No summary available.
ሰኔ 03 ቀን 2003 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ አሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ፋዳራል ዐቃቤ ህግ - ዐ/ህግ አበባው መንግስቱ ቀረበ።
ተጠሪ፡- በሪሁን ፍቃደ - የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የወንጀል ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። በዚህ ፍ/ቤት የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ ላይ የመሰረተው የወንጀል ክስ ተጠሪ በ1996 ዓ/ም በወጣው የወ/ህ/አንቀጽ 540 ስር የተመለከተውን በመተላለፍ መስከረም 15 ቀን 2002 ዓ.ም ከላሉቱ በግምት 8፡30 ሲሆን በቂ/ክ/ከተማ ቀበላ 02/03 ልዩ ቦታው ‘’ኤልሲባር’’ አካባቢ ሟች ከድር አብደልቃር ያሽከረክር ከነበረው መኪና ሲወርድ ልትገጨን ነው እንዳ በማለት የሟችን ግንባር በቦክስ መትቶ ከጣለው በሁዋላ በወደቀበት ግንባሩንና ሆደን ደጋግሞ በመረጋገጥ በብርጭቆ ጭንቅላቱን በመምታት ለከፍተኛ ጉዲት በመዲረግ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ሕይወቱ እንዱያልፍ በማድረጉ ተራ የሆነ ሰው ግድያ ወንጀል ፈጽሟል የሚል ነው። የአሁኑ ተጠሪም የዐቃቤ ሕጉን ክስ በመካደ ዐቃቤ ሕግ እንደክሱ ሉያስረደ የሚችለ ማስረጃዎች ያለት መሆኑን ገልጾ ማስረጃዎቹ ከተሰሙ በሁዋላ የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ድርጊቱን መፈፀሙ ተረጋግጦበታል በሚል ምክንያት እንዱከላከል አድርጎ የመከላከያ ምስክሮች እንዱያሰማ መብቱን ጠብቆለት የመከላከያ ማስረጃዎቹን አሰምቷል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ጉዲዩን መርምሮ ተጠሪ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን በመከላከያ ማስረጃዎቹ ያላስተባበለ መሆኑን ዘርዝሮ የመከላከያ ማስረጃዎቹን ቃል ውድቅ ከአደረገ በሁዋላ ተጠሪን በዓቃቤ ሕግ በኩል ተጠቅሶ በቀረበበት ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ አድርጎ በ3/ሦስት/ አመት ጽኑ እስራት እንዱቀጣ ሲል ወስኗል።
በተጠሪ ላይ በተላለፈው የቅጣት ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ የቅጣት ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች በቁጥር 3-9590/02 በቀን 11-12-2002 ዓ.ም በተፃፈ 5/አምስት/ ገፅ የሰበር አቤቱታ የበታች ፍርድ ቤቶች በቅጣት አወሳሰን ረገድ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ፈፅመዋል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርቧል። ይዘቱም ባጭሩ፡- ተጠሪ ጥፊተኛ ከተባለት ድንጋጌ መነሻ ቅጣት ወርድ ቅጣት መሰጠቱ የወ/መ/ሕ/ቁጥር 189/1/ ድንጋጌን ይዘትና መንፈስ ያላገናዘበ በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም ተጠሪ ጥፊተኛ ከተባለበት ድንጋጌ መነሻ ቅጣት ዝቅ ተደርጎ በሦስት ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት መቀጣታቸው ባግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ነጥብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጓል። በዚህም መሰረት ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች አኳያ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ የበታች ፍርድ ቤቶች የቅጣት አወሳሰን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት ወይስ የለበትም? የሚለው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ሟች ከድር አብደልቃድር ያሽከረክር ከነበረው መኪና ሲወርድ ‛ልትገጨን ነው እንዳ?‛ በማለት የሟችን ግንባር በቦክስ መትቶ ከጣለው በሁዋላ በወደቀበት ግንባሩንና ሆደን ደጋግሞ በመረጋገጥ በብርጭቆ ጭንቅላቱን በመምታት ለከፍተኛ ጉዲት በመዲረግ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ህይወቱ እንዱያልፍ ማድረጉ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ጉዲይ መሆኑን ነው። በመሆኑም ለወንጀል ድርጊቱ መፈፀም ወይም መሰራቱ እንዱሁም ድርጊቱን የፈጸሙት ወይም የሰሩት ተጠሪ መሆናቸው በሚገባ መልኩ እና በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23 ስር በተመለከተው ድንጋጌ መሰረት የተረጋገጠ ስለመሆኑ ከክርክሩ ሂደት በመገንዘብ በቅጣቱ ላይ የተሰጠውን ውሳኔ ሕጋዊነት ተመልክተናል።
የአመልካች መሰረታዊ ክርክር የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ጥፊተኛ የተባለበት ድንጋጌ ከሚያስቀጣው ድንጋጌ መነሻ ቅጣት ዝቅ በማለት የሰጡት የሦስት አመት ፅኑ እስራት ቅጣት በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡትን ፍሬ ጉዲዮችና የቅጣት አወሳሰኑን በተመለከተ የወንጀል ህጉ ያስቀመጣቸውን መርሆዎች ያላገናዘበ ነው የሚል ነው። እኛም ይህንኑ ቅሬታ ከህጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
በመሰረቱ የኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ የወንጀል ህግ የአገሪቱን የወንጀል ህግ ግብ በአዋጅ ቁጥር 414/1996 አንቀጽ 1 ስር ሲደነግግ ‛የወንጀል ህግ ወንጀል እንዲይፈፀም መከላከል ሲሆን ይህንን የሚያደርገው ስለ ወንጀልችና ስለ ቅጣታቸው በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ማስጠንቀቂያነቱ በቂ ባልሆነበት ጊዜ ወንጀል አድራጊዎቹ ተቀጥተው ላላ ወንጀል ከመፈፀም እንዱቆጠቡና ለላልች ማስተማሪያ እንዱሆኑ ወይም እንዱታረሙ በማድረግ ወይም ተጨማሪ ወንጀልች እንዲይፈፀሙ እርምጃዎች እንዱወሰደባቸው በማድረግ ነው‛ በማለት ያስቀምጣል። ህጉ በአንቀጽ 87 ላይ ቅጣቶችና የጥንቃቄ እርምጃዎች ህጉ ሉደርስበት ያሰበውን ዓላማ ለማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ በህጉ መንፈስ መሰረት መፈፀም እንዲለበቸው በመርህ ደረጃ ይደነግጋል። ይኸው አንቀጽ ቅጣቶችና የጥንቃቄ እርምጃዎቹ ምንጊዜም ሰብዓዊ ክብርን በሚጠብቅ መንገድ መፈፀም እንደሚኖርባቸው ያስገነዝባል። የወንጀል ህጉ አንቀጽ 88 ሲታይም የቅጣቶች እና የጥንቃቄ እርምጃዎች አወሳሰንን በተመለከተ ዘርዘር ያለ ንዐስ ድንጋጌዎችን አካቶ ይዟል። በዚህ አንቀጽ ስር ያለ ንዐስ አንቀጾች የሚያሳዩት ፍርድ ቤቱ ቅጣቶችንና የጥንቃቄ እርምጃዎችን የሚወስነው የወንጀል ህጉን ጠቅላላ ክፍል ድንጋጌዎችን እንዱሁም ስለወንጀልችና ስለ ቅጣታቸው የሚደነግጉትን የልዩ ክፍለ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ መሆኑን፣ ቅጣት ሉወሰን የሚገባው የወንጀል አድራጊውን ግላዊ የአደገኛነት መጠን ያለፈ የህይወት ታሪኩን ወንጀል ለማድረግ ያነሳሱትን ምክንያቶችና የሃሣቡን ዓላማ የግል ኑሮውን ሁኔታ፣ የትምህርቱን ደረጃ፣ እንዱሁም የወንጀለን ከባድነትና የአፈፃፀሙን ሁኔታዎች በማመዛዘን መሆኑን፣ የወንጀል ህግ ልዩ ክፍል ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ፍርድ ቤቱ እጅግ ቀላል ከሆነው ቅጣት አንስቶ እስከ ከባደ ድረስ ያለውን በጥንቃቄ በመመርመር ለእያንዲንደ ጉዲይ ተገቢ የሆነውን ቅጣት እንደሚወስንና የቅጣት አወሳሰን ትክክለኛነትና አንድ ወጥነት ለማረጋገጥ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የቅጣት አወሳሰን መመሪያ (manual) እንደሚወጣ የሚያስገነዝቡን ናቸው።
ከላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች የምንረዲው አቢይ ነጥብ ቅጣቶች መወሰን ያለባቸው የህጉን መንፈስ በመከተል ዓላማዎችና ግቦቹንም ተፈፃሚ በማድረግ ሀሣብ መሆኑን ነው። የህጉን መንፈስ ከመተግበር አኳያ ወንጀለኛውን ማዕከል የማድረግ ፅንሰ ሀሣብ አፅንኦት የተሰጠው ጉዲይ ነው። ዳኞች በፅንሰ ሀሣቡ መሰረት የተሰጣቸውን አመዛዝኖ የመወሰን ስልጣን (Discretion) በስራ ላይ ሲያውለ ሰብአዊ ክብርን ከማስጠበቅ ዓላማ ጋር መሆን ያለበት ከመሆኑም በላይ ህግ አውጪው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 87 እና 1 ስር የተመለከቱትን መሰረት በማድረግ ዳኞች የቅጣት ውሣኔ በምን መንገድ መወሰን እንደሚገባቸው በአንቀጽ 88 ስር አስቀምጧል። በወንጀል ህጉ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ስንመለከትም ዳኞች ከተሰጣቸው የቅጣት ክልል ሳይወጡ የአጥፉውን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ቅጣት እንዱወስኑ ህጉ ስልጣን የሰጣቸው መሆኑ ነው። ዳኞች አጥፉውን በተመለከተ ከግምት ውስጥ ሉያስገቡዋቸው የሚገባቸው በርካታ የአጥፉ፣ ሁኔታዎች ቢኖሩም የቅጣት አወሳሰናቸው መሰረት የሚያደርገው የወንጀል አድራጊውን ግላዊ የአደገኛነት መጠን /degree of individual guilt/ ስለመሆኑ የአንቀጽ 88/2/ ድንጋጌ ይዘትና አቀራረፅ ያስረዲል። ይህም በሕጉ አግባብ የወጣውና ከግንቦት 09 ቀን 2002 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሆነው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ እንደተጠበቀ ሁኖ በቅጣት አወሳሰን ወቅት ዳኞች ሰፉ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ጠቋሚ ነው። አንቀጽ 88/2/ በመጀመሪያ ደረጃ የወንጀል አድራጊውን የአደገኛነት መጠን መሰረት በማድረግ ዳኞች ቅጣት እንዱወስኑ ማድረጉና ይህንን ሲወስኑም በድንጋጌው የተመለከቱትን የወንጀለን አፈፃፀም የአጥፉውን ያለፈ የህይወት ታሪኩን እና የኑሮ ሁኔታ ከግምት በማስገባት በማመዛዘን ለወንጀለኛው የሚገባውን የቅጣት መጠን እንዱወስኑ መደንገጉ የቅጣት ውሣኔዎችንና እርምጃዎችን እየተራራቁ እንዲይወስኑ የማድረግ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብል ከመታሰቡም በተጨማሪም ችግሩ የሚቀረፍበትና የሚቀነስበትን ሥርዓትም ህጉ ዘርግቷል። ዳኞች ቅጣት ሲወስኑ በህጉ አንቀጽ 88/2/ ለአጥፉው ተገቢ ነው ያለትን ቅጣት ከወሰኑ በኋላ በህጉ የተመለከቱትን የማቅለያና የማክበጃ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ቅጣቱን ከፍ ወይም ዝቅ ለማድረግ የሚችለ ስለመሆኑ ህጉ ያሳያል።
የኢ.ፋ.ዱ.ሪ. የወንጀል ህግ በአንቀጽ 82/1/ ከፉደል /ሀ/ እስከ ፉደል /ሰ/ ድረስ ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶችን ካስቀመጠ በኋላ በአንቀጹ ንዐስ ቁጥር ሁለት ስር በንዐስ ቁጥር አንድ ስር የተመለከቱት የማቅለያ ሁኔታዎች በህጉ ልዩ ክፍል ተካተው ሲገኙ በድጋሚ በማቅለያነት ዳኞች እንዲይጠቀሙ ያሳስባል። የህጉ አንቀጽ 84 ደግሞ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶችን የዘረዘረ ሲሆን ዳኞች የህጉን አንቀጽ 183 ባገናዘበ መልኩ ቅጣት የሚያከብደባቸውን ሁኔታዎች ያሳያል። ዳኞች ቅጣትን የሚቀንሱትም ሆነ የሚያከብደት ተገቢ ሁኖ ሲገኝ ስለመሆኑ የአንቀጽ 179 እና 183 ድንጋጌዎች ያሳያለ። አንቀጽ 179 የቅነሣውን ገደብ የሚያሳይ ሲሆን ከዚህ መደበኛ ቅነሣ በተጨማሪ ልዩ ቅነሣ ለማድረግ እንደሚቻልም ህጉ በአንቀጽ 180 ስር አስቀምጧል። በህጉ አንቀጽ 86 ቅጣትን በማቅለልም ሆነ በማክበድ ረገድ ከህጉ አንቀጽ 179፣ 182 ውጪ የሆኑ ምክንያቶች ሲያጋጥማቸው ዳኞች ምክንያታቸውን በመግለፅ ቅጣቶችን ለመቀነስ ወይም ለማክበድ እንደሚችለ ተደንግጓል። እነዚህ ስለቅጣት አወሳሰን በህጉ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ሲታዩ የሚያስገነዝቡን አቢይ ነጥብ ቅጣቶችን በመጣልና እርምጃዎችን በመውሰድ ረገድ ዳኞች አመዛዝነው የመወሰን ከፍተኛ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ነው። እንግዱህ ህጉ ለዳኞች የሰጠውን አመዛዝኖ የመወሰን ስልጣን ተግባራዊ የሚሆንበትን ሁኔታና በሕጉ የሰፈረውን የቅጣት አጣጣል መርህ ከላይ ተመልክተናል። ዐ/ህግ በዚህ ረገድ ያቀረቡትን ቅሬታ ስንመለከተው ከመነሻው ቅጣቱ እንዱወርድ የተደረገው ልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ሳይኖርና እና የቅጣት ማቅለያው አለ ቢባል እንኳ የወንጀለ ማቋቋሚያ የሆነው ነገር ስለመሆኑ ጠቅሶ መከራከሩን የሚያሳይ ነው። እኛም ጉዲዩን ስንመለከተው የስር ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ቅጣቱን ሲጥል በማቅለያነት የያዘው ድርጊቱ በድንገተኛ አጋጣሚ መፈጸሙን፣ በተጠሪ ላይ ሪኮርድ ያለመቅረቡንና በወቅቱ የነበረው ያልተገባ የሟች መኪና አነዲድ የፈጠረው ጫና ነው የሚለትን ምክንያቶችን ነው። ይሁን እንጂ ተጠሪ የተከሰሱትና ጥፊተኛ የተባለት ተራ በሆነ የሰው ግድያ ወንጀል ሲሆን ድርጊቱ በድንገት የተፈፀመ ነው የሚለው ምክንያት ተጠሪ የተከሰሱበትን የወንጀል ድርጊት የሚያቋቁም ነው ከሚባል በስተቀር በቅጣት ማቅለያነት በድጋሚ ሉወሰድ የሚችል ሕጋዊ ምክንያት አይደለም። በክርክሩ ሂደት የተረጋገጠውን የወንጀለን ማቋቋሚያ ፍሬ ነገር ፍ/ቤቱ ይዞ በቅጣት ማቅለያነት መወሰደም የወንጀል ህጉ በአንቀጽ 82/2/ ስር ያስቀመጠውን መርህ የሚጻረር ሲሆን ይኸው ሕግ በአንቀጽ 86 ስር ለዳኞች የሰጠውን ስልጣንም መሰረት ያደረገ ነው ልባል የሚችል አይደለም።
ፍርድ ቤቱ በወንጀል ህጉ ቁጥር 540 ስር የተመለከተውን መነሻ ቅጣት ተገቢ መስል ሲታየው በህጉ አንቀጽ 108/1/ የተመለከተውን የፅኑ እስራት ቅጣት መነሻ ሳይወርድ ማቅለል የሚችል ስለመሆኑ የአንቀጽ 179/ሐ/ ድንጋጌ ያሳያል። ከዚህ በህጉ ለዳኞች ከተሰጠው ስልጣን አኳያ ተገቢነት ያለው ውሳኔ ተሰጥቷል ልባል የሚችለው በጠቅላላ ወይም ልዩ ቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ስር የሚወድቁና የወንጀለ ማቋቋሚያ ያልሆኑ ማቅላያ ምክንያቶች መገኘታቸው ሲረጋገጥ ነበር። በተያዘው ጉዲይ ድርጊቱ በድንገተኛ አጋጣሚ የተፈፀመ ነው የሚለው ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት የወንጀል ድርጊቱ መቋቋሚያ ከሚሆን በስተቀር በወ/መ/ሕጉ አንቀጽ 82/2/ እንደተመለከተው በድጋሚ በቅጣት ማቅለያነት ሉያዝ የሚችል አይደለም። በዚህ ምክንያት የቅጣት ማቅለያ አይሆንም እንጂ ይሆናል ቢባል እንኳ ተጠሪ ሟችን ለሕልፈተ - ሕይወት ሲዲርግ የድርጊቱ አፈፃፀም ከባድ የነበረ መሆኑን የክርክሩ ሂደት በግልፅ የሚያሳይ በመሆኑ ተጠሪ ጥፊተኛ የተባለት ድንጋጌ ሉያስቀጣ ከሚችለው መነሻ ቅጣት መውረድም ሆነ መነሻ ቅጣቱን ለመጣል የሚያስችል ሕጋዊና በቂ ምክንያት አይደለም። ስለሆነም ድርጊቱ በድንገተኛ አጋጣሚ የተፈጸመ ነው የሚለው ምክንያት በቅጣት ማቅለያነት መወሰደ ከድርጊቱ አፈፃፀም አንጻር ሲታይ የበታች ፍርድ ቤቶች በህጉ ለዳኞች የሚሰጠውን አመዛዝኖ የመወሰን ስልጣንን ሲጠቀሙ በቅጣት አወሳሰን ረገድ ህጉ ያስቀመጣቸውን መሰረታዊ መርሆዎች በተለይም በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 82/2/ እና 189 ስር የተመለከቱትን፤ ጥሰው መገኘታቸውን የሚያሳይ ሁኖ አግኝተናል። ተጠሪ የወንጀል ሪኮርድ የላለባቸው መሆኑም ቅጣቱን ከመነሻው ለመውረድ የሚያሰችል አይደለም። ሲጠቃለልም በተጠሪ ላይ የተጣለው ቅጣት የወንጀል ሕጉን መሰረታዊ ግብና ዓላማ እንዱሁም የቅጣት አወሳሰን መርሆዎች ከድርጊቱ አፈጻጸም ጋር ያገናዘበ ባለመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
በፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት በወ/መ/ቁ. 87623 ሚያዝያ 22 እና 26 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ሐምል 09 ቀን 2002 ዓ.ም የጸናው ውሳኔ በወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ 195/2//መ/ መሰረት ተሻሽል ተጠሪ ሉቀጣ የሚገባው በጉዲዩ ላይ የታሰረው የሚታሰብለት ሁኖ በአስር አመት ጽኑ እስራት ነው በማለት ወስነናል።
ውሳኔው የተሻሻለ መሆኑን አውቆ ቅጣቱን ተከታትል እንዱያስፈጽም ለማ/ቤቱ ይፃፍ ብለናል።
No topics extracted.