No summary available.
ግንቦት 26 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አረጋኸኝ መርዕድ - ጠበቃ ግሩም አየለ ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል የሥነ ምግባርና የፀረሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ህግ አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ የሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ እያለ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መፅናቱ ተገቢ ባለመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልካች ጥር 24 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ስለጠየቁ ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። በከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካችና በላልች አራት ሰዎች ላይ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቧል። ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው የክስ ይዘትም አመልካች የኢትዮጵያ ፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የህግ ኤክስፏርት ሆኖ በሚሰራበት ጊዜ ንብረትነቱ የወ/ሮ ኤስሚንግ አግኑያ የሆነውንና በአዱስ አበባ ከተማ ወረዲ 20 ቀበላ 29 ቁጥሩ 214 የሆነውን መኖሪያ ቤት በከፍተኛው ፍርድ ቤት አራተኛ ተከሳሽና አምስተኛ ተከሳሽ የነበሩትንና ክሳቸው የተቋረጠውን አቶ አብዱሣ ሁሪሣና አቶ ሳምሶን ጋርቮልድ አላግባብ ብልፅግና እንዱያገኙ በማሰብ የአባታችን ቤት አላግባብ የተወረሰብን ስለሆነ ይመለስልን በማለት ለኤጀንሲው ያቀረቡትን አቤቱታ የሚያረጋግጥ የይዞታ የምስክር ወረቀት መብራትና ውሀ ያስገቡበት ውልና የቤት ሥራ ፈቃድ ሣያቀርቡ በቀበላ ፍርድ ሸንጎና በምስክር የተረጋገጠ ስለሆነ እንዱመለስላቸው የሚል የውሣኔ ሀሳብ በሥር አንደኛና ሶስተኛ ተከሳሾች ለነበሩት የፔራይቬታይዜሽን የሥራ ኃላፉዎች በማቅረብ በወንጀል ህግ 33 እና 32(1)ሀ እና በተሻሻለው ልዩ ወንጀለኛ መቅጫ ህግ 214/74 አንቀፅ 23 የተደነገገውን በመተላለፍ በዋና ወንጀል አድራጊነት በሥልጣን አላግባብ የመገልገል ወንጀል ፈፅመዋል በማለት ነው።
አመልካች ወንጀለን አልፈፀምኩም ብለው የተከራከሩ ቢሆንም ከላይ መለያው የተገለፀውን ቤት በሚመለከት በሳምሶን ጋርቮልድ ስም ሁለት ሺህ ካሬ ሜትር ካርታና ፔላን፣ በወ/ሮ ኤስሚንግ አግኑያን ስም አንድ ሺህ ካርታና ፔላን በማስረጃነት ቀርቦ የአዱስ አበባ ከተማ ልማት ቢሮ ተጠይቆ ቢሮው ቤቱ ያረፈው በወ/ሮ ኤስሚንግ አግኑያን ቦታ ላይ እንደሆነ አረጋግጦ መፃፈን፣ ቤቱ የገባው የውሀና የመብራት ቢል የወ/ሮ ኤስሚንግ አግኑያን ስም መሆኑን እንደሚያረጋግጥና አመልካች የውሣኔ ሀሳብ ለማቅረብ የምስክርነት ቃላቸውን ያሰማቸው ምስክሮች ቤቱ ከአዋጅ ውጭ የተወረሰ መሆኑን ለማስረዲት የቀረቡ ቢሆንም የተጠሩበትን ጭብጥ የሰጡት ምስክርነት የላለ መሆኑና ከመጡበት ጭብጥ ውጭ ቤቱ የሳምሶን ጋርልቮልድ ነው በማለት መመሥከራቸውንና ይህንን መነሻ በማድረግ አመልካች ቤቱ ለሳምሶን ጋልቮልድ ወራሾች እንዱመለስ የውሣኔ ሀሳብ በሥር አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሽ ለነበሩት የኤጀንሲው ሀላፉዎች ማቅረባቸው በዐቃቤ ህግ አንደኛ ምስክርና በላልች የሰነድ ማስረጃዎች ተረጋግጧል በማለት አመልካች የመከላከያ ማስረጃ እንዱያቀርቡ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ብይን ሰጥቶ፣ አመልካች ከአንደኛና ሶስተኛ ተከሳሾች ጋር በጋራ ሶስት የመከላከያ ምስክሮችን አቅርቧል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራቀኙን ማስረጃ ከመዘነ በኋላ አመልካች በዐቃቤ ህግ ክስ የተጠቀሰውን ወንጀል የፈፀሙ ጥፊተኛ ናቸው በማለት የጥፊተኝነት ውሣኔ ሰጥቶ አመልካች በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ፅኑ እስራት እንዱቀጡ ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች በከፍተኛው ፍርድ ቤት በተሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ይግባኝ ችልት የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195(2)ለ(2) መሰረት አፅንቶታል።
አመልካች ለሰበር አቤቱታው የውሣኔ ሀሳብ ያቀረቡት የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ ከሥራና ከተማ ልማት ሚኒስትር ከአዱስ አበባ ሥራና ከተማ ልማት ቢሮ የተፃፈውን ደብዲቤና ማህደር በማየት ነው። ካርታው እውነተኛ መሆኑ ተረጋግጧል ይህ የተሣሣተ ከሆነ ፍርደ እንዱታረም በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 6 ከሚጠየቅ በስተቀር እኔ በወንጀል መጠየቄ ተገቢ አይደለም። ተጠያቂም የምሆን ከሆነ በኢፋዱሪ የወንጀል ህግ 420(1) የሙያ ግዳታን ጥሰሀል በሚል መሆን ሲገባው በሥልጣን አላግባብ ተገልግሎል ተብዬ ጥፊተኛ መባላ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት። የዐቃቤ ህግ ማስረጃ ወንጀል መሥራቴን ከተገቢው ጥርጣሬ ውጭ አላስረደብኝም። ምስክርነት መስማት በአዋጅ ቁጥር 110/87 እና በመመሪያ ቁጥር 001/88 የተፈቀደ ነው በወንጀል ሉያስጠይቀኝ አይገባም ስለዚህ የህግ አስተያየት ስለሰጠሁ ብቻ ወንጀል ሰርተሀል ተብዬ የተወሰነብኝ የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩለ አመልካች ቤቱ በሥር አራተኛና አምስተኛ ተከሳሽ ለነበሩ ሰዎች እንዱመለስ የውሣኔ ሀሳብ የቀረበው ማስረጃ ሣይቀርብለትና ማስረጃ በላለበት ሁኔታ ነው። ስለሆነም በግብረአበርነት መከሰሳቸውና ጥፊተኛ መባላቸው ተገቢ ነው። የዐቃቤ ሕግ በሰውና በፅሐፍ ማስረጃ አመልካች ተገቢውን ማጣራት ማድረግ የነበረባቸው መሆኑን አስረድተዋል በአጠቃላይ አመልካች በሰበር ያቀረቡት የህግ ሣይሆን የፍሬ ጉዲይ ክርክር በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ፍርድ እንዱፀናልን በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው አመልካች ፈፀመ የተባለው አከራካሪው ቤት በተመለከተ በአራተኛና አምስተኛ ተከሳሽ በነበሩት ሰዎች በኩል ያቀረቡትን ማስረጃዎች በማገናዘብ የሙያ አስተያየትና የውሣኔ ሀሳብ አቅርቧል። አመልካች አከራካሪው ቤት ለአራተኛና ለአምስተኛ ተከሳሾች ቢመለስ የህግ ድጋፍ ያለው ነው የሚል የውሣኔ ሀሳብ ከማቅረብ ውጭ በጉዲዩ ውሣኔ የመስጠት ሥልጣንና ኃላፉነት የለውም። ይኸም በመሆኑ አመልካች በዐቃቤ ህግ ማስረጃ የተዘረዘሩትን ስህተቶች የፈፀመው በሥር አራተኛና አምስተኛ ተከሳሽ የነበሩትን አላግባብ ለመጠቀምና ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና እንዱያገኙ ነው ወይስ እንደማንኛውም ባለሙያ የሙያ ሥራውን በሚሰራበት ወቅት ተገቢውን የሙያ ትጋት እና ጥንቃቄ ባለማድረጉ ነው የሚለውን ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠው ፍሬ ጉዲይ አመልካች ለመኖሪያ ቤቱ የሙያ ግልጋልት ሲሰጥ ሉመራባቸው በሚገቡት የሕግ ማዕቀፍች ማለትም አዋጅ ቁጥር 110/87 እና ይህንኑ አዋጅ ለማስፈጸም ከወጣው መመሪያ 001/88 ከሚፈቅደት ውጭ በመውጣት በሥር አራተኛና አምስተኛ ተከሳሾች የነበሩትን ሰዎች ጥቅም ለማስገኘት ሲል የፈፀመው ተግባር ያለ መሆኑ አልተረጋገጠም። አመልካች የሚመራባቸውን የህግ ማዕቀፍችን መሰረት በማድረግ ተገቢውን ሙያዊ ማጣራት ሲያደርግ ሁለንም ማስረጃዎች በአግባቡ ያላገናዘበ በተለይም የአራተኛና አምስተኛ ተከሳሾች ቤት ነው የተባለው ሰው በተመለከተ ካርታና ፔላን የቀረበለት ቢሆንም የመብራትና የውሀ ቢል በግል ተበዲይ ወ/ሮ ኤስሚንግ አግኑያን ስም የሆነበትን ትክክለኛ ምክንያት ሣያገናዝብና ሣያጣራ የውሣኔ ሀሳብ በሥር ፍርድ ቤት ሶስተኛ ተከሳሽ ለነበሩት የመምሪያ ኃላፉውና ለአንደኛ ተከሳሽ ማቅረቡ ነው። የመወሰን ሥልጣን የላላቸውና የሙያ ግልጋልት የመስጠት ኃላፉነት ብቻ ያለባቸው ሰዎች ግልፅ በሆነ ሁኔታ አንድን ሰው ለመጥቀም ወይም ራሳቸውን ለመጥቀም በማሰብና ኃላፉዎቻቸውን ለማሣሣት የፈፀሙት ጉልህ ተግባር መኖሩ እስካልተረጋገጠ ድረስ በሥልጣን አላግባብ የመገልገል ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው ሉጠየቁ አይገባም። ስለሆነም አመልካች የሙያ ተግባሩንና ሥራው በአግባቡና በጥንቃቄ ባለመፈፀሙ ምክንያት በመንግስትና በግል ተበዲይ ላይ ዐቃቤ ህግ በክሱ የገለፀው ጉዲት ቢኖርም አመልካቹ ጥፊተኛ መባል የሚገባው በልዩ ወንጀለኛ መቅጫ ህግ አዋጅ ቁጥር 214/74 አንቀጽ 23(1)ሀ መሆን ያለበት ሆኖ አላገኘነውም። ከዚህ አንፃር የከፍተኛው ፍርድ ቤት በአብላጫ ድምፅ የሰጠው የጥፊተኝነት ውሣኔና የጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ይግባኝ ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
አመልካች የፈፀመው የተቀጠረበትን የሙያ ሥራ በጥንቃቄና በአግባቡ አለመፈፀም ወንጀል ነው። ይህ ወንጀል ከሶስት ዓመት በማይበልጥ እስራት እንደሚያስቀጣ በአዋጅ ቁጥር 214/74 አንቀፅ 25 ተደንግጓል። ሆኖም ከአዋጅ ቁጥር 214/74 በኋላ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ህግ በአዋጅ ቁጥር 414/1996 የተደነገገ በመሆኑና በወንጀል ህጉ የሥራ ሀላፉነትን አለመወጣት ከአንድ ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ ወይም ከስድስት ወር በማይበልጥ እስራት የሚያስቀጣ መሆኑ በወንጀል ህግ አንቀፅ 420 ንዐስ አንቀፅ 1 የተደነገገ በመሆኑና በኢፋዱሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 22 ንዐስ አንቀፅ 2 ወንጀለ ከተፈፀመ በኋላ የወጣው የወንጀል ህግ ተከሳሹን የሚጠቅም ሆኖ ሲገኝ ተፈፃሚ እንደሚሆን የሚደነግግ በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡትን የጥፊተኝነት ውሣኔ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 113/2/ እና በህገ መንግስቱ አንቀፅ 22 ንዐስ አንቀፅ 2 መሰረት በመለወጥ አመልካች በወንጀል ህግ አንቀፅ 420 ንዐስ አንቀፅ 1 የተደነገገውን በመተላለፍ የሥራ ሀላፉነትን ያለመወጣት ወንጀል ፈፅሟል በማለት የጥፊተኝነት ውሳኔ ሰጥተናል።
የቅጣቱን መጠን በተመለከተ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ቅጣቱን አቅልል ለመወሰን የሚያስችለ ምክንያቶች ያለ መሆኑን በቅጣት ውሣኔው የመዘገባቸውን ነጥቦችና አመልካች ጥፊተኛ ሆኖ የተገኘበት የወንጀል ህግ አንቀፅ 420 ንዐስ አንቀፅ 1 ከስድስት ወር በማይበልጥ እሥራት የሚያስቀጣ መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባትና በወንጀል ህግ አንቀፅ 88 ንዐስ አንቀፅ 2 መሰረት የአመልካችን ግላዊ ሁኔታዎች ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በሶስት ወር እስራት እንዱቀጣ በማለት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195(2)ለ2 መሰረት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡትን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ በማሻሻል ፍርድ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት የሰጡት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ተሻሽሎል።
አመልካች የሥራ ሀላፉነትን ባለመወጣት ወንጀል ጥፊተኛ ሆኖ በመገኘቱ በሶት ወር እስራት እንዱቀጣ ወስነናል።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምፅ ተሰጠ።
No topics extracted.