No summary available.
ሐምል 25 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- መምህር ዓወት ተካ - አልቀረበም።
ተጠሪ፡- የትግራይ ዐቃቤ ሕግ - አልቀረበም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የትግራይ ብሓራዊ ክልል የምሥራቃዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። የክርክሩ መነሻ የዞኑ ዐቃቤ ሕግ አመልካች በአንደኛ ተከሳሽ ስሙን በመመዝገብ በሥር ፍርድ ቤት አብረው ክስ ከቀረበባቸው ላልች ሦስት ተከሳሾች ጋር በመሆን በወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 የተመለከተውን በመተላለፍ ጳጉሜ 2 ቀን 1998 በአዱግራት ከተማ ቀበላ 01 ዞን 4 ዓለም መስፍን ሆቴል ፉት ለፉት ከላሉቱ ሰባት ሰዓት አቶ ፅጌ ባህታን በድንጋይ አናቱንና ላላውን ሰውነቱን መትተው የገደለት ስለሆነ የሰው መግደል ወንጀል ፈፅሟል በማለት ያቀረበው ክስ ነው። አመልካች ዐቃቤ ሕግ በጠቀሰው ቀንና ሰዓት አብረውት ከተከሰሱት ሦስት ሰዎችና ክስ ካልቀረበበት ኃይለማርያም አብርሀ ከተባለ ልጅ አህዋ ሆቴል ከተባለው ሆቴል ሲጠጡ ቆይተው ወደ ቤት በመሄድ ላይ እያለ ዓለም መስፍን ሆቴል ሲደርስ ሙዚቃ ሰምቶ ቀድሞ ከዓለም መስፍን ሆቴል ሲደርስ ሟች ከሆቴለ ውስጥ ሲወጣ በር ላይ አግኝቶት ሟች ሂድ አንተ ምናባህ ብል እንደገፊው፣ አመልካችም ሟች ወታደር ስለመሰለው ምን አደረግሁህ ጋሼ እንዲለውና ሟች አከታትል መትቶት ከአስፊልት ላይ እንደጣለውና መነሳት እንዲልቻለ አመልካችም ኡኡ ብል እንደጮኸና ከዚያ በኋላ ሟችን በድንጋይ ማን እንደመታው እንዲላየና ተፈንክቶ ስለነበር ተነስቶ እየተንገዲገደ እንደሄደ በመግለፅ በሟች ግድያ ተካፊይ አይደለሁም ወንጀለን አልፈፀምኩም በማለት ተከራክሯል።
ተጠሪ አመልካችና ላልቹ ተከሳሾች ዋና ወንጀል አድራጊና የወንጀል ተካፊይ በመሆን ሟችን መግደላቸውን ያስረዲልኛል በማለት አምስት ምስክሮችና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል።
ዐቃቤ ሕግ ክሱን ለማስረዲት ካቀረባቸው ምስክሮች ውስጥ ዐቃቤ ሕግ በአራተኛው ተራ ቁጥር የማስረጃ ዝርዝር ላይ ስሙን የገለፀው ምስክር ሥራው ፕሉስ መሆኑን ገልፆ በሥር ፍርድ ቤት ሁለተኛ ተከሳሽ እና አራተኛ ተከሳሽ ለፕሉስ ቃል ሲሰጡ የሰማ መሆኑንና ሟች አመልካችን ወድቀው ሟች ከላይ በሥር አንደኛ ተከሳሽ የነበረው አመልካች ከታች ሆነው እንዲገኟቸውና ሁለተኛ ተከሳሽ ሟችን በድንጋይ አናቱን የመታው መሆኑንና አራተኛ ተከሳሽ በእግሩ ሟችን የመታው መሆኑን ሲናገሩ ሰምቻለሁ አንደኛ ተከሳሽ /አመልካች/ መናገሩን አላስታውስም በማለት መስክሮ ተመልሷል። ዐቃቤ ሕግ በማስረጃ ዝርዝሩ ስሙ በአምስተኛው ተራ ቁጥር የጠቀሰው ምስክር ሥራው ፕሉስ መሆኑን ገልፆ በሥር ሁለተኛና አራተኛ ተከሳሽ የነበሩት ሰዎች ስለወንጀለ አፈፃፀም ለፕሉስ ቃላቸውን ሲሰጡ የሰማ መሆኑን በዝርዝር መስክሮ የተመለሰ ነው። ለፕሉስ የተሰጠን ቃል የመሰከረው የዐቃቤ ሕግ ሶስተኛ ምስክር ሁለም በጠቡ ተሳታፉ መሆናቸውን የመሰከሩ መሆኑንና ሁለተኛና አራተኛ ተከሳሾች በድምፅና በምስል በተቀረፀ ካሴት የሰጡት ቃልና ከአዱግራት ሆስፑታል የተሰጠ ማስረጃ በማስረጃነት የቀረበ መሆኑን ያሳያል። ከዚህ በተጨማሪ ሁለተኛና አራተኛ ተከሳሾች በወረዲ ፍርድ ቤት የሰጡት የእምነት ቃል ሶስት የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች በቀዲሚ ምርመራ ፍርድ ቤት የሰጡት የምስክርነት ቃልና በማስረጃነት እንደቀረበ የዞኑ ፍርድ ቤት በውሣኔው ገልጿል።
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካችና ላልች ተከሳሾች የመከላከያ ማስረጃ እንዱያቀርቡ ብይን ሰጥቶ የአመልካችና የላልቹን ተከሳሾች መከላከያ ማስረጃ ከሰማ በኋላ በሥር ሶስተኛ ተከሳሽ የነበረው በነፃ እንዱሰናበት ፍርድ ሰጥቷል። አመልካች በሥር ሁለተኛ ተከሳሸና አራተኛ ተከሳሽ የነበሩት ሰዎች በወንጀል ሕግ አንቀፅ 540ን በመተላለፍ የሰው መግደል ወንጀል የፈፀሙ ጥፊተኞች ናቸው በማለት አመልካች በሰባት ዓመት ፅኑ እስራት እንዱቀጣ ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቦ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የዞኑን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ አፅንቷል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አቅርቧል። የክልለ የሰበር ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት በአብላጫ ድምፅ ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች ጥር 14 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ዐቃቤ ሕግ እኔን ሟችን በመግደል ወንጀል የከሰሰኝ ቢሆንም ዐቃቤ ህግ ያቀረበው የሰውና የፅሐፍ ማስረጃ በወቅቱ ሟች እኔን መሬት ላይ ጥል እየደበደበኝ እያለ ኡኡታ የሰማሁ መሆኑንና በሥር ሁለተኛ ተከሳሽና አራተኛ ተከሳሽ የነበሩት ሟችን የመቱት መሆኑንና እኔም ከወደቅሁበት ተነስቼ መሄዳን የሚያስረደ ናቸው። ሟች መሬት ላይ ጥል ሲደበድበኝ የኡኡታና የጩኸት ድምፅ ማሰማቴ በወንጀለ ድርጊት ተካፊይ ወይም ግብረ አበር የነበርኩ መሆኑን አያስረዲም። ስለሆነም በወንጀለ ድርጊት የተሳተፍኩ መሆኔን የሚያሳይ ምንም ዓይነት ማስረጃ ተጠሪ አቅርቦ ባላስረዲበት ሁኔታ ጥፊተኛ ተብዬ መቀጣቴ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በፅሐፍ መልሱን እንዱያቀርብ መጥሪያ ከደረሰው በኋላ በፅሐፍ መልሱን ባለማቅረቡ መልስ የመስጠት መብቱ እንዱታለፍ ችልቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር አመልካች ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም አመልካች ሟችን በመግደል ወንጀል ጥፊተኛ ነው ተብል የተወሰነበት የቅጣት ውሳኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል። ከላይ የተገለፀውን ጭብጥ ለመወሰን በመጀመሪያ ዐቃቤ ህግ /ተጠሪ/ ባቀረበው ማስረጃ አመልካች የወንጀለ ሥራ ዋና ወንጀል አድራጊ /ተካፊይ/ አባሪ ወይም ረዲት መሆኑን የማስረዲት ኃላፉነቱን ተወጥቷል ወይስ አልተወጣም የሚለውን ነጥብ ማየት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
በአጠቃላይ አመልካች ሟች መሬት ላይ ጥል እየደበደበው እያለ የኡኡታና የጩኸት ድምፅ በማሰማቱና የአመልካችን ጩኸት ሰምተው የመጡት ሁለተኛና አራተኛ ተከሳሾች በቦታው የደረሱና ሟችን በድንጋይ የመቱት መሆኑን እንጂ ተጠሪ ዐቃቤ ሕግ አመልካች ሟችን ለሞት ያበቃው ድርጊት ላልቹ ተከሳሾች ሲፈፅሙ በተግባር ወይም በመላ ሃሳቡ ተካፊይ የነበረ ስለመሆኑ የሚያስረዲ ማስረጃ ያላቀረበ መሆኑን ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ተገንዝበናል።
በመሰረቱ ዐቃቤ ሕግ በወንጀል በተከሰሰ ሰው ላይ የሚያቀርበው የወንጀል ክስ የወንጀለን ዝርዝር ሁኔታ መያዝ እንዲለበት በተለይም ተከሳሹ የተከሰሰበትን ወንጀል ለይቶ አውቆ መልስ ለመስጠት እንዱችል ክሱ ወንጀለንና ሁኔታውን መግለፅ ያለበት መሆኑ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀፅ 112 በግልፅ ተደንግጓል። ከዚህ አንፃር ስንመለከት ተጠሪ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ አመልካች በወንጀለ ድርጊት በምን ሁኔታ እንደተሳተፈ የሚገልፅ አይደለም። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ አመልካችና ከአመልካች ጋር የተከሰሱት ላልች ሰዎች በወንጀለ ሥራ ያደረጉትን ተሳትፍና በወንጀለ ተካፊይ ናቸው የሚልበትን ምክንያት በመዘረዘርና ክሱን እንዱያሻሻል በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 119 መሰረት ትዕዛዝ መስጠት ሲገባው የአመልካች የወንጀል ተሳትፍና ተካፊይነት በዝርዝር የማይገልፀውን የወንጀል ክስ ተቀብል ማከራከሩ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 112 ድንጋጌን መሰረታዊ ግብ ሳይከተል ክርክሩን የመራው መሆኑን የሚያሳይ ሆኖ አግኝተነዋል።
አንድ ሰው በዋና ወንጀል አድራጊነት በኃላፉነት የሚጠየቀው በወንጀል ሕግ አንቀፅ 32 ንዐስ አንቀጽ 1 /ከሀ-ሐ/ በተደነገጉት መሰረት በወንጀለ ሥራ ተካፊይ ሆኖ ሲገኝ ነው። አመልካች በወንጀል ሕግ አንቀፅ 32 ንዐስ አንቀጽ 1 /ከሀ-ሐ/ በተደነገገው መሰረት ሟችን ለሞት ያበቃውን ድብደባ ላልቹ ተከሳሾች ሲፈፅሙ ተካፊይ የነበረ መሆኑ ተጠሪ አላስረዲም። በተለይም አመልካች ሟችን ሀሳብና አድርጏቱ እንደዚሁም በወንጀለ ድርጊትና በሚሰጠው ውጤት ተካፊይ በመሆን ድርጊቱን የራሱ ያደረገ መሆኑን ተጠሪ የማስረዲት ኃላፉነቱን /Burden of proof/ የተወጣ መሆኑን ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ያላቸው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በውሣኔያቸው አላረጋገጡም። በአንፃሩ የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የአመልካች ጓደኞች የነበሩት ሁለተኛና አራተኛ ተከሳሽ ሟችን በድንጋይ ሲደበድቡት አመልካች የሟች ጥቃት ሰለባ ሆኖ መሬት ላይ ወድቆ ሟች እየደበደበው የነበረና አመልካችም የኡኡታና የጩኸት ድምፅ እያሰማ እንደነበር ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበውን ማስረጃ ይዘት በማጠቃለል የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በውሣኔው ካሰፈረው ለመረዲት ችለናል።
አንድ ሰው ከላልች ሰዎች ጋር የወንጀል ተካፊይ ሆኗል የሚባለው በወንጀለ አፈፃፀም የግዙፍ ተግባር፣ የሃሳብና የሕግ ሁኔታዎች በመተላለፍና በወንጀል ሕግ አንቀፅ 32 ንዐስ አንቀጽ 1 በተደነገገው መሰረት በወንጀለ ድርጊት ተሳታፉ ሆኖ ሲገኝ እንደሆነ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 23 ንዐስ አንቀጽ 2 እና ከወንጀል ሕግ አንቀፅ 32 ንዐስ አንቀጽ 1 በጣምራ በማንበብ ለመገንዘብ ይቻላል። በልላ ሰው ጥቃት እየተፈፀመበት ከመሬት ላይ ወድቆ እየተደበደበ ያለ ሰው የጩኸትና የኡኡታ ድምፅ ማሰማቱን በወንጀልነት የሚፈርጅ የሕግ ድንጋጌ የለም። አመልካችን ሟች መሬት ላይ ጥል ሲደበድበው የጩኸትና የኡኡታ ድምፅ ከመስማቱ ውጭ ሁለተኛና አራተኛ ተከሳሾች ሟችን እንዱገድለት ያነሳሳ ወይም የወንጀለ አባሪ ስለመሆኑ አያሳይም። በአጠቃላይ አመልካችን ሟች በመሬት ላይ ጥል እየደበደበው እያለ የጩኸትና የኡኡታ ድምፅ ማስማቱ የወንጀል ግዙፍ ተግባር አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች ሟችን የመግደል ሃሳብ የነበረው ወይም በመላ ሃሣቡ አድራጎቱ የሚሰጠውን ውጤት የራሱ በማድረግ በወንጀለ ተካፊይ መሆኑን ተጠሪ በቂ ማስረጃ በማቅረብ እንዲላስረዲ ከሥር ፍርድ ቤት የውሣኔ ይዘት ለመገንዘብ ችለናል። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች ኡኡታና ጩኸት ማሰማቱ ለሟች መሞት ያስከተለ ተግባር ነው ብል በወንጀል ሕግ አንቀፅ 24 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት በምክንያትና በውጤት መካከል ግንኙነት እንዲለ ለመደምደም አይቻልም። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤት ሟች አመልካችን መሬት ላይ ጥል ሲደበድበው የጩኸትና ኡኡታ ድምፅ ባያሰማ ኖሮ፣ ሟችን በድንጋይ ደብድበው የገደለት ላልቹ ተከሳሾች ከቦታው አይደርሱም ነበር። ላልቹ ተከሳሾች ጩኸቱን ሰምተው መጥተው ሟች አመልካችን እየደበደበው ባያገኙት ኖሮ ሟችን በድንጋይ አይደበድቡትም ነበር የሚል ሕጋዊ መሰረት የላለው መነሻ በመያዝ አመልካችን በወንጀል ሕግ አንቀፅ 32/1/ እና አንቀጽ 540 የተመለከተውን በመተላለፍ ሟችን ለመግደል በተፈፀመው የወንጀል ድርጊት ተካፍሎል በማለት የሰጠው ውሳኔ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 23/1/ ንዐስ አንቀጽ 2፣ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32 ንዐስ አንቀጽ 1፣ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 24 ንዐስ አንቀጽ 1 እና የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 141 ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘት መንፈስና ዓላማ የሚጥስና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልትም ከላይ በዝርዝር የተገለፀውና የሕግ ስህተት ያለበትን የከፍተኛ ፍርድ ቤት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ማረምና ማስተካከል ሲገባቸው ውሣኔውን በአብላጫ ድምፅ ማፅናታቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው።
በአጠቃላይ ተጠሪ በሥር ፍርድ ባቀረበው የወንጀል ክስ በገለፀው ስፍራና ጊዜ ሟች ከመሬት ላይ ጥል ሲደበድበው አመልካች የኡኡታና ጩኸት ድምፅ ከማሰማቱ ውጭ አመልካች ሟች በላልች ተከሳሾች በድንጋይ ሲደበደብ በወንጀለ ዋና አድራጊነት /ተካፊይነት/ በአነሳሽነት፣ ወይም በአባሪነት የተሳተፈ መሆኑን ተጠሪ የማስረዲት ግዳታና ኃላፉነቱን አልተወጣም። ተጠሪ አመልካች የተከሰሰበትን የወንጀል ድርጊት ወይም ከተከሰሰበት የወንጀል ድርጊት ውጭ የሆነ በወንጀል የሚያስጠይቅ ድርጊት የፈፀመ መሆኑን በበቂ ማስረጃ እንዲላስረዲ የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ስላቀረበው ማስረጃ ይዘት በውሣኔው ካስፈረው ለመገንዘብ ችለናል። ተጠሪ አመልካች ሟችን ለህልፈት ባበቃው ድርጊት በመላ ድርጊቱ፣ ወይም ሃሣቡ ተሳታፉ መሆኑን በበቂ ማስረጃ ካላስረዲ የሥር ፍርድ ቤት አመልካች የመከላከያ ማስረጃ ማቅረብ ሳያስፈልገው በነፃ እንዱሰናበት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ቁ. 141 መሰረት በነፃ ማሰናበት ሲገባው አመልካች የመከላከያ ማስረጃ እንዱያቀርብ በማድረግ የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ መስጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ውሣኔ ማፅናቱ ከላይ የተገለፁትን የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎች የሚጥስና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈፅመዋል በማለት ወስነናል።
የትግራይ ብሓራዊ ክልል የምስራቃዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ እንደዚሁም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ፍርድ በማፅናት የሰጡት ውሣኔ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀፅ 2 /ለ/ -1 መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ከተከሰሰበት ወንጀል በነፃ ይሰናበታል በማለት በወንጀለኛ ሕግ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀፅ 2/ለ/ -1 መሰረት ወስነናል።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.