No summary available.
ሚያዝያ 18 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ኤልያስ ገረመው - አልቀረቡም ተጠሪ፡- የኢት/ገ/ጉ/ባ/ዐ/ህግ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አመልካች በስር የመ/ደ/ፍ/ቤት 3ኛ ተከሣሽ የነበረ ሲሆን ፍ/ቤቱም የቀረበለትን የዋስትና ጥያቄ ከመረመረ በኋላ አመልካች ለብር 3ዐዐ,000 /ሶስት መቶ ሺህ/ የሚበቃ ዋስትና እንዱያቀርቡ በመ/ዐ በቀን 18/10/2002 ዓ.ም በዋለው ችልት ብይን የሰጠ ሲሆን የስር ከሣሹ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 74ን በመጥቀስ አዱስ ነገር የተገኘ ስለሆነ ቀደም ሲል የተፈቀደው የዋስትና መብት እንዱነፈግ በማመልከቱ ፍ/ቤቱም የስር ከሣሽን አቤቱታ በመቀበል የተፈቀደው ዋስትና ቀሪ እንዱሆንና አመልካች /የስር 3ኛ ተከሣሽ/ በማረሚያ ቤት ሆኖ ክርክሩን እንዱቀጥል ማዘዙን የስር ፍ/ቤት መዝገብ ያመለክታል።
የሰበር አመልካችም የተፈቀደለትን ዋስትና በመከልከለ ምክንያት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ከፍተኛው ፍ/ቤትም የስር መ/ደ/ፍ/ቤት የፈቀደውን ዋስትና እንደገና መከልከለ ተገቢ አይደለም ሐምል 7/2002 ዓ.ም በዋለው ችልት አመልካች በዋስ እንዱወጣ አዟል።
ይሁን እንጂ ያሁን ተጠሪ አዱስ ነገር ተገኝቷል በማለት የአመልካች የዋስትና መብት እንደገና እንዱነፈግ በመጠየቁ ከፍተኛው ፍ/ቤትም አዱስ ነገር መገኘቱንና አለመገኘቱን ለማጣራት ማስረጃ የሰማ ሲሆን ለማስረጃነት የቀረበውም የማስፈራራት ድርጊት ተፈጽሞበታል የተባለው ሰው ነው።
የስር ከፍተኛ ፍ/ቤትም የቀረበውን ምስክር ቃል ከመረመረ በኋላ የተጠሪን አቤቱታ በመቀበል በመ/ በቀን 12/12/2002 ዓ.ም በዋለው ችልት ተፈቅድለት የነበረውን ዋስትና ከልክሎል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ በከፍተኛ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት ሲሆን የዘረዘራቸውም ዋና ዋና የቅሬታ ነጥቦች፣ አመልካች የተከሰሰበት ወንጀል ዋስትናን አያስከለክልም፣ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 74 መሰረት አዱስ ነገር ተገኝቷል በሚል በቀረበው አቤቱታ መነሻ ቀርቦ የምስክርነት ቃለን የሰጠው የተጠሪ ምስክር ለቀረበለት መስቀለኛ ጥያቄ ሲመልስ ማን እዲስፈራራው እንደማያውቅ ተናግሮ እያለ አዱስ ነገር ተገኝቷል በሚል የተፈቀደው ዋስትና መነፈጉ ተገቢነት የለውም የሚለ ናቸው።
ተጠሪው በበኩለ በሰጠው መልስ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 74 መሰረት አዱስ ነገር የተገኘ እንደሆነ ፍ/ቤቱ በማንኛውም ጊዜ በዋስትና ላይ የሰጠውን ውሣኔ መሻር ይችላል፣ ፍ/ቤቱም አዱስ ነገር ስለመገኘቱ ማስረጃ ሰምቶ አረጋግጧል፣ በማስረጃ ዙሪያ በሰበር ደረጃ ክርክር ላደረግ አይገባም። በመሆኑም የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ ህግን መሰረት ያደረገ ስለሆነ የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከዚህ በላይ እንደተገለጸው አጥሮ የቀረበ ሲሆን እኛም የስር ከፍተኛው ፍ/ቤት የፈቀደውን ዋስትና አዱስ ነገር ተገኝቷል በሚል በሰጠው ትዕዛዝ መከልከለ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚያሰኝ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ ይዘን እንደሚከተለው መርምረናል።
በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህግ-መንግስት አንቀጽ 19/6/ በተደነገገው መሰረት የተያዙ ሰዎች በዋስ የመፈታት መብት ያላቸው ሲሆን በህግ በተደነገጉ ሁኔታዎች ግን ፍ/ቤት ዋስትናን ላለመቀበል ይችላል። ዋስትና ከተፈቀደ በኋላም ቢሆን አዱስ ነገር የተገኘ እንደሆነ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 74 መሰረት ፍ/ቤቱ በማናቸውም ጊዜ ቢሆን በስልጣኑ ወይም በማናቸውም ባለጉዲይ አመልካችነት ተከሣሹ በዋስትና ወረቀት የተለቀቀበትን ሁኔታዎች እንደገና ለማየት ይችላል። በዚሁ መሰረት ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች በከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ በዋስትና ከተለቀቀ በኋላ የከሣሽ ምስክር የሆነውን ግለሰብ ማስፈራራቱን ምስክሩ ለስር ከፍተኛ ፍ/ቤት ከሰጠው የምስክርነት ቃል መመልከት ይቻላል።
አመልካች በዋስትና ከተለቀቀ በኋላ የፈጸመው ድርጊት ደግሞ አዱስ ድርጊት ስለሚሆን ፍ/ቤቱ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 74 ከተቀመጡት ሁለት አማራጮች ማለትም ተከሣሽ አዱስ ዋስ እንዱያመጣ ወይም በማረፉያ ቤት እንዱቆይ ይደረጋል ከሚለት ሁለተኛውን አማራጭ በመውሰድ የዋስትና መብቱን በመከልከል ማረፉያ ቤት እንዱቆይ አድርጓል።
በልላ በኩል አመልካች የቀረበው የተጠሪ ምስክር ለቀረበለት መስቀለኛ ጥያቄ ማን እንዲስፈራራው እንደማያውቅ ተናግሯል በማለት የተከራከረውም ቢሆን በዚህ በሰበር ደረጃ መጣራት የላለበት የፍሬ ነገር ክርክር በመሆኑ ተቀባይነት የለውም።
በአጠቃላይ ይህ ችልት በሰበር መ/ በቀን 28/3/2003 ዓ.ም በአመልካች ወ/ሮ ሉዊዛ ፍርቤታ እና በተጠሪ ዐ/ሕግ መካከል በተደረገው የዋስትና ክርክር ችልቱ በኢ/ፋ/ዱ/ሪ/ህገ መንግስት አንቀጽ 8ዐ/3/ /ሀ/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 1ዐ መሰረት የተሰጠው ስልጣን ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃ መመዘን ባለመሆኑ በዚህ ችልት ላታይ አይገባም በማለት እና በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 74 መሰረት አዱስ ነገር ሲገኝ የተፈቀደው ዋስትና ሉከለክል ስለመቻለ የሰጠው ትርጉም በዚህ በተመሣሣይ ጉዲይ አስገዲጅነት ስላለው በዚህ በተያዘውም ጉዲይ በስር ከፍተኛ ፍ/ቤት በተሰጠው ትዕዛዝ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት አላገኘንም።
ው ሣ ኔ
የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 12/12/2002 ዓ.ም በዋለው ችልት ሐምል 7 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ለአመልካች ተሰጥቶት የነበረውን የዋስትና ፈቃድ ትዕዛዝ በማንሣቱ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም ብለናል።
መዝገቡ የተዘጋ ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.