No summary available.
ግንቦት 19 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አደነ ንጉሴ አመልካቾች፡- ሃለቃ ገ/እግዚአብሓር ኃይለ -ጠበቃ ፈቃደ ያሚ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የኦሮሚያ ክልል ዓ/ሕግ - በላለበት የሚታይ ነው።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ የቀረበው አመልካች በተከሰሱበት የወንጀል ድርጊት የበታች ፍ/ቤቶች በሰጡት ጥፊተኛነት እና የቅጣት ውሳኔ የክልለ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት እና ሰበር ሰሚ ችልት መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ነው።
አመልካች የተከሰሱት የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 የተመለከተውን በመተላለፍ በቀን 02/06/2001 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት ላይ የደን ጠባቂ ሆኖ ሲሰራ መንግስት ባስታጠቀው ክላሽ ጠመንጃ ሶስት ጥይት ተኩሶ ሟች አቶ ግደይ ትኩእ የተባለትን መትቶ ገድልታል በሚል ሲሆን አመልካች ስለድርጊቱ አፈፃፀም ክደው በመከራከራቸው ዐቃቤ ሕግ አለኝ ያላቸውን የሰውና የሰነድ ማስጃዎችን በማቅረብ አስምቷል። ከዚህም በኋላ አመልካች እንዱከላከለ ብይን ተሰጥቶ አመልካች የመከላከያ ማስረጃ የላላቸው መሆኑን በማረጋገጣቸው በዐቃቤ ሕግ በኩል ተጠቅሶ በቀረበባቸው ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ ተብለው በ2ዐ /ሃያ አመት/ ፅኑ እስራት እንዱቀጡ ተወስኖባቸዋል። በዚህ ውሳኔ አመልች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለትግራይ ማዕከላዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ የሰጠውን የጥፊተኛነት ውሳኔ በማጽናት ቅጣቱን ብቻ በማሻሻል 15/ አስራ አምስት ዓመት/ ጽኑ እስራት እንዱቀጡ በማለት ወስኗል። ከዚህም በኋላ አመልካች ይግባኛቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። ጉዲዩ በሰበር አቤቱታ የቀረበለት የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም በጉዲዩ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም በሚል ምክንያት አቤቱታውን ሳይቀበለው ቀርቷል። የአሁኑ የሰበር አበቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የሰበር አቤቱታው መሰረታዊ ይዘትም አመልካች ጥፊተኛ የተባለት ያላግባብ ከመሆኑም በላይ የጥፊተኝነት ውሳኔ የተሰጠበት ድንጋጌም በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮችን ያላገናዘበ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚየሳይ ነው ። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ መታየት ያለበት መሆኑ ታምኖበት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት መጥሪያ ደርሶት ባለመቅረቡ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል ባጭሩ የተመለከተው ሲሆን እኛም ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምረናል። ይህ ሰበር ሰሚ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር እና የሥር መዝገብ ውሳኔ ይዘት ከመረመረ በኋላ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ምላሽ የሚያሻው የሕግ ጥያቄ ሆኖ ያገኘው አመልካች ጥፊተኛ ሉባለ የሚገባው በወ/ሕ/ ድንጋጌ አንቀጽ 540? ወይንስ 541? የሚለውን ነው። የህንኑ ለመፍታት የጉዲዩን አፈፃፀም እና መነሻ ሁኔታዎች በአጭሩ መመልከት ተገቢ ነው።
ከሥር ፍ/ቤት መዝገብ መረዲት የተቻለው ፍሬ ነገር ወንጀለ ተፈፀመ በተባለበት ቀን ላሉቱን አመልካች ደን ለመጠበቅ ተቀጥረው ባለበትና መሳሪያውንም ለዚሁ አላማ ለማዋል በያዙት ሁኔታ የስር አቃቤ ሕግ ምስክሮችና ሟቹ ወደ ደኑ በመሄድ ዛፍ በመቁረጥ ላይ እያለ በተፈጠረው አለመግባባት አመልካች ሁለት ጥይቶችን ከተኮሱ በኋላ ሶስተኛውን ጥይት በመተኮስ ሟችን በመምታት ለሕልፈት የዲረጉት መሆኑ በክርክሩ ሂደትና በአቃቤ ሕግ ምስክሮች ቃል ጭምር ከተነገረው የአመሰካከር ይዘት መስፈሩን ነው።
በልላ በኩል አመልካች የተከሰሱበትን ወንጀል ስለመፈጸማቸውም አምነው ክደው የሚከራከሩት የአፈጻጸሙን ሁኔታ ስለመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች የውሳኔ ግልባጭ ያስረዲል።
እንግዱህ አጠቃላይ የወንጀለ አፈፃፀም ሁኔታ ይህንን የሚመስል ሲሆን አመልካች ለወንጀል ድርጊቱ ኃላፉነት የለብኝም በማለት እስከዚህ ችልት አጥብቀው የተከራከሩ ቢሆንም ስለወንጀለ አፈፃፀም እና የማስረጃ ምዘና ጉዲይ በዚህ ሰበር ስሚ ችልት ሥልጣን የሚታይ ባለመሆኑ በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር እንዲለ በመቀበል በህግ ረገድ የሚኖረውን ውጤት ብቻ መመልከቱ ተገቢ መሆኑን ከኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብሉክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 8ዐ/3/ሀ/ እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 1ዐ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ በመሆኑ ጉዲዩን በሚከተለውን መልኩ አይተናል።
አመልካች የተከሰሱበትን የወንጀል ድርጊት በሕዝብ ደን ላይ አደጋ ለመከላከል እንደሆነ ከፍ ሲል የተመለከተውን ፍሬ ነገር እና ከወንጀለ አፈፃፀም ከባቢያዊ ሁኔታ መረዲት ይቻላል።
ድርጊቱ ወንጀል ነው ቢባልም በሕግ በተመለከተ ልዩ ሁኔታ በሕግ በተፈቀደ ድርጊቶች የማያስቀጡ እና ይቅርታ የሚያሰጡ ሁኔታዎች በወንጀል ሕጉ ጠቅላላ ክፍል የተመለከተውን ድንጋጌ ከተያዘው ጉዲይ ጋር ማየት ተገቢ ሆኖ አግኝተናል። ለተያዘው ጉዲይ ቀጥታና አግባብነት ያለውን የወንጀል ሕግ ድንግጋጌ ቁጥር 78 እንመለከታለን።
በዚህ ድንጋጌ መሰረት የራሱን ወይም የላላውን ሰው መብት ሕገወጥ ከሆነ ጥቃት ወይም በቅርብ ከሚደርስ ሕገ ወጥ ጥቃት ለማዲን ጥቃቱ እንዲይደርስ ለማድረግ ላላ መንገድ ሳይኖር ከሁኔታው መጠን ባለመለፍ የተፈፀመ ድርጊት አያስቀጣም ተብል ተደንግጓል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ተከሳሹ ከቅጣት ነፃ የሚሆነው ሕገወጥ ጥቃት በራሱ ወይም በልላው ሰው መብት ላይ የተሰነዘረ ወይም በእርግጠኛነት ሉደርስ የሚችል ጥቃት ስለመኖሩ ይህንንም ለማስወገድ ወይም ለመከላከል ላላ አማራጭ የላለው ስለመሆኑ እና የወሰደው የመከላከል ወይም ጥቃቱን የማስወገድ እርምጃ ከተሰነዘረው ጥቃት ጋር ተመጣኝ ኃይል የተጠቀመ መሆኑን ማስረዲት ሲችል ብቻ ነው።
ይህንኑ የሕጉን መንፈስ እና ይዘት መሰረት አድርገን የተያዘውን ጉዲይ ስንመለከት በስር አቃቤ ሕግ ምስክሮች ቃል የተረጋገጠው ፍሬ ነገር በሕዝብ ደን ሟችና የአቃቤ ሕግ ምስክሮች በላሉት ሰዓት የዛፍ መቁረጥ ተግባር መፈፀማቸው አመልካችም ለደኑ ጥበቃ ከመንግስት የታጠቁትን መሣሪያ በወቅቱ ይዘው በጥበቃ ላይ የነበሩ ስለመሆኑ አመልካች ደኑን ለማስከበር ያደረጉትን ጥረት በሟች ጥቃት ተሰንዝሮባቸው የነበረ ስለመሆኑ እና በደኑ ላይ አደጋ ሲሰነዘር አመልካች ሟች ከሁለት ጥይት ተኩስ በኋላ በሶስተኛው ጥይት የመቱት መሆኑ ተመልክቷል። ይህ ፍሬ ነገር የሚያስገነዝበን በደኑ የተቃጣ ሕገወጥ ጥቃት ስለመኖሩ ነው። ይህንን ጥቃት ለማስወገድ አመልካች ተኩሰው ሰው መግደላቸው እና ማቁሰላቸው ተረጋግጧል። ነገር ግን ተከትል የሚነሳው ጥያቄ አመልካች የተሰነዘረውን ጥቃት ለማስወገድ ላላ አመራጭ ያልነበራቸው ስለመሆኑ እና የወሰደት አማራጭም ተመጣጣኝ ስለመሆኑ አስረድተዋል ወይ? የሚለው ነው። በዚህ ረገድ አመልካች በሥር ፍ/ቤት ያቀረቧቸው መከላከያ ማስረጃዎች የለም። አመልካች ሕገወጥ ጥቃትን ለማስወገድ እርምጃ ስለመውሰዲቸው የተመለከተ ቢሆንም እርምጃው ላላውን አማራጭ የጨረሱ ስለመሆኑ እና ተመጣኝ ስለመሆኑ ለማስረዲት ያልቻለ ስለሆነ በወ/ሕግ አንቀጽ 78 የተመለከተውን ድንጋጌ ይዘት አሟልተዋል ለማለት የሚቻል ሆኖ አላገኘነውም ። ስለዚህም ድርጊታቸው ሕገወጥ ጥቃትን ለማስወገድ ነው የሚያስብል መነሻ ቢኖረውም የፈፀሙት የነፍስ ግድያ ወንጀል በሕጉ ከተመለከተው መጠን በማሳለፍ መሆኑን መገንዘብ ችለናል።
ሕጋዊ መከላከልን ከመጠን በማሳለፍ የተፈፀመ የወንጀል ድርጊት ደግሞ ከቅጣት ነፃ የማያደርግ ስለመሆኑ የወ/ሕ ድንጋጌ ቁጥር 79/1/ ያመለክታል። ይልቁንም ይህ አድራጎት የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ስለመሆኑ የዚህ ድንጋጌ ቁጥር 79/1/ ይገልፃል።ይህንን መሰረታዊ ጉዲይ ከተረዲን የአመልካች ድርጊት ጥፊተኛ ሉያሰኝ የሚገባው በየትኛው የወ/ሕጉ ድንጋጌ ነው የሚለውን መሰረታዊ ጭብጥ ወደ ማየት ስንመለስ የአመልካች ድርጊት ህጋዊ መከላከልን ከመጠን ማሳለፍ መሆኑን መሰረት በማድርግ የወ/ሕጉ ልዩ ክፍል በዚህ ጊዜ ተፈፃሚ የሚሆን ድንጋጌ እንዲለው እንረዲለን። ይኸውም በወ/ሕጉ አንቀጽ 541/ሀ/ ሥር ከተመለከቱት የድንጌጋው ማቋቋምያ ምክንያቶች አንደ ሕጋዊ መከላከልን ከመጠን በማሳለፍ የተፈፀመ የነፍስ ግድያ ወንጀል እንደሆነ ተመልክቷል። ከፍ ሲል እንደተመለከትነው የወ/ሕጉ አንቀጽ 79/1/ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት አድርጏ በገለፀው አኳኋን አንቀጽ 541/ሀ/ ሁለተኛው ሐረግ ደግሞ ወንጀለን ለማቋቋም እንደሚችል ደንግጓል።
እንዱህ አይነት ሁኔታ በተፈጠረ ጊዜ ደግሞ በወ/ሕጉ አንቀጽ 82/2/ እንደተደነገገው ድርጊቱን ለማቋቋም የተደነገገው ልዩ ክፍል ተፈፃሚነት ይኖረዋል። ይህንን ለማለት የወንጀል ሕጉን ድንጋጌ ቁጥር 82/2/ እና 84/2/ ይዘት እና አቀራረጽ አገናዝቦ መመልከት ተገቢ ነው።
ስለሆነም አመልካች የፈፀሙት የወንጀል ድርጊት የወ/ሕጉን አንቀጽ 54ዐ የሚያቋቁም ነው በማለት የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት የጥፊተኛነት እና የቅጣት ውሳኔ የድርጊቱን አፈፃፀም ከባቢያዊ ሁኔታና ምክንያት በአግባቡ ባለማገናዘብ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን መረዲት ችለናል።
ስለሆነም አመልካች የፈፀሙት የወንጀል ድርጊት የሕዝብ ደን ላይ ሉደርስ ይችል የነበረን ሕገወጥ ጥቃት ለማስወገድ እና ለመከላከል ቢሆንም ድርጊቱ የተፈፀመው ላልች አማራጮችን ሁለ አሟጠው ሳይጨርሱ መሆኑን አፈፃፀሙ ሲታይ ሕጋዊ መከላከልን ከመጠን በማሳለፍ መሆኑን የሚያሳይ ነው። እንዱህ ከሆነ ደግሞ የድርጊቱ አፈፃፀም የወ/ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 541/ሀ/ን የሚያቋቁም ይሆናል።
ስለዚህም አመልካች በ54ዐ ሥር ጥፊተኛ መባላቸው አግባብ ሆኖ ስላላገኘው ይህንኑ የጥፊተኝነት ውሳኔ የተሰጠበትን ድንጋጌ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 113/2/ መሰረት ለውጠን አመልካች በወ/ሕግ ቁጥር 541/ሀ/ ሥር ጥፊተኛ ናቸው ብለናል።
ቅጣትን በተመለከተ አመልካች በዚህ ፍ/ቤት ጥፊተኛ የተባለበት አንቀጽ አስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት እንደሚያስቀጣ ድንጋጌው ያመለክታል። በመሰረቱ ቀላል እስራት በመደቡ የሚጣለው ከአሥር ቀን እስከ ሦስት ዓመት የሚደርስ ስለመሆኑ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 1ዐ6/1/ ድንጋጌ ያመለክታል። ቀላል እስራት ቅጣት ከዚህ መደብ ጣሪያ ከፍ ብል አምስት ዓመት ሉደርስ የሚችለው በዚሁ አንቀጽ ሥር የተመለከቱት ምክንያቶች ወይም ሁኔታዎች ውሰጥ ቢያንስ አንደ ተሟልቶ ሲገኝ ስለመሆኑም ተደንግጓል። ይህንኑ በማገናዘብ አመልካች ላይ ሉፈፀም የሚገባውን ቅጣት እንደሚከተለው ወስነናል።
የትግራይ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ032878 ሚያዝያ12 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የፀናው የበታች ፍርድ ቤቶች የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በ195/2/ለ/2/ መሰረት ተሻሽሎል።
በዚሁ መሰረት አመልካች በወ/ሕግ 541/ሀ/ ድንጋጌ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ የግድያ ወንጀል የፈጸሙ ጥፊተኛ ናቸው ብለን ወስነናል።
አመልካች በዚህ ጉዲይ እጃቸው ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ በአመስት /5/ ዓመት ቀላል እስራት እንዱቀጡ ብለናል።
የጥፊተኛነት አንቀጽ እና ቅጣቱ የተሻሻለ መሆኑን እንዱያውቀው የዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ይፃፍ።
ማረሚያ ቤቱ በዚህ ችልት በተሻሻለው ቅጣት መሰረት እንዱያስፈጽም ብለናል።
ይፃፍ።
No topics extracted.