No summary available.
ሰኔ 17 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኦሮሚያ ክልል ዐቃቤ ሕግ-አቶ ደሳላኝ ደንገላ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- 1.ኢዮሲያስ አበራ ገ/ሚካኤል-አልቀረበም።-የሁለም ጠበቃ አቶ ጎበና እጅጉ ቀረቡ።
ለአለም አበራ ገ/ሚካኤል-ቀረቡ።
ወ/ሮ ትርንጎ ወ/ሚካኤል -ቀረቡ።
አብያለው አበራ ገ/ሚካኤል-ቀረቡ።
መላኩ ግዛው ማሩ-ቀረቡ።
መዝገቡ ከሰ/መ/ ከሆነው ጋር ተጣምሮ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የሰው ግድያ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በተጠሪዎች ላይ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው።የአሁኑ አመልካች በተጠሪዎች ላይ የመሰረተው ክስ ይዘት ሲታይም በ1996 ዓ/ም በወጣው የኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1(ሀ፣ለ)) እና 539(1(ሀ)) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ሟች አቶ የማነ መስፍንና ሟች የትናየት ጌቱ ጥር 12 ቀን 1999 ዓ/ም በነገላ ወረዲ ላንጋኖ በቀለ ሞላ ሆቴል ልዩ መዝናኛ ስፍራ ውስጥ እያለ 1ኛ ተጠሪ ሟች የትናየት ጌቱ እጮኛዬ ሆና እያለች ከሟች የማነ መስፍን ጋር ወደ መዝናኛ ሥፍራው ሄዲለች በማለት ከላሉቱ ወደ 6፡00 አከባቢ ሲሆን ከአዱስ አበባ እስከ መዝናኛ ቦታው በመሄድ በዚያው ሆቴል አልጋ በመያዝ ሟቾችን አይቷቸው ከለያቸው በኋላ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ተራ ቁጥር ስማቸው ለተጠቀሱት ተጠሪዎች ደውል ሟቾችን መግደል እንደሚፈልግ ነግሯቸው፣እነዚህ ተጠሪዎች በእለቱ ከላለቱ 8፡00 አከባቢ ላይ ተሰባስበው በመወያየት ሲጓዙ አድረው፣ ጥር 13 ቀን 1999 ዓ/ም ከጥዋቱ 12፡30 ሲሆን ወደ ሆቴለ ሲደርሱ አቶ አበራ ወ/ሚካኤል ፈቃድ ያወጡበትንና የሆነ ኮልት ሽጉጥ ባልታወቀ ሁኔታ ወደ ሆቴለ በድብቅ ካስገቡና ከ1ኛ ተጠሪ ጋራ ከተመካከሩ በሁዋላ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 1፡30 ሲሆን 1ኛ ተጠሪ(ኢዪሲያስ አበራ) ሟቾች ያለበትን የሆቴለ አልጋ ቁጥር 9 በአልጋ በኩል ያለውን መስኮት በመስበር በመግባት፣2ኛ ተጠሪ(ለአለም አበራ) ደግሞ በበር ገብቶ 1ኛ ተጠሪ በክሱ በተጠቀሰው ሽጉጥ ተኩሶ ሟቾችን የተለያየ አካላቸውን በመምታት ሲገድላቸው 2ኛ ተጠሪ አብሮ ገብቶ በሃሳብ ሲረዲው የነበረ ሲሆን ከ3ኛ እስከ 5ኛ ተራ የተጠቀሱት ተጠሪዎች ደግሞ ወንጀለ በሚፈጸምበት ወቅት በጋራ እነሱን ልኳቸው የወንጀለን ውጤት በሆቴለ ቁጥር 9 እና 8 መካከል ቆመው ሲጠባበቁ የነበሩ ከመሆኑም በላይ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ተራ የተጠቀሱት ተጠሪዎች ከሕግ ተጠያቂነት ራሳቸውንም ሆነ 1ኛ ተጠሪን ለማስመለጥ አስበው ወንጀለ የተፈፀመበትን ሽጉጥ 2ኛ ተጠሪ በሆቴለ አልጋ ቁጥር 9 ክፍል ውስጥ በጃኬት ጠቅልል ይዞ ለ4ኛ ተጠሪ ሲሰጥ ይኸው ተጠሪም ለ3ኛ ተጠሪ በማቀበል በመጡበት መኪና ውስጥ እንዱቀመጥ የደበቁ መሆኑን ዘርዝሮ በአጠቃላይ ተጠሪዎች አስበው፣ተባብረው፣ተረዲድተውና የወንጀለን ውጤት በመቀበል በቅናት ተነሳስተው ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ ሁለት ሰዎችን በግፍ ገድለዋል የሚል ነው።
ከዚህም በተጨማሪ 1ኛ ተጠሪ የወንጀል ሕጉን 808(ሀ) ድንጋጌን በመጣስ የተከሰሰ ስለመሆኑ የስር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ ያሳያል።ተጠሪዎች ክሱ ደርሷቸው በግልጽ ችልት ከተነበበላቸውና እንዱረደት ከተደረገ በሁዋላ የእምነት ክህደት ቃል ሲጠየቁ 1ኛ ተጠሪ ድርጊቱን መፈፀሙን አምኖ መብቱን ጠብቆ የተከራከረ ሲሆን ላልች ተጠሪዎች ግን የድርጊቱን አፈጻጸም ክደው ተከራክረዋል።ዐቃቤ ሕግ በበኩለ አለኝ ያላቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ያቀረበ ሲሆን ተጠሪዎችም ድርጊቱን እንደአቃቤ ሕግ የክስ አመሰራረት ስለመፈፀማቸው በዐቃቤ ሕግ ማስረጃዎች ተረጋግጦባቸዋል ተብል እንዱከላከለ ተደርጎ የመከላከያ ማስረጃዎችን አሰምተዋል።ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ጉዲዩን መርምሮ 1ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎችን በአቃቤ ሕግ በኩል ተጠቅሶ በቀረበባቸው ክስ መሰረት የጥፊተኛነት ውሳኔ ሰጥቶ 1ኛውን ተጠሪ በ18(አስራ ስምንት አመት)፣3ኛዋን ተጠሪ(ትርንጎ ወ/ሚካኤልኝ) ደግሞ በ15(አስራ አምስት አመት) ጽኑ እስራት እንዱቀጡ ሲወሰን 2ኛ፣4ኛ እና 5ኛ ተጠሪዎችን ግን ክሱን ተከላክለዋል በማለት በነፃ አስተናብቷቸዋል።በዚህ ውሳኔ የአሁኑ አመልካች በ1ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ላይ በተሰጠው የቅጣት ውሳኔ፣በላልች ተጠሪዎች ላይ የተሰጠው የነፃ መለቀቅ ውሳኔ ላይ እንዱሁም የአሁኑ 1ኛና 3ኛ ተጠሪዎች በጥፊተኝነት ውሳኔ ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መደበኛ ችልት በተለያዩ መዛግብት አቅርበው ጉዲዩ ከታየ በሁዋላ የአሁኑ አመልካች እና የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ ይግባኝ ተቀባይነት ሳያገኝ የቀረ ሲሆን የአሁኗ 3ኛ ተጠሪ ይግባኝ ግን ተቀባይነት አግኝቶ ክርክር ከተደረገበት በሁዋላ 3ኛ ተጠሪ ድርጊቱን መፈፀማቸው በሚገባ አልተረጋገጠባቸውም በሚል ምክንያት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሸሮ በነጻ እንዱሰናበቱ ተወስኗል። በዚህ ውሳኔ የአሁኑ አመልካችና የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው የአሁኑ አመልካች አቤቱታ ተቀባይነት ሲያጣ የ1ኛ ተጠሪ አቤቱታ ግን ተቀባይነት አግኝቶ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ 1ኛ ተጠሪ ድርጊቱን መፈፀሙ የተረጋገጠበት ቢሆንም ድርጊቱ ሉሸፈን የሚገባው በአቃቤ ሕግ በኩል ተጠቅሶ በቀረበው ድንጋጌ ሳይሆን ተራ የሰው ግድያ ወንጀል በሚያስጠይቅበት ድንጋጌ ነው ተብል ድንጋጌው ዝቅ ተደርጎለት የጥፊተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ በሁዋላ ቅጣቱም 16(አስራ ስድስት አመት) እንዱሆን ተድርጎ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሻሽል ተወስኗል።የሰበር አቤቱታው የቀረበውም በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነው።
አመልካች በሰ/መ/ በሆነው የሰበር አቤቱታውን ያቀረበው በ1ኛ ተጠሪ ላይ በስር ፍርድ ቤት የተጣለው ቅጣት ተገቢነት የለውም፣ከ2ኛ እስከ 5ኛ ተራ የተጠቀሱት ተጠሪዎችም ከክሱ በነጻ መሰናበታቸው ያላግባብ ነው በሚል ሲሆን በሰ/መ/ የቀረበው የሰበር አቤቱታ ይዘትም ደግሞ 1ኛ ተጠሪ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ድርጊቱ በወ/መ/ሕግ አንቀጽ 540 የሚሸፈን ነው ተብል የተሰጠው የሕግ ትርጉም ያላግባብ ነው በሚል ነው።በሁለቱም መዛግብት የቀረቡት የአቃቤ ሕግ የሰበር አቤቱታ ቅሬታ ነጥቦች ተመርምረውም በሰበር ችልት ሉታዩ የሚገባቸው ናቸው ተብል በመታመኑ ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በጠበቃቸው አማካኝነት የተጻፈ የጹሐፍ መልስ አቅርበዋል።የመልሳቸው መሰረታዊ ይዘትም በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የላለበት በመሆኑ ሉፀና ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆኑት ውሳኔዎችና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ በሰበር ችልት ሲቀርብ በሁለቱም መዛግብት የተያዙትን ጭብጦች በሚከተለው መልኩ መርምሯቸዋል።
1ኛ ተጠሪ ጥፊተኛ የተባለበት የሕግ ድንጋጌና በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው የቅጣት መጠን ተገቢ መሆን ያለመሆኑን በተመለከተ፡- 1ኛ ተጠሪ የተከሰሰው በወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1(ለ)፣(ሀ)) እና 539(1ሀ) የስር የተመለከተውን በመተላለፍ የትናየት ጌቱ እና የማነ መስፍን የተባለትን ሰዎች በተመሳሳይ ጊዜና ቦታ በግፍ ገድሎል በሚል ሲሆን ተጠሪ ድርጊቱን መፈፀሙን አምኖ ኃላፉነት የለብኝም፣ኃላፉነት አለብህ ከተባለም ቅጣትን ሉያቀልለ የሚችለ ሁኔታዎች በተገኙ ጊዜ የሰው መግደል ወንጀል ሉያስጠይቅ በሚችለው ድንጋጌ መሰረት ነው በማለት መሆኑን ከመዝገቡ ተመልክተናል።አቃቤ ሕግ በበኩለ የድርጊቱ አፈፃፀም በቅናት እና በጨካኝነት የተፈፀመ ስለመሆኑ ያሳያለ ያላቸውን ማስረጃዎችን አቅርቦ አሰምቷል።1ኛ ተጠሪ ራሱ በሰጠው ቃልም ሆነ በአቃቤ ሕግ ማስረጃዎች በፍሬ ነገር የተረጋገጠው ነጥብ የሚያሳየው ሟች የትናየት ጌቱና ተጠሪ ትዲር ሉመሰርቱ ስምምነት ተድርጎ ጋብቻው ሉፈፀም ሶስት ወራት ያህል በቀሩበት ጊዜ ውስጥ ጥር 12 ቀን 1999 ዓ/ም ከሟች የማነ መስፍን ጋር ወደ ላንጋኖ መዝናኛ በመሄድ በመዝናናት ላይ የነበሩ መሆኑን ተጠሪ ከአዱስ አበባ ወደ ላንጋኖ ላሉቱን ሄድ መኖራቸውን አረጋግጦና አጠቃላይ ሁኔታውን ከተመለከተ በሁዋላ በበነጋው ላይ ግን ተጠሪዎችን ከአገኘ በሁዋላ ሟቾች ወደ ተኙበት አልጋ በመስኮት በመግባት ሟቾችን በወቅቱ በያዘው ሽጉጥ ተኩሶ መግደለ ነው።ተጠሪ ድርጊቱ የተፈፀመው በንዳትና በብሥጭት ነው፣ራሴን ለመከላከል ነው በማለት ያቀረበውን መከራከሪያ ሁለም የበታች ፍርድ ቤቶች ያልተቀበለት ጉዲይ ሲሆን የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የ1ኛ ተጠሪ ድርጊት በግፍ ሰው የመግደል ወንጀል ሉያቋቁም የሚችል አይደለም ወደ ሚለው ድምዲሜ የደረሰው ተጠሪ ከሟች የትናየት ጌቱ ጋር እጮኛ ሁኖ ጋብቻ ሉመሰርት ሶስት ወር በቀረው ጊዜ ውስጥ ከላላ ሰው ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀሟ መረጋገጡና ተጠሪ ከአዱስ አበባ ተነስቶ ላንጋኖ እስኪደርስ ድረስ ሰው ለመግደል ሀሳብ ያለው ስለመሆኑ በዐቃቤ ሕግም ሆነ በፈፀመው ድርጊት የተረጋገጠ አይደለም በሚል ምክንያት ነው።
በመሰረቱ የሰው ግድያ ወንጀል በወንጀል ሕግ አንቀፅ 539(1(ሀ)) መሰረት ድርጊት ፈጻሚውን ሉያስጠይቅ የሚችለው ድርጊቱ ሆነ ተብል አስቀድሞ በማሰብና በመዘጋጀት ሲፈፀም ወይም በአንቀጽ 84 ወይም 86 ስር የተመለከቱት አክባጅ ሁኔታዎች በተገኙበት ሁኔታ የወንጀል አድራጊው በተለይ ጨካኝ፣ነውረኛ ወይም አደገኛ መሆኑን ሲያመለክቱ ስለመሆኑ ተጠቃሹ ድንጋጌ በግልጽ ያሳያል።ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው በድንጋጌው ስር የተመለከቱት የወንጀለ ማቋቋሚያ ነጥቦች በየራሳቸው መቆም የሚችለ ነጥቦች ስለመሆናቸው ነው።
በተያዘው ጉዲይ 1ኛ ተጠሪ ሟቾችን የገደለው ሟች የትናየት ጌቱ ፍቅረኛው ሁና ለጋብቻ ዝግጅት እየተደረገ ባለበት ጊዜ ከሟች የማነ መስፍን ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ስትፈፅም አረጋግጬአለሁ በማለት ሲሆን ድርጊቱን የፈፀመውም ከአዱስ አበባ ወደ ላንጋኖ ሂድ ሲሆን ከአዱስ አበባ ወደ ላንጋኖ ሲሄድም የላላ ሰው መሣሪያ ይዞ መሆኑ፣ላንጋኖ መዝናኛ ሲደርስም ሟቿ ከላላ ሰው ጋር መሆኗን ከአዱስ አበባ በሄደበት እለት አረጋግጦ እዚያው ላንጋኖ መዝናኛ አድሮ ጥዋት ላይ የአሁኑ ተጠሪዎች ከቦታው ከደረሱለት በሁዋላ ሟቾች ወደ ተኙበት አልጋ በመስኮት ገብቶ ነው።ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው ተጠሪ ቀድሞውኑም ከአዱስ አበባ ሲነሳና እስከ ላንጋኖ ላሉቱን በመጓዝ ሲደርስ ሰውን ለመግደል ሀሳብና ቅድመ ዝግጅት ያለው ስለመሆኑ በራሱ አረጋጋጭ ሲሆን ይህ ቅድመ ዝግጅቱን አያረጋግጥም ቢባል እንኳ ተጠሪ እዚያው አድሮ ላልች ሰዎች ወደ ቦታው ከደረሱ በሁዋላ ድርጊቱን መፈጸሙ ከላንጋኖ መዝናኛ ከደረሰ በሁዋላ ሁኔታውን አይቶና ተገንዝቦ፣አጠቃላይ ሁኔታዉን አውጥቶና አውርድ ከአሰበና ሉከተል የሚችለውን ውጤት ሙለ በሙለ ለመቀበል ዝግጁ ከሆነ በሁዋላ ሲሆን በቅፅበት ደም ሉያፈላ የሚችል ሁኔታ ሲያልፍና መንፈሱ ሲረጋጋ የፈፀመው ድርጊት መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው።እነዚህ ፍሬ ነገሮች 1ኛ ተጠሪ የግድያ ወንጀለን አስቦበትና ቀድሞ ተዘጋጅቶበት በጭካኔ ወይም በአደገኛነት በተለይም በማንአለብኝነት የፈፀመው ስለመሆኑ ያሳያለ ከሚባለ በስተቀር በእለታዊ ፀብ እና አለመግባባት ምክንያት የፈፀመው ድርጊት ነው ለማለት የሚያስችለ አይደለም።አንድ ሰው እጮኛው የሆነችውና ጋብቻ ለመፈፀም በዝግጅት ላይ ያለች ሴት ጋብቻው ከመፈፀሙ በፉት ከላላ ሰው ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ፈፅማለች ብል ከሴቷ ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነት ሲፈፀም ነበር ከተባለው ሰው ጋር ይገኙበታል እስከተባለው ቦታ ድረስ ላሉቱን ረዥም ጉዞ በመጓዝ ከደረሰና ሁኔታውን ከተመለከተ በሁዋላ ቀላል የማይባል ሰዓት አሳልፍ ሕግና ሥርዓት ባለበት አገር ሁለት ሰዎችን በአንድ ላይ አከታትል መግደለ በማንአለብኝነት፣በቂምና በቅናት መንፈስ ክቡሩን የሰው ሕይወት አጥፍቷል ከሚባል በስተቀር በማናቸውም መመዘኛ ግድያውን ተራ የሰው ግድያ ወንጀል ሉያደርግ የሚችል አይደለም።በመሆኑም የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በአቃቤ ሕጉ ማስረጃ የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር ከሕጉ ጋር ማገናዘብ ሲገባው ያለሕጋዊና በቂ ምክንያት በ1ኛ ተጠሪ ላይ በአቃቤ በኩል ተጠቅሶ የቀረበውን ድንጋጌ መቀየሩ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል።በዚህም መሰረት 1ኛ ተጠሪ ለፈመው የሰው ግድያ ወንጀል ሉጠየቅ የሚገባው በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 539(1(ሀ)) ስር እንጂ በአንቀጽ 540 ስር ባለመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች በ1ኛ ተጠሪ ላይ በወ/ሕ/ቁጥር 539(1ሀ) ስር የሰጡትን የጥፊተኝነት ውሳኔ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የቀየረው ያላግባብ ሁኖ ስላገኘነው በ1ኛ ተጠሪ (ኢዮስያስ አበራ) ላይ በወ/ሕ/ቁጥር 540 ስር የተሰጠውን የጥፊተኝነት ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195(2(ለ-2)) መሰረት ለውጠን ተጠሪ በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 539(1ሀ) ስር ጥፊተኛ ተብል ሉቀጣ የሚገባ ሆኖ አግኝተናል።
2ኛ. በላልች ተጠሪዎች(ከ2ኛ እስከ 5ኛ ተራ በተጠቀሱት) ላይ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን በተመለከተ፡ሁለተኛ ተጠሪ(ለአለም አበራ) በስር ፍርድ ቤት በነፃ የተሰናበተ ሲሆን ለውሳኔው የስር ፍርድ ቤት መሰረት ያደረገው ምክንያትም ተጠሪው የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈጸሙ አልተረጋገጠም፣በመከላከያ ምስክርም ወደ ቦታው የሄደበትን ምክንያት አስረድቷል በሚል ምክንያት ነው።2ኛ ተጠሪ በአቃቤ ሕግ የተከሰሰው ለ1ኛ ተጠሪ ግብረ አበር በመሆን በድርጊት አፈጻጸሙ ተሳትፎል በሚል ምክንያት ሲሆን በድርጊት አፈፃጸሙ የነበረው ተሳትፍን በተመለከተም ሟቾች ወደ ተኙበት አልጋ 1ኛ ተጠሪ በመስኮት ሲገባ 2ኛ ተጠሪ በአልጋው በር በኩል ገብቷል፣ድርጊቱ ከተፈጸመ በሁዋላም በበር በኩል ወጥቷል በማለት በክሱ ላይ ገልጿል።ይህንኑ የተጠሪን የወንጀል ድርጊት ተሳትፍ ለማረጋገጠም የሰው ምስክሮችን ያቀረበ ሲሆን 1ኛው የአቃቤ ምስክር በወቅቱ በቦታው ላይ የነበረ መሆኑን ገልፆ ሁለት ሰዎች ሲሯሯጡ እንደነበርና አንደ ሟቾች ወደ ተኙበት አልጋ በበር ሲገባ ላላው በመስኮት መግባቱን መመልከቱን በአከባቢ ማስረጃነት የመሰከረ ሲሆን 3ኛ የአቃቤ ሕግ ምስክር 2ኛ ተጠሪ ሟቾች ከተኙበት አልጋ ውስጥ ጥይት ከተተኮሰ በሁዋላ በበር በኩል ጃኬቱን ይዞ መውጣቱን መስክሯል።ላልች የአቃቤ ሕግ ምስክሮች በሰጡት ቃልም 2ኛ ተጠሪ ድርጊቱ በተፈፀመበት ቦታ የነበረ መሆኑንና 1ኛ ተጠሪን ላልች ሰዎች ለመያዝ ሲሞክሩም እንዲይያዝና ጉዲት እንዲይደርስበት ጥረት ሲያደርግ የነበረ መሆኑን አረጋግጠዋል።እንግዱህ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠው ነጥብ ሲታይ 2ኛ ተጠሪ ሟቾች በተገደለበት ጊዜና ቦታ በመገኘት 1ኛ ተጠሪ በመስኮት ሲገባ እሱ ደግሞ በቤርጎው በር በመግባት ጥይት ከተተኮሰ በሁዋላ እንደገና በቤርጎው በር ሩጦ የወጣና ጃኬትም ለላላ ሰው ያቀበለ መሆኑ እንዱሁም 1ኛ ተጠሪን በቦታው የነበሩት ላልች ሰዎች ከተኩሱ በሁዋላ ቁም ሲለትም ይህንኑ ይከላከል የነበረ መሆኑ ነው።እነዚህ ፍሬ ነገሮች ሲታዩ ደግሞ 2ኛ ተጠሪ ሟቾችን ራሱ በቀጥታ ተኩሶ መግደለ ባይረጋገጥም ሟቾችን ለህልፈት የዲረገውን የተኩስ ተግባር 1ኛ ተጠሪ ሲፈፅም ከዚሁ ተጠሪ ጋር ተባብሮ ሟቾች ወደ ተኙበት አልጋ በበር በኩል መግባቱም ሆነ ከተኩሱ በሁዋላ በበር ሩጦ መውጣቱ በመላ ሀሳቡና አድራጎቱ በወንጀለ ድርጊትና በሚሰጠው ውጤት ሙለ ተካፊይ በመሆን ድርጊቱን የራሱ ያደረገ መሆኑን የሚያስገነዝቡን ናቸው። የስር ፍርድ ቤት 2ኛ ተጠሪን ነጻ ያደረገበት ምክንያት ድርጊቱን ስለመፈፀሙ አልተረጋገጠም፣በመከላከያም አስረድቷል በሚል ነው።ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ ወደዚህ ድምዲሜ የደረሰው በአቃቤ ሕግ ማስረጃዎች የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር በአግባቡ ባለመያዝ በደፈናው የ2ኛ ተጠሪ የድርጊቱ ተሳትፍ አልተረጋገጠም በማለት ነው። አንድ ፍርድ ቤት በሕግ በኩል የቀረቡትን ማስረጃዎችን ውድቅ ሉያደርግ የሚገባው በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠውን ነገር ሙለ በሙለ በመመዘን እንጂ ከማስረጃዎቹ ውስጥ የተወሰነውን ፍሬ ነገር ብቻ በመያዝ ላሆን እንደማይገባው ተቀባይነት ያላቸው የማስረጃ ሕግ ፅንሰ ሀሳቦች የሚያስገነዝበን ሐቅ ነው።በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎች በ2ኛ ተጠሪ ላይ የድርጊቱን ተሳትፍ አላረጋገጡም ወደሚለው ድምዲሜ የደረሰው ተጠሪ እንዱከላከል ትዕዛዝ ከሰጠ በሁዋላ ሁለም የአቃቤ ሕግ ምስክሮች የሰጡትን የምስክርነት ቃል አንድ ባንድ ባለማየት ነው።ተጠሪው በመከላከያ ማስረጃ የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን አስተባብሎል የሚለው ድምዲሜም ተጠሪው ወንድሙ የሆነው 1ኛ ተጠሪ ያለበትን ሁኔታ ለማየት ከአዱስ አበባ ወደ ላንጋኖ መሄደ ተመስክሯል በሚል ምክንያት ነው።ሆኖም የ2ኛ ተጠሪ የመከላከያ ማስረጃ ያረጋገጠው ይኸው ፍሬ ነገር ተጠሪው ላንጋኖ ከደረሰ በሁዋላ የነበረውን የድርጊት ተሳትፍን የሚያስተባብል አይደለም።በመሆኑም ሁለተኛ ተጠሪ(ለአለም አበራ ገ/ሚካኤል) የወንጀል ድርጊቱን በመላ አሳቡና አድራጎቱ የወንጀለ ድርጊት የሚሰጠውን ውጤት ሙለ ተካፊይ በመሆን ድርጊቱን የራሱ ያደረገ መሆኑ በአቃቤ ሕግ የአከባቢና የአይን ምስክሮች ተረጋገጦበት እያለ በማስረጃ የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር በመተው ተጠሪውን የስር ፍርድ ቤት በነጻ ማሰናበቱም ሆነ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች አለመታረሙ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ ስለአገኘነው 2ኛ ተጠሪ ላይ የተሰጠውን የነጻ መለቀቅ ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ስ/ስ/ቁጥር 195(2(ሀ)) መሰረት ለውጠን 2ኛ ተጠሪ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 32(1(ለ)) እና 539(1(ሀ)) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ የተላለፈ ጥፊተኛ ነው ብለናል።
ላላው በአቃቤ ሕግ በኩል የቀረበው የሰበር ቅሬታ በ3ኛ ተጠሪ(ትርንጎ ወ/ሚካኤል) ላይ የተሰጠውን ውሳኔ የሚመለከት ነው።የስር ፍርድ ቤት 3ኛ ተጠሪን በተመለከተ በተከሰሱበት የሕግ ድንጋጌ ጥፊተኛ በማድረግ በአስራ አምስት አመት ፅኑ እስራት እንዱቀጡ ወስኗል።ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው ፍርድ ቤት ደግሞ ተጠሪ በግድያው ወንጀል የነበራቸው ተሳትፍ አልተረጋገጠም በማለት ሙለ በሙለ በነጻ እንዱሰናበቱ አድርጓል።ይህ ችልትም ጉዲዩን ሲመለከተው ማስረጃን የመመዘንና ፍሬ ነገርን የማጣራት ስልጣን ያለው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ቸልት የአቃቤ ሕግን ማስረጃ ዝርዝር ይዘት በመመልከት 3ኛ ተጠሪ በግድያው ወንጀል የነበራቸው ተሳፍቶ አልተረጋገጠም ወደሚለው ድምዲሜ ደርሷል።አቃቤ ሕግ ደግሞ የተጠሪ የወንጀል ተሳትፍ በማስረጃ የተረጋገጠ ነው በማለት ቅሬታውን አቅርቧል።ይሁን እንጂ አቃቤ ሕግ ክሱን ሲመሰርት 1ኛ ተጠሪ ሟቾችን እንደሚገድል ለ3ኛ ተጠሪ ስልክ ደውልላቸው ይህንኑ ሰምተው ላሉቱን በመኪና ሲጓዙ አድረው ድርጊቱ ወደተፈጸመበት ቦታ በመድረስ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ከተመካከሩ በሁዋላ ድርጊቱ መፈፀሙን፣ድርጊቱ ሲፈፀምም በቦታው ላይ 3ኛ ተጠሪ ቁመው ውጤቱን ሲጠባበቁ የነበሩ መሆኑን የጠቀሰ ቢሆንም ይህ በአቃቤ ሕግ ማስረጃ አለማረጋገጡን የስር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ የሚያስገነዝብ ሲሆን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም 3ኛ ተጠሪ ወደላንጋኖ የሄደበትን ምክንያትና ከሄደ በሁዋላ ስለግድያው የነበራቸውን ተሳትፍ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በግድያ ወንጀለ 3ኛ ተጠሪ ተሳትፍ የነበራቸው ስለመሆኑ አልተረጋገጠም ወደሚለው ድምዲሜ ደርሷል።ይህ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ድምዲሜ የማስረጃ ምዘናን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት ከተሰጠው የመሰረታዊ ሕግ ስህተት የማረም ስልጣን አንፃር ሲታይ በዚህ ችልት ሉታረም የሚገባው ሁኖ አልተገኘም።በመሆኑም አቃቤ ሕግ 3ኛ ተጠሪን በተመለከተ በከባድ የግድያ ወንጀል ተጠያቂ ሉሆኑ ይገባል በማለት ያቀረበው ቅሬታ የመሰረታዊ ሕግ ስህተትን መመዘኛ የሚያሟላ ሁኖ ባለማግኘታችን አልፈነዋል።ሆኖም 3ኛ ተጠሪ ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ የነበሩ፣ተኩስ ከተሰማ በሁዋላም የወንጀል ድርጊቱ ከተፈፀመበት ቤርጎ ውስጥ በልላ ሰው ወጥቶ የተሰጣቸውን ጃኬት ተቀብለው መኪና ውስጥ በማስገባት ቆልፈው በኋላ መኪናው ተከፍቶ ጃኬቱ ሲታይ ሽጉጥ መገኘቱ በስር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ በሚገባ የተረጋገጠ ጉዲይ መሆኑ ሲታይ 3ኛ ተጠሪ ሙለ በሙለ ነፃ ሉሆኑ ይችላለ? ወይስ በተረጋገጠባቸው መጠን አግባብነት ባለው የሕግ ድንጋጌ ሉጠየቁ ይገባቸዋል? የሚለውን ጥያቄ የሚያስነሳ ሁኖ አግኝተነዋል።በመሰረቱ አንድ ሰው በአቃቤ ሕግ በኩል የተመሰረተበት ክስ እንደክሱ አመሰራረት ሳይረጋገጥ ቢቀርም የቀረበው ማስረጃ ከቀረበው ክስ ያነሰ የወንጀል ድርጊት በተከሳሽ መፈጸሙ ከተረጋገጠ ተከሳሹ በተመሰከረበት የወንጀል ድርጊት የማይጠየቅበት ሕጋዊ ምክንያት የላለ መሆኑን ከወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 113 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው።በተያዘው ጉዲይ 3ኛ ተጠሪ የግድያ ወንጀል ከተፈጸመ በኋላ ሽጉጡ የተጠቀለለበትንና የተሰጣቸውን የግድያ ወንጀል ከተፈጸመበት ቤርጎ የወጣውን ጃኬት ተቀብለው ከመኪና ውስጥ መደበቃቸው የተረጋገጠ ሲሆን ይህም ወንጀል ከተደረገ በሁዋላ ሆነ ብለው ወንጀል አድራጊው ከመከሰስና ከመቀጣት እንዱያመልጥ የረደት መሆኑን በግልፅ የሚያሳይ ሲሆን አድራጎቱ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 40 መሰረት በአንቀጽ 445 ስር ተጠያቂነት የሚያስከትል ነው።በመሆኑም የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት 3ኛ ተጠሪን በግድያ ወንጀል ሉጠየቁ አይገባም ወደሚለው ድምዲሜ የደረሰበት መንገድ የማስረጃ ምዘና ሁኖ በዚህ ችልት ላታይ የሚችል ባይሆንም ይግባኝ ሰሚው ችልት ተጠሪ ስለመፈፀማቸው በፍሬ ነገር ደረጃ በሚገባ የተረጋገጠውንና ወንጅለ ከተደረገ በኋላ ወንጀል አድራጊውን መርዲትን በተመለከተ የተደነገገውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ 3ኛ ተጠሪን ጥፊተኛ ያለማድረጉ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል።ስለሆነም 3ኛ ተጠሪ በአቃቤ ሕግ በኩል ተጠቅሶ የቀረበባቸውን ድንጋጌ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 113(2)መሰረት በመለወጥ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 40 እና 445 ስር የተመለከተውን የተላለፈ ጥፊተኛ ናቸው ብለናል።
ላላው በአቃቤ ሕግ በኩል የቀረበው ቅሬታ በስር 4ኛ ተከሳሽ(አብያለው አበራ) ላይ የተሰጠውን የነጻ መለቀቅ ውሳኔ የሚመለከት ነው።አቃቤ ሕግ ይህ ተጠሪም በግድያው ወንጀል ሉጠየቅ የሚገባ መሆኑን ጠቅሶ የሰበር አቤቱታ አቅርቧል።ይሁን እንጂ የስር ፍርድ ቤትም ሆነ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው ፍርድ ቤት ይህንኑ ተጠሪ ከግድያ ወንጅለ ያሰናበቱት በጉዲዩ ላይ የቀረቡትን ማስረጃዎችን በመመዘን ስለመሆኑ የውሳኔው ግልባጭ ያሳያል።በመሆኑም ከላይ እንደተጠቀሰው ይህ ችልት በሕግ ከተሰጠው የመሰረታዊ ሕግ ስህተት የማረም ስልጣን አንፃር ሲታይ በዚህ ረገድ የተሰጠው የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት የሚቻል ሁኖ አልተገኘም።ይሁን እንጂ 4ኛ ተጠሪ በግድያ ወንጅለ የነበረው የተሳትፍ ሁኔታ አልተረጋገጠም የተባለው ማስረጃ ተመዝኖ ቢሆንም ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ ተገኝቶ ድርጊቱ ከተፈጸመበት የቤርጎ ቁጥር ከድርጊቱ በሁዋላ ወዱያውኑ የወጣውንና ድርጊቱ የተፈጸመበት ሽጉጥ መጠቅለለ የተረጋገጠበትን ጃኬት ድርጊቱ ከተፈጸመበት ቤርጎ ከወጣው ሰው ተቀብል ለ3ኛ ተጠሪ መስጠቱ በአቃቤ ሕግ የአይንና የአካባቢ ማስረጃ የተረጋገጠበት ሲሆን ይህንኑ ፍሬ ነገር ላለመቀበል የሚያስችል ምክንያት የላለ መሆኑን የክርክሩ ሂደት በግልጽ ያሳያል።ስለሆነም 4ኛ ተጠሪ( አብያለው አበራ) ወንጀል ከተደረገ በሁዋላ ወንጀል አድራጊውን በመርዲት ወንጀል መጠየቅ ሲገባው ከዚሁ የወንጀል አድራጎቱ ሁለ ነፃ መደረጉ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር በመተው በመሆኑ በዚህ ረገድ የተሰጠው ውሳኔ ሉታረም የሚገባው ሁኖ ስለአገኘን 4ኛ ተጠሪ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 40 እና 445 መሰረት ጥፊተኛ ላሆን የሚገባው ነው ብለናል።
5ኛ ተጠሪን (መላኩ ግዛው ማሩን) በተመለከተ የቀረበውን የአቃቤ ሕግን ቅሬታ ስንመለከተው ደግሞ ይህ ተጠሪ ከድርጊቱ ሙለ በሙለ ነፃ የተባለው በጉዲዩ ላይ የቀረቡት ማስረጃዎች ተመዝነው ሲሆን በፍሬ ነገር ደረጃም ከግድያው ባነሰ የወንጀል ድርጊት ሉያስጠይቀው የሚችል የወንጀል ተሳትፍ ስለመኖሩ የክርክሩ ሂደት የማያረጋገጥ ሁኖ ስለአገኘነው በዚህ ረገድ በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም።
3ኛ ተጠሪን በተመለከተ ይህ ችልት ጥፊተኛ ያደረጋቸው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 40 እና 445 ስር ሲሆን ቅጣቱ ሉተላለፍ የሚገባውም በዚሁ ድንጋጌ መሰረት ነው። በዚህ ድንጋጌ ጥፊተኛ የተባለ ሰው ሉቀጣ የሚችለው በቀላል እስራት ወይም በመቀጮ ነው። ቅጣት የሚወሰነው ደግሞ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 88(2) ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎችን በማመዛዘን ሲሆን ይህ ችልትም 3ኛና 4ኛ ተጠሪዎች በስር ፍርድ ቤት ያስመዘገቡትን የቅጣት አስተያየት ከድርጊቱ አፈጻጸም ጋር አገናዝቦ ተመልክቷል። በዚህም መሰረት 3ኛ ተጠሪ በጉዲዩ የታሰሩት ማንኛውም ጊዜ የሚታሰብላቸው ሁኖ በሶስት አመት ቀላል እስራት ሉቀጡ የሚገባ ሁኖ አግኝተናል። ሲጠቃለልም በጉዲዩ ላይ በበታች በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ሉሻሻል የሚገባው ሁኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሚያዚያ 01 ቀን 2000 ዓ/ም የተሰጠ ውሳኔ ፣ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ጳገሜ 04 ቀን 2000 ዓ/ም የተሰጠው ትእዛዝ ፣ በዚሁ ችልት በመ/ ህዲር 02 ቀን 2001 ዓ/ም የተሰጠው ውሳኔ ፣ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ የካቲት 18 ቀን 2001 ዓ/ም የተሰጠው ትእዛዝ እንዱሁም በዚሁ ችልት በመ/ ታህሳስ 19 ቀን 2002 ዓ/ም የተሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 195(2(ለ-2) መሰረት ተሻሽሎል።
1ኛ ተጠሪ (ኢዮስያስ አበራ) ጥፊተኛ ልባል የሚገባው በወንጀል ህጉ አንቀጽ 539(1(ሀ)) ሲሆን ቅጣቱም እድሜ ልኩን ጽኑ እስራት እንዱሆን ተወስኗል ፣ 3ኛ ተጠሪ የፈጸሙት ድርጊት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 445 ስር የሚሸፈን ሁኖ ቅጣቱን በተመለከተ በጉዲዩ ላይ የታሰሩት ጊዜ የሚታሰብላቸው ሁኖ በሶስት አመት ቀላል እስራት እንዱቀጡ በማለት ወስነናል።
5ኛ ተጠሪ (መላኩ ግዛው)ን በተመለከተ በነፃ መሰናበቱ ባግባቡ ነው ብለናል።
በ1ኛ ተጠሪ ላይ ቅጣቱ ተሻሽል የተወሰነ መሆኑን አውቆ ተከታትል እንዱያስፈፅም ለማረ/ቤቱ ይገለፅለት ብለናል።ይፃፍ።
ከተባለ በኋላ በ2ኛ እና በ4ኛ ተጠሪዎች ላይ ቅጣት ለመወሰን ይቻል ዘንድ የግራ ቀኙኝ የቅጣት አስተያየት በመጠየቅ ግራ ቀኙ ያቀረቡት የቅጣት አስተያየት በመቅረጸ ደምፅ ተቀርጿል።
ግራ ቀኙ ያቀረቡት የቅጣት አስተያየት ከመቅረፀ- ደምጽ ወደ ፅሐፍ ተቀይሮ ከመዝገቡ ጋር ይያያዝ ብለናል።
የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት መርምሮ ተገቢውን ቅጣት ለመወሰን ለሰኔ 21 ቀን 2003 ዓ/ም ተቀጥሯል።
2ኛ፣3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎችን የአራዲ ክፍለ ከተማ ፕሉስ መምሪያ አቆይቶ ለሰኔ 21 ቀን 2003 ዓ/ም ችልት እንዱያቀርባቸው ታዝዟል። ማሰሪያ ዋራንት ይፃፍ።
No topics extracted.