No summary available.
ሰኔ 03 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡-
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የወንጀል ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። በዚህ ፍ/ቤት የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካቾች ላይ የመሰረተው የወንጀል ክስ በሁለት ምድብ የተከፈለ ሲሆን 1ኛው ክስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወ/ህ/አንቀጽ 32(1(ሀ)(ለ))እና 539(1ሀ) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ አመልካቾች በሙለ ሐሳባቸውና አድራጎታቸው በወንጀለ ስራና በሚሰጠው ዉጤት ሙለ ተካፊይ በመሆን ተበዲዮች ጌታነህ ወ/ማሪያም እና ደስታ ወ/ማሪያም የተባለት በጥቅምት ወር 1985 ዓ/ም በኢ.ሕ.አ.ዱ.ግ ታጋዮች 1ኛ/ ጌታነህ ወ/የስ ፣ 2ኛ/ መኮንን ጌታነህ ፣ 3ኛ/ በቀለች ወ/አረጋይ የተባለ ቤተሰቦቻችንን አስገድለውብናል በሚል ቂም በቀል ተነሳስተው ቤት ንብረታቸውን በእሳት አውድመው ከአገር እንዱሰደደ ካደረጓቸው በኋላ እንደገና በፍርድ ቤት ከሰዋቸው በነፃ ሲሰናበቱ 1ኛዋ አመልካች በተሰጠው የፍርድ ውሳኔ የበቀል ጥማቷ ባለመርካት ከአስር አመት በላይ ተበዲዮቹ የሚኖሩበትን ቦታ ለማወቅ በግብረአበሮቿ አማካኝነት ስትከታተል ቆይታ በ2ኛው አመልካች አማካኝነት ቤታቸውን ካገኘች በኋላ በተጨማሪም የተበዲይን ወንድሞች ቤት ጭምር ራሷ ፈልጋ በማግኘት ከቤታቸው ድረስ እየሄደች ስታጠና ቆይታ የወንጀለን ሥራ መሪ ተዋናይ በመሆን 3ኛ እና 4ኛ አመልካቾችን ከደብረ ብርሃን ፣ 2ኛ አመልካችን ከአዱስ አበባ በማሰባሰብ የአከባቢው ሰው በስራ የሚሰማራበትንና ጭር የሚልበትን አመቺ ጊዜ አጥንተው ሰኔ 25 ቀን 1999 ዓ/ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 6፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር በየካ ክፍለ ከተማ ቀበላ 07 ክልል ወደሚገኘው የሟቾች መኖሪያ ቤት በመሄድ ዘመድ ነን ብለው ሕፃናቱን በር ካስከፈቱ በኋላ ጨካኝታቸውንና አደገኛነታቸውን እንዱሁም ነውረኝነታቸውን በሚገልፅ አስቃቂ ሁኔታ፡- 1ኛ/ ህፃን ፍቅረተ በቀለ እድሜዋ 12 አመት የሆነችውን ፣ 2ኛ/ ሕፃን ሐና በቀለ እድሜዋ 8 አመት የሆነችውንና 3ኛ ሕፃን ነጻነት በቀለ እድሜዋ 1 አመት ከ8 ወር የሆነችውን ከሟች ሕፃን ፍቅረተ በቀለ ጀርባ እንደታዘለች ሶስቱንም ሕጻናት በደላ ጭንቅላታቸውን እና መላ ሰውነታቸውን እየተፈራረቁ ቀጥቅጠው በግፍ ገድለዋል የሚል ሲሆን 2ኛው ክስ ደግሞ ሁለም አመልካቾች በ1996 ዓ/ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 669(3(ለ)) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ አመልካቾች ሕገ ወጥ ብልፅግና ለራሳቸው ለማግኘት በማሰብ በቡድን ተደራጅተው በ1ኛው ክስ ላይ በተገለጸው ጊዜና ስፍራ በክሱ ላይ የተመለከተውን የግፍ ግድያ ወንጀል ከፈጸሙ በሁዋላ ንብረትነቱ የአቶ በቀለ ወ/ማሪያም የሆኑ፡- ባለ 14 ኢንች ኤልጂ (LG) ቴላቭዥን ፣ ሶስት ጋቢዎች ፣ አንድ ሰማያዊ ሸራ ላስቲክ እና አንድ አሮጌ የማዲበሪያ ከረጢት ሰርቀው በመውሰዲቸው ከባድ የስርቆት ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ነው።
አመልካቾች ክሱን ክደው በመከራከራቸውም ዐቃቤ ሕግ አለኝ ያላቸውን የሰውና የሰነድ ማስዎችን አቅርቦ አሰምቷል።ከዚህም በኋላ የአመልካቾች የመከላከል መብት ተጠብቆላቸው የመካለከያ ማስረጃዎችን አቅርበው አሰምተዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም አመልካቾች የዐቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን ያላስተባበለ መሆኑን ዘርዝሮ የመከላከያ ማስረጃዎቻቸውን ቃል ውድቅ ያደረገ ሲሆን አመልካቾችን በዐቃቤ ሕግ በኩል ተጠቅሰው በቀረቡባቸው ድንጋጌዎች ስር ጥፊተኛ በማድረግ የጥፊተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል። በቅጣት ረገድም የአሁኗ 1ኛ አመልካችን (መስታወት ጌታነህን) በሞት ፣ ላልች አመልካቾችን ደግሞ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዱቀጡ ሲል በድምፅ ብልጫ ወስኗል። አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት በተሰጠው የጥፊተኝነም ሆነ የቅጣት ውሳኔ ይግባኛቸው ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። በልላ በኩል ዐቃቤ ሕግ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተራ በተጠቀሱት አመልካቾች ላይ የተሰጠውን የቅጣት ውሳኔ ሕጋዊነት የለውም ፤ ያነሰ ነው በሚል ምክንያት ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የአመልካቾችን የድርጊት አፈጻፀም ከሕጉ ጋር በመመርምር አመልካቾች ሉቀጡ የሚገባው በሞት ነው በማለት የስር ፍርድ ቤትን የቅጣት ውሳኔ አሻሽል ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በጥፊተኝነት እና በቅጣት ውሳኔው ላይ ነው።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ድርጊቱን አመልካቾች ስለመፈጸማቸው በወንጀል ሕግ የማስረጃ ምዘና መርህ ባልተረጋገጠበት ሁኔታና በፕሉስና በፍርድ ቤት አመልካቾች ሰጡ የተባለት የእምነት ቃል በኃይል የተገኘ ሁኖ እያለ የወንጀል ድርጊቱን ፈጽማችኋል ተብል የመከላከያ ማስረጃዎችን እንድናቀርብ ብይን መሰጠቱ ያላግባብ ከመሆኑም በላይ የመከላከያ ማስረጃዎች ቃል ውድቅ የተደረገው ያላግባብ ነው ፣ የቅጣቱ ውሳኔም ሕጉን የተከተለ ሳይሆን የተጋነነ ነው በማለት ውሳኔው እንዱታረም ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም አመልካቾች እያንዲንዲቸው በሞት እንዱቀጡ ተብል የተወሰነው የቅጣት ውሳኔ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን የግራ ቀኙ የቃል ክርክር ታህሳስ 07 ቀን 2002 ዓ/ም በዋለው ችልት ተሰምቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች አኳያ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት አለበት ወይስ የለበትም? የሚለው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካቾች ሶስቱን ህፃናት ለሕልፈተ- ሕይወት ዲርገዋል ፣ ከባድ የስርቆት ወንጀል ፈጽመዋል ተብል በግፍ የሰው ግድያና በከባድ የስርቆት ወንጀል ጥፊተኛ የተባለበት በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 27(2) ለፕሉስ ፣ በወ/መ//ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 35 ደግሞ ለፍርድ ቤት ሰጡ በተባለት የእምነት ቃል ፣ የድርጊቱን አፈጻጸም መርተው ሲያሳዩ በተነሱት ገላጭ ማስረጃና በጠንካራ አካባቢ የሰው ምስክሮች ቃል ስለመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በግልፅ ተጠቅሷል። የአመልካቾች የመከላከያ ምስክሮች ቃል ውድቅ የተደረገውም አመልካቾች የእምነት ቃለን የሰጡት በኃይል ስለመሆኑ ለማስረዲት እምነት ሉጣልበት የሚችል አይደለም በሚል ምክንያት ነው። እንግዱህ የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካቾች ድርጊቱን ፈፀሙ በማለት ድምዲሜ ላይ የደረሱት አመልካቾች እያንዲንዲቸው በድርጊቱ አፈጻጸም ላይ የነበራቸውን ቀጥተኛ ተሳትፍ በሚገባ አቃቤ ሕግ አስረድቷል ፣ በመከላከያ ማስረጃዎቻቸውም አልተደገፈም በሚል ነው።የአመልካቾች ጠበቃ ከሚከራከሩባቸው ነጥቦች ውስጥ የአመልካቾችን የድርጊት ፈጻሚነት በተገቢው መንገድ አቃቤ ሕግ በማስረጃ ያለማስደገፈንና የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን አመልካቾች በመከላከያ ምስክሮች የማስተባበላቸው ሁኔታን የሚመለከቱ ነጥቦች የሚገኙ ሲሆን የበታች ፍርድ ቤቶች ተገቢውን የማስረጃ ምዘና መርህ ተከትለው አመልካቾችን ጥፊተኛ ያደረጉ ስለመሆኑ የክርክሩ ሂደት የሚያሳየን ሁኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም ከዚሁ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መገንዘብ የሚቻለው አመልካቾች ጥፊተኛ የተባለት በጉዲዩ ላይ የቀረቡት ማስረጃዎች ተመዝነው መሆኑን ነው። እንደሚታወቀው ይህ ሰበር ሰሚ ችልት አንድ የመጨረሻ ፍርድ ያገኘን ጉዲይ ማረም የሚችለው በውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት መኖሩ ሲረጋገጥ ስለመለሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ተመልክቷል። ከእነዚህ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው ደግሞ ይህ ሰበር ችልት ፍሬ ነገርን የማጣራት ወይም ማስረጃን የመመዘን ስልጣን የላለው መሆኑን ነው። በተያዘው ጉዲይም የአመልካቾች ጠበቃ አጥብቀው የሚከራከሩባቸው ነጥቦች የመሰረታዊ ሕግ ስህተት መመዘኛን መሰረት ያደረጉ ሳይሆን የፍሬ ነገርንና የማስረጃ ምዘናን መሰረት ያደረጉ በመሆናቸው በዚህ ችልት ሉታዩ የሚችለ ሁነው አላገኘናቸውም።በመሆኑም አመልካቾች የእምነት ቃላቸው በመገደድ የተገኘ ስለመሆኑ ማረጋገጥ ባልቻለበት ሁኔታና በራሳቸው ምሪት ወንጀለ የተሰራበትን ቦታና የአፈጻጸሙን ሁኔታ ስለማሳየታቸው በሰነድ ማስረጃ ተረጋግጦ ባለበት የክርክር ሂደት እንዱሁም ወንጀለ በአመልካቾች ስለመፈጸሙ ደግሞ በበርካታ ጠንካራ የአካባቢ ማስረጃዎች ተደግፍ በቀረበበት መንገድ አመልካቾች የአቃቤ ሕግ ማስረጃ በሕጉ መመዘኛ የሚያሟላ አይደለም በማለት የሚያቀርቡት ክርክር የሕግ መሰረት ያለው ሁኖ አልተገኘም። አመልካቾች ለድርጊቱ ኃላፉነት አለባቸው ተብል የተወሰነው ወንጀለ መሰራቱ ወይም መፈጸሙና ተሰራ ወይም ተፈጸመ የተባለው ወንጀል ደግሞ በአመልካቾች መፈጸሙ በማያጠራጥር ሁኔታ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ጉዲይ በመሆኑና ይህም በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ የሚያሟላ በመሆኑ በዚህ ረገድ የቀረበውን ክርክር የምንቀበለው ሁኖ አላገኘነውም። ወደዋናው ጭብጥ ስንመለስም የአመልካቾች መሰረታዊ ክርክር የበታች ፍርድ ቤቶች ያስተላለፈት የሞት ቅጣት የቅጣት አወሣሰኑን በተመለከተ የወንጀል ህጉ ያስቀመጣቸውን መርሆዎች ያላገናዘበ ነው የሚል ነው። እኛም ይህንኑ ቅሬታ ከህጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
በመሰረቱ የኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፕብሉክ የወንጀል ህግ የአገሪቱን የወንጀል ህግ ግብ በአዋጅ ቁጥር 414/1996 አንቀጽ 1 ስር ሲደነግግ ‛የወንጀል ህግ ግብ ወንጀል እንዲይፈፀም መከላከል ሲሆን ይህንን የሚያደርገው ስለወንጀልችና ስለቅጣታቸው በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት፣ ማስጠንቀቂያነቱ በቂ ባልሆነበት ጊዜ ወንጀል አድራጊዎቹ ተቀጥተው ላላ ወንጀል ከመፈፀም እንዱቆጠቡና ለላልች ማስተማሪያ እንዱሆኑ ወይም እንዱታረሙ በማድረግ ወይም ተጨማሪ ወንጀልች እንዲይፈፀሙ እርምጃዎች እንዱወሰደባቸው በማድረግ ነው“ በማለት ያስቀምጣል። ህጉ በአንቀጽ 87 ላይ ቅጣቶችና የጥንቃቄ እርምጃዎች ህጉ ሉደርስበት ያሰበውን ዓላማ ለማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ በህጉ መንፈስ መሰረት መፈፀም እንዲለባቸው በመርህ ደረጃ ይደነግጋል። ይኸው አንቀጽ ቅጣቶችና የጥንቃቄ እርምጃዎቹ ምን ጊዜም ሰብዓዊ ክብርን በሚጠብቅ መንገድ መፈፀም እንደሚኖርባቸው ያስገነዝባል። የወንጀል ህጉ አንቀጽ 88 ሲታይም የቅጣቶች እና የጥንቃቄ እርምጃዎች አወሣሰንን በተመለከተ ዘርዘር ያለ ንዐስ ድንጋጌዎችን አካቶ ይዟል። በዚህ አንቀጽ ስር ያለ ንዐስ አንቀጾች የሚያሣዩት ፍርድ ቤቱ ቅጣቶችንና የጥንቃቄ እርምጃዎችን የሚወሰነው የወንጀል ህጉን ጠቅላላ ክፍል ድንጋጌዎችን እንዱሁም ስለወንጀልችና ስለቅጣታቸው የሚደነግጉትን የልዩ ክፍለ ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ መሆኑን ፣ ቅጣት ሉወሰን የሚገባው የወንጀል አድራጊውን ግላዊ የአደገኛነት መጠን ያለፈ የህይወት ታሪኩን ወንጀል ለማድረግ ያነሣሡትን ምክንያቶችና የአሣቡን ዓላማ የግል ኑሮውን ሁኔታ፣ የትምህርቱን ደረጃ ፣ እንዱሁም የወንጀለን ከባድነትና የአፈፃፀሙን ሁኔታዎች በማመዛዘን መሆኑን፣ የወንጀል ህግ ልዩ ክፍል ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ፍርድ ቤቱ እጅግ ቀላል ከሆነው ቅጣት አንስቶ እስከ ከባደ ድረስ ያለውን በጥንቃቄ በመመርመር ለእያንዲንደ ጉዲይ ተገቢ የሆነውን ቅጣት እንደሚወስንና የቅጣት አወሣሰን ትክክለኛነትና አንድ ወጥነት ለማረጋገጥ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የቅጣት አወሣሰን መመሪያ (Manual) እንደሚወጣ የሚያስገነዝቡን ናቸው።
ከላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች የምንረዲው አቢይ ነጥብ ቅጣቶች መወሰን ያለባቸው የህጉን መንፈስ በመከተል ዓላማዎችንና ግቦቹንም ተፈፃሚ በማድረግ ሀሣብ መሆኑን ነው። የህጉን መንፈስ ከመተግበር አኳያ ወንጀለኛውን ማዕከል የማድረግ ፅንሰ ሀሣብ አጽንኦት የተሰጠው ጉዲይ ነው። ዳኞች በፅንሰ ሀሣቡ መሰረት የተሰጣቸውን አመዛዝኖ የመወሰን ስልጣን (Discretion) በስራ ላይ ሲያውለ ሰብአዊ ክብርን ከማስጠበቅ ዓላማ ጋር መሆን ያለበት ከመሆኑም በላይ ህግ አውጪው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 87/1/ ስር የተመለከቱትን መሰረት በማድረግ ዳኞች የቅጣት ውሣኔ በምን መንገድ መወሰን እንደሚገባቸው በአንቀጽ 88 ስር አስቀምጧል። በወንጀል ህጉ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ስንመለከትም ዳኞች ከተሰጣቸው የቅጣት ክልል ሣይወጡ የአጥፉውን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ቅጣት እንዱወስኑ ህጉ ስልጣን የሰጣቸው መሆኑ ነው። ዳኞች አጥፉውን በተመለከተ ከግምት ውስጥ ሉያስገቧቸው የሚገባቸው በርካታ የአጥፉ ፡ ሁኔታዎች ቢኖሩም የቅጣት አወሣሰናቸው መሰረት የወንጀል አድራጊውን ግላዊ የአደገኛነት መጠን /degree of individual guilt/ ስለመሆኑ የአንቀጽ 88/2/ ድንጋጌ ይዘትና አቀራረፅ ያስረዲል። አንቀጽ 88(2) በመጀመሪያ ደረጃ የወንጀል አድራጊውን የአደገኛነት መጠን መሰረት በማድረግ ዳኞች ቅጣት እንዱወስኑ ማድረጉና ይህንን ሲወስኑም በድንጋጌው የተመለከቱትን የወንጀለን አፈፃፀም የአጥፉውን ያለፈ የህይወት ታሪኩንና የኑሮ ሁኔታ ከግምት በማስገባት በማመዛዘን ለወንጀለና ለወንጀለኛው የሚገባውን የቅጣት መጠን እንዱወስኑ መደንገጉ የቅጣት ውሣኔዎችንና እርምጃዎችን እየተራራቁ እንዲይወሰኑ የማድረግ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብል ከመታሰቡም በተጨማሪ ችግሩ የሚቀረፍበትና የሚቀነስበትን ሥርዓትም ህጉ ዘርግቷል። ዳኞች ቅጣት ሲወስኑ በህጉ አንቀጽ 88(2) ለአጥፉው ተገቢ ነው ያለትን ቅጣት ከወሰኑ በኋላ በህጉ የተመለከቱትን የማቅለያና የማክበጃ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ቅጣቱን ከፍ ወይም ዝቅ ለማድረግ የሚችለ ስለመሆኑ ህጉ ያሣያል።
የኢ.ፋ.ዱ.ሪ. የወንጀል ህግ በአንቀጽ 84(1) ከፉደል (ሀ) እስከ ፉደል (ሰ) ድረስ ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶችን ካስቀመጠ በኋላ በአንቀጹ ንዐስ ቁጥር ሁለት ስር በንዐስ ቁጥር አንድ ስር የተመለከቱት የማክበጃ ሁኔታዎች በህጉ ልዩ ክፍል ተካተው ሲገኙ በድጋሚ በማክበጃነት ዳኞች እንዲይጠቀሙ ያሣስባል። ስለሆነም የህጉ አንቀጽ 84 ደግሞ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶችን የዘረዘረ ሲሆን ዳኞች የህጉን አንቀጽ 183 ባገናዘበ መልኩ ቅጣት የሚያከብደባቸውን ሁኔታዎች ያሣያል።
ዳኞች ቅጣትን የሚቀንሱትም ሆነ የሚያከብደት ተገቢ ሁኖ ሲገኝ ስለመሆኑ የአንቀጽ 179 እና 183 ድንጋጌዎች ያሣያለ። አንቀጽ 179 የቅነሣውን ገደብ የሚያሣይ ሲሆን ከዚህ መደበኛ ቅነሣ በተጨማሪ ልዩ ቅነሣ ለማድረግ እንደሚቻልም ህጉ በአንቀጽ 180 ስር አስቀምጧል። በህጉ አንቀጽ 86 ቅጣትን በማቅለልም ሆነ በማክበድ ረገድ ከህጉ አንቀጽ 179፣182 እና ውጪ የሆኑ ምክንያቶች ሲያጋጥማቸው ዳኞች ምክንያታቸውን በመግለፅ ቅጣቶችን ለመቀነስ ወይም ለማክበድ እንደሚችለ ተደንግጓል። ግንቦት 09 ቀን 2002 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ በሆነው የቅጣት መመሪያ ውስጥ የተቀመጠው የቅጣት አወሳሰን ሥርዓት እንደተጠበቀ ሁኖ ከላይ ስለቅጣት አወሣሰን በህጉ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ሲታዩ የሚያስገነዝቡን ዓቢይ ነጥብ ቅጣቶችን በመጣልና እርምጃዎችን በመውሰድ ረገድ ዳኞች አመዛዝነው የመወሰን ከፍተኛ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካቾች ጥፊተኛ የተባለት ግዙፍነት ባላቸው ተደራራቢ ወንጀልች ሲሆን የግድያ ወንጀለ በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 32(1(ሀ)(ለ)) እና 539(1ሀ)) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ በቂም ፣ ጨካኝነት ፣ ነውረኝነት ፣ አሰቃቂና አደገኛነትን በሚያሳይ ሁኔታ ምንም የማያውቁ ጨቅላ ሕጻናትን በግፍ ገድለዋል ተብል ነው። በዚህ ድንጋጌ ጥፊተኛ የተባለ አጥፉ ሉቀጣ የሚገባው እድሜ ልኩን በጽኑ እስራት ወይም በሞት ነው። ከላይ እንደተመለከተው ፍርድ ቤት ቅጣት ሲወስን ሉከተላቸው የሚገባቸው የቅጣት አወሳሰን መርሆዎች በሕጉ ላይ ተቀምጠዋል። የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችልት በአመልካቾች ላይ ያስተላለፈው የሞት ቅጣት ስለመሆኑም ከላይ ገልፀናል።
በመሰረቱ ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር መብት እንዲለውና በሕግ በተደነገገው ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን ሉያጣ እንደማይገባ የኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት በአንቀፅ 15 ስር በኃይለ ቃል የደነገገው ጉዲይ ነው። በመሆኑም በሕጉ አግባብ ከባድ ወንጀል መፈጸሙ በተረጋገጠበት ሰው ላይ የሞት ቅጣት ማስተላለፍ የሚፈቀድ መሆኑን ሕገ መንግስቱ አስቀምጧል። በልላ በኩል የሞት ቅጣት ሉተላለፍ የሚገባበትን አግባብ የወንጀል ሕጉ በአንቀጽ 117 ስር ድንግጎ እናገኛለን። በዚህ አንቀፅ ንዐስ ቁጥር አንድ ድንጋጌ መሰረት የሞት ቅጣት የሚወሰነው ወንጀለ ፍጻሜ ያገኘ ሁኖ እጅግ በጣም ከባድ በመሆኑና ወንጀለኛውም በተለይ አደገኛ በመሆኑ ለወንጀለ ቅጣት እንዱሆን በሕጉ በግልጽ ተደንግጎ በተገኘ ጊዜ እንዱሁም ለወንጀለኛው ቅጣትን የሚያቀልለት ምክንያት በታጣ ጊዜ እድሜው ቢያንስ አስራ ስምንት አመት የሞላው ሁኖ ሲገኝ መሆኑ ተመልክቷል። አመልካቾች ጥፊተኛ የተባለበት ድንጋጌ እድሜ ልኩን በፅኑ እስራት ወይም በሞት የሚያስቀጣ ነው። የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሞት ቅጣቱን ለመወሰን የቻለውም ድርጊቱን ለመፈጸም ያነሳሳቸውን ምክንያት ፣ ድርጊቱን ለመፈጸም ለረዥም አመታት ሲደረግ የነበረውን ቅድመ ዝግጅትና እና ድርጊቱ የተፈጸመባቸው ምንም የማያውቁና ከማንኛውም ሰው እንክብካቤ የሚሹ ሶስት ጨቅላ ህጻናት ላይ መሆኑን እንዱሁም የአፈጻጸሙን ዘግናኝነትና አስቃቂነት ከአመልካቾች አደገኛ ባህርይና ቅጣቱ ለላላው ማህበረሰብ ሉያስተላልፈው ከሚችለው መልዕክት በመነሳት ከመሆኑም በላይ ለአመልካቾች በሕጋዊ ማቅለያነት ሉያዙ የሚችለ ምክንያቶች የላለ መሆኑን በመረዲት መሆኑን ከውሳኔው ይዘት ተገንዘበናል። በመሆኑም በዚህ ረገድ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተያዘው ምክንያትና የተደረሰው ድምዲሜ በቅጣት አወሳሰን ጊዜ ግንዛቤ ውስጥ ሉገቡ የሚችለ የቅጣት አወሳሰን መሰረታዊ መርሆዎችን ያልተከተለ ነው ለማለት የሚቻል ሁኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለልም በአመልካቾች ላይ የተጣለው የሞት ቅጣት የወንጀል ሕጉን መሰረታዊ ግብና ዓላማ እንዱሁም የቅጣት አወሳሳን መርሆዎችን ከድርጊቱ አፈጻፀም ጋር ያገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
No topics extracted.