No summary available.
ቀን 29/9/ 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ዘለቀ ካሣዬ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- የፋዳራል ዐ/ሕግ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የወንጀል ክስ ሲሆን በፋ/ከ/ፍ/ቤት ቀርቦ የነበረው በቸልተኝነት ሰው በመግደል የሚል ነበር። ዐቃቤ ሕጉ አቅርቦት የነበረው ክስ ተከሳሸ /የአሁን አመልካቹ / የትራንሰፕርት ማሻሻያ ደንብ ቁ . 279/56 አንቀጽ 35 እና የ1996 ዓ/ም ወ/መ/ህግ አንቀጽ 543 /3/ የተመለከተውን ተላለፍ የሚያሽከረክረው ታርጋ ቁ 1-10432 አ/አ የሆነውን መኪና ታህሳስ 20/01 ዓ/ም ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ተኩል ላይ በዬሐንስ ቤተክርስቲያን ልዩ ስሙ ሰባራ ባቡር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በእግረኛ ማቋርጫ ዜብራ ላይ ቅድሚያ ባለመስጠት ተክለ ጌታሁን የተባለውን በቸልተኝነት ገጭቶ ገድልአል የሚል ነበር ።
ክሱን የሰማው የፋ/ከ/ፍ/ቤት ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ ድርጊቱን መፈፀሙን አምኖ ግን ጥፊቱ ያለመሆኑን ስለካደ የግራ ቀኙን ማስረጃ ሰምቶ በወ/መ/ሕግ አንቀፅ 59/1/ /ሀ/ እና 543/3/ ስር ጥፍተኛ ነው በማለት የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ተቀብል በአንድ አመት ከ6 ወር ፅኑ እሰራትና ብር 10,000 / አስር ሺህ/ እንዱቀጣ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ የፋ/ዐቃቤ ሕግ ቅር በመሰኘት ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅረቦ ፍ/ቤቱም ካከራከረ በኃላ ቅጣቱ በአምስት አመት ፅኑ እስራት ከፈ አድርጏ የወሰነ እና የገንዘብ መቀጮውን ባለበት ያልተነሳ መሆኑን ወሰኗል ።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን አመልካች በጠበቃው አማካኝነት ህዲር 14 ቀን 2003 ዓ/ም 3 ገፅ ማመልከቻ ያቀረበ ሲሆን ይዘቱ በአጭሩ የተለያዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶችን በማቅረባችን የከፍተኛው ፍ/ቤት ከግምት አስገበቶ ቅጣት የቀለለና ከመነሻው ዝቅ ብል መቅጣቱ ግልፅ ሆኖም እያለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ተጏጅን ወደ ሕክምና ቦታ መውሰድ በሕግ ማለትም በወ/መ//ሕግ ቁ . 575/2/ ሥር የተጣለበትን ኃላፉነት መወጣቱ እንጅ ፅኑ እሰራት እንዱቀጣ መወሰኑ አግባብ አይደለም የሚል ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ዐ/ ሕግ በቀን 10/6/2003 ዓ/ም በ2 ገፅ መልስ ስጥቷል ። የመልሱ ፍሬ ሀሳብ የተባለው የቅጣት ማቅለያ መክንያት ቅጣቱን ከመነሻው ዝቅ የሚደርግ ባለመሆኑ የጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ በአግባቡ በመሆኑ እንዱፀና በማለት ተከራክሯል።
የአመልካች ጠበቃ የመልስ መልስ አቅርቧል። በግራ ቀኙ የቀረበው ክርክር በአጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን በአቤቱታውም የቀረበውን ክርክር ከተያዘው ጭብጥና አግብበነት ካላቸው ሕጉ ጋር በማገናዘብ መርመሮታል ። እንደመረመረውም በዚህ ጉዲይ የፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች ከመነሻ ቅጣት / አምስት ዓመት ፅኑ እስራት / በታች የሚቀጣበት ምከንያት የለም የማለቱን አግባብነት በመመልከት መፍትሓ ማግኘት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል ። በዚሁ መሰረት በሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩ ያስቀርባል ሲባል አመልካች ግጭቱን ካደረሰ በኋላ ማለትም የሐኪም ዕርዲታ እንድታገኝ ማደረጉ በወ/መ/ሕግ አንቀጽ 82/1/ /ሰ/ መሰረት ቅጣቱን ሉያቀለው የሚገባ ነው ወይስ አይደለም ? የሚል በመሆኑ ችልቱም ከዚህ ጭብጥ አኳያ ብቻ በመመልከት መፍትሓ ማግኘት ያለበት ሆኖ አግኝቶታል። በመሰረቱ አንድ ጉዲት የደረሰበት ስው ወይም በአደጋ ላይ የሚገኘውን ሰው አለመርዲት የወንጀል ኃላፉነት የሚያስከትል መሆኑ በወ/መ/ሕግ ቁ 575 ሥር የተደነገገ ከመሆኑም በላይ ጉዲቱን ያደረሰው ተከሳሽ ራሱ በሆነበት ጊዜ ደግሞ የበለጠ የወንጀል ኃላፉነት የሚጥል ስለመሆኑ ከወ/መ/ ሕግ ቁጥር. 575 /2/ ሥር መረዲት ይቻላል ። ይሄንን ኃላፉነት ያልተወጣ ተከሳሽ ለዚህም ተጨማሪ የወንጀል ኃላፉነት በተደራራቢነት ሉጠየቅ እንደሚችልና አመልካች ወደ ሕክምና ማዕከል ማድረሱ የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ የተጣለበትን ኃላፉነት መወጣቱን የሚያመለከት መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
በልላ በኩል በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 82/1/ /ሰ/ መሰረት ተከሳሽ በእዉነት የተፀፀተ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ሲገነዘብ ቅጣት ሉያቀልለት እንደሚችልና በእውነት ስለመፀፀቱ ከመገልጫዎቹ አንደ በደል ለደረሰበት ሰው አስፈላጊውን እርዲታ ማድረጉ ላሆን እንደሚችል ተቀምጧል ። ይሄ ማለት ግን ተከሳሽ ተበዲይን ወደ ሕክምና ማዕክል ማድረሱ ብቻ በፈፀመው ድርጊቱ በእውነት ተፀፅቷል የሚያሰኝ ሳይሆን ጉዲዬን በመጀመሪያ ደረጃ ወይም በይግባኝ ያየው ፍርድ ቤት አጠቃላይ የግራ ቀኙን ማስረጃ በመስማትና በማመዛዘን የሚደርስበት መደመደሚያ ነው።
አመልካች ተበዲይን ወደ ሕክምና ማዕክል ማድረሱ አጠቃላይ የክሱን ሂደት ከግምት በማስገባት አመልካች በእውነት ተፀፅቷል የሚያሰኝ ነው ወይስ አይደለም ? የሚለው ነጥብ የማስረጃ ምዘና በመሆኑና የዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ስልጣን ደግሞ በሕግ መንግስቱ አንቀፅ 10 መሰረት መሰረታዊ የህግ ስህተት ማረም እንደመሆኑ መጠን የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የደረሰበትን መደምደሚያ መቀበለ ተገቢ ይሆናል። በዚህ መሰረት አመልካች ተበዲይን ለሕክምና ማዕከለ ማድረሱ ላላ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በአመልካች ላይ የተጣለውን ኃላፉነት መወጣቱን እንጂ ቅጣቱን ለማቅለል የሚያበቃ አይደለም ማለቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አላገኘንም። በዚሁ መሰረት ቀጥል የተመለከተው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝ. በቀን 24.2.2003 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 195/2/ /መ/ መሰረት ፀንቷል። መዝገቡ ተዝግቷል። ወደ መዝገብ ቤት ይመልስ ።
ሰ/ረ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.