጠቀም ዕቃውን አስወጥቶ በመጫን የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች የራሳቸውን ሱቅ ሥራ ለመሥራት መለስ ሲለ ይዞ የጠፊ መሆኑ በፍሬ ነገር ረገድ ተረጋግጧል። የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር ከወ/መ/ሕግ ቁ.692(1) አኳያ ሲታይ አመልካች የማይገባ ብልፅግና ለራሱ ወይም ለላላ ሰው ለማስገኘት ቀድሞ ከግል ተበዲይ ጋር የመምጣቱን አጋጣሚ በመጠቀም የግል ተበዲይ ከእሱ ጋር ሣትመጣ አብራው እንደመጣች በማስመሰል የባለ ሱቆቹን የተሣሣተ እምነት በመጠቀም፣ ትክክለኛውን ነገር በመደበቅ ካምፑዮኑን ይዞ በመጣው መኪና ላይ ከጫነ በኋላ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች በልላ ሥራ መጠመድ አጋጣሚ በመጠቀም ይዞት የሄደ በመሆኑ በሕጉ የተቀመጠውን ወንጀል ሕጉ ሥር የወንጀል ኃላፉነቱን የሚያረጋግጡ መመዘኛዎች መሟላታቸውን ያመለክታል።
በመሆኑም የተፈፀመው ድርጊት የወንጀል ኃላፉነቱን የሚያቋቁሙ በመሆኑ ስለተረጋገጠ በዚህ አንቀጽ ስር ጥፊተኛ ተብል መቀጣቱ በአግባቡ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አልተገኘም። የተላለፈበት ቅጣትም የግራቀኙን የቅጣት አስተያየትና አጠቃላይ የቅጣት አጣጣል ሥርዓቶች የተከተለ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተው ውሣኔ ተሰጥቷል።
ው ሣ ኔ
195(2)(ለ)(2) መሰረት ፀንቷል።
አመልካች በተከሰሰበት የማታለል ወንጀል ጥፊተኛ ተብል የተጣለበት ቅጣት በአግባቡ ነው ብለናል።
በትውስት የመጣው የመዝ.ቁ.80841 ወደ መጣበት ይመለስ መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.