No summary available.
ግንቦት 16 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የስልጤ ዞን ምርመራና ክስ ዐቃቤ ህግ ቃሲም ባዳ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ህዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ የተጀመረው በዲልቻ ወረዲ ፍ/ቤት ነው። ለወረዲው ፍ/ቤት የወረዲው መርማሪ ከሣሽ ዐቃቤ ህግ ተጠሪዎች በወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና በወንጀል ህግ አንቀጽ 686 ንኡስ አንቀጽ 2 የተመለከተውን በመተላለፍ በዲልቻ ከተማ ዐ1 ቀበላ ልዩ ስሙ ሰሉም ሰፈር ከሚባለው አንደኛ ተከሣሽ ለመኖሪያ ቤት የተፈቀደለትንና የሰራውን ቤት አላግባብ ለመሰረተ ክርስቶስ አማኞች በመጸለያነት እንዱጠቀሙበት በመስጠቱ በርካታ የእምነት ተከታዩች ተሰባስበው ከግንቦት 22 ቀን 2001 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ከቀኑ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ ሶስት ሰዓት ከፍተኛ ጩኸት በማሰማትና በድምጽ ማጉሉያ መሣሪያ በመጠቀም የሁከት ማድረስ ወንጀል ፈጽመዋል በማለት ክስ አቅርቧል። ተጠሪዎች ክሱን ክደው ተከራክረዋል። የስር ፍ/ቤት ዐቃቤ ህግን ማስረጃ ከሰማ በኋላ ተጠሪዎች መከላከያ ማስረጃ እንዱያቀርቡ ብይን ሰጥቷል። ተጠሪዎች የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አቅርበው አሰምተዋል። የወረዲው ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ዐቃቤ ህግ በክሱ የተጠቀሰውን የወንጀል ህግ ድንጋጌ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ህግ ቁጥር 113 ንኡስ አንቀጽ 2 መሰረት በመለወጥ ተጠሪዎች በወንጀል ህግ አንቀጽ 815 ንኡስ አንቀጽ 1 የተመለከተውን የደንብ መተላለፍ ጥፊት የፈጸሙ ጥፊተኞች ናቸው በማለት ተጠሪዎች እያንዲንዲቸው በብር 8ዐ /ሰማኒያ ብር/ መቀጮ እንዱቀጡ ወስኗል። ተጠሪዎቹ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበዋል። የስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የወረዲው ፍ/ቤት የሰጠውን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ አጽንቶታል።
ተጠሪዎች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ይግባኝ አቅርበዋል። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የክልለ መርማሪ ከሣሽ የሰጠው አስተያየትና የቀረበውን ክርክር ተቀብል ከመዘነ በኋላ የክልለ መርማሪ ከሣሽ የተጠሪዎችን የሰበር አቤቱታ በመደገፍ የተከራከረ መሆኑን በውሣኔው በገጽ 9 ካሰፈረ በኋላ የወረዲው ፍ/ቤትና የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር በወረዲው ፍ/ቤት በትዕዛዝ የተዘጋው የጸልት ቤት እንዱከፈት ትዕዛዝ ሰጥቷል።
አመልካች ሐምል 26 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ በዲልቻ ወረዲ ፍ/ቤት የወረዲው መርማሪ ከሣሽ ያቀረበው የወንጀል ክስ በወንጀል መዝገብ ቀርቦና ክርክር ተደርጏበት ፍ/ቤቱ የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ በተጠሪዎች ላይ ሰጥቷል። ተጠሪዎች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ያቀረቡትን የወንጀል ይግባኝ የስልጤ ዞን በመዝገብ በማየት የወረዲው ፍ/ቤት የሰጠውን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ አጽንቶታል።
ተጠሪዎች የወረዲው ፍ/ቤት የሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ማጽናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረቡት የወንጀል ሰበር አቤቱታ በሰበር መዝገብ ሲታይና ክርክርና አስተያየት የተደረገበት እንደሆነ በየደረጃው የተከፈቱትን መዛግብትና አመልካች ያቀረበውን ክርክር ይዘት በማየት ለመረዲት ይቻላል።
በልላ በኩል የዲልቻ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ከአንደኛው ተጠሪና ከአምስተኛው ተጠሪ ጋር የከተማዋን ፔላን መከበር ማዕከል ያደረገ ክስ የፍታብሓር ክርክር ለዲልቻ ወረዲ ፍ/ቤት አቅርቦ ጉዲዩ ከወረዲው ፍ/ቤት የመዝገብ ክርክር ከተደረገበት በኋላ አንደኛና አምስተኛ ተጠሪ የመኖሪያ ቤት እንዱገነቡ በተሰጣቸውና በሰሩት ቤት ከመኖሪያነት ውጭ ለሆነ አገልግልት ማዋል የላለባቸዉ መሆኑ ተወስኗል። በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት አንደኛና አምስተኛ ተጠሪ የፍታብሓር ይግባኝ ለስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበዋል። የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የአንደኛና የአምስተኛ ተጠሪን የፍታብሓር ይግባኝ በመዝገብ በማየት የወረዲው ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ የሚነቀፍበት የህግም ወይም የፍሬ ጉዲይ ስህተት የላለ መሆኑን ገልጾ ይግባኙን በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ህግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል። አንደኛና አምስተኛ ተጠሪ የወረዲው ፍ/ቤት በፍታብሓር መዝገብ ቁጥር ዐ2428 የሰጠውን ወሣኔ የዞኑ ከፍተኛው ፍ/ቤት በፍታብሓር ይግባኝ መዝገብ ቁጥር ዐ56ዐ7 ማጽናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑን በመግለጽ ራሱን የቻለ የሰበር አቤቱታ አቅርበው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰበር መዝገብ ሲመረምር ከቆየ በኋላ የፍታብሓሩን ጉዲይ የወንጀለ ጉዲይ ከሚታይበት የሰበር መዝገብ ጋር በማጣመር ውሣኔ ሰጥቷል። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ከህግ ውጭ ሁለቱን መዛግብት በማጣመርና አግባብነት የላላቸዉን የህግ ድንጋጌዎች በመጥቀስ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክቷል።
ተጠሪዎች በበኩላቸው ጥር 9 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተጻፈ መልስ በወንጀለ መዝገብም ሆነ በፍታብሓር መዝገብ የሚነሣው ክርክርና የሚያዘው ጭብጥ ተመሣሣይ በመሆኑ የክልለ ሰበር ችልት ሁለቱን መዛግብት በማጣመር መርምሮ ውሣኔ መስጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም። አመልካች የመኖሪያ ቤት በመስራት እንድትገለገለበት በተፈቀደ ቦታ ላይ ለአምልኮ አገልግልት አውለዋል በማለት ያቀረበው ክስ በህገመንግስቱ የተረጋገጠልንን የሀይማኖትና የእምነት ነጻነት የሚጋፊ ነው። አገሪቱ ኋላ ቀር አገር በመሆኑ የመኖሪያ ሰፈር የኢንደስትሪ ሰፈር የሚባል የላላት ሲሆን ቤተክርስቲያንና መስጊድችን በመኖሪያ ቤት ውስጥ ማግኘት የተለመደ ነው። ስለዚህ በመኖሪያ ሰፈር ለጸልትና የአምልኮት ማከናወን አይቻልም በማለት አመልካች ያቀረበውን ክርክር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ችልት ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክረዋል። አመልካች ጥር 2ዐ ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርቧል። በመልስ መልሱ ከተማዋ እድገቷን የምትመራበት ፔላን አለ። በከተማዋ ፔላን መሰረት መስጊድች ፣ ቤተክርስቲያንና የጸልት ቤቶች መገንባት ሲያስፈልግ የሚገነቡበት ቦታ ተለይቷል።
በፔላኑ መሰረትም የጸልት ቤት መገንቢያ ቦታ ተሰጥቷቸው እያለ የመኖሪያ ቤታችን ተቀይሮ የጸልት ቤት ላሆን ይገባል በማለት ያቀረቡት ክርክር የህግ ድጋፍ የለውም በማለት ተከራክሯል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የጽሁፍ ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት የወንጀል መዝገብ እና የፍታብሓር መዝገብ ጋር በማጣመር ተጠሪዎች የፈጸሙት የሁከት ተግባር የለም በማለት የሰጠው ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
በልላ በኩል የመኖሪያ ቤት ለመስራት የተፈቀደላቸውን ቦታና ለመኖሪያነት የሰሩትን ቤት ለአምልኮት አገልግልት ለዘላቂነት እንዱውለ ማድረጋቸው ተገቢ አይደለም። ከዚህ ድርጊታቸው እንዱታቀቡ ውሣኔ ይሰጥልን በማለት የፍታብሓር ክስ የመሰረተው የዲልቻ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ነው። የዲልቻ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ክስ ያቀረበው በአምስቱ ተጠሪዎች ላይ ሣይሆን በአንደኛ ተጠሪና በአምስተኛው ተጠሪ ላይ ብቻ ነው። የወረዲው ፍ/ቤት በማዘጋጃ ቤቱ የቀረበውን የፍታብሓር ክርክር በፍታብሓር መዝገብ በማየት ውሣኔ የሰጠ ሲሆን አንደኛና አምስተኛ ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ያቀረቡትን ይግባኝ የስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍታብሓር መዝገብ በማየት ውሣኔ ሰጥቷል። አንደኛና አምስተኛ ተጠሪዎች የወረዲውና የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ችልት አቅርበው የሰበር አቤቱታቸው በሰበር መዝገብ ሲመለከት የቆየ መሆኑን ተገንዝበናል።
የፍታብሓር ክርክር ከወንጀል ክርክር ጋር ሉጣመር የሚችልበት መሰረታዊ ሁኔታ በወንጀል ህግ አንቀጽ 101 የተደነገገ ሲሆን የፍታብሓር ክርክሩ የወንጀል ሰለባ የሆነ ሰው የሚያቀርበው የካሣ ጥያቄ በሆነ ጊዜ ከወንጀል ክስ ጋር ተጣምሮ እንዱወሰንለት ማመልከት እንደሚችል ይደነግጋል። በያዝነው ጉዲይ የፍታብሓር ክርክር በወንጀለ ጉዲት ደርሶብናል የሚለ ሰዎች ካሣ እንዱከፈላቸው ያቀረቡት ጥያቄ አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ በወንጀል የሚደረገው ክርክርና በፍታብሓር በሚደረገው ክርክር የሚያዘው ጭብጥና የሚቀርቡ ማስረጃዎች እንደዚሁም የማስረጃ አመዛዘን ሥርዓቱ የተለያየ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በወንጀል መዝገብና በፍታብሓሩ መዝገብ ተከራካሪ የሆኑት ሰዎች የተለያዩ ናቸው።
በፍታብሓር መዝገብ ተከራካሪ የሆነው የዲልቻ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሲሆን አመልካች የሚከራከረው የዲልቻ ከተማ ማዘጋጃ ቤትን በመወከል ነው። የዲልቻ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የሚከራከረው ከአምስቱ ተጠሪዎች ጋር ሣይሆን ከአንደኛውና ከአምስተኛው ተጠሪ ጋር ብቻ ነው።
በወንጀለ መዝገብ ከስር ጀምሮ የመርማሪ ከሣሽና በአምስቱ ተጠሪዎች ተከራካሪ መሆናቸውን መዝገቡ ያሣያል።
ስለሆነም የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት የዲልቻ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና አንደኛና አምስተኛ ተጠሪ በፍታብሓር የሚከራከሩበትን የሰበር መዝገብ አመልካችና ተጠሪዎች ከሚከራከሩበት የወንጀል መዝገብ ጋር በማጣመር ማየቱ የወንጀል ህግ አንቀጽ 101 መሰረታዊ የህግ ድንጋጌ የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
No topics extracted.