No summary available.
15/10/2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ አደኛ አንበል - ጠበቃ ሰለሞን እምሩ ከቀረቡ ተጠሪ፡- የፍደራል ዐቃቤ ሕግ ወርቅነህ ዘነበ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የአሁን ተጠሪ ባቀረበው የወንጀል ክስ በፋ/የከፍተኛ ፍ/ቤት የተጀመረ ሲሆን ቀርቦ የነበረው ክስ፡- 1ኛ ክስ ተከሣሽ በ1996 ዓ.ም የወንጀል ህግ አንቀጽ 693/1/ ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ የቢ.ኤ.ኦሜጋ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ ማህበር ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ይሰራ በነበረበት ወቅት በባንክ የሚያዝበት በቂ ገንዘብ ያለመኖሩን እያወቀ በ05/2/01 ዓ.ም ከዲሸን ባንክ ጥቁር አንበሣ ቅርንጫፍ ወጪ ሆኖ የሚከፈል ብር 3,ዐዐዐ,ዐዐዐ /ሶስት ሚሉዮን ብር / የያዘ ቁጥሩ ኤች 257/638 የሆነ ቼክ ለአቶ ፍትዊ ወልዲይ ፈርሞ ከሰጠ በኋላ በ15/7/01 ዓ.ም ቀርቦ ክፍያ ሣይፈፅሙለት በመመለሱ በፈፀመው ገንዘብ ሣይኖር ቼክ ማውጣት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው።
2ኛ ክስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወ.ህ በአንቀጽ 693/1/ ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ በ1ኛ ክስ የተጠቀሰው የንግድ ድርጅት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ይሰራ በነበረበት ወቅት በባንክ የሚያዝበት በቂ ገንዘብ አለመኖሩን እያወቀ በዐ6/2/2002 ዓ.ም ከላይ ከ1ኛ ክስ በተመለከተው ዲሸን ባንክ ቅርንጫፍ ወጪ ሆኖ የሚከፈል ብር 3ዐዐ,ዐዐዐ /ሶስት መቶ ሺህ ብር/ የያዘ ቁጥር ኤች 257/680 የሆነ ቼክ በ1ኛው ክስ ስማቸው ለተጠቀሰው ግለሰብ ፈርሞ ከሰጠ በኋላ ቼኩ በ11/07/01 ዓ.ም ለባንክ ቀርቦ በቂ ገንዘብ የለውም ተብል ክፍያ ሳይፈፀምለት በመመለሱ የሚያዝበት ገንዘብ ሳይኖር ቼክ በማውጣት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው።
3ኛ ክስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወ/ህግ አንቀጽ 3ዐ2/1/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ የላላውን ሰው መብት ወይም ጥቅም ለመጉዲት አስቦ በቦላ ክ/ከተማ ቀበላ 12/13 ክልል ልዩ ቦታው ዲሚና ሩፊ ህንፃ ላይ ከሚገኘው ቢ.ኤ ኦሜጋ ኃ/የተ/የግ ማህበር ውስጥ የማህበሩ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ሲሰራ በእጁ የነበረ ለሥራ አስኪያጅ አቶ በላይነህ ሰርጉአለም ብቻ የሚፈረም የዲሸን ባንክ ጥቁር አንበሣ ቅርንጫፍ ቼክ ውስጥ ሐምል 1 ቀን 2000 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 4፡ዐዐ ሰዓት ሲሆን TF 4948565 የሆነ ቼክ የግል ተበዲይ በላይነህ ሰርጉአለም ፊርማን አስመስል ፉርሞ ከማህበሩ ገንዘብ ጠያቂ ለነበረው ሞክሮ ጀነራል ኮንተራክተር 225,477.38/ሁለት መቶ ሃያ አምስት ሺህ አራት መቶ ሰባ ሰባት ብር ከሰላሣ ስምንት ሣንቲም/ እንዱከፍል ለተወካዩ አቶ ኤልያስ ማሞ ከሰጠው በኋላ ቀኑ ይርዘም ቢቻል ሲለው በ17/8/08 የሚለውን እላዩ ላይ በ15/8/08 በሚል አስተካክል ለማረጋገጥ በላዩ ላይ የግል ተበዲዩን ፊርማ አስመስል ከቀኑ በላይ ፈርሞ በመስጠት በፈፀመው ሃሰተኛ ሰነድ በመፍጠር ላላው እንዱገለገልበት ማድረግ ወንጀል ተከሷል የሚል ነው።
አመልካች የቀረበባቸውን ክሶች አልፈፀምኩም ጥፊተኛ አይደሁም በማለት ተከራክሯል።
በዚሁ መሰረት ከሣሽ ( ዐ/ሕግ ) አለኝ ያለውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማቅረብ አሰምቷል።
ተከሣሽ/አመልካች/ መከላከያውን እንዲያቀርብ በተሰጠው መብት መሰረት የሰነድና የሰው ማስረጃ አቅርቦ አሰምቷል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ እና 2ኛ ክስ ተደራራቢ ወንጀል ነው ማለት ስለማይቻል በአንድ አንቀጽ ሥር በወ.መ.ሕግ ቁ 693/1/ ሥር ጥፊተኛ በማድረግ ሶስተኛውን ክስ በክሱ በተመለከተው አንቀጽ 382/1/ ሥር ጥፊተኛ በማለት የጥፊተኛነት ውሣኔ ሰጥቷል። ቅጣትን በተመለከተ ጥፊተኛ በተባለበት ሁለቱ አንቀጾች ሥር በ1 ዓመት ከ4 ወር ፅኑ እሥራት እንዱቀጡ ከወሰነ በኋላ በሁለት ዓመት የፈተና ጊዜ ገድቧል። በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት አመልካችም ሆኖ ተጠሪ ይግባኙ ለፋ/ጠ/ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን የአመልካች ቅሬታ ውድቅ ሲደረግ የአሁን ተጠሪ ይግባኝ ግን ተቀባይነት አግኝቶ በዐቃቤ ሕግ በቀረባቸው ሶስቱም ክስ ሥር ጥፊተኛ ነው በማለት ፍርድ ከሰጠ በኋላ ለ1ኛው ድርጊት 4 ዓመት ፅኑ እሥራት ፣ ለሁለተኛ ድርጊት 1 ዓመት ፅኑ እሥራት እና ለ3ኛው ድርጊት 1 ዓመት ፅኑ እሥራት ሆኖ ባጠቃላይ በ6 ዓመት ፅኑ እሥራት እንዱቀጣና በ1ኛ ና 2ኛ ድርጊቶች በተጨማሪ የገንዘብ መቀጮ ባጠቃላይ 11,ዐዐዐ/አሥራ አንድ ሺህ ብር/ እንዱቀጣ በማለት ወስኗል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን አመልካች ይግባኝ ያቀረበበት የመዝ. ንም በመጨመር የቀረበ ነው። የቅሬታው ፍሬ ሃሣብ በ1ኛ እና 2ኛ ክስ ሥር የተጠቀሰው አቶ ፍትዊ ወልዲይ ላይ የተፈፀመ የማታለል ተግባር የላለ መሆኑን አቶ ፍትዊ ወልዲይ ለድርጅቱ የኮንስትራክሽን ዕቃዎችንና ቢሮ ሲያከራዩ ድርጅቱ ከደንበኞቹ ገንዘብ ሰብስቦ እስኪሰጣቸው ድረስ ሁለቱ ቼኮች በዋስትና መልክ የተሰጠ እንጅ ባንክ ቤት ሄደው እንዱመነዝሩት አይደለም፣ ተበዲይ የተባለትም ቼኮቹ በቂ ስንቅ እንደላላቸው የሚያውቁ ስለመሆኑ ለፍ/ቤቱ አስረድተዋል፣ ቼክ ደግሞ በዋስትና ላሰጥ የሚችል ሰነድ ስለመሆኑ የሰበር ሰሚ ችልት ከዚህ በፉት በመዝገብ የህግ ትርጉም የሰጠበት በመሆኑ፣ አመልካች ቼኮቹን በፈረሙበት ወቅት ከዋና ሥራ አስኪያጅ በተሰጣቸው ውክልና መሰረት ሲሆን ለባንክ በቀረበበት ጊዜ ግን ውክልናቸው በመውረደ ተከታትለው ሃሣቡን ማስተካከል የማይችለ በመሆኑ፣ ቼኩ ለክፍያ ቀርቦ ሉመለስ የቻለው በቂ ስንቅ የለውም በማለት ሣይሆን ሂሣቡ በመዝጋቱ በመሆኑ እና ጥፊተኛ ሉባለ ይገባል ቢባል እንኳ 1ኛ እና 2ኛ ክስ በአንድ የወንጀል የመሥራት ሃሣብ የተሰራ በመሆኑ እንደሁለት የተለያዩ ወንጀልች መታየት የለባቸውም የሚል ሲሆን፣ ሶስተኛውን ክስ በተመለከተ የተጠቀሰው ቼክ በአቶ በላይነህ ሰርጉአለም ያልተፈረመ ስለመሆኑ በቴክኒክ ምርመራ ከመረጋገጥ አልፍ በአመልካች ስለመፈረሙ አልተረጋገጠም፣ የሰነድ ማስተካከያ አድርገዋል ቢባል እንኳ የነበረን ዕዲ ከመክፈል አኳያ እንጅ ሀሰተኛ ሰነድ ለመፍጠር ባለመሆኑ በቸልተኝነት አደረጉ ቢባል እንኳ እንደሚያስቀጣ ባለመደንገጉ ጥፊተኛ የሚያደርግ አይደለም ፣ ቼኩ የተሰጠው የድርጅቱን ትክክለኛ ዕዲ ለመክፈል እንጅ ድርጅቱን ለመጉዲት ወይም አመልካች ራሱን ወይም ላላውን ለመጥቀም ያደረገው ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም የሚል ነው።
ቅጣትን በተመለከተ አመልካች ጥፊተኛ የሚባል ከሆነ እንኳ ከዚህ በፉት ወንጀል ፈፅመው ሪከርድ የላለባቸው በመሆኑ፣ የቤተሰብ ኃላፉ መሆናቸው፣ አጠቃላይ የጉዲዩ አፈፃፀም እና ያበረከቱት አስተዋጽኦ ታይቶ ቅጣቱ ተሻሽል በገደብ እንዱለቀቁ በማለት የቀረበ ነው።
ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ዐቃቤ ሕግ መልስ እንዱሰጥበት ታዞ በቀን 06/10/03 6 ገፅ የጽሐፍ መልስ አቅርበል። የመልሱ ፍሬ ሃሣብ የቀረበው ቅሬታ የፍሬ ነገር ክርክር እንጂ መሰረታዊ የሕግ ስህተትን የማይመለከት በመሆኑ በሰበር ሰሚ ችልት የማይታይ በመሆኑ ውድቅ ሆኖ እንዱሰናበት ፣ በ1ኛ እና 2ኛ ክስ ሥር ማታለለ ከተከፊይ አቶ ፍትዊ ወልዲይ አኳያ ብቻ የሚታይ ከሆነ መታለል የለም ብል መከራከር ይቻላል ሆኖም በወ.መ.ሕግ ቁ 692 ሥንመለከት በቼኩ መታለል መፈፀሙን ለማስረዲት ብቸኛው መመዘኛ ቼኩ ለክፍያ ሲቀርብ በቂ ስንቅ የላለው መሆኑን ማረጋገጥ በቂ ነው።
በዚህ ጉዲይ የግል ተበዲይ ጠየቀም አልጠየቀም የህጉ አላማና ፍላጎት የሕዝብን ጥቅም ከማስከበር አኳያ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው ክርክር አይደለም፣ የተሰጠውም ቼክ በዋስትና የተሰጠ ስለመሆኑ የተረጋገጠ ነገር የለም፣ ሶስተኛው ክስ ሥርም ፊርማውን ከሥራ አስኪያጁ ጋር አመሣስል የፈርመው ተበዲይን ለመጉዲት እንደሆነ ግልፅ በመሆኑ እና የተሰጠው የጥፊተኝነትም ሆኖ ቅጣት የሚነቀፍ ባለመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልተፈፀመበትም ተብል እንዱሰናበት በማለት ተከራክሯል። አመልካች በቀን 1ዐ/10/2003 ዓ.ም 3 ገፅ የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የክርክር ሂደት አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም መዝገቡን መርምሮታል። በዚሁ መሰረት መፍትሓ ማግኘት ያለባቸው ጭብጦች፡-
በዚሁ መሰረት ወደ ተያዙት ጭብጦች ስንመለስ፡- 1ኛ እና 2ኛውን ክስ በተመለከተ በእርግጥ በወ.መ.ሕ.ቁ 692/1/ ሥር ስለማታለል የተሰጠውን ትርጉም በምናይበት ጊዜ ‛…….የማይገባ ብልፅግና ለራሱ ለማስገኘት ወይም ለላላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ አሳሳች የሆኑ ነገሮችን በመናገር ፣ የራሱን ማንነት ወይም ሁኔታ በመሰወር ወይም መግለፅ የሚገባውን ነገር በመደበቅ ወይም የላላውን ሰው የተሳሳተ እምነት ወይም ግምት በመጠቀም ፣ በማድረግም ሆነ ባለማድረግ ላላውን ሰው አታል የራሱን ወይም የሶስተኛ ወገን የንብረት ጥቅም የመጉዲት አድራጎት እንዱፈፀም ያደረገ እንደሆነ……“ በሚል ይደነግጋል።
አሁን በቀረበው ክርክር ላይም የቀረበው ክርክር የተፈፀመ የማታለል አድራጎት የለም፣ ቼኩ በሚሰጥበት ጊዜ በቂ ስንቅ እንደላለው ተበዲዩም ያውቅ ነበር ገንዘብ ከደንበኞች ተሰብስቦ እስኪሰጠው ድረስ ለመያዥ የተሰጠ እንጅ ባንክ ቤት ቀርቦ እንዱመነዘር አይደለም የሚል ከመሆኑ አኳያ ተበዲይን መሰረት ያደረገ ማታለል የተፈፀመ ስለመሆኑ ከላይ ከተመለከተው የሕግ ድንጋጌ አኳያ ጥያቄ ውስጥ ሉገባ ይችል ይሆናል። ሆኖም ግን የወ.መ.ሕግ ቁ 693/1/ን በምንመለከትበት ጊዜ ርዕሱ ‛ የሚያዝበት ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ማውጣት“ የሚል ሲሆን በዚሁ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ አንድ ሥር የተደነገገው 693/1/ ማንም ሰው ቼክ በሚያወጣበት ወይም ቼኩ ለባንክ በሚቀርብበት ጊዜ የሚያዝበት በቂ ገንዘብ ያለመኖሩን እያወቀ ቼክ ያወጣ /የሰጠ / እንደሆነ በሚል ተደንግጓል።
ይሄንን ስለቼክ የሚደነግገውን የወንጀል አንቀጽ ስንመለከት በወንጀለኛ መቀጫ ሕግ ቁ 692/1/ ሥር ከላይ የተመለከተውን የወንጀለን አፈፃፀም ከግል ተበዲይ/ተታልአል/ ከሚባል ግለሰብ አኳያ ያልታዬ መሆኑን ነው። ይሄ ማለት ደግሞ በተለይም የቼክ ሰነድ ለአምጭው ወድያውኑ የሚከፍል እና በንግድ ሕጉ ከተቀመጡት ውስን መቃወሚያዎች ውጪ ሉቀርቡበት የማይገባ በመሆኑ በቼክ አውጪው ላይ ኃላፉነት የጣለ ይመስላል። ይሄም ማለት ከላይ የተመለከተው የወ.መ.ሕግ ንባብ አንድ ቼክ ያወጣ /የሰጠ/ ሰው በቂ ስንቅ መኖርን ማረጋገጥ እንዲለበትና ቼኩ በተሰጠበት ጊዜ ወይም ለክፍያ በቀረበበት ጊዜ በቂ ስንቅ ያለመኖሩ ብቻ የተጠቀሰውን የወንጀል ኃላፉነት እንደተቋቋመ የሚቀበለው መሆኑን መረዲት ይቻላል።
ከዚህ አኳያ የግል ተበዲዩ በየትኛውም ተቋም በወንጀል ክስ ያልመሰረተ መሆኑ ሆኖም ግን ቼኩን ለክፍያ ሲያቀርበው በቂ ገንዘብ የለውም ተብል መመለሱ እስከተረጋገጠ ድረስ ሕግ አውጪው ደግሞ ቼክን በተመለከተ የተደነገገዉ የማታለል ወንጀል እስከ ተሟላ ድረስ ከኃላፉነት ነፃ ሉያደርገው አይችልም ።
በልላ በኩል ቼኩ የተሰጠው ለባንክ ቀርቦ እንዱመነዘር ሣይሆን ለዋስትና የተሰጠ ነው በማለት የቀረበውን ክርክር ስንመለከተው ከዚህም ጋር ተያይዞ ከዚህ በፉት ይሄ ሰበር ሰሚ ችልት በመዝ. በሆነ መዝገብ ቼክ በዋስትና መያዝ እንደሚቻል የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል በማለት ተያያዥ ክርክር ቀርቧል። ይሄንን በተመለከተ ቀድሞ የሕግ ትርጉም ተሰጥቶበታል የተባለው መዝገብ አንድ ቼክ ለክፍያ ሲቀርብ /ገንዘብ ስጠየቅ ለቀረቡበት ከሚችለት መቃወሚያዎች አንድ የግል ግንኙነት /personal Relation/ መኖር ስለመሆኑ በፍትሕብሓር ክርክር ላይ የተያዘ አቋም እንጅ አሁን እየታየ ካለው የወንጀል ኃላፉነት አኳያ ቀጥታ ግንኙነት ያለው ባለመሆኑ ፣ የተባለውም የግል ግንኙነት ከላይ ከተመለከተው የወንጀል ኃላፉነት አኳያ አላፉነቱን ቀሪ የሚያደርግበትን አግባብ ያስረዲ /ያመለከተ/ባለመሆኑ አልፈነዋል።
የአመልካች ኃላፉነት መታየት ያለበት በወ/መ/ሕግ ቁ 693/1/ ወይስ 693/2/ ሥር የሚለውን በተመለከተ ባንክ ቤት የነበረው ሂሣብ የተዘጋው በተደጋጋሚ በቂ ስንቅ ሣይኖር ቼክ በመሰጠቱ ባለው መመሪያ መሰረት የሂሣብ ቁጥሩ መዝጋቱን ያመለከተና ይሄንንም የበታች ፍርድ ቤቶች በፍሬ ነገር ረገድ ያረጋገጡት በመሆኑ በቸልተኝነት የተሰጠ ነው የሚያሰኝ አይደለም ።
1ኛ እና 2ኛው ክስ የተሰራው በአንድ የወንጀል ሐሣብ ነው በሚል የተነሣውን ክርክር በተመለከተ የተፈፀመው በአንድ ቀን ልዩነት ከመሆኑም በላይ የተሰጠበት ዓላማም ለተለያዩ ይሄውም የድርጅቱን ደረጃ ለማሣደግና ለዕዲ መክፈያ በሚል በመሆኑ በአንድ የወንጀል ሃሣብ የሚያሰኝ ሣይሆን በወ.መ.ሕግ ቁ 62 መሰረት በአዱስ ሃሣብ እንደሰራው ይቆጠራል።
ሶስተኛውን ክስ በተመለከተ በቼኩ ላይ የተፈረመው ፊርማ የተበዲይ አለመሆኑ በቴክኒክ ምርመራ የተረጋገጠ በመሆኑ ፈራሚው ማን ላሆን ይችላል? የሚለው ነጥብ መታየት አለበት።
በዚሁ መሰረት ቼኩን የተቀበለው ሰው ለፍርድ ቤት ቀርቦ በሰጠው የምስክርነት ቃል ቼኩን የሰጠው አመልካች እንደሆነ ፣ ቀድሞ የተፈረመበት እንደሆነና ቀኑ እንዱያጥርለት አመልካችን እንደጠየቀና በጠየቀው መሰረት ቀኑን አሣጥሮ ፕራፍ አድርጎበት የሰጠው መሆኑን መስክሯል።
በዚህ ቼክ ላይ የቴክንክ ምርመራ ሲደረግ ቢያንስ ፕራፍ የተደረገው እንኳ የአመልካች ፊርማ ስለመሆኑ ያልተመለከተ በመሆኑና የበታች ፍ/ቤትም አመልካች የተበዲዩን ፊርማ አስመስል ፈርሟል የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል። ይሄ ደግሞ የማስረጃ ምዘና በመሆኑ የፋ/ጠ/ፍ/ቤት የደረሰበትን መደምደሚያ መቀበለ ተገቢ ይሆናል። ምክንያቱም የዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ሥልጣን በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ እና አዋጅ ቁ 25/88 አንቀጽ 10 መሰረት መሰረታዊ የሕግ ስህተት ማረም እንጂ ማስረጃን መመዘን ባለመሆኑ በልላ በኩል አመልካች የተበዲዩን ፊርማ አመሣስል ፈርሟል ወይስ አልፈረመም? የሚለው ደግሞ የማስረጃ ምዘና በመሆኑ ነው።
ባጠቃላይ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠው የጥፊተኝነት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አላገኘነውም። ቅጣትን በተመለከተ የአመልካች ቀድሞ ባህርይ መልካም መሆኑ፣ የቤተሰብ አስተዲዲሪ መሆኑና በበርካታ ማህበራዊ አገልግልቶች ተሣታፉ መሆኑ ከግምት ውስጥ በማስገባት የተላለፈ በመሆኑ ከዚህም አኳያ የቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
በመሆኑም የተላለፈበት የጥፊተኝነት ውሣኔና ቅጣት መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አልተገኘም።
በዚህ መሰረት ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
በቀን 30/6/2003 እና ሚያዝያ 10 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ እና ውሣኔ በወ/መ/ሕ/ቁ 195/2/ /ለ/2/ መሰረት ፀንቷል።
No topics extracted.