No summary available.
መጋቢት 5 ቀን 2003 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ነብይ በድሩ ሸፊ ጠበቃ ማርቆስ ወ/ሰንበት - ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል ሥ/ፀ/ሙ/ኮሚሽን ዐቃቤ ሕግ ዋልተ ንጉስ ፍቅሬ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በወንጀል መዝገብ የሰጠው የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሣኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የወንጀል ይግባኝ ችልት የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠውን ፍርድ በወንጀል ይግባኝ መዝገብ ማፅናቱ በሰበር የሚጣራ ነጥብ ያለው መሆኑ ጭብጥ ተይዞ በመቅረቡ ነው።
በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪ ከሣሽ አመልካች ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪ አመልካችና በሥር ሁለተኛ ተከሣሽ የነበረው አቶ ቶውፉቅ ሹፋ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሰ/ እና /ለ/ በአንቀጽ 427 ንዐስ አንቀጽ 1 እና ንዐስ አንቀጽ 3 ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ ግብረ አበር በመሆን የፋዳራል የሥነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን መረጃና ክትትል ሰራተኛ የሆነውን አቶ ሰለሞን ታደሰን በሥራው ኃላፉት ማድረግ የሚገባውን እንዲያደርግ በማሰብ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ባለመክፈል የማታለልና የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ለመያዝ ይደረግባቸው የነበረውን ምርመራና ክትትል እንዱቋረጥ አድርግልን በማለት መጋቢት 18 ቀን 2000 ዓ.ም. ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ከፋዳራል ሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ህንፃ ቢሮ ቁጥር 207 ድረስ በመግባት ብዛቱ አሥራ አምስት እሽግ የሆነ እያንዲንደ አሥር ሺህ ብር የያዘ በሁለተኛው ተከሣሽ አማካኝነት ለአቶ ለለሞን ታደሰ የሰጡ በመሆናቸው በግብረአበርነት በመላ ሀሳባቸውና አድራጎታቸው ሙለ ተካፊይ በመሆን የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በማለት ያቀረበው የወንጀል ክስ ነው። የሥር ፍ/ቤት ግራ ቀኙ የቅድመ ክስ ክርክር እንዱያደርጉ ካደረገ በኋላ የተማመኑበት ነጥብ የላለ በመሆኑ የተጠሪን ምስክሮች ሰምቷል።
የመጀመሪያው የዐቃቤ ሕግ ምስክር የፋዳራል የሥነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የክትትል ሰራተኛ መሆኑን ገልፆ፣ መጋቢት 17 2000 ዓ.ም. ከጧቱ ሦስት ሰዓት ሲሆን ሁለተኛ ተከሣሽ አቶ ቶፉቅ ሹሬ አቶ ታደሰ ከሚባል ሰው ጋር ከቢሮ ድረስ መጥተው ሁለተኛ ተከሣሽ የአጎቴ ልጅ አንደኛው ተከሣሽ በኮሚሽኑ ምርመራ እየተደረገበት ነው። ቤተሰብ እየተጨነቀ ነው።
በአንደኛው ተከሣሽ ላይ የተጀመረውን ክትትልና ምርመራ አቋርጥልን ለአንተም ትጠቀማለህ ብር 150,000 /አንድ መቶ ሀምሣ ሺህ ብር/ እንሰጥሀለን። ሁለተኛ ተከሣሽ 18/07/2000 ብሩን ይዞ እንዱመጣ ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ቀጠርኩት፣ ሁለተኛ ተከሣሽ ብር ይዞ እንደሚመጣና በአንደኛ ተከሣሽ ላይ የሚደረገው ምርመራና ክትትል እንዱቋረጥለት እንደሚፈልግ፣ ይህ ከሆነ አንደኛ ተከሣሽ ከተቀበለለት እንደሚመጣ ለኮሚሽነሩና በየደረጃው ጉዲዩ ለሚመለከታቸው ኃላፉዎችና የሥራ ባልደረቦች ሪፕርት አደረግሁ። ከሁለተኛ ተከሣሽ ጋር ሣደርግ የነበረውን ንግግር በመቅረፀ ድምፅ ቀረፅኩ። ሁለተኛ ተከሣሽ 18/07/2000 ብሩን በፋስታል ይዞ መጥቶ ዘበኞች አናስገባም ሲለ እንዱያስገቡት ነገርኳቸው። አሥራ አምስት ባለ አሥር ሺ ብር ጥቅል ገንዘብ አመጣ ንግግራችንን ቀረፅኩት። አንደኛ ተከሣሽ ምርመራው የሚቋረጥለት ከሆነ እንደሚመጣ ነገረኝ።
መጋቢት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት አንደኛ ተከሣሽን ይዞ ለመምጣት ተቀጣጠርን። 21/07/2000 ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ይዞት መጣ። አንደኛ ተከሣሽ 21/07/2000 ዓ.ም. ከሁለኛ ተከሣሽ ጋር ቢሮዬ ድረስ መጥቶ በጉምሩክ ማጭበርበር እንደተከሰሰ ለእኔ ብር 150,000 የላከልኝ መሆኑን ምርመራውና ክትትለ ከተቋረጠለት ወደፉት ውለታ እንደሚውልልኝና ላልች ዝርዝር ነገሮችን አወራ። እኔም በመቅረፀ ድምፅ ቀረፅኩት። ከዚያ በኋላ ወጥተው ሲሄደ አንደኛ ተከሣሽና ሁለተኛ ተከሣሽ በቁጥጥር ሥር ዋለ። ገንዘቡ በኃላፉዎች ትዕዛዝ ባንክ ገቢ ሆኗል በማለት መሥክሯል። ላልቹ ምስክሮች ሁለተኛ ተከሣሽ በፋስታል ገንዘብ ይዞ ሉገባ ሲል በመፈተሽ አናስገባም ብለው በአንደኛው የዐቃቤ ሕግ ምስክር ትዕዛዝ ገንዘቡን ይዞ የገባ መሆኑንና አንደኛና ሁለተኛ ተከሣሾች አንደኛ ዐቃቤ ሕግ ምስክር ጋር ቀጠሮ አለን ብለው ከገቡ በኋላ ሲወጡ የያዟቸው መሆኑን መስክሯል። አመልካች በ18/07/2000 አገር ውስጥ ያልነበሩ መሆኑን በማስረዲት ፒስፕርት ያቀረቡ መሆኑን ከበታች ፍ/ቤት ለመገንዘብ ችለናል። የሥር ፍ/ቤት 1ኛ ተከሣሽ /አመልካች/ በሁለተኛ ተከሣሽ በኩል ሲደራደሩ ቆይተው የዐቃቤ ሕግ አንደኛ ምስክር የሆነው የኮሚሽኑ የክትትልና ምርመራ ሰራተኛ በሥራ ኃላፉነት ማድረግ የሚገባውን እንዲያደርግ ብር 150,000 በሁለተኛ ተከሣሽ በኩል ከሰጡ በኋላ መጋቢት 27/2000 ዓ.ም. በግንባር ከሁለተኛው ተከሣሽ ጋር ከአንደኛው የዐቃቤ ሕግ ምስክር ጋር በመቅረብ ገንዘቡን የላኩት እሳቸው መሆናቸውንና ወደፉትም ውለታ እንደሚውለለት መግለፃቸውና ገንዘቡ ከጉምሩክ ቀረጥ በማጭበርበር የተገኘ መሆኑን ያረጋገጡ መሆናቸው በማስረጃ ስለተረጋገጠ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 427/1/ እና /3/ የተመለከተውን በመተላለፍ የሙስና ወንጀል የፈፀሙ ጥፊተኞች ናቸው ብል አመልካች በሰባት ዓመት ፅኑ እሥራትና በብር አሥር ሺህ ብር መቀጮ እንዱቀጡ ወስኗል።
አመልካች በዚህ ፍርድ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኙ የሚጣራ ሕግ ወይም የፍሬ ነገር ነጥብ የላለው መሆኑን ገልፆ የአመልካችን ይግባኝ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195/1/ መሰረት ሰርዞታል። አመልካች በኮሚሽኑ እንደሚፈለግ መጥሪያ በተጻፈበት መጋቢት 12 ቀን 2000 ዓ.ም. ከአንደኛው የዐቃቤ ሕግ ምስክር ጋር ሁለተኛው ተከሣሽ ጉቦ ለመቀበል ተደራድረዋል በተባለበት መጋቢት 17 ቀን 2000 ዓ.ም.፣ ሁለተኛ ተከሣሽ ገንዘቡን ለአንደኛው የዐቃቤ ሕግ ምስክር ሰጥተዋል በተባለበት መጋቢት 18 ቀን 2000 ዓ.ም. አመልካች በኢትዮጵያ ውስጥ አልነበሩም ስለዚህ በወንጀለ ተካፊይ ነው ተብል የተሰጠብኝ የጥፊተኝነት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት። ጉቦ ተቀባይ ሣይኖር ጉቦ የመስጠት ወንጀል ሉፈፀም ስለማይችል አንደኛው የዐቃቤ ሕግ ምስክር ጉቦ ተቀባይ ነው ባልተባለበት ሁኔታ ጉቦ የመስጠት ወንጀል ፈፅመሀል ተብዬ ጥፊተኛ መባላ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። አመልካች የጉምሩክ ቀረጥ ባለመክፈል ወንጀል ተጠርጥሮ ክትትል ይደረግበት የነበረው ወንጀል ክስ በተመሰረተበት ሂደት ላይ ይገኛል። ስለዚህ ፍ/ቤቱ በዚህ ጉዲይ የጥፊተኝነት ውሣኔ ወስኖ የቅጣት ውሣኔውን እንዱያቆይልን ያቀረብነውን ጥያቄ ባለመቀበል ቅጣት መወሰኑ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 63 እና አንቀጽ 184 ያልተከተለና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። አመልካች ጥፊተኛ መባል አይገባኝም እንጂ ጥፊተኛ እንኳን ብባል በወንጀል ሕግ አንቀጽ 27/1/ እና በአንቀጽ 427/1/ መሆን ሲገባው ወይም በአናሣው ድምፅ ውሣኔ መሰረት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 427/1/ ጥፊተኛ መባል ሲገባኝ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 427/1/ እና /3/ ጥፊተኛ ነው በማለት የተሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩለ ታህሣስ 6 ቀን 2003 ዓ.ም. በተጻፈ መልስ አመልካችና በሥር ፍ/ቤት ሁለተኛ ከሣሽ የነበረው ሰው ያሰቡትን ውጤት ያላገኙ ቢሆንም ጉቦ የመስጠት ወንጅለን ሙለ በሙለ ፈፅመው አጠናቀዋል። ስለዚህ ወንጀለ የሞራላዊ ግላዊና ሕጋዊ መስፈርቶችን በማያሟላ መልኩ የተፈፀመ ሆኖ እያለ ሙከራ ነው እንዱባል የቀረበው የሰበር አቤቱታ የሕግ መሰረት የለውም። አመልካች ከአሥራ ሦስት ሚሉዮን ብር በላይ የቀረጥ ማጭበርበር ፈፅሞ ይደረግበት የነበረው ክትትል እንዱቋረጥለት ለማድረግ የፈፀመው ድርጊት በአዋጅ ቁጥር 433/97 አንቀጽ 2/9/ በተሰጠው ‛ከባድ ሙስና“ ትርጉም የሚካተት ነው። ስለዚህ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 427/1/ ጥፊተኛ መባል ይገባኝ ነበር በማለት ያቀረቡት አቤቱታ የሕግ መሰረት የለውም። የቅጣት ውሣኔውን በተመለከተ አመልካች ያቀረቡት መከራከሪያ የበታች ፍ/ቤቶች መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የፈፀሙ መሆኑን የሚያሣይ አይደለም። በአጠቃላይ የአመልካች ክርክርና አቤቱታ የበታች ፍ/ቤቶች መሰረታዊ የሕግ ስህተት የፈፀሙ መሆኑን የሚያረጋግጥ ባለመሆኑ አቤቱታውን ውድቅ በማድረግ እንዱያሰናብተን በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች ጥር 26 ቀን 2003 ዓ.ም. በተጻፈ የመልስ መልስ አመልካች ከመጋቢት 2 ቀን እስከ መጋቢት 19 ቀን 2000 በአገር ውስጥ ስላልነበረ በወንጀለ ተካፊይ መሆኑ አልተረጋገጠም። የኮሚሽኑ ሰራተኛ ጉቦ የመቀበል ወንጀል ከፈፀመ አመልካች ጉቦ የመስጠት ወንጀል ፈፅሟል በማለት ለማጠቃለል አይችልም። የወንጀል ሕጉ ቅጣት ተጠቃልል የሚወስንበትን ሁኔታ ያስቀመጠ ስለሆነ አመልካች በልላ ወንጀል ተከስሶ እያለ በዚህ መዝገብ ጥፊተኛ ተብል መቀጣቱ ተገቢ አይደለም የሚል ይዘት ያለው ክርክር አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራ ቀኙ ያቀረቡት የጽሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የከፍተኛው ፍ/ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ፍርድ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች የጉምሩክ ቀረጥ የማጭበርበርና የሙስና ወንጀል ፈፅሟል በሚል ምክንያት ተጠርጥሮ በፋዳራል ሥነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ክትትል እና ምርመራ እየተደረገበት የነበረ መሆኑ ተረጋግጧል። አመልካች በኮሚሽኑ የሚደረግበት ክትትል እንዱቋረጥለት ለማድረግ የኮሚሽኑ የክትትልና የምርመራ ባለሙያ የሆነውን አንደኛ የተጠሪ ምስክር ጋር በሥር ሁለተኛ ተከሣሽ በሆነው አቶ ቶውፉቅ በኩል መጋቢት 17 ቀን 2000 ዓ.ም.
ገንዘብ ለመስጠት ሀሳብ ያቀረበ መሆኑን፣ ከዚያም በኋላ በስልክ አንደኛውን የተጠሪ ምስክር በስልክ ካነጋገረና ገንዘብ በሁለተኛው ተከሣሽ በኩል እንደሚልክ ከነገረው በኋላ መጋቢት 18 ቀን 2000 ዓ.ም. 150,000 /አንድ መቶ ሀምሣ ሺህ ብር/ በመላክ ገንዘቡ ለአንደኛ የተጠሪ ምስክር ከተሰጠ በኋላ በኮሚሽኑ የሚደረገው ክትትልና ምርመራ ተቋርጧል በሚል ዕምነት መጋቢት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. ከአንደኛው የተጠሪ ምስክር ቢሮ ድረስ ከሁለተኛው ተከሣሽ ጋር የመጣና ገንዘቡን የላከው እሱ መሆኑን ወደፉትም ውለታ እንደሚውልለት ካረጋገጠለት በኋላ ሁለቱም በቁጥጥር ሥር የዋለ መሆኑ ተረጋግጧል። አንደኛው የተጠሪ ምስክር ከአመልካቾች ጋር በስልክና በአካል ያደረጋቸው ንግግሮች በመቅረፀ ድምፅ የተቀዲ መሆኑን መሥክሯል። በአጠቃላይ አመልካች በወንጀለ ሥራ በመላ ሀሳቡ ሙለ ተካፊይ መሆኑ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው የከፍተኛው ፍ/ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተረጋግጧል።
አንድ ሰው ጉቦ የመስጠት ወንጀል ፈፅሟል የሚባለው አንድ የመንግሥት ሰራተኛ በኃላፉነቱ ማድረግ የሚገባውን እንዲያደርግ ወይም ማድረግ የማይገባውን እንዱያደርግ ጥቅም ወይም ጥጦታ የሰጠ ወይም ያቀረበ ሆኖ በተገኘ ጊዜ እንደሆነ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 427 ንዐስ አንቀጽ 1 በግልፅ ይደነግጋል። አመልካች በመላ ሀሳቡና ድርጊቱ ሙለ ተካፊይ በመሆን የተጠሪ አንደኛ ምስክር የሆነው የክትትልና የምርመራ ሰራተኛ በአመልካች ላይ የሚደረገውን ክትትል እንዱያቋርጥ ለማድረግ ብር 150,000 /አንድ መቶ ሀምሣ ሺህ ብር/ በመደለያነት ያቀረበ መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል። አመልካች ከውጭ አገር የገባሁት መጋቢት 19 ቀን 2000 ዓ.ም. ነው በማለት ፒስፕርቱን በማስረጃነት ያቀረበ ቢሆንም አንደኛው የተጠሪ ምስክር በአመልካች ላይ የሚያደርገውን ክትትል ቢያቆም የሚጠቀምና ገንዘብ የሚሰጠው መሆኑን በሁለተኛው ተከሣሽ በኩል ሀሳብ ካቀረበበት መጋቢት 17 ቀን 2000 ዓ.ም. ጀምሮ አመልካችና ሁለተኛ ተከሣሽ ጋር ከሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ቢሮ እስከተያዘበት መጋቢት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. ድረስ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/ለ/ በሚደነግገው መሰረት በመላ ሀሳቡና አድራጎቱ በወንጀለ ድርጊት በሚሰጠው ውጤት ሙለ ተካፊይ መሆኑ በተጠሪ ማስረጃና አንደኛው የተጠሪ ምስክር ጋር በስልክ ካደረጋቸው ንግግሮችና በሁለተኛ ተከሣሽ በኩል ከፈፀሙ ተግባራትና
No topics extracted.