No summary available.
ሰኔ 21 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኦሮሚያ ክልል ዐቃቤ ሕግ ዐ/ህግ ደሣለኝ ደንገላ ቀረቡ ተጠሪ፡- 1.ኢዮስያስ አበራ ገ/ሚካኤል-አልተጠራም 2. ለአለም አበራ ገ/ሚካኤል-ቀረቡ።
ትርንጎ ወ/ሚካኤል-ቀረቡ።
አብያለው አበራ ገ/ሚካኤል-ቀረቡ።
መላኩ ግዛው -አልተጠራም።
መዝገቡ የተቀጠረው በ2ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች ላይ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ተብል ነው።በዚህም መሰረት ጉዲዩን መርምረን ተከታዩን የቅጣት ውሳኔ ሰጥተናል።
ቅ ጣ ት 2ኛ ተጠሪ ለአለም አበራ ጥፊተኛ የተባለው በግፍ ሰው መግደል ወንጀል በሚያስጠይቅበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 539(1ሀ) ስር ነው። በዚህ ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ የተባለ አጥፉ ሉቀጣ የሚገባው እድሜ ልኩን በፅኑ እስራት ወይም በሞት ነው።
ቅጣት የሚወሰነው ደግሞ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 88(2) መሰረት ነው። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ቅጣት ሉወሰን የሚገባው የወንጀል አድራጊውን ግላዊ የአደገኛነት መጠን ያለፈ የህይወት ታሪኩን ወንጀል ለማድረግ ያነሣሡትን ምክንያቶችና የአሣቡን ዓላማ የግል ኑሮውን ሁኔታ፣ የትምህርቱን ደረጃ፣ እንዱሁም የወንጀለን ከባድነትና የአፈፃፀሙን ሁኔታዎች በማመዛዘን መሆኑን፣ የወንጀል ህግ ልዩ ክፍል ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ፍርድ ቤቱ እጅግ ቀላል ከሆነው ቅጣት አንስቶ እስከ ከባደ ድረስ ያለውን በጥንቃቄ በመመርመር ለእያንዲንደ ጉዲይ ተገቢ የሆነውን ቅጣት እንደሚወስን መገንዘብ ይቻላል፡ በዚህ መሰረት ይህ ችልትም እነዚህ ሁኔታዎችን ተመልክቷል፤ አመዛዝኗልም። 2ኛ ተጠሪ ሪከርድ ያልቀረበበት መሆኑም ያለፈ የሕይወት ታሪኩ መልካም የነበረ መሆኑን እንደሚያሳይ የሚያስገነዝብ ነው።ይህ ደግሞ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 82(1(ሀ)) መሰረት የቅጣት ማቅላያ ምክንያት ሲሆን ከዚህ ውጪ 2ኛ ተጠሪ የተለየና ልዩ የሆነ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት የለውም። የቅጣት መጠኑንም በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 179(ሀ) መወሰኑ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል።ሲጠቃለልም 2ኛ ተጠሪ ጥፊተኛ የተባለበት ድንጋጌ ሉያስቀጣ ከሚችለው የቅጣት መጠንና ከቅጣት ዓይነተኛ ዓላማ አንፃር ሲታይ ተጠሪ ሉቀጣ የሚገባው በጉዲዩ ላይ የታሰረው ጊዜ የሚታሰብለት ሁኖ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ሁኖ አግኝተናል። 4ኛ ተጠሪን በተመለከተ ጥፊተኛ የተባለበት ድንጋጌ ሉያስቀጣ የሚችለው በቀላል እስራት ወይም በመቀጮ ነው።
በተጠሪው ላይ ሉተላለፍ የሚገባውን የቅጣት መጠን በወንጀል ሕግ አንቀፅ 88(2) ስር ከተመለከቱት ሁኔታዎች እና ከቅጣት አላማዎች ጋር አገናዝበን ተመልክተናል። በዚህም መሰረት 4ኛ ተጠሪ ሉቀጣ የሚገባው በጉዲዩ ላይ የታሰረው የሚታሰብለት ሁኖ በ3 (ሶስት) አመት ቀላል እስራት ነው በማለት ወስነናል።
2ኛ ተጠሪ ለአለም አበራ ገ/ሚካኤል በጉዲዩ ላይ የታሰረው የሚታሰብለት ሁኖ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ፣ 3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች ደግሞ በጉዲዩ ላይ የታሰሩት የሚታሰብላቸው ሁኖ እያንዲንዲቸው በሶስት አመት ቀላል እስራት የተቀጡ መሆኑን አውቆ የአዱስ አበባ ማረሚያ ቤት ከአራዲ ክፍለ ከተማ ፕሉስ መምሪያ በመረከብ በእያንዲንዲቸው ላይ በተላለፈው ቅጣት መሰረት ተከታትል እንዱያስፈፅም። የማሰሪያ ዋራንት ይጻፍ።
መዝገቡ ያለቀለት በመሆኑ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.