No summary available.
ሐምል 14 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴአመልካች ፡- ብሩክ ሚካኤል የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ፋዳራል ዐቃቤ ሕግ የቀረበ የለም መዝገቡ ተመረምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በወንጀል የቀረበውን ክርክር የሚመለከት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ የተጀመረ ነው። የክሱ ይዘትም አመልካች በ1996 ዓ/ም የወጣውን የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 675(1) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ የማይገባውን ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት በማሰብ ጥቅምት 02 ቀን 2002 ዓ/ም በግምት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ሲሆን በአቃቂ ቃሉቲ ክፍለ ከተማ ቀበላ 09 ውስጥ ካለው ኒያላ የቤትና የቢሮ እቃዎች ማምረቻ ድርጅት ውስጥ የድርጅቱ ንብረት የሆነውን አንድ ቱርቦ ቻርጀር ግምቱ ብር 46,000.00(አርባ ስድስት ሺህ ብር) እና አንድ ፑስተርነ ሪንግ ግምቱ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በአጠቃላይ ግምቱ ብር 56,000.00(አምሳ ስድስት ሺህ ብር) የሚያወጣ ንብረት ሉጠግን መጥቶ ንብረቶችን ከዚሁ ስለማይጠገኑ በራሴ ድርጅት ጠግኜ አመጣቸዋለሁ ብል ከወሰደ በሁዋላ ሳይመለሱ የቀሩ በመሆኑ ከባድ የእምነት ማጉደል ወንጀል ፈፅሟል በማለት ነው። አመልካችም ክሱ ደርሶትና ተነቦለት እንዱረዲው ከተደረደገ በሁዋላ ስለእምነት ክህደት ቃል ሲጠየቅ የድርጊቱን አፈፃፀም በተመለከተ የክህደት ቃለን ሰጥቷል። አቃቤ ሕግ በበኩለ አለኝ ያላቸውን ማስረጃዎች አቅርቦ ካሰማ በሁዋላ አመልካች የመከላከል መብታቻው ተጠብቆላቸው የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አሰምተዋል። የሥር ፍርድ ቤትም ጉዲዩን መርምሮ አመልካች በመከላከያ ምስክሮቻቸው የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን ሉያስተባብለ አልቻለም በሚል ምክንያት ክስ በቀረበባቸው ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ አድርጎ በአንድ አመት ከስድስት ወር እስራት እንዱቀጡ በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የስር ፍርድ ቤት የጥፊተኛነት ውሳኔ ሙለ በሙለ ሲጸና ቅጣቱን በተመለከተ ደግሞ የቅጣት መመሪያውን ያላገናዘበ ነው በሚል ምክንያት ወደ ሰባት ወር ቀላል እስራት ዝቅ ተደርጎ ተሻሽል ተወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ጉዲዩ የፍትሒ ብሓር ጉዲይ ከሚሆን በስተቀር በወንጀል የሚያስጠይቅበት አግባብ የለም ፣ የአቃቤ ሕግ ምስክሮች እንደክሱ አላስረደም ፣ የመከላከያ ምስክሮች ቃል ውድቅ የተደረገው ያላግባብ ነው የሚል ሲሆን አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች በወንጀል ጥፊተኛ ተብለው የመቀጣታቸውን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለትም መጥሪያው መድረሱ ተረጋግጦ ያልቀረበ በመሆኑ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነውን ውሳኔ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
በመሰረቱ አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለው ወንጀለን የሚያቋቋሙት ሕጋዊ ፣ ግዙፊዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ መሆኑን በአዋጅ ቁጥር 414/1996 የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23(2) በግልፅ ደንግጓል። እንግዱህ አንድን ድርጊት ወንጀል ነው ብል ለመወሰን ሕጋዊ ፣ ግዙፊዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች ተጣምረው መገኘት የግድ ይላል። ሕጋዊ ፍሬ ነገሮች የሚባለት ደግሞ ለጉዲዩ አግባብነት አለው ተብል የተጠቀሰውን ድንጋጌ ለማቋቋም ሙለ በሙለ መሟላት ያለባቸውን ነጥቦች የሚመለከት ሲሆን ግዙፊዊና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች የሚባለት ደግሞ እንደየቅደምተከተላቸው ከድርጊት ማድረግ ወይም አለማድረግና ከሐሳብ ክፍል ጋር በሕጉ አንቀፅ 24 ፣ 57 እና 58 ድንጋጌዎች ስር የተመለከቱት ሁኔታዎችን የሚመለከቱ መሆኑ ይታመናል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመጣ አመልካች መውሰዲቸው የተረጋገጠውን እቃ ወደ እጃቸው ያስገቡት ለጥገና በሚል ምክንያት ሲሆን ይህም ከንብረቱ ባለቤት ከሆነው ድርጅት ፈቃድ ያገኘ እንደነበር ፣ ከንብረቱ ባለቤት ከሆነው ድርጅት ውስጥ ሉጠገን ባለመቻለ ምክንያት ወደራሳቸው ድርጅት ወስደው ለመጠገን ጥያቄ ሲያቀርቡም ድርጅቱ ፈቅድላቸው አመልካች ንብረቶቹን እንደወሰደ በአቃቤ ክስና ማስረጃዎች የተገለፀና የተረጋገጠ ጉዲይ ሲሆን አመልካችም ግዳታዬን ተወጥቼአለሁ ከማለት በስተቀር ከንብረቱ ባለቤት ድርጅት ጋር የጥገና ውል የነበራቸው መሆኑን የሚክደት ጉዲይ አይደለም። እንግዱህ የንብረቶቹ ባለቤት የሆነው ድርጅት ንብረቶቹን ለማስጠገን መስማማቱ ከተረጋገጠና ለጥገና የሄደት ንብረቶች ተጠግነው ካልተመለሱ ከአመልካች የሚጠይቁት ጉዲይ ፍትሒ ብሓራዊ መፍትሓ ወይም ውልን መሰረት ያደረገ እንደሚሆን ግልፅ ነው። በውል መሰረት ግዳታውን ያልተወጣ ተዋዋይ ወገን እምነት አጉድሎል ተብል በወንጀል የሚጠየቅ ስለመሆኑ ስለእምነት ማጉደል የሚደነግጉት የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎችም ሆነ ላልች ድንጋጌዎች አያሳዩም። በመሆኑም በሕግ አግባብ ወንጀል ነው ተብል ያልተጠቀሰ ድርጊት በወንጀል የማያስጠይቅ መሆኑን ከወንጅል ሕግ አንቀጽ 23(2) ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ በግልፅ መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው።በዚህም መሰረት አመልካች ለጉዲዩ በወንጀል ጥፊተኛ የተባለት የፍትሒ ብሓር ይዘት ባለው ጉዲይ በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የወ/መ/ሕ/አንቀጽ 23(2) እና 675(1) ድንጋጌዎችን የጣሰ ሁኖ በመገኘቱ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.