No summary available.
ግንቦት 17 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ያሲን አሕመድ መሐመድ አልቀረበም።
ተጠሪ፡- ፋዳራል ዐቃቤ ሕግ ባምላኩ አንዲርጌ ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች በሥር ፍ/ቤቶች የተላለፈበትን የጥፊተኛነት እና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል የሚል ቅሬታ ስላነሳ ነው። ከመዝገቡ እንደሚታየው አመልካች የተከሰሰው በኢ.ፋ.ዳ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 675(1) የተመለከተውን በመተላለፍ የእምነት ማጉደል ወንጀል ፈጽሞአል ተብል ነው። ድርጊቱም ብር 10,000(አስር ሺህ ብር) የሚያወጣ ቆርቆሮ ገዝቼ አመጣለሁ በማለት ከግል ተበዲይ ገንዘቡን የወሰደና ቆርቆሮውን ግን ሳያመጣ መቅረቱን የሚያመለክት ነው። አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ ድርጊቱን አለመፈጸሙን በመግለጽ ጥፊተኛ አይደለሁም በማለት ተከራክሮአል። ከዚህ በኋላም ክሱን የሰማው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መጀመሪያ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን ሰምቶ አመልካች ሉከላከል ይገባል የሚል ብይን ሰጥቶአል። በመቀጠልም የአመልካችን የመከላከያ ማስረጃ የሰማ ሲሆን በመጨረሻም አመልካች በዐቃቤ ህግ ክስ የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት የፈጸመ መሆኑን አረጋግጫለሁ በማለት የጥፊተኛነት እና የቅጣት ውሳኔ ሰጥቶአል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች ውሳኔውን በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ክርክሩ በድጋሚ የተሰማ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱም የጥፊተኛነት ውሳኔውን እንዲለ በማፅናት በሥር ፍ/ቤት ተሰጥቶ የነበረውን የአንድ ዓመት ከሁለት ወር ጽኑ እስራት ወደሰባት ወር ቀላል እስራት ዝቅ በማድረግ ወስኖአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ጥር 25 ቀን 2003 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው አመልካች ዐቃቤ ሕግ (ተጠሪ) ባቀረበበት ክስ መሰረት ጥፊተኛ መባለ በአግባቡ ነው ወይ? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው። በመሆኑም ግራቀኝ ወገኖች ይህን ጭብጥ መሰረት በማድረግ ያሰሙትን ክርክር አቤቱታው ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከላይ በዝርዝር እንዲመለከትነው በዐቃቤ ሕግ ክስ የተመለከተውን ድርጊት አልፈጸምኩም በማለት አመልካች ቢከራከርም፤ ክሱን የሰማው ፍ/ቤት ግን ድርጊቱን ስለመፈጸሙ በማስረጃ አረጋግጦአል። ጉዲዩን በይግባኝ የሰማው ፍ/ቤትም እንደዚሁ የተሰማውን ማስረጃ በመመዘን በድርጊቱ መፈጸም እርግጠኛ ሆኖአል። እንደሚታየው ድርጊቱ ተፈጽሞአል ወይስ አልተፈጸመም የሚለው የፍሬ ነገር ጭበጥ በመሆኑ የሚነጥረው (የሚጣራው) በማስረጃ ነው። የፍሬ ነገር ጭብጥን በማስረጃ የማጣራት እና የተሰማውን ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ያላቸው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክሩን በዚህ መልክ በመምራት መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል። በዐቃቤ ሕግ ክስ የተመለከተው ድርጊት በአመልካች መፈጸሙን በማረጋገጣቸውም ድርጊቱ ከተጠቀሰው የወንጀል ሕጉ ድንጋጌ ጋር አገናዝበው የጥፊተኛነት ውሳኔ ሰጥተዋል።
በበኩላችንም እንደምናየው አመልካች በዐቃቤ ሕግ ክስ የተመለከተውን ድርጊት ፈጽሞአል ወይስ አልፈጸመም የሚለውን የፍሬ ነገር ጭብጥ የማጣራት ሥልጣን ለሰበር ችልቱ የተሰጠ ባለመሆኑ በዚህ ደረጃ የምንመረምረው አይደለም። በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠው እውነታ በክሱ በተጠቀሰው ድንጋጌ የተመለከተውን ወንጀል ያቋቁማል ወይ የሚለው ነጥብ ግን የሕግ ጭብጥ በመሆኑ ተመልክተነዋል።
አመልካች የተከሰሰው በወንጀል ሕጉ በአንቀጽ 675(1) የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፍ ወንጀል ፈጽሞአል ተብል እንደሆነ ከላይ ተመልክተናል። ድንጋጌው የሚለው ‛ማንም ሰው ተገቢ ያልሆነ ብልጽናግ ለማግኘት ወይም ለላላ ሰው ለማሰገኘት በማሰብ፣ የላላ ሰው የሆነውንና ለአንድ ለተወሰነ አገልግልት ወይም በአደራ የተሰጠውን ዋጋ ያለውን ነገር ወይም ጥሬ ገንዘብ በሙለ ወይም በከፉል ለራሱ ያደረገ፣ ወይም ለላላ ሰው ያደረገ የወሰደ፣ ያስወሰደ፣ የሰወረ ወይም ለራሱ ወይም ለላላ ሰው አገልግልት ያዋለ ወይም ይህን የመሳሰለውን ማናቸውንም አድራጎት የፈጸመ እንደሆነ፣“ ጥፊተኛ ተብል በሕጉ የተመለከተውን ቅጣት ይወስንበታል ነው። በያዝነው ጉዲይ እንደምናየው አመልካች የግል ተበዲይ ለቆርቆሮ መግዣ በማለት የወሰደውን ገንዘብ ወስድ አስቀርቶአል። ገንዘቡ ቆርቆሮውን አልገዛበትም ወይም ለሰጠው የግል ተበዲይ አልመለሰም። ይህ በፍሬ ነገር ረገድ ተረጋግጦበታል። ገንዘቡን አስካልመለሰ ወይም ለተባለው አገልግልት ስለማዋለ እስካላስረዲ ድረስ ደግሞ በድንጋጌው የተመለከተውን ወንጀል ፈጽሞአል ለማለት ነው የሚቻለው።
በልላ አነጋገር አመልካች የፈጸመው በማስረጃ የተረጋገጠበት ድርጊት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 675(1) የተመለከተውን ወንጀል የሚያቋቁም ነው። በመሆኑም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞአል የምንልበት ምክንያት የለም። በዚህ መሰረትም ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በወ/መ/ ጥር 16 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሕግ ሥ/ሥ/ቁ 195(2)(ለ)(2) መሰረት ፀንቶአል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቶአል። ይመለስ።
ራ/ታ
No topics extracted.