No summary available.
ሐምል 28 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ህዝቦች ክልል የሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አልቀረቡም ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦች ህዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ የዋስትና ጥያቄን የሚመለከት ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታያው የስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ተጠሪዎች የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 676 ንኡስ አንቀጽ 1 የተመለከተውን በመተላለፍ ከባድ የእምነት ማጉደልና የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በማለት የወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።
ተጠሪዎች የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ክርክሩን እንድንቀጥል ይፈቀድለን በማለት አመልክተዋል። አመልካች ተጠሪዎች የተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ከአምስት ዓመት እስከ ሀያ አምስት ዓመት ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ የተደነገገ በመሆኑና ከአስር ዓመት በላይ በሚያስቀጣ የሙስና ወንጀል የተከሰሰ ሰው የዋስ መብት እንደማይፈቀድለት በአዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 4 የተደነገገ በመሆኑ በዋስትና ወረቀት ሉለቀቁ አይገባም በማለት ተከራክሯል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 4ን በመጥቀስ ተጠሪዎች በማረሚያ ቤት ሆነው እንዱከራከሩ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ተጠሪዎች የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበዋል።፡ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 4 ከአስር ዓመት በላይ በሚያስቀጣ የሙስና ወንጀል የተከሰሰ የሚለው ሀረግ አስር ዓመት ዝቅተኛው የቅጣት መነሻ ወይም ከፍተኛ የቅጣት ጣሪያን መሰረት በማድረግ እንደሚወስን ግልጽነት የጏደለው ነው። ተጠሪዎች የተከሰሱበት የወንጀል ህግ ድንጋጌ ዝቅተኛው መነሻ አምስት ዓመት ከፍተኛው ጣሪያ ሀያ አምስት ዓመት በመሆኑ ተጠሪ ላላ ዋስትና የሚያስከለክል ተጨማሪ ምክንያት ያላቀረበ ስለሆነ በዋስትና ወረቀት ሉለቀቁ ይገባል በማለት ወስኗል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠውን ውሣኔ አጽንቶታል።
አመልካች ታህሣስ 11 ቀን 2003 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ከአርሶ አደር በደረሰኝ የሰበሰቡትን ገንዘብ አንደኛ ተጠሪ ብር 382,895.01 ለመንግስት ገቢ ሣያደርጉ ከባድ የዕምነት ማጉደል ወንጀል የፈጸሙ መሆናቸዉን ሁለተኛው ተጠሪ ከሰበሰቡት ግብር ብር 333,940.91 ለመንግስት ገቢ ባለማድረጋቸዉ ከባድ የዕምነት ማጉደል ወንጀል ፈጽመዋል በማለት የወንጀል ህግ አንቀጽ 676 ንኡስ አንቀጽ 1ን በመጥቀስ ክስ አቅርበናል። ከአስር ዓመት በላይ በሚያስቀጣ የሙስና ወንጀል የተከሰሰ ተከሣሽ በዋስትና ወረቀት የማይለቀቅ መሆኑ በአዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 4 በግልጽ ተደንግጓል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት ይህንን ድንጋጌ በተመሣሣይ መንገድ በመተርጏም ተጠሪዎች በዋስ እንዱለቀቁ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪዎች የፍርድ ቤቱ መጥሪያ ደርሷቸው በቀነ ቀጠሮው መልስ ይዘው ያልቀረቡ በመሆኑ መልስ የመስጠት መብታቸዉ ታልፎል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና አመልካች ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት ተጠሪዎች በዋስትና ወረቀት እንዱለቀቁ የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ድንጋጌው ከአስር ዓመት በላይ በሚያስቀጣ የሙስና ወንጀል የተከሰሰ ሰው በዋስትና ወረቀት መለቀቅ እንደማይፈቀድለት ይደነግጋል። ተከሣሹ የከሰሰበት ወንጀል ከአስር ዓመት በላይ የሚያስቀጣ መሆኑን ወይም ከአስር ዓመት በላይ በእስራት የማያስቀጣ መሆኑን ለመወሰን ፍርድ ቤቶች ተከሣሹ የተከሰሰበት የህግ ድንጋጌ የሚደነግገውን ዝቅተኛውን የመነሻ ቅጣት ነው መሰረት የሚያደርጉት ወይም ተከሣሹ በተከሰሰበት ወንጀል በህጉ የተደነገገውን ከፍተኛውን የቅጣት ጣሪያ የሚለውን ነጥብ ለመተርጏም በመጀመሪያ የጸረ ሙስና ልዩ የሥነ ምግባርና ልዩ የማስረጃ ህግ በልዩ ሁኔታ መደንገግ ያስፈለገበትን ምክንያትና የጸረ ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ህግን በማወጅ ህግ አውጭው ሉያሳካው የፈለገውን ግብ መመልከት አስፈላጊ ነው። ህግ አውጭው የሙስና ወንጀል ያለውን ልዩ ባህሪ ግምት ውስጥ በማስገባት ሙስናን ለማጋለጥ ሙስናን ለመመርመርና የሙስና ክስን ውጤታማ ለማድረግ በማሰብ የጸረ ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ህግ አዋጅ በመሆኑ በአዋጅ መግቢያ ላይ ግልጽ አድርጓል። ስለሆነም የአዋጁ ድንጋጌዎች ትርጉምና ተግባራዊ አፈጻጸም ይህንን የህግ አውጭውን መሰረታዊ ግብ የሚያሣካ በሚሆንበት መንገድ መተርጏምና ስራ ላይ ማዋል ፍርድ ቤቶች ሉከተለት የሚባው አተረጓጏም መርህ ነው።
በሁለተኛ ደረጃ አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 4 ድንጋጌ በልዩ ሁኔታ አሁን ያለውን ቅርጽና ይዘት እንዱኖረው ተደርጏ የተደነገገበትን መሰረታዊ ምክንያት ማየት ያስፈልጋል። አዋጅ ቁጥር 434/97 በአዋጅ ቁጥር 236/93 እና አዋጅ ቁጥር 239/93 የታወጀውን የፀረሙስና ልዩ የሥነ ሥርአት ሕግ የማስረጃ ህግ ለማሻሻል የወጣ የህግ ማእቀፍ ነው። የአዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 4 በአዋጅ ቁጥር 239/93 አንቀጽ 2 በሙስና ተጠርጥሮ የተያዘ ማናቸውም ሰው የዋስትና መብት አይኖረውም በማለት የተደነገገውን ለማሻሻል ታስቦ የተደነገገ ድንጋጌ ነው። ድንጋጌው ዓላማ ሁለንም በሙስና ወንጀል የተከሰሱ ሰዎች የዋስ መብት በህግ ከመከልከል ይልቅ የተከሰሱበት ወንጀል የሚያስከትለውን ከፍተኛውን የቅጣት ጣሪያ መሰረት በማድረግ በቀላል የሙስና ወንጀል የተከሰሰና ከአስር ዓመት በታች በሚያስቀጣ የሙስና ወንጀል የተከሰሱት በዋስትና የሚለቀቁበትና የዋስትና መብታቸው የሚጠበቅበትና በከባድ ሙስና ወንጀልች የተከሰሱትና የተከሰሱበት ወንጀል ከዓስር አመት በላይ የሚያስቀጣ በሆነ ጊዜ በማረሚያ ቤት ሆነው እንዱከራከሩ ለማድረግ ታስቦ የወጣ ድንጋጌ መሆኑን የአዋጅ ቁጥር 434/97 ሀተታ ዘምክንያት በግልጽ የሚያሳይ በመሆኑ የአዋጅ ቁጥር 434/97 ንዐስ አንቀጽ 4 ድንጋጌ ከዚሁ አንፃር መተርጉምና ተፈፃሚ መሆን የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል። በሶስተኛ ደረጃ የአዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 4 ድንጋጌ ውጤታማ በሚሆንበት መንገድ መተርጏምና ሥራ ላይ መዋል ይኖርበታል። በወንጀል ህጉ በአንቀጽ 404 ንዐስ አንቀጽ 4 የሙስና ወንጀል እንደሆኑ የተዘረዘሩት የወንጀል ድንጋጌዎች በአብዛኛው ዝቅተኛው የመነሻ ቅጣት ከአስር ዓመት በታች እንደሆነ የድንጋጌዎቹን ይዘትና የሚያስከትለትን አነስተኛ ቅጣትና ከፍተኛ የቅጣት ጣሪያ በማየት ለመገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም ተከሳሹ የተከሰሰበትን ዝቅተኛ የቅጣት መነሻ በማድረግ አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 4 የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የይግባኝ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ትርጓሜ ድንጋጌውን ውጤታማ በሆነ ሁኔታ ተፈፃሚ የማያደርግና ህግ አውጭው የፀረሙስና ልዩ የሥነ ሥርዐትና የማስረጃ ህግን በማውጣት ለማሳካት የሚፈልገውን ግብ የማያሳካና ህግ አውጭው ድንጋጌውን ሲያውጅ የነበረውን መሰረታዊ ሀሳብ ያላገናዘበ ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ በዝርዝር ባስቀመጥናቸው ምክንያቶች የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የአዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 4 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ ተጠሪዎች የተከሰሱበት የወንጀል ህግ ድንጋጌ ለወንጀል የሚደነግገውን ከፍተኛ የቅጣት ጣሪያ ሣይሆን ዝቅተኛውን የቅጣት መነሻ መሰረት በማድረግ መተርጏም አለበት በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
1 የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሳኔ ተሽሯል።
2 ተጠሪዎች የተከሰሱበት የወንጀል ህግ አንቀጽ 676 ንኡስ አንቀጽ 1 እስከ ሀያ አምስት ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ በዋስትና ወረቀት ሉለቀቁ አይገባም በማለት በአዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 4 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት ወስነናል።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.