No summary available.
ሐምል 14/2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- 1- አቶ አደም አብደ የቀረበ የለም 2- አቶ ጀማል አሉ ተጠሪ፡- የፍደራል ሥነ - ምግባርና ፀረ - ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ሕግ ዋልተንጉስ ፍቅሬ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ አመልካቶች በተከሰሡበት የሙስና ወንጀል የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት በግራ ቀኙ መካከል የነበረውን የቅድመ ክስ ክርክር ሂደት ከሰማ በኋላ ወደ ዋና ክስ እንዱገባና የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች እንዱሰሙ የመወሰኑን እና ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ይሄንኑ ትዕዛዝ የማፅናቱን አግባብነት ለመመርመር የቀረበ ነው።
አመልካቾች ቅሬታቸውን ከላልች 3ኛ እና 4ኛ አመልካቾች ከነበሩት እና ጉዲያቸው አያስቀርብም ከተባለት ጋር ያቀረቡ ሲሆን ሰኔ 23 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በ3 ገፅ በተፃፈ አቤቱታ የአሁን አመልካቾችን የሚመለከተው ክፍል ፍሬ ሃሣብ ከሣሽ የአሁን አመልካቾችን ከገቢያቸው በላይ ንብረት አፍርተዋል በማለት ስለተከሣሾቹ የያዘው የሀብት ማስረጃ ሣይኖር በወ/መ/ሕግ ቁ 419/ለ/ መሰረት ክስ ማቅረቡ ያለአግባብ ነው በሚል ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ በቀን 21/4/2003 ዓ.ም በሁለት ገፅ የሰጠው የመልስ ፍሬ ሃሣብ አመልካቾች የለሲ አንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር አባል ብቻ ሣይሆኑ በአፊር ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የሥራና ከተማ ልማት ቢሮ ውስጥ ባላቸው ኃላፉነት በመጠቀም ማህበሩ ያለአግባብ ጨረታዎቹን እንዱያሸንፍ አድርገዋል።
ከገቢያቸው ጋር ያልተመጣጠነ ንብረት አፍርተዋል በማለት የከሰሰ ሲሆን ወደ ክሱ ሲገባ በማስረጃ ነጥሮ የሚወጣ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ወደ ዋና ክስ እንድንገባ መወሰኑ በአግባቡ በመሆኑ የቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል።
በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የክርክር ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። በዚሁ መሰረት የወንጀል ጉዲዩን እየተመለከተ ያለው ፍርድ ቤት የቅድመ ክሱን ክርክር በመስማት ወደ ዋናው ክስ ተገብቶ ምስክር እንዱሰማ መወሰኑ በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ ተይዞ የተያዘው ጉዲይ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
በዚህ መሰረት በሙስና ወንጀልች ላይ የቅድመ ክስ ዝግጅት የሚመራበት አግባብ በአዋጅ ቁ 434/97 አንቀጽ 35 እስከ 41 ድረስ የተዘረዘሩ ሲሆን ሂደቱ ውስጥ ማለፍ አስገዲጅ ያልሆነና እንደ ክሱ ዓይነት ታይቶ የክሱ ጭብጦችና ማስረጃው ዝርዝር ውስብስብ በመሆኑ የፍርድ ሂደቱን ሉያራዝምና ሉያወሣስብ ይቻላል ብል ፍርድ ቤቱ ሲገምት ሉያዝ የሚችል ስለመሆኑ የዚሁ አዋጅ አንቀጽ 35 በግልፅ ያስቀምጣል።
የቅድመ ክስ ዝግጅት ዓላማ ለክሱ አወሣሰን ሉረደ የሚችለ ጭብጦችን ለመለየት ፣ ባለጉዲዮች ጭብጦችን እንዱረደ ማድረግ ፣ የክሱን ሂደት ለማፊጠንና ችልቱ አካሄደን ለመምራት እንዱችል ለማስቻል ስለመሆኑ በአዋጅ ቁ 434/97 አንቀጽ 36/1/ ሥር የተዘረዘረ ሲሆን የማስረጃዎች ተቀባይነት ላይ እና መደበኛው ክስ ከመጀመሩ በፉት ውሣኔ ሉያገኙ በሚገባቸው የህግ ጥያቄዎች ላይ ውሣኔ የሚሰጥ ስለመሆኑ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 36/2/ ሥር ተደንግጓል።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካቾች ከገቢያቸው በላይ ንብረት አፍርተዋል በማለት የተከሰሡ በመሆኑ ጉዲዩን የያዘው ፍርድ ቤት የቅድመ ክሱን ሂደት ካዲመጠ በኋላ ወደ ዋና ጉዲዩ ተገብቶ ምስክሮች ይሰሙ በማለት ትዕዛዝ መስጠቱ በአመልካቾች ላይ ከቀረበው ክስ አኳያ ሲታይ የተከሰሱበት ጉዲይ በማስረጃ የሚጣራ ከመሆኑ አኳያ ተፈፀመ ልባል የሚችል መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም። በተጨማሪም በዚህ ቅድመ ክስ ዝግጅት ሂደት ውስጥ መታለፍ ራሱ አስገዲጅ በሆነ ሁኔታ የተቀመጠ ባለመሆኑና ፍርድ ቤቱ የጉዲዩን ውስብስብነት እየተመለከተ የሚወሰነው ጉዲይ በመሆኑ የቀረበው የወንጀል ክስ በማስረጃ እንዱጣራ መታዘዙ ቅሬታ የሚቀርብበት ላሆን አይገባም ብለናል። በዚሁ መሰረት የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ዋና ክስ ተገብቶ ምስክሮች ይሰሙ በማለት የሰጠው ብይን እና ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝ. ሰኔ 11 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝ. መጋቢት ዐ9 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሣኔ በተሻሻለው የፀረ ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና ማስረጃ ህግ አዋጅ ቁ 434/97 አንቀጽ 40 መሰረት ፀንቷል።
የቅድመ ክስ ዝግጅት ሂደት እንደተጠናቀቀ በወንጀል ክሱ የተመለከቱት ነጥቦች ላይ ምስክሮች እንዱሰሙ መታዘዙ በአግባቡ ነው ብለናል።
No topics extracted.