No summary available.
ግንቦት 15 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ አሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ መሐመድ ሰይድ አሉ - ጠበቃ እሸቱ ዓሉ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የፋዳራል ዐቃቤ ሕግ - በላለበት የሚታይ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የወንጀል ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- በ1996 ዓ/ም የወጣውን የኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብሉክ ወንጀል ህግ አንቀጽ 27 እና 593ን በመተላለፍ በሕገ ወጥ መንገድ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ውጪ አገር ለመላክ መሞከር ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ነው። አመልካችም ፍርድ ቤት ቀርበው የአቃቤ ሕግ የክስ ቻርጅ ተነቦላቸው እንዱረደት ከተደረገ በኋላ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሲጠየቁ የወንጀል ድርጊቱን መፈፀማቸውን በዝርዝር በማመናቸው በእምነታቸው መሰረት በአቃቤ ሕግ በኩል ተጠቅሶ በቀረበበት አንቀጽ ሥር ጥፊተኛ ተብለውና የቅጣት አስተያየት ቀርቦ ከተመዘገበ በኋላ በቅጣት መመሪያው መሰረት በሁለት ዓመት ከስድስት ወር ፅኑ እስራት እና በብር 100 (አንድ መቶ) እንዱቀጡ ተወስኗል። በሥር ፍርድ ቤት በተሰጠው የቅጣት ውሳኔ ብቻ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት የቅጣት ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195 /2/መ/ መሰረት ሙለ በሙለ ጸንቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ታህሳስ 25 ቀን 2003 ዓ.ም በጻፈት ሶስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። የሰበር አቤቱታው መሰረታዊ ይዘትም አመልካች ድርጊቱን እንደአመኑ ተደርጎ የተሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ ያላግባብ ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው መሆኑ ታምኖበት ተጠሪን ያስቀርባል ተብል ትዕዛዝ ተሰጥቶ ተጠሪ ባለመቅረቡ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመለኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የአመልካችን ቅሬታ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለሰበር ችልት ያስቀርባል ተብል ሲታዘዝ ከተያዘው ጭብጥ ከድርጊቱ አፈፃፀም አንዱሁም አመልካች ላይ ከተጣለው የቅጣት መጠን አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
አመልካች ጥፊተኛ የተባለት ኢትዮጵያዊያኑን ከሕግ ውጪ ወደ ውጭ አገር ሉልኩ ሲለ ተይዘዋል በሚል ሲሆን ይህንኑ ደርጊት መፈፀማቸውን በዝርዝር አምነዋል። የሥር ፍርድ ቤት አመልካች ድርጊቱን በዝርዝር ማመናቸውን መሰረት በማድረግም በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 134/1/ መሰረት የጥፊተኝነት ውሳኔ ተሰጠቷል። እንዱህ ከሆነ አመልካች ጥፊተኛ የተባለት ጉዲዩን በዝርዝር ማመናቸው ተረጋግጦ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት በእምነቱ መሰረት በሚሰጠው የቅጣት ውሳኔ ሕጋዊነት ላይ ይግባኝ ማለት ከሚቻል በስተቀር በእምነት መሰረት በሚሰጠው የጥፊተኘነት ውሳኔ ላይ ይግባኝ ላቀርብ የማይችል ስለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 185/1/ ድንጋጌ በግልጽ ያሳያል ። አመልካች ይህንኑ በመገንዘብም ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሲያቀርቡ በስር ፍርድ ቤት የጥፊተኝነት ውሳኔ ላይ ይግባኝ አለማቅረባቸውን በሰበር አበቱታቸው በግልጽ የገለፁት ከመሆኑም በላይ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ ይህንኑ በሚገባ ይረጋገጣል። ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 8ዐ/3/ሀ/ እና በአዋጅ ቁጠር 25/1988 አንቀጽ 1ዐ መሰረት የተሰጠው ስልጣን በማናቸውም የመጨረሻ ፍርድ ላይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ሲኖር ማረም ነው። በመሆኑም አመልካች በጥፊተኘነት ውሳኔ ላይ ያቀረቡት ቅሬታ የእምነት ቃላቸው በዝርዝር የተሰጠ ነው ተብል በስር ፍርድ ቤት ከተመዘገበው ይዘት ውጪ በመሆኑና ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ካለው ሥልጣን አንፃር ሲታይ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ በሕጉ አተገባበርና በውጤት ደረጃ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት አላገኘንም። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
በጉዲዩ ላይ የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195/2/መ/ መሰረት ጸንቷል።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.