No summary available.
ታህሣስ 25 ቀን 2003 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ሰማኸኝ በለው - ባለቤቱ ነኝ ብለው ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል ዐቃቤ ሕግ - ወርቅነህ ዘነበ ቀረቡ መዝገቡ የቀረበው ለምርመራ ሲሆን መርምረን በአብላጫ ድምፅ ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የቀረበው በአመልካች ላይ ይግባኝ ሰሚው የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በወ/ይ/መ/ቁ. 48189 መጋቢት 30 ቀን 2002 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚልበትን ምክንያት በመግለፅ አመልካች ባቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ ሲሆን ተጠሪ የፋዳራል ዐቃቤ ሕግም የሰበር አቤቱታ የቀረበበት የጥፊተኝነትም ሆነ የቅጣት ውሣኔ በሕግ መሰረት የተሰጠ መሆኑን ገልፆ ተከራክሯል።
አመልካች በሰበር ሰሚው ችልት እንዱታረምለት የሰበር አቤቱታ ያቀረበበት የጥፊተኝነት ውሣኔ በይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠው በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 193/2/ መሰረት የአሁን አመልካች በመልስ ሰጭነቱ ተጠርቶ ላቀርብ ባለመቻለ ምክንያት በላለበት ይግባኙን በመስማት በመሆኑ በዚህ አኳኋን የተሰጠን የጥፊተኝነት ውሣኔ ይህ ሰበር ሰሚው ችልት በሰበር የማረም ሥልጣን አለው ወይስ የለውም? የሚለው የሥልጣን ጉዲይ በቅድሚያ ላታይ የሚገባው ነጥብ ሆኖ ተገኝቷል።
ለጉዲዩ አወሳሰን እንዱረዲ የጉዲዩን አመጣጥ ባጭሩ ለመግለፅ ያህል ለዚህ ለሰበር መ/ቁ.
57632 መነሻ የሆነው ውሣኔ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ኮ/ቁ. 20464 ሰኔ 18 ቀን 2001 ዓ.ም. በዋለው ችልት የተሰጠው ፍርድ ሲሆን ይዘቱም፡ተከሣሽ /የአሁን አመልካች/ በወ/መ/ሕ/ቁ. 522/1/ሀ/ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ሟች አርቲስት ግሩም ተስፊዬን በግፍ ገድሎል፣ ህይወቱ እንዱያልፍ አድርጓል በማለት የፋዳራል ዐቃቤ ሕግ ከእነ ሙለ የወንጀል ዝርዝሩ በቀረበው ክስ መነሻ ተከሣሽ /የአሁን አመልካች/ ቀርቦ እንዱከራከር ተጠርቶ ላቀርብ ያልቻለ፣ በጋዜጣም ቢጠራ ያልቀረበ መሆኑን በማየት በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 163/1/ መሰረት ጉዲዩን ተከሣሹ በላለበት እንዱታይ ካደረገ በኋላ፤ ከሣሽ ዐቃቤ ሕግ እንደ የወንጀል ክሱ አቀራረብ ተከሣሹ የወንጀለን ድርጊት ሆን ብል አስቦ የፈፀመ ለመሆኑ አላረጋገጠም። ስለሆነም በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 163/3/ መሰረት ከክሱ ነፃ ነው የሚል ፍርድ የተሰጠበት ነው።
በዚህ ፍርድ ላይ የአሁን ተጠሪ ቅር ተሰኝቶ ባቀረበው የይግባኝ ቅሬታ መነሻ ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍ/ቤት ለዚህ የሰበር መዝገብ ምክንያት የሆነውን በወ/ይ/መ/ቁ. 48189 መጋቢት 30 ቀን 2002 ዓ.ም. በዋለው ችልት የአሁን አመልካች በላለበት ፍርድ ሰጥቷል።
በዚሁ ፍርድ ላይ የአሁን አመልካች በላለበት ላታይ የቻለበትን ምክንያትም እንደሚከተለው አስፍሮታል።
ተከሣሽ የሆነው የአሁኑ አመልካች በመልስ ሰጪነት እንዱቀርብ የይግባኙ ማመልከቻና መጥሪያ ምርመራውን ባጣራው የፕሉስ ክፍል በኩል እንዱደርሰው ተልኮ የአ/አበባ ከተማ አስተዲደር ፕሉስ ኮሚሽን የትራፉክ መቆጣጠሪያና ምርመራ መምሪያ መልስ ሰጭ ከኢትዮጵያ ውጭ ሄዶል የሚል ጥቆማ እንደደረሰው በመግለፅ ያላገኘው መሆኑን በጽሐፍ በማሳወቁና መዝገቡም ሲታይ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም መልስ ሰጭ ተፈልጏ ባለመገኘቱ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጏለት ባለመቅረቡ ክሱ በላለበት የታየ ሆኖ በመገኘቱ እንደገና ተጨማሪ በጋዜጣ ጥሪ ማድረግ ሳያስፈልግ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 193/2/ መሰረት ይግባኙ መልስ ሰጭ በላለበት ታይቶ እንዱወሰን ተበይኗል።
በዚህ መሰረትም የሥር ፍ/ቤት ፍርድና የይግባኝ ባይ ዐቃቤ ሕግ ቅሬታ ከህጉ ጋር በማገናዘብ ከመረመረ በኋላ፡በይግባኝ የቀረበለት መዝገብ ከአሁን አመልካች ጉዲይ ጋር በተያያዘ ለሦስተኛ ጊዜ የቀረበ መሆኑንና የአመጣጡንም ሂደት እንደሚከተለው ገልፆታል።
በመጀመሪያ የአሁን አመልካች በተባለው ጊዜና ቦታ ሟችን በቸልተኝነት ገድሎል በሚል የወ/መ/ሕ/ቁ. 526/1/ ተጠቅሶ በቀረበበት ክስ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ተከሣሹን መከላከል ሳያስፈለገው በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 141 መሰረት በብይን በማሰናበቱ የተነሣ የይግባኝ ክርክር ቀርቦበት በወ/ይ/መ/ቁ. 26293 ታህሣስ 16 ቀን 1999 ዓ.ም. በዋለው ችልት በሥር ፍ/ቤት የተሰማው ማስረጃ ተከሣሹ እንዱከላከል የሚያበቃ መሆኑን ጠቅሶ ይከላከል ሲል መመለሱን።
በዚህ መሰረት መዝገቡ ከተመለሰ በኋላ ዐቃቤ ሕጉ የድርጊቱ አፈፃፀም በቸልተኝነት የተፈፀመ ሳይሆን ሆን ብል የፈፀመው መሆኑን ስለተረዲን ክሱን እንድናሻሽል ይፈቀድልን በማለት ጥያቄ ቢያቀርብም የከፍተኛው ፍ/ቤት ይህንን ጥያቄ ባለመቀበል የተከሳሹን ቃል በመከላከያ ማስረጃነት ተቀብል ጥር 23 ቀን 2000 ዓ.ም. በዋለው ችልት ተከሣሹ የአሁን አመልካች በወ/መ/ሕ/ቁ. 526/1/ ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ ድርጊቱን የፈፀመ መሆኑን አረጋግጦ የጥፊተኝነት ውሣኔ ከሰጠ በኋላ ለዚሁ ጥፊት በብር 3000.00 /ሦስት ሺህ ብር/ የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጣ ወስኗል።
ዐቃቤ ሕግ በዚህ ውሣኔ ለሁለተኛ ጊዜ በወ/ይ/መ/ቁ. 36932 በክስ ማሻሻል ጥያቄው ላይ አተኩሮ የይግባኝ ክርክሩን ሲያቀርብ በዚህ መነሻ መልስ ሰጭ የነበረው የአሁን አመልካች እንዱቀርብ ተፈልጎ ሉገኝ ባለመቻለ እንዱሁም በጋዜጣ በተደረገው ጥሪ ባለመቅረቡ የይግባኝ ጉዲዩን በላለበት ሰምቶ ዐቃቤ ሕግ ከፍርድ በፉት የክስ መሻሻል ጥያቄ ለማቅረብ የሥነ-ሥርዓቱ ሕጉ አይከለክለውም ከፍርደ በፉት በማናቸውም ጊዜ ክስ የማሻሻል መብቱን የሥር ፍ/ቤት ሳይቀበለው መቅረቱ አግባብ አይደለም በማለት ቀደም ሲል የሰጠውን የጥፊተኝነት እና የብር 3000.00 /ሦስት ሺህ ብር/ የገንዘብ መቀጮ ቅጣት ውሣኔ ሽሮ ተዘጋጅቶ በሚቀርበው አዱስ ክስ መሰረት ጉዲዩ እንዱታይ መልሶታል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በዚህ ውሣኔ መሰረት ያንኑ የኮ/መ/ቁ. 20464 የሆነውን መዝገብ አንቀሳቅሶ በዚሁ መዝገብ ላይ ተሻሽል የቀረበውን ክስ መነሻ በማድረግ ተከሣሽ /የአሁን አመልካች/ ቀርቦ ባለው የመከራከር መብት እንዱከራከር ተጠርቶ ያለመቅረብ እና በጋዜጣ ጥሪም ተደርጏለት አለመቅረቡን በማየት ከላይ በመግቢያው ላይ እንደተገለፀው ሰኔ 18 ቀን 2001 ዓ.ም.
በዋለው ችልት የአሁን አመልካች በክሱ ላይ የተገለፀውን ድርጊት እንደ ተከሰሰበት ድንጋጌ ሆን ብል የፈፀመው ለመሆኑ በማስረጃ አልተረጋገጠም። ስለሆነም በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 163/3/ መሰረት በነፃ ይሰናበታል በማለት ለመጨረሻ ጊዜ በጉዲዩ ላይ ፍርድ የሰጠ መሆኑን ጠቅሶ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በይግባኝ ሥልጣኑ የዚህኑ ፍርድ አግባብነት እንደሚከተለው መርምሮ የእራሱን ፍርድ መልስ ሰጭ የነበረው የአሁን አመልካች በላለበት በአብላጫ ድምፅ ሰጥቷል።
የድርጊቱ ሆን ተብል የተፈፀመ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው የሰውና የሰነድ ማስረጃ ሉያረጋግጥ አልቻለም። በልላ በኩል ይህ የአሁን አመልካች በዚሁ ድርጊት የተነሣ በቸልተኝነት ጥፊተኛ ተብል የብር 3000.00 /ሦስት ሺህ ብር/ የገንዘብ መቀጮ ተቀጥቷል። በዚህ ውሣኔ ላይ ከክስ ማሻሻል ጥያቄ ጋር በማያያዝ ይግባኝ የጠየቀበት ዐቃቤ ሕግ እንጂ ተከሣሹ አይደለም። ስለሆነም ድርጊቱ የተፈፀመው ሆነ ተብል ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጉዲይ ከሚያከራክር በቀር የድርጊቱ ፈፃሚ ተከሣሹ መሆኑ የታወቀ ጉዲይ ነው።
በመሆኑም ማስረጃው በወ/መ/ሕ/ቁ. 522/1/ሀ/ በተመለከተው መሰረት ጥፊተኛ ለማድረግ ደካማ ሆኖ ቢገኝም የፈፀመው አድራጏት በቸልተኝነት የግድያ ወንጀል ነው ለማለት በቂ ሆኖ ስለተገኘ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 113/2/ መሰረት በወ/ሕ/ቁ. 526/2/ የተመለከተውን ተላልፍ የተገኘ ጥፊተኛ ነው ልባል ስለሚገባው የሥር ከፍተኛው ፍ/ቤት ሰኔ 18 ቀን 2001 ዓ.ም. የሰጠውን ፍርድ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 195/2/ሀ/ መሰረት ተሰርዞ በወ/ሕ/ቁ. 526/2/ ጥፊተኛ ነው ካለ በኋላ ከዐቃቤ ሕግ በኩል ከቀረበው የቅጣት አስተያየት አንፃር በማየት የአሁን አመልካችን በአራት ዓመት እሥራት እንዱቀጣ በማለት ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍ/ቤት መጋቢት 30 ቀን 2002 ዓ.ም. በዋለው ችልት በአብላጫ ድምፅ ወስኗል።
የይግባኝ መዝገቡ በዚህ አኳኋን ከተቋጨና ከተዘጋ በኋላ የአሁን አመልካች የይግባኝ ክርክር በቀጠሮ ጊዜ ውጪ ሀገር ነበርኩኝ ክሱ ስለመቀጠለ አላወቅኩም መጥሪያም አልደረሰኝም የሚለትን ምክንያቶች በመጥቀስ በላለበት ታይቶ የተሰጠው ፍርድ ውድቅ ሆኖ ጉዲዩ ባለበት እንዱታይ ይደረግለት ዘንድ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 197 አቤቱታ በማቅረቡ በዚህ መነሻ ዐቃቤ ሕግ እንዱቀርብ አድርጎ ጉዲዩን በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 201 መሰረት ከሰማ በኋላ የወንጀል ክሱ ተሻሽል በወ/ሕ/ቁ. 522/1/ሀ/ መሰረት በከባድ ወንጀል ክስ ሲታይ ላቀርብ ባለመቻለ ጥሪ ተደርጏም ባለመቅረቡ ጉዲዩ በላለበት መወሰኑን መዝገቡ ያስረዲል።
በመጀመሪያው ክስ በነፃ ከተሰናበተ በኋላ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው የይግባኝ መነሻ በይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍ/ቤት ቀርቦ ተከራክሯል። ይከላከል ተብል መዝገቡ ከተመለሰ በኋላም በከፍተኛው ፍ/ቤት በጠበቃ ታግዞ ተከራክሯል።
በዚሁ የወንጀል ጉዲይ ከአንዳም ሁለቴ በይግባኝ ሰሚውና በሥር ፍ/ቤቶች በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎለት ለመቅረብ ስላልቻለ በላለበት ተፈርዶል።
ከአገር ወጥቷል ለተባለ ሰው መጥሪያ በግንባር ማድረስ ስለማይቻል ጥሪው በጋዜጣ መደረጉ ሥነ-ሥርዓታዊ ነው።
ወደ ውጭ አገር ለምን እንደሄደና ከአንድ ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ ምን ይሰራ እንደነበርና ለምን ወደ አገር ውስጥ ሳይመለስ የቆየበትን ምክንያት እንኳን አልገለፀም።
በቀረበበት በቸልተኝነት ሰው መግደል ወንጀል እየቀረበ ሲከራከር ከቆየ በኋላ ክሱ ወደ ከባድ ወንጀል ከተቀየረበት ጊዜ ጀምሮ ከአገር መውጣቱና ክርክሩ በከፍተኛው ፍ/ቤት ሲቀጥል ያን ያህል ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ሳይመለስ መቆየቱ በተሻሻለው ወንጀል ምክንያት የዋስ መብቱ ስለማይፈቀድ ታስሮ ክርክሩን የሚቀጥል መሆኑን በመረዲት ከፍርደ ሂደት መሸሹን ስለሚያመለክት ባለቤቱ በየቀጠሮው እየቀረበች ጉዲዩን ትከታተል ነበር፤ ለዚህም ማስረጃ አለኝ በማለት ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ክርክር አለመካደ ሁለ ሲታይ አመልካች በዚህ መዝገቡ ቀርቦበት የነበረውን የወንጀል ይግባኝ ክርክር አያውቅም ነበር ለማለት አያስችልም። ስለሆነም ከከባድ የወንጀል ክስ በመሸሽ አገር ጥል በመውጣት ሳይመለስ በመቅረቱ ምክንያት በላለበት ላታይ የቻለ ሆኖ ስለተገኘ በላለበት የተሰጠው ፍርድ ውድቅ የሚሆንበት የሕግ ምክንያት የለም በማለት አቤቱታውን ውድቅ አድርጎታል።
የጉዲዩ አመጣጥ ይህን ሲመስል አመልካቹ ይህን የሰበር አቤቱታው ያቀረበው ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት እኔ በላለሁበት የሰጠው የጥፊተኝነት ውሣኔ እና የቅጣት አወሳሰን መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል የሚልበትን በክርክር አካሄድ ተፈፀመ የሚላቸውን የሥነ-ሥርዓት ጉድለቶችን በቸልተኝነት ወንጀል ተፈፀመ ለማለት በሕግ የሚጠይቀውን ሟሟያ የመሳሰለትንና በቅጣት አጣጣል ረገድ እንደ ሕጉ አልተፈፀመም የሚላቸውን በመጥቀስ የተከራከረ በመሆኑ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት አንድ ፍርድ ተከሳሽ /ይግባኝ ባይ/ በላለበት ታይቶ የተሰጠ መሆኑ ሲታወቅ እርሱ ባለበት ክርክሩ ታይቶ እንዱወሰን የማድረግ መብቱን ሳያስጠብቅ በቀጥታ ያንኑ በላለበት ታይቶ የተሰጠውን ውሣኔ በሰበር ለማሳረም የሚያስችል ሥልጣን አለው ወይስ የለውም የሚለውን ጥያቄ ሉያስነሳ ችሎል።
የዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ሥልጣን ከኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 80/3/ እና ይህንኑ ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ ተከትል ከወጣው ከአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 የሚመነጭ በመሆኑ እንደ ሕገ መንግሥቱ እና አዋጁ ሥልጣን ያለው መሆኑንና አለመሆኑን ከላላው ተከራካሪ ወገን በክርክር መልክ ባይቀርብለትም በእራሱ መርምሮ የመለየት ግዳታ አለበት። ከዚህም አንፃር ይህንኑ ጉዲይ ተመልክተናል።
እንደተመለከትነውም የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚው ችልት የሥልጣን ምንጭ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 80/3/ሀ/ የተመለከተው ድንጋጌ ሲሆን ይዘቱም የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ማናቸውንም የመጨረሻ ውሣኔ ለማረም በሰበር ችልት የማየት ሥልጣን ይኖረዋል ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል የሚል ነው።
ከዚህም ድንጋጌ ‛… የመጨረሻ ውሣኔ …“ የሚለው ሀረግ አንድ ጉዲይ በሀገሪቱ በተዋቀሩት ፍ/ቤቶች ታይቶ እንዱወሰን ከታች ወደ ላይ ስንት የክርክር ደረጃ ማለፍ አለበት።
ስንት የክርክር ደረጃ ሉፈቀድ ይገባል የሚለውን አስመልክቶ በወጣው ሕግ መሰረት የክርክሩ ደረጃውን አሟጦ የጨረሰ መሆኑን የሚያመለክት ነው። የዚሁ ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌን አፈፃፀም አስመልክቶ በወጣው አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 9 እና 10 የተመለከተውም የመጨረሻ ውሣኔ ማለት በፍ/ቤቶች አደረጃጀት አንፃር አንድ ጉዲይ ከታች ወደ ላይ እስከምን ያህል ደረጃ መዝለቅ ይችላል የሚለውን መሰረት በማድረግ የተቀመጠ የክርክር ደረጃ ወሰን መሆኑን እስረጂ ነው።
አሁን የተያዘውን አንድ የወንጀል ጉዲይ ተከሣሽ በላለበት ታይቶ ፍርድ በተሰጠ ጊዜ በዚህ ፍርድ ላይ ይግባኝ የማሰማት መብት ያለው መሆኑንና አለመሆኑን አስመልክቶ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 202 የተመለከተው ድንጋጌ ከላይ በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 9 እና 10 የተመለከተውን የክርክር ደረጃ ወሰን የሚያመለክት ሳይሆን የተለየ ዓላማ ያለው ነው።
በዚሁ ድንጋጌ ንዐስ አንቀጽ 3 ላይ አንድ ፍርድ ተከሣሽ በላለበት ታይቶ ከተፈረደ በኋላ ፍርደኛው ከወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 197 ቀጥል ባለት ድንጋጌዎች መሰረት ፍርደ ውድቅ ሆኖ የመከራከር መብቱ እንዱጠበቅለት ያቀረበው ማመልከቻ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቶ ውድቅ እንዱሆን ከተደረገ ይግባኝ ማለት አይቻልም። ነገር ግን ስለተፈረደበት ቅጣት ብቻ ማመልከቻው ውድቅ እንዱሆን ከተወሰነበት ቀን አንስቶ በ15 ቀን ጊዜ ውስጥ ይግባኝ ማለት አይከለክልም በማለት በጥፊተኝነት ውሣኔው ላይ ይግባኝ ማለት እንደማይቻል በግልፅ ተደንግጓል።
በላለሁበት ታይቶ የተሰጠው ፍርድ ይነሳ ለማለት በምክንያትነት የሚቀርቡት በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 199/ሀ/ እና /ለ/ የተመለከቱት የመጥሪያ አደራረስ እና ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ለመቅረብ አለመቻል ናቸው። እነዚህን ምክንያቶች ማስረዲት የቻለ ፍርደኛ ፍርደን ውድቅ አድርጎ እንደገና እርሱ ባለበት ክርክሩ እንዱሰማ የማድረግ መብት ያለው ሲሆን ከእነዚህ ሁለት ምክንያቶች አንደኛውን ለማስረዲት ያልቻለ ተከሣሽ ወይም ፍርደኛ ከፍትህ ርቆ ወይም ሸሽቶ የነበረ (considered as a convicted perform who was actually seeking to evade justice) መሆኑን የሚያስረዲ ነው።
ከወንጀል ጉዲዮች የትኞቹ ተከሣሽ በላለበት ሉታዩ የሚችለ ስለመሆኑ በላለበት እንዱታይ ከመደረጉ በፉት ስለሚፈፀመው ሥርዓት በመዘርዝር አንድ የወንጀል ክስ ጉዲይ ተከሣሽ በላለበት እንዱታይ ማድረግ ስለሚቻልበት ሁኔታ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 160 እስከ 164 መደንገጉም ጥሪ ተደርጎለት አለመቅረቡ ቢታወቅም በወ/ሕ/ቁ. 1 እንደተመለከተው የተከሣሽ አለመቅረብ የወንጀልን ሕግ ግብ አፈፃፀም ሉያሰናክል የሚችል እና ሕጉም ተገቢ ባልሆነ ምክንያት ወደ ሕግ ሉቀርቡ የማይችለን ያለማበረታት ቀዲሚ ግብ ያለው መሆኑንና በዚህም የተነሣ ተጏጂዎች ከሚፈልጉት ፍትህ የማግኘት መብት አንፃር ታይቶ የተዘረጋ ሥርዓት ሲሆን፤ በአንፃሩ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 2/ሀ//1/ እንደተደነገገው የተከሰሰ ሰው ካለው መሰረታዊ መብት አንደ የመሰማት መብት እንደመሆኑ መጠን በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 13/2/ እንደተመለከተው ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ህግጋት አንደ በሆነው የሲቪልና የፕለቲካ መብቶች ስምምነት /እ.ኤ.አ. 1966/ አንቀጽ 14/3/መ/ ተከሣሽ ባለበት የመዲኘትና እራሱን የመከላከል መሰረታዊ መብት ያለው በመሆኑ እና ይህም በማናቸውም ምክንያት በልላ ሕግ ሉገደብ ስለማይችል በዚህ መብቱ ለመገልገል እንዲይችል ጥሪ በሚገባ ያልተደረገላቸው ከሆነ ጥሪ ቢደረግላቸውም ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በክርክሩ ጊዜ መቅረብ ያልቻለ ወገኖች ካለ ይኸው ከላይ በተቀመጠው ሕገ መንግሥታዊ መብት መጠቀም እንዱችለ ሥርዓቱ በወ/ሕ/ቁ. 197-202 ተዘርግቷል።
ስለሆነም ከእነዚህ ምክንያቶች አንደን ያላስረዲ ፍርደኛ ፍርደን ውቅድ የማስደረግ መብት ያለው ሲሆን ይህንን ለማስረዲት ያልቻለው ግን በሕገ መንግሥቱ በተሰጠው በሕግ መሰረት የመዲኘት መብት /The right to fair trial) ለመጠቀም ሳይፈልግ ከሕግ ለመራቅ ያቀደ ከሕግ ርቆ የቆየ በመሆኑ ግምት የሚወሰድበት ስለሆነ በተሰጠው የቅጣት ውሣኔ ላይ ካልሆነ በቀር በተሰጠው ጥፊተኝነት ውሣኔ ላይ ይግባኝ የማቅረብ መብት የላለው መሆኑን በመግለፅ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.
202 ተደንግጓል። በዚህም መሰረት በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 202 መሰረት በጥፊተኝነቱ ውሣኔ የይግባኝ መብት አይኖረውም በሚል መደንገጉ ከላይ ከተቀመጠው ምክንያት አንፃር የመከራከር መብቱን የነፈገ እንጂ በዚህ ድንጋጌ መሰረት የይግባኝ አቤቱታ ማቅረብ አይቻልም መባለ ፍርደን የመጨረሻ አድርጎታል የሚል ትርጉም ለመስጠት የሚቻል አይደለም።
ስለ ወንጀል ይግባኝ ጉዲይ አስመልክቶ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 193/2/ በዐቃቤ ሕግ ይግባኝ መነሻ በነፃ የተሰናበተውን ተከሣሽ ጉዲይ በላለበት እንዱታይ ለማድረግ በሚያስችል አኳኋን መደንገጉም በይዘቱም ሆነ በዓላማው የመጀመሪያ ደረጃ ክስን ተከሣሽ በላለበት እንዱታይ ከማድረግ ተለይቶ የሚታይ ስለሆነ መልስ ሰጭ በላለበት የተሰጠውን ፍርድ እርሱ ባለበት ክርክሩ እንዱታይ ፍርደን ውድቅ ካላደረገው በቀር በላለበት ታይቶ የተሰጠውን ፍርድ እንደመጨረሻ ፍርድ ተቆጥሮ በሰበር እንዱታረም ለማድረግ የሚያስችል መብት አይሰጥም ፍርደም እንደመጨረሻ ፍርድ ስለማይቆጠር ሰበር ሰሚው ችልት በሰበር የማረም ሥልጣን የለውም።
በዚህ ሁለ ምክንያት በአሁን አመልካች ላይ የተሰጠው የጥፊተኝነት ውሣኔ ለአንዳና ለመጨረሻ ጊዜ የተቋጨ እንጂ በሰበር ላታይ የሚችል ጉዲይ ሆኖ አላገኘነውም።
በቅጣት ውሣኔ ረገድ የሰበር ጉዲዩን መመርመር የሚቻል በመሆኑ በዚህ ረገድ የቀረበውን ክርክር እንደተመለከትነውም በቅጣት አጣጣል /አወሳሰን/ ረገድ የሥር ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የፈፀመው የሕግ ስህተት አልተገኘም።
ስለሆነም የሰበር አቤቱታ የቀረበበትን የጥፊተኝነት ውሣኔ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 80/3/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 9 እና 10 እንዱሁም በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 202 መሰረት ከክርክሩ ደረጃ ወሰን አንፃር በማየት እንደተቀመጠ የመጨረሻ ውሣኔ ሆኖ ባለመገኘቱ ይህ ሰበር ችልት ለማየት ሥልጣን የላለው በመሆኑ በሰበር ሉታረም የሚችል አይደለም።
የቅጣት አወሳሰኑም ቢሆን መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም ብለናል።
በዚህም መነሻ የሚተለውን ውሣኔ በአብላጫ ድምፅ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ኮ/ቁ. 20464 ሰኔ 18 ቀን 2001 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ የተሻረ ሲሆን ይግባኝ ሰሚው የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በወ/ይ/መ/ቁ. 48189 መጋቢት 30 ቀን 2002 ዓ.ም. የሰጠውን ፍርድ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 195/2/ለ/2/ መሰረት በተለየም ምክንያት ቢሆን አፅንተናል።
ስማችን በአራተኛውና በአምስተኛው ተራ ቁጥር የተገለፀው ዳኞች አብላጫው ድምፅ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 193 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ይግባኙን አይቶ አመልካች በላለበት የሰጠው የጥፊተኝነት ውሣኔ ላይ አመልካች የሰበር አቤቱታ እንዱያቀርብ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 202 ንዐስ አንቀጽ 3 የሚፈቀድ አይደለም በማለት በሰጠው የሕግ ትርጉምና በደረሰበት መደምደሚያ ያልተስማማን በመሆኑ በሀሳብ ተለይተናል። ከሥራ ባልደረቦቻችን የተለየንበት የመጀመሪያው ምክንያት ጉዲዩን በመጀመሪያ ያየው የከፍተኛው ፍ/ቤት ተጠሪ አሻሽል ያቀረበውን የወንጀል ክስ ከወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 160 እስከ አንቀጽ 163 አመልካች በላለበት አይቶ የሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ በላለበት ሁኔታ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 197 እስከ አንቀጽ 202 የተደነገገው ሥርዓት በጠቅላላውና የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 202 ንዐስ አንቀጽ 3 በልዩ ሁኔታ ለጉዲዩ አግባብነትና ተፈፃሚነት ያለው የሕግ ድንጋጌ እንደሆነ አድርጎ በመተርጎም አብላጫው ድምፅ በሰጠው ውሣኔ የማንስማማ በመሆናችን ሲሆን ሁለተኛው ለጉዲዩ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከአንቀጽ 197 እስከ አንቀጽ 202 የተደነገጉት ድንጋጌዎች በጠቅላላውና የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር አንቀጽ 202 ንዐስ አንቀጽ 3 በልዩ ሁኔታ ለያዝነው ጉዲይ ተፈፃሚነት አላቸው የሚባል ቢሆን እንኳ እነዚህ ድንጋጌዎች አመልካች ይግባኝ ሰሚው ችልት በሰጠው ፍርድ ላይ ተፈፅሟል የሚለውን መሰረታዊ የሕግ ስህተት በሰበር ታይቶ እንዱታረምለት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 80 ንዐስ አንቀጽ 3/ሀ/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ከመጠየቅ የሚገድብ አይደለም የሚል አቋም ያለን በመሆኑ ነው።
አመልካችና ተጠሪ በዚህ መዝገብ የሚከራከሩበት ጉዲይ መነሻ ተጠሪ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሚያዚያ 14 ቀን 1995 ዓ.ም. ጽፍ ያቀረበው የወንጀል ክስ ነው። ተጠሪ ያቀረበው ክስ ይዘትም ተከሣሹ/አመልካች/ በ1949 ዓ.ም. የወጣውን የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 526 ንዐስ አንቀጽ 1 የተደነገገውን በመተላለፍ ሐምል 7 ቀን 1994 ዓ.ም. በግምት ከላሉቱ አሥር ሰዓት ሲሆን የመለያ ቁጥር 2-72538 አ.አ. የሆነ መኪና ባለመጠንቀቅና ጥፊት በሆነ ቸልተኝነት ሲያሽከረክር የመኪናውን መንገድ ወደ ቀኝ በመልቀቅ ባምቢስ ድልድይ ውስጥ ገብቶ በመገልበጡና በአደጋው በመኪናው ውስጥ ተሣፍሮ የነበረው አቶ ግሩም ተስፊዬ ላይ የሞት አደጋ ያደረሰበት በመሆኑ በቸልተኝነት የሰው መግደል ወንጀል ፈጽሟል የሚል ነው። አመልካች/ተከሣሽ/ ሚያዚያ 14 ቀን 1995 ዓ.ም. ጽፍ ተጠሪ ያቀረበውን የወንጀል ክስ አልፈፀምኩም ጥፊተኛ አይደለሁም በማለት በመከራከሩ ተጠሪ ክሱን ያስረደልኛል የሚላቸውን ማስረጃዎች አቅርቧል። የከፍተኛው ፍ/ቤት የተጠሪን ማስረጃ ከሰማና ከመረመረ በኋላ የተጠሪ ማስረጃ አመልካች በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር 526 ንዐስ አንቀጽ 1 የተመለከተውን በመተላለፍ በቸልተኝነት የሰው መግደል ወንጀል የፈፀመ መሆኑን በአጥጋቢ ሁኔታ አላስረዲም በማለት አመልካች የመከላከያ ማስረጃ ማቅረብ ሳያስፈልገው በነፃ እንዱሰናበት በወንጀል መዝገብ ሰኔ 30 ቀን 1998 ዓ.ም. ውሣኔ ሰጥቷል።
ተጠሪ የከፍተኛው ፍ/ቤት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 141 መሰረት በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይገባኝ ሰሚ ችልት አቅርቧል።
ይግባኝ ሰሚው ችልት የተጠሪንና የአመልካችን ክርክር በይግባኝ መዝገብ ከሰማ በኋላ ተጠሪ ሚያዚያ 14 ቀን 1995 ዓ.ም. ያቀረበውን የወንጀል ክስ በአጥጋቢ ሁኔታ ያስረዲ በመሆኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተከሣሽን/አመልካችን/ በነፃ ማሰናበቱ ተገቢ አይደለም በማለት የከፍተኛውን ፍ/ቤት ውሣኔ በመሻር የከፍተኛው ፍ/ቤት የአመልካችን መከላከያ ማስረጃ በመስማት ጉዲዩን እንዱወስን በማለት ታህሣስ 16 ቀን 1999 ዓ.ም. በመወሰን ጉዲዩን ለከፍተኛው ፍ/ቤት መልሶ ልኮታል።
በዚህ ውሣኔ መሰረት የከፍተኛው ፍ/ቤት ጉዲዩን ማየት ቀጥሎል። የከፍተኛው ፍ/ቤት አመልካች የመከላከያ ማስረጃ እንዱያቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል። አመልካች የመከላከያ ማስረጃ የላለው በመሆኑ ፍ/ቤቱ የክሱን ቃል እንዱሰማው የጠየቀ ሲሆን ተጠሪ በበኩለ አመልካች በቸልተኝነት ሳይሆን አስቦና ሆነ ብል ሟችን የገደለው መሆኑን የሚያስረዲ አዱስ ማስረጃ አግኝተናል። ስለሆነም በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር 522 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት ክሳችንን አሻሽለን እንድናቀርብ ይፈቀድልን በማለት አመልክተዋል። የከፍተኛው ፍ/ቤት ተጠሪ የወንጀል ክሱን ለማሻሻል ያቀረበውን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ አመልካች በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር 526 ንዐስ አንቀጽ 1 የተደነገገውን በመተላለፍ በቸልተኝነት የሰው መግደል ወንጀል የፈፀመ ጥፊተኛ ነው በማለት አመልካች በብር 3000 /ሦስት ሺህ ብር/ መቀጮ እንዱቀጣ ጥር 23 ቀን 2000 ዓ.ም. ውሣኔ ሰጥቶ አመልካች የገንዘብ መቀጮውን የከፈለ መሆኑን ከመዝገቡ ለመረዲት ችለናል።
ተጠሪ ያቀረብነውን የወንጀል ክስ በማሻሻል ለማቅረብ ያቀረብነውን ጥያቄ የከፍተኛው ፍ/ቤት ውድቅ ማድረጉ ተገቢ አይደለም። የከፍተኛው ፍ/ቤት ለማሻሻል ጥያቄ ያቀረብንበትንና ሚያዚያ 14 ቀን 1995 ዓ.ም. ጽፈን ያቀረብነውን የወንጀል ክስ መሰረት በማድረግ የሰጠው የጥፊተኝነት የቅጣት ውሣኔ ተገቢ አይደለም በማለት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ለሁለተኛ ጊዜ የይግባኝ ቅሬታውን አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚ ችልቱ አመልካች ይግባኙ በሚሰማበት ቀነ ቀጠሮ እንዱቀርብ በጋዜጣ ጥሪ እንዱደረግለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። አመልካች ይግባኙ በሚሰማበት ቀነ ቀጠሮ ያልቀረበ በመሆኑ ይግባኙን በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 193 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ጉዲዩን መልስ ሰጭ/አመልካች/ በላለበት አይቶ ተጠሪ ከፍርድ በፉት የወንጀል ክሱን የማሻሻል መብት ያለው መሆኑ በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ተደንግጎ እያለ የከፍተኛው ፍ/ቤት ተጠሪ ክሱን ለማሻሻል ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተገቢ አይደለም በማለት የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠውን ፍርድ በመሻር የከፍተኛው ፍ/ቤት ተጠሪ አሻሽል የሚያቀርበውን የወንጀል ክስ በመቀበልና ክርክሩን በስማት እንዱወሰን በማለት ጉዲዩን ለሁለተኛ ጊዜ መልሶ ልኮለታል።
የከፍተኛው ፍ/ቤት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ጥቅምት 26 ቀን 2001 ዓ.ም. በሰጠው ውሣኔ መሰረት ተጠሪ አመልካች የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር 522 ንዐስ አንቀጽ 1 የተመለከተውን በመተላለፍ ሟች ግሩም ተስፊዬ ላይ ከባድ የሰው መግደል ወንጀል ፈፅሟል በማለት ጥር 12 ቀን 2001 ዓ.ም. አሻሽል ያቀረበውን የወንጀል ክስ በመቀበል ጉዲዩን ለሦስተኛ ጊዜ ለመስማት ተጠሪና አመልካች /ተከሣሽ/ እንዱቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ሆኖም አመልካች ባለመቅረቡ መጥሪያው በጋዜጣ እንዱወጣ ካደረገ በኋላ ወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከአንቀጽ 160 እስከ አንቀጽ 163 በተደነገገው መሰረት ተከሣሽ/አመልካች/ በላለበት በ(default) የተጠሪን ማስረጃና ክርክር በመስማትና በመመርመር ተጠሪ የወ/መ/ሕ/ቁ. 522/1/ በመጥቀስ ጥር 12 ቀን 2001 ዓ.ም. አሻሽል ባቀረበው የወንጀል ክስ መሰረት አመልካች ከባድ የሰው መግደል ወንጀል የፈፀመ መሆኑን የሚያረጋግጥ አጥጋቢ ማስረጃ አላቀረበም በማለት ተከሳሽ /አመልካች/ን ተሻሽል ከቀረበው የወንጀል ክስ በነፃ እንዱሰናበት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 163 ንዐስ አንቀጽ 3 እና በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 141 መሰረት ወስኗል።
ከላይ በአጭሩ የገለጽነው ክርክሩ ያለፈባቸው ሂደቶች ተከሣሹ/አመልካች/ በላለበት (default) ክሱ ታይቶ ጉዲዩን በመጀመሪያ ባየው የከፍተኛው ፍ/ቤት በአመልካች ላይ የሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ያለ መሆኑን የሚያረጋግጥ አይደለም። ተጠሪ ያቀረበው የተሻሻለ የወንጀል ክስ ተከሳሹ/አመልካች/ በላለበት (default) በከፍተኛው ፍ/ቤት የታየ ቢሆንም የሥር ፍ/ቤት አመልካች በነፃ እንዱሰናበት ፍርድ ሰጥቷል። አመልካች በነፃ እንዱሰናበት ጉዲዩን በመጀመሪያ ያየው ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ እንዱታረም ለማድረግ ዐቃቤ ሕግ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 181 እና በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 185 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ይግባኝ ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በማቅረብ ጉዲዩ በይግባኝ እንዱታረምለት ጠይቋል። በእኛ እምነት የከፍተኛው ፍ/ቤት አመልካች በላለበት (default) በማየት የሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ባለመኖሩ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ 160 እና ተከታዮቹ አንድ ተከሣሽ በላለበት የተሰጠውን ፍርድ ውድቅ እንዱደረግለት ስለሚያመለክትበትና ጉዲዩ ፍርደን በሰጠው ፍ/ቤት በድጋሚ ስለሚታይበት ሥርዓት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 197 እስከ አንቀጽ 202 የተደነገጉት ድንጋጌዎች በጠቅላላውና የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 202 ንዐስ አንቀጽ 3 በልዩ ሁኔታ ለጉዲዩ አግባብነትና ተፈፃሚነት ያላቸው ድንጋጌዎች አይደለም።
በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከንቀጽ 160 እስከ አንቀጽ 163 የተደነገጉት የ(default procedure) ጉዲዩን በመጀመሪያ የሚያየው ፍ/ቤት አሥራ ሁለት ዓመትና ከዚህ በላይ በሆነ ጽኑ እሥራት የሚያስቀጡ የወንጀል ክሶችን ተከሣሹ በላለበት አይቶ ለመወሰን የሚከተለውን ልዩ ሥርዓት የሚደነግግ ሲሆን የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 193 ንዐስ አንቀጽ 2 በማናቸውም ጉዲይ የሥር ፍ/ቤት በሰጠው ፍርድ ቅር በመሰኘት ተከሣሹ ወይም ዐቃቤ ሕግ ያቀረቡት ማናቸውም ይግባኝ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በሚሰማበት ጊዜ መልስ ሰጭ ካልቀረበ ተፈፃሚ የሚሆን ሰፉ ሥርዓት ነው።
የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 193 ንዐስ አንቀጽ 2 በጥቅል አገላለጽ የተደነገገና በበርካታ ጉዲዮች ሰፉ ተፈፃሚነት ያለው ሥርዓት ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በዚህ ሥርዓት መሰረት አይቶ የሰጠው ውሣኔ መልስ ሰጭ ውድቅ እንዱሆንለትና ይግባኙ መልስ ሰጭ ባለበት ታይቶ እንዱወሰን ማመልከቻ የሚያቀርብበት ሥርዓት አይደለም። በወንጀለኛ መቅጫ ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 193 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት የቀረበለትን ይግባኝ መልስ ሰጭ በላለበት አይቶ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀጽ 2 በተደነገጉት ድንጋጌዎች መሰረት የሰጠው ፍርድ እንዱሰረዝና ውድቅ እንዱሆን በማድረግ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከአንቀጽ 197 እስከ አንቀጽ 202 መሰረት በማድረግ መጠየቅም ሆነ ማመልከት አይቻልም።
በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከአንቀጽ 197 እስከ አንቀጽ 202 የተደነገገው ሥርዓት ጉዲዩን ተከሣሹ በላለበት (default) በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከንቀጽ 160 እስከ አንቀጽ 163 በተደነገገው መሰረት አይቶ የተሰጠውን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ውድቅ ለማስደረግ የሚያገለግል እንጂ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 193 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ይግባኙን መልስ ሰጭ በላለበት አይቶ የወሰነውን ውሣኔ በድጋሚ አይቶ ውድቅ ለማስደረግ የሚያገለግል ሥርዓት አይደለም። ስለሆነም አብላጫው ድምፅ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከአንቀጽ 197 እስከ አንቀጽ 202 የተደነገጉት ድንጋጌዎች ይግባኝ ሰሚው ችልት ይግባኙን አመልካች/መልስ ሰጭ/ በላለበት አይቶ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀጽ 2/ሀ/ መሰረት የሰጠውን ፍርድ ለማሰረዝ አግባብነትና ተፈፃሚነት እንዲላቸው አድርጎ በሰጠው ትርጉም ያልተስማማን በመሆኑ በሀሳብ ተለይተናል።
የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 193 ንዐስ አንቀጽ 2 በሚከተለት ሁኔታዎች ሁለ ተፈፃሚነት ያለው ሥርዓት ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በዚህ ሥርዓት መሰረት መልስ ሰጭ በላለበት ይግባኙን አይቶ የሰጠው ውሣኔ ላይ የተፈፀመ የሕግ ወይም የፍሬ ጉዲይ ስህተት ሉታረም የሚቻለው በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 9 ንዐስ አንቀጽ 2 በተደነገገው የይግባኝ ሥርዓት በመጠቀምና ይህ የይግባኝ ሥርዓት በላለበት ሁኔታ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሣኔ በሰበር ታይቶ እንዱታረም በመጠየቅ መሆን አለበት የሚል እምነት አለን። በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 193 ንዐስ አንቀጽ 2 በተደነገገው ሥርዓት መሰረት ይግባኙ መልስ ሰጭ በላለበት ታይቶ የሚወሰነው፡ተከሣሽ የወንጀል ክሱን በመጀመሪያ በሚሰማበት ጊዜ ቀርቦ ተከራክሮ የሥር ፍ/ቤት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ሉወስን፣ ተከሣሹ የጥፊተኝነቱን ውሣኔ ወይም የቅጣቱን ውሣኔ ወይም የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔውን በመቃወም ያቀረበው ይግባኝ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በሚሰማበት ጊዜ መልስ ሰጭው /ዐቃቤ ሕግ/ ያልቀረበ በሆነ ጊዜ፣ ተከሣሹ የተወሳሰቡትን የወንጀል ድርጊት የፈፀመና ጥፊተኛ መሆኑን በማመን ክሱን ለሚሰማው ፍ/ቤት በሰጠው የዕምነት ቃል መሰረት የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሣኔ የተሰጠበት በሆነ ጊዜና ተከሣሹ የቅጣት ውሣኔውን በመቃወም በወንጀለኛ መቅጫ ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 185 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት ያቀረበው ይግባኝ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በሚሰማበት ጊዜ መልስ ሰጭ/ዐቃቤ ሕግ/ ያልቀረበ በሆነ ጊዜ፣ ጉዲዩን በመጀመሪያ ያየው ፍ/ቤት የወንጀል ክሱንና ክርክሩን ተከሣሹ በላለበት (default) በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከአንቀጽ 160 እስከ አንቀጽ 163 መሰረት አይቶ በተከሣሹ ላይ የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ የሰጠ ሲሆንና ተከሣሹ በላለበት የተሰጠውን ፍርድ ለማሰረዝ ያቀረበው ማመልከቻ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከንቀጽ 197 እስከ አንቀጽ 201 በተደነገጉት ድንጋጌዎች መሰረት ከታየ በኋላ ማመልከቻው በአንቀጽ 202 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ተቀባይነት ያላገኘ ተከሣሽ በላለበት የተሰጠውን የቅጣት ውሣኔ በመቃወም በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 202 ንዐስ አንቀጽ 3 መሰረት ያቀረበው ይግባኝ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በሚሰማበት ጊዜ መልስ ሰጭ /ዐቃቤ ሕግ/ ያልቀረበ ሲሆን፣ ተከሣሽ ባለበት ጉዲዩን ያየው ፍ/ቤት ተከሣሽ ለጊዜው እንዱለቀቅ ወይም በነፃ እንዱሰናበት የሰጠውን ፍርድ በመቃወም ዐቃቤ ሕግ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 181 እና አንቀጽ 185 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ያቀረበው ይግባኝ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በሚሰማበት ጊዜ መልስ ሰጭ/ተከሣሹ/ ያልቀረበ ሲሆን፣ ተከሣሽ ባለበት ጉዲዩን ያየው ፍ/ቤት በተከሣሽ ላይ የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ የወሰነ ሲሆንና ዐቃቤ ሕግ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን የጥፊተኝነት ውሣኔ ወይም የቅጣት ውሣኔ ወይም የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔውን በመቃወም በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 181 እና አንቀጽ 185 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ያቀረበው ይግባኝ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በሚሰማበት ጊዜ መልስ ሰጭ/ተከሣሽ/ ያልቀረበ ሲሆን፣ የወንጀል ክሱን በመጀመሪያ ያየው ፍ/ቤት የወንጀል ክሱን በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከንቀጽ 160 እስከ አንቀጽ 163 በተደነገገው መሰረት ተከሣሹ በላለበት (default) በማየት ተከሣሹ በነፃ እንዱሰናበት የሰጠውን ውሣኔ በመቃወም ዐቃቤ ሕግ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 181 እና አንቀጽ 185 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ያቀረበው ይግባኝ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በሚሰማበት ጊዜ መልስ ሰጭ/ተከሣሽ/ ያልቀረበ ሲሆን፣ የወንጀል ክሱን በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከአንቀጽ 160 እስከ አንቀጽ 163 በተደነገገው ሥርዓት መሰረት ተከሣሹ በላለበት ያየው ፍ/ቤት የሰጠውን የጥፊተኝነት ውሣኔ ወይም የቅጣት ውሣኔ ወይም የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ በመቃወም ዐቃቤ ሕግ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 181 እና አንቀጽ 185 ንዐስ አንቀጽ 2 ያቀረበው ይግባኝ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በሚሰማበት ጊዜ መልስ ሰጭ/ተከሣሽ/ ያልቀረበ ሲሆን፣ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት መልስ ሰጭ ባለበት ወይም በላለበት ይግባኙን አይቶ በሰጠው ፍርድ ላይ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 9 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ሁለተኛ ይግባኝ ማቅረብ የሚቻል በሆነ ጊዜ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠውን ፍርድ በመቃወም ዐቃቤ ሕግ ወይም ተከሣሹ ያቀረቡትን ይግባኝ ለማሰማት በተያዘው ቀነ ቀጠሮ መልስ ሰጭ ሳይቀርብ ሲቀር በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 193 አንቀጽ 2 ተፈፃሚነት አለው።
ከላይ በተገለፁት ሁኔታዎች ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት መልስ ሰጭው በላለበት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 193 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ይግባኙን መርምሮ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀጽ 2 ከተደነገጉት ድንጋጌዎች በአንደኛው የተመለከተውን ውሣኔ የመስጠት ሥልጣን አለው። በያዝነው ጉዲይ የከፍተኛው ፍ/ቤት ተከሣሹ አመልካች በላለበት የወንጀል ክሱን በማየት ተከሣሽ በነፃ እንዱሰናበት የሰጠው ፍርድ ላይ ተጠሪ ያቀረበውን ይግባኝ መልስ ሰጭ/አመልካች/ በላለበት ሰምቶ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀጽ 2/ሀ/ መሰረት የከፍተኛው ፍ/ቤት ውሣኔን በመሻር በአመልካች ላይ የጥፊተኝነትና የጥፊት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ይግባኙን በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ 193 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት በማየት የሰጠውን ፍርድ ይግባኝ ሰሚው ችልት ጉዲዩን በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከአንቀጽ 197 እስከ አንቀጽ 202 በተደነገገው ሥርዓት መሰረት አይቶ ፍርደን ውድቅ እንዱያደርግለት ያቀረበው ማመልከቻ የሕግ መሰረት የለውም። ይግባኝ ሰሚው ችልትም ይግባኙን መልስ ሰጭ በላለበት አይቶ የሰጠውን ፍርድ ውቅድ እንዱያደርግለት አመልካች በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከአንቀጽ 197 እስከ አንቀጽ 202 በተደነገገው ሥርዓት መሰረት ያቀረበውን ማመልከቻ በመቀበል የአመልካችንና የተጠሪን ክርክር ከሰማ በኋላ አመልካች በቂ ምክንያት ያላቀረበ በመሆኑ ፍርደ አይሰረዝም በማለት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 202 ንዐስ አንቀጽ 2ን በመጥቀስ ሰኔ 7 ቀን 2002 ዓ.ም.
የሰጠው ውሣኔ የሕግ መሰረት የለውም።
ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በማናቸውም ምክንያት የቀረበለትን ይግባኝ መልስ ሰጭ በላለበት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 193 ንዐስ አንቀጽ 2 ሰምቶ የሰጠው ፍርድ ውድቅ እንዱደረግ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከአንቀጽ 197 እስከ አንቀጽ 202 በተደነገገው ሥርዓት መሰረት ለመመልከት የሚፈቅድ የሕግ ድንጋጌ የለም። ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት መልስ ሰጭ በላለበት አይቶ የሰጠው ፍርድ ላይ የተፈፀመ የሕግ ወይም የፍሬ ጉዲይ ስህተት የሚታረምበት ሥርዓት በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 9 ንዐስ አንቀጽ 2 የተደነገገው መስፈርት የተሟላ ሲሆን በዚህ ድንጋጌ የተዘረጋውን የይግባኝ ሥርዓት በመጠቀም ነው። ጉዲዩ ከላይ በተገለፀው የሕግ ድንጋጌ የተዘረጋውን መሥፈርት የማያሟላ ሲሆን ወይም በዚህ መዝገብ እንደተያዘው ጉዲዩን ለሁለተኛ ጊዜ በይግባኝ አይቶ የመወሰን ሥልጣን ያለው ፍ/ቤት ወይም ይግባኝ ሰሚ ችልት በላለ ጊዜ ስህተቱ የሚታረመው በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 80 ንዐስ አንቀጽ 3/ሀ/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 የተዘረጋውን የሰበር ሥርዓት በመጠቀም ነው።
ከላይ ከደረስንበት መደምደሚያ ላይ ለመድረስ ከዚህ በፉት በሰፉው ከገለፅናቸው ምክንያቶች በተጨማሪ የአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 9 አቀራረፅ እና የቃል በቃል ንባብ መገናዘብ አለበት የሚል እምነት አለን። ‛የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሥልጣን“ የሚል ርዕስ ያለው የአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 9 ‛የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሚከተለትን ጉዲዮች በይግባኝ የማየት ሥልጣን ይኖረዋል“
በያዝነው ጉዲይ የከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች በላለበት አይቶ በነፃ እንዱሰናበት በተሰጠው ውሣኔ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቦ ይግባኝ ሰሚ ችልቱ የከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ወስኗል።
በአዋጁ አንቀጽ 10 መሰረት የሰበር አቤቱታ ለማቅረብ ይግባኝ ሰሚው ችልት ይግባኙን በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 9 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት መልስ ሰጭ ባለበት አይቶ ውሣኔ መስጠቱ በመስፈርትነት አልተደነገገም። ስለሆነም ይግባኝ ሰሚው ችልት መልስ ሰጭ በላለበት ይግባኙን ሰምቶ በሰጠው ውሣኔ የከፍተኛው ፍ/ቤት ውሣኔ ከሻረ ወይም ካሻሻለ መልስ ሰጭ ያለው ብቸኛ አመራጭ የሰበር አቤቱታ ማቅረብ መሆኑን የሚደነግግ የሕግ ድንጋጌ ነው።
በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ አሻሽል ያቀረበውን የወንጀል ክስ ተከሳሹ/አመልካች/ በላለበት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከአንቀጽ 160 እስከ አንቀጽ 163 በተደነገገው መሰረት አይቶ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተከሣሹ/አመልካች/ በነፃ እንዱሰናበት የሰጠውን ፍርድ በመቃወም ተጠሪ ያቀረበውን ይግባኝ መልስ ሰጭ/አመልካች/ በላለበት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 192 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት በማየትና የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠውን ፍርድ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀጽ 2/ሀ/ መሰረት በመሻር በአመልካች ላይ የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ሰጥቷል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በሰጠው ውሣኔ ይግባኝ የሚያይ ላላ ችልት ወይም ፍ/ቤት የለም ይህም በመሆኑ አመልካች ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኙን በላለበት አይቶ በሰጠው ውሣኔ ላይ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 9 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ይግባኝ ለማቅረብ አይችልም። የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አመልካች/መልስ ሰጭ/ በላለበት ይግባኙን በማየት የሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ በይግባኝ የማይታይ ወይም ከሰበር ውጭ በልላ መንገድ ላታይም የማይችል የመጨረሻ ውሣኔ ነው።
ስለሆነም አመልካች የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተጠሪ ያቀረበውን ይግባኝ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 193 ንዐስ አንቀጽ 3 መሰረት መልስ ሰጭ/አመልካች/ በላለበት አይቶ የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሙለ በሙለ በመሻር በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 195 ንዐስ አንቀጽ 2/ሀ/ መሰረት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ሲወስን ፈፅሞታል የሚለውን መሰረታዊ የሕግ ስህተት በሰበር ታይቶ እንዱታረምለት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 80 ንዐስ አንቀጽ 3/ሀ/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ በሰበር ችልቱ እንዲይታይ የሚገድብ ወይም የሚከለክል ግልፅ የሆነ የሕግ ድንጋጌ የለም። በዚህ በኩል አብላጫው ድምፅ ጉዲዩ በሰበር የሚታይና የሚታረም አይደለም ከሚለው መደምደሚያ ላይ የደረሰው በጉዲዩ የተሰጠ ‛የመጨረሻ ውሣኔ“ የለም በማለት ሲሆን በእኛ በኩል ጉዲዩ በይግባኝ ሰሚ ችልት የመጨረሻ ውሣኔ የተሰጠበትና በሰበር ላታይ የሚችል ውሣኔ በመሆኑ ተጠሪ ይግባኝ ሰሚው ችልት ያቀረበለት ይግባኝ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 193 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት በማየት የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀጽ 2/ሀ/ መሰረት በሰጠው ፍርድ ላይ ተፈፅሟል የሚለውን መሰረታዊ የሕግ ስህተት በሰበር ታይቶ እንዱታረምለት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 80 ንዐስ አንቀጽ 3/ሀ/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት የሰበር አቤቱታ እንዲያቀርብ የሚገድብ ወይም የሚከለክል የሕግ ድንጋጌ የለም። በዚህ በኩል አብላጫው ድምፅ ጉዲዩ ‛የመጨረሻ ውሣኔ“ አላገኘም በማለት የሰጠውን የሕግ ትርጉም ከላይ በዝርዝር በገለጽነው ምክንያት አልተቀበልነውም።
ይህ ድንጋጌ የወንጀል ክስ ተከሣሹ በላለበት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከአንቀጽ 160 እስከ አንቀጽ 163 በማየት ወንጀል ክሱን ተከሣሹ በላለበት (default) ያየው ፍ/ቤት በተከሣሽ ላይ የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ የሰጠ በሆነ ጊዜ ብቻ ተፈፃሚነት ያለው የሕግ ድንጋጌ ነው። ድንጋጌው ሁለት ደንቦች ያለት ሲሆን የመጀመሪያው የወንጀል ክሱ በላለበት የታየ ተከሣሽ በላለበት የተሰጠው ፍርድ ውድቅ እንዱሆንለት ያቀረበው ማመልከቻ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነሥርዓት ሕግ ከአንቀጽ 197 እስከ አንቀጽ 201 በተደነገገው ሥርዓት ከታየ በኋላ ማመልከቻው ተቀባይነት የለውም ተብል በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 202 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት የተወሰነበት ተከሣሽ የሥር ፍ/ቤት አቤቱታውን ውድቅ በማድረግ በሰጠው ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ ማለት የማይችል መሆኑን የሚደነግግ ነው። ሁለተኛው ደንብ በላለበት የወንጀል ክሱ ታይቶ ፍርድ የተሰጠበት ተከሣሽ ፍርድ ውድቅ እንዱደርግለት ፍርደን ለሰጠው ፍ/ቤት ያቀረበው ማመልከቻ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 202 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት አቤቱታው ተቀባይነት ያላገኘ ተከሣሽ ፍ/ቤቱ ክሱን በላለበት አይቶ በሰጠው የጥፊተኝነት ውሣኔን በመቃወም ይግባኝ ለማቅረብ የማይችል መሆኑንና በቅጣት ውሣኔ ላይ ብቻ ይግባኝ የማለት መብት ያለው መሆኑን የሚደነግግ ነው። ይህ የሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 202 ንዐስ አንቀጽ 3 ድንጋጌ ገዥ ደንብ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 181 በወንጀል ፍርድ ላይ ይግባኝ ስለሚቀርብበት ሁኔታ ከደነገገው ጠቅላላ መርህ በልዩ ሁኔታ የተደነገገ ሆኖ እናገኘዋለን።
የወንጀለኛ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 202 ንዐስ አንቀጽ 3 በይዘቱም ሆነ በሚያስከትለው ህጋዊ ውጤት ከወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 185 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ ጋር ተመሣሣይነት ያለውና በላለበት የወንጀል ክስ ታይቶ የተሰጠን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ውድቅ ለማስደረግ ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት ያላገኘ ተከሣሽ በቅጣት ውሣኔው ላይ ብቻ ይግባኝ ማለት እንደሚችል ግልጽ የሚያደርግ ነው።
የቀረበበትን የወንጀል ክስ በሙለ በማመኑ ምክንያት በዕምነቱ መሰረት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 134/1/ መሰረት የጥፊተኝነት ውሣኔ የተሰጠበት ሰው የቅጣት ውሣኔውን በመቃወም ካልሆነ በስተቀር በጥፊተኝነቱ ውሣኔ ላይ ይግባኝ ማቅረብ እንደማይቻል የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 185 ንዐስ አንቀጽ 1 ከደነገገው በተጨማሪ ተከሣሽ የጥፊተኝነት ውሣኔውን በመቃወም ይግባኝ የማያቀርብበት ሁኔታ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 202 ንዐስ አንቀጽ 3 የተደነገገው ሁኔታ ነው። ይህ ድንጋጌ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነሥርዓት ሕግ በአምስተኛው መጽሐፍ በሁለተኛው አንቀጽ ተከሣሹ በላለበት ከወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ከአንቀጽ 160 እስከ አንቀጽ 163 ታይቶ የተሰጠውን ፍርድ ውድቅ ለማድረግ በሚቀርብ ማመልከቻ ላይ ብቻ ተፈፃሚነት ያለው ነው። ድንጋጌው በሥነ-ሥርዓት ሕጉ አምስተኛው መጽሐፍ አንደኛ አንቀጽ የወንጀል ፍርድ በይግባኝ ስለሚታረምበት ሁኔታ ከአንቀጽ 181 እስከ አንቀጽ 196 በደነገገው ጉዲይ ላይ ተፈፃሚነት የላለው በመሆኑ አብላጫው ድምፅ ጉዲዩ በሰበር የሚታይ አይደለም በማለት የተሰጠው ትርጉም ተገቢ ሆኖ አልታየንም።
ለዚህም የመጀመሪያው ምክንያት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከአንቀጽ 197 እስከ አንቀጽ 202 ያለትን ድንጋጌዎች ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት መልስ ሰጭ በላለበት አይቶ በሰጠው ፍርድ ላይ የማመሳሰል የሕግ አተረጓጎም ዘዳን በመጠቀም ተፈፃሚ ሲሆኑ ጥብቅና ጠባብ የሆነ ትርጉም ሉሰጣቸው የሚገባ መሆኑ ነው። የሥነ-ሥርዓት ሕጉ ድነጋጌዎች የሙግት ሂደትን በአግባቡ ለመምራትና የተከሣሹን መሰረታዊ መብቶች የሚከበሩበትን ሥርዓት የሚደነግጉ ናቸው።
ስለሆነም አንድ የሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌ በሚተረጎምበት ጊዜ ሰፉና የተለጠጠ ትርጉም በመስጠት መሰረታዊ መብቶችንና ነፃነቶችን በሚያሣጣ መንገድ ሉተረጎም አይገባውም። የሥነሥርዓት ድንጋጌዎችን በጥብቅና በጠበበ መንገድ በመተርጎም በህገ መንግሥቱ እና በላልች የሕግ ማዕቀፍች የተደነገጉ የስህተት ማረሚያ ሥርዓቶች ጥቅም ላይ የሚውለበትን ሁኔታ የማያሰናክል ወይም አላስፈላጊ ገደብ በማይጥል መንገድ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል የሚል እምነት አለን።
የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 202 ንዐስ አንቀጽ 3 ተከሣሹ በላለበት የተሰጠው የጥፊተኝነት ውሣኔ ላይ ይግባኝ እንዲያቀርብ ገደብ የሚጥል ነው። በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከአንቀጽ 181 እስከ እስከ አንቀጽ 196 የተደነገገው የይግባኝ ሥርዓት የሰበር ችልት በሚጠቀምበት ጊዜ በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 80 ንዐስ አንቀጽ 3/ሀ/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 የተዘረጋውን የሰበር ሥርዓት ጥቅም ላይ የሚውልበትን ሁኔታ የማያጣብብና ዜጎች መሰረታዊ የሕግ ሥህተት አለበት የሚለትን የመጨረሻ ውሣኔ በሰበር እንዱታረምላቸው የመጠየቅ እድላቸውን በማያጣብብ ሁኔታ መተርጎምና ተፈፃሚ መሆን አለበት።
ሁለተኛው ምክንያት በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 80 ንዐስ አንቀጽ 3/ሀ/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 የተዘረጋው የሰበር ሥርዓት መሰረታዊ ዓላማና ግብ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ማናቸውም የመጨረሻ ውሣኔ በሰበር ታይቶ ሉታረም የሚችልበትን እድል በመፍጠርና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበትን ውሣኔ በሰበር አይቶ በማረም በአገሪቱ ውስጥ ወጥ የሆነ የሕግ አተረጓጎምና ተፈፃሚነት እንዱቀር ማድረግ ነው። ላላው የሰበር ዓላማ ህጋዊ ያልሆነ ውሣኔ እንዲይፀና ማድረግ ሲሆን ከይግባኝና ከላልች ሥርዓቶች የተለየ መሆኑን ይህ የሰበር ችልት በሰበር መዝገብ ጥቅምት 29 ቀን 2003 ዓ.ም. በሰባት ዳኞች በተሰየሙበት በሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም አቋም የያየዘበት ነው። በመሆኑም የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት መልስ ሰጭ/አመልካች/ በላለበት በማየትና የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠውን ፍርድ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀጽ 2/ሀ/ መሰረት በመሻር በሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ላይና የአመልካችና የተጠሪ ክርክር ባለፈባቸው ሂደቶች ተፈፅሟል የሚለው የሕግ ስህተት እንዱታረምለት አመልካች ያቀረበው የሰበር አቤቱታ መመርመር የሰበር ሥርዓት ከተዘረጋበት መሰረታዊ ዓላማና ግብን መሰረት ያደረገ ሆኖ እያለ ጉዲዩ ለሰበር ቀርቦ እንዲይታይ የሚከለክል የሕግ ድንጋጌ በላለበት ጉዲዩ በሰበር የሚታይ አይደለም መባለ ተገቢ ነው የሚል እምነት የለንም።
የከፍተኛው ፍ/ቤት አመልካች በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 526 ንዐስ አንቀጽ 1ን በመተላለፍ በቸልተኝነት የሰው መግደል ወንጀል የፈፀመ ጥፊተኛ ነው በማለት ፍርድ የሰጠው ይግባኝ ሰሚው ችልት ተጠሪ ክሱን የማያስረዲ ማስረጃ ስላቀረበ የአመልካችን መከላከያ ሰምተህ ወስን በማለት የሰጠውን ፍርድ መሰረት በማድረግ ነው። የወንጀል ክስ ከተጀመረበት 1995 ዓ.ም.
ጀምሮ የከፍተኛው ፍ/ቤት ጥር 13 ቀን 2000 ዓ.ም. የሰጠውን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ አመልካች እስከፈፀመበት ጊዜ ድረስ ረዥም ጊዜ አመልካች በክርክር የቆየ መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል።
ተጠሪ ከወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 119 ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ ውጭና ይግባኝ ሰሚው ችልት ተጠሪ በክሱ በጠቀሰው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር 526 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት የአመልካችን መከላከያ ማስረጃ ሰምቶ የከፍተኛው ፍ/ቤት እንዱወስን በወንጀል ይግባኝ መዝገብ የሰጠውን ፍርድ በማያስለውጥ ሁኔታ ተጠሪ አቅርቦት የነበረውን የወንጀል ክስ በመተው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር 522 ንዐስ አንቀጽ 1ን በመጥቀስ ክሱን ለማሻሻል ያቀረበውን ጥያቄ የከፍተኛው ፍ/ቤት ውድቅ ያደረገው በመሆኑ ተጠሪ ይግባኝ አቅርቦ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የከፍተኛው ፍ/ቤት የተጠሪን የተሻሻለ ክስ ተቀብል አከራክሮ እንዱወስን በሰጠው ውሣኔ መሰረት የተሻሻለው ክስ ሲሰማ አመልካች ያልቀረበ መሆኑን በመዝገቡ የተደረገው የክርክር ሂደት ያሣያል። ይህ ሂደት አመልካች ከፍትህ ርቆና ሸሽቶ የኖረ መሆኑን አያሣይም።
ይግባኝ ሰሚው ችልት በወንጀል ይግባኝ መዝገብ የሰጠውን ፍርድ በሚለውጥና የሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 119 ከሚደነግገው ሥርዓት ውጭ ተጠሪ ክሱን እንዱያሻሽል በመፍቀደ ምክንያት በክርክሩ ሂደት ችግሮች የተፈጠሩ መሆኑን የሚያሣይ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ የወንጀል የፍትህ ሥርዓቱን ግብ ለማሣካት የሚቻለው በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 22 እና በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 2 የተደነገገውን የህጋዊነት መርህ በሚያከብር ሁኔታ የፍትህ አካላቱ ኃላፉነታቸውን ሲወጡ ነው የሚል እምነት አለን። ሰበር በወንጀል ጉዲይ በተሰጠ የመጨረሻ ውሣኔ በህገ መንግሥቱና በወንጀል ሕጉ የተደነገጉ መሰረታዊ መርሆች መከበራቸው የሚረጋገጥበት ሥርዓት ነው። ስለሆነም ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካች በላለበት የሰጠው ፍርድ ላይ አለ በማለት በሰበር አቤቱታው የገለፃቸው የሕግ አተረጓጎም የወንጀል ሕጉን ግብ የማያሣካ ነው የሚል እምነት የለንም።
ከላይ ከተገለፀው በተጨማሪ የተጠቀሰው የሲቪልና የፕለቲካ መብት ቃል ኪዲን ስምምነት ድንጋጌ መተርጎም ያለበት መብትን በሚያሣጣ ወይም በሚያጣብብ መንገድ መሆን አይገባውም። ይህ ድንጋጌ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች መብት በሚያሣጣ ወይም በሚያጣብብ መንገድ ሉተረጎም የማይገባው መሆኑን ዓለም አቀፍ ህብረተሰብ እንደ አውሮፒውያን አቆጣጠር 1948 ዓ.ም. ባወጀው የሰብዓዊ መብቶች ሁለንተናዊ መግለጫ /The Universal Decleration of Human Rights) አንቀጽ 30 የደነገገውን የአተረጓጎም መርህ መሰረት ባደረገ ሁኔታ ትርጉም ሉሰጠው ይገባዋል የሚል እምነት አለን።
በአጠቃላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ ተራ ቁጥር 8 በተጠቀሱት ምክንያቶች የሰበር ችልት አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታና ተጠሪ ያቀረበውን መልስና ይግባኝ ሰሚ ችልቱ የሰጠውን ውሣኔ በመመርመር መዝገቡ ለሰበር ሲቀርብ በተያዘው ጭብጥ መሰረት ውሣኔ እንዲይሰጥ የሚከለክለው ሕግ በላለበት ሁኔታ ጉዲዩ በሰበር የሚታይ አይደለም በማለት አብላጫው ድምፅ በሰጠው ውሣኔ ያልተስማማን በመሆናችን በሀሳብ ተለይተናል።
/አተ
ጥር 10 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፣ ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች፣ ዬርዲኖስ አባይ አሰፊ የቀረበለት የለምተጠሪ፣ የፋዳራል ዐቃቤ ሕግ አልቀረበም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
የሰበር አቤቱታው የአሁኗ አመልካች በተከሰሰችበት የስርቆት ወንጀል በክሱ ላይ ተላልፊለች ተብል በተጠቀሰባት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 665/1/ መሰረት ጥፊተኛ ተብላ በ2 ዓመት ቀላል እሥራትና በብር 2500 የገንዘብ መቀጮ እንድትቀጣ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በሚል በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 80/3//ሀ/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10/3/ መሰረት የቀረበ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ጉዲዩን በመጀመሪያ ያየው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ሆነ በይግባኝ ቀርቦለት የተመለከተው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በጥፊተኛነቱም ሆነ በቅጣት አወሳሰኑ ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈጽመዋል የሚለባቸውን ምክንያቶች ግንቦት 5 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ዘርዝረው አቅርበዋል።
አቤቱታው ተመርምሮ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ቀርቦ ይታይ በመባለ ማመልከቻው ለተጠሪው ተልኮ ቀርቦ መልስ እንዱሰጥበት አድርጓል ተጠሪው በጽሐፍ የሰጠው መልስ ለአመልካች ጠበቃ ደርሷቸው በጽሐፍ የመልስ መልስ ሰጥተውበታል።
ይህ ችልትም ጉዲዩን መርምሯል።
እንደመረመረውም የአሁኑ አመልካች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 665/1/ን በመተላለፍ የስርቆት ወንጀል ፈጽማለች ተብላ የተከሰሰችው ከላልች ዋና የወንጀል አድራጊዎች ጋር በመሆን ቀን የግል ተበዲይዋ ቤት ገብተው ቁምሣጥን በመስበር በርካታ መጠን ያለው ገንዘብ የተለያዩ የወርቅ ጌጣጌጦች እና ላልች ቁሳቁሶችን ሰርቀው ወስደዋል በሚል ምክንያት መሆኑን መዝገቡ ያስረዲል።
የአሁኗ አመልካች ክሱን ክዲ ብትከራከርም ዐቃቤ ሕግ ማስረጃዎች አቅርቦ አስረድቷል።
ዐቃቤ ሕግ ካቀረባቸው ማስረጃዎች መካከል አንደ የጽሐፍ ሲሆን የጽሐፍ ማስረጃውም የአሁኗ አመልካች በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 35 መሰረት ፍ/ቤት ቀርባ የስርቆቱን ድርጊት ስለመፈፀሜ በማመን ሰጥታለች የተባለው ቃል ነው። ይህንንም የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በ14/11/2001 ዓ.ም በሰጠው የጥፊተኛነት ውሣኔ ላይ ገልጾታል። የአመልካች ጠበቃ በሰበር አቤቱታቸው ላይ እንዱህ አይነት የጽሐፍ ማስረጃ አልቀረበባትም አላለም። ሚስጥር ሰለሞን የተባለችው የግል ተበዲይ ልጅ ከአሁኗ አመልካች ጋር በዚሁ የስርቆት ወንጀል አንደኛ ተከሣሽ መሆኗን ተከሳ እያለ የዐቃቤ ሕግ ምስክር እንድትሆን ተደርጏ ቀርባ ዐቃቤ ህግ በእርሷ ላይ አቅርቦት የነበረውን ክስ በማንሣት ምስክር እንድትሆን አድርጓል ከላልች ሰዎች ጋር በመሆን ወንጀለን ፈጽሟል ተብል ምርመራ ተጣርቶበት ክስ እንዱቀርብበት የተደረገው ሰው ተከሣሽ ከመሆን ይልቅ ምስክር መሆኑ ይጠቅመኛል ብል ዐቃቤ ሕግ በእርሱ ላይ አቅርቦት የነበረውን ክስ ማንሣት ምስክር እንዱሆን ማድረግን የሚከለክለው ሕግ ስለላለ በዚህ ጉዲይ በ1ኛም ተከሣሽ ላይ አቅርቦት የነበረውን ክስ በማንሣት ምስክር አድርጏ ማቅረቡ የሚጥሰው ሕግ የለም። በአሁኗ አመልካች ላይ የቀረበባት ማስረጃ ምስክሯ ብቻ ሣትሆን ከፍ ሲል እንደተገለፀው የፅሐፍ ማስረጃም ቀርቦባታል አመልካች ወንጀለን መፈፀሟ ተረጋግጦባታል የተባለው በእነዚህ ሁለት ማስረጃዎች ስለሆነ የአመልካች ጠበቃ ምስጥር ሰለሞን ክሱ ሣይነሣላት በተከሣሽነት ደረጃ እንዲለች እርሷ ብቻ ቀርባ እንዲመሰከረችባት አድርገው የገለጹት ትክክል አይደለም።
የአሁኗን አመልካች በሚመለከት በማስረጃ የተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች ስለሥርቆት ወንጀል የሚያሣዩ አይደለም በሚል የተነሣውን ክርክር በተመለከተም በማስረጃ የተረጋገጡበት ፍሬ ነገሮች በወንጀል ሕግ አንቀጽ 665 ላይ የተመለከተውን የስርቆት ወንጀል በሚገባ የሚያቋቁሙ ሆነው ስለተገኙ በዚህ የሕግ አንቀጽ መሰረት ጥፊተኛ በመባሎ የተፈፀመ የሕግ ስህተት የለም።
የተወሰነባትን ቅጣት በሚመለከት ፍ/ቤቱ በርካታ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች መኖራቸውን በቅጣት ውሣኔው ላይ ከገለፀ በኃላ ሁለተኛውን አማራጭ እስከ አምስት አመት የሚደርሰውን የጽኑ እሥራት ቅጣት በመተው የቀላል እሥራቱን ቅጣት በመከተል በ2 ዓመት ቀላል እሥራት እንድትቀጣ መወሰኑ ዕድሜዋ 17 አመት ነው የተባለውን ግምት ውስጥ ያስገባ የሚባል እንደሆነ እንጂ ያለአግባብ ከብድባታል የሚያሰኝ አይደለም። በመሆኑም በቅጣት አወሳሰኑም ረገድ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም። ስለሆነም የሚከተለው ተወሰኗል።
ው ሣ ኔ
ም.አ የሰበር መ/ ግንቦት 5 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፣ ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴአመልካች፣ የፋዳራል ዐቃቤ ሕግ ዐቃቤ ሕግ ወርቅነህ ዘነበ ቀረበተጠሪ፣ አቶ ሚፍታህ ኑረዱን ጠበቃ ግርማ ደጀኔ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት አመልካች በተጠሪና በዚህ ክርክር ተካፊይ ባልሆኑ ላልች ሁለት ሰዎች ላይ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና አንቀጽ 346 የተመለከተውን በመተላለፍ በተጠሪ በተመዘገበ የንግድ ድርጅት /ሱቅ/ ውስጥ ተጠሪ ፈቃድ ሣይኖረው የውጭ አገር ገንዘብ በመመንዘርና የዘጠኝ የውጭ ሀገር ገንዘብ አከማችቶ የተገኘ ሲሆን ላልች ተከሣሾች የወንጀለ ሥራ ተካፊይ በመሆናቸው የውጭ አገር ገንዘብ በህገወጥ መንገድ የመመንዘር ወንጀል ፈፅመዋል በማለት ክስ አቅርቧል። አመልካች ካቀረበው የወንጀል ክስ ጋር በተጠሪ ሱቅ ውስጥ
የሥር ፍርድ ቤት የጥፊተኝነት ውሣኔ ከሰጠ በኃላ አመልካችና ተጠሪ የቅጣት ውሣኔ አስተያየት እንዱሰጡ ትዕዛዝ ሰጥቷል። አመልካች ፍርድ ቤቱ ተጠሪን ሉያርምና ሉያስተምር የሚችል የቅጣት ውሣኔ እንዱሰጥለትና በተጠሪ ሱቅ ውስጥ የተገኙት የውጭ አገር ገንዘቦች ውርስ ሆነው ለመንግስት ገቢ እንዱሆኑ የፍ/ቤቱ ትዕዛዝ እንዱሰጥለት የቅጣት አሰተያየት አቅርቧል።
ተጠሪም 4 ገጽ የቅጣት አስተያየት በፅሐፍ አቅርቧል። የሥር ፍርድ ቤት የግራቀኙን የቅጣት አስተያየት ከመረመረ በኃላ ተጠሪ በሁለት ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 30‚000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ እንዱቀጣ ወስኖ የፅኑ እስራት ቅጣቱን በሁለት ዓመት የሙከራ ጊዜ እንዱገደብ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ከዚህ በተጨማሪ የሥር ፍርድ ቤት በተጠሪ ሱቅ ውስጥ የተያዙት የውጭ አገር ገንዘቦች በመንግስት እንዱወረሱ ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች የሥር ፍርድ ቤት በተጠሪ ሱቅ ውስጥ የተያዘው የኢትዮጵያ ገንዘብ እንዱወርስ ትዕዛዝ ሣይሰጥ ማለፈ የወንጀል ህጉን አንቀጽ 346 እና አንቀጽ 48 የሚጥስ ነው ስለዚህ የሥር ፍርድ ቤት በተጠሪ ሱቅ ውስጥ የተያዘው የኢትዮጵያ ገንዘብ እንዱወረስ ትዕዛዝ ሣይሰጥ በዝምታ ማለፈ ተገቢ ባለመሆኑ በይግባኝ ታይቶ ይታረምልኝ በማለት የይግባኝ ቅሬታ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርቧል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን የቅጣት ውሣኔና ትዕዛዝ አፅንቶታል።
አመልካች ሀምላ 11 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በይግባኝ ያነሳቸውን የቅሬታ ነጥቦች በማንሣት ተከራክሯል። አመልካች ተጠሪ በህገወጥ መንገድ የውጭ አገር ገንዘብ የመመንዘር ወንጀል የፈፀመ መሆኑ ተረጋግጦ ጥፊተኛ ተብሎል። ስለዚህ የወንጀለ ድርጊት የሥራ ፍሬ የሆነውና በተጠሪ ሱቅ ውስጥ የተያዘው የኢትዮጵያ ገንዘብ እንዱወረሱ ትዕዛዝ ሣይሰጥ የሥር ፍርድ ቤት በዝምታ ማለፈና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሥር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩለ ሚያዚያ 19 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ባደረግነው ክርክር ከተጠሪ ሱቅ ውስጥ የተያዘው የኢትዮጵያ ብር እንዱወረስ ትዕዛዝ ይሰጥልኝ በማለት አላመለከተም። በተቃራኒው አመልካች እንዱወረስ ትዕዛዝ እንዱሰጥለት የሚፈልገው የውጭ አገር ገንዘቦችን ብቻ መሆኑንና በተጠሪ ሱቅ የተያዘውን ገንዘብ እንደማይጨምር በግልፅ አስተያየት ሰጥቷል። ስለዚህ በስር ያልተከራከረበትን ፍርድ ቤቱ አለፈብኝ በማለት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ የህግ መሰረት የለውም በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች ሚያዚያ 20 ቀን 2002 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ ሰጥቷል።
ግራቀኙ በፅሐፍ ካደረጉት ክርክር በተጨማሪ ችልቱ ሀምላ 15 ቀን 2002 ዓ.ም የግራቀኙን ክርክር ሰምቷል። አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በተጠሪ ሱቅ የተገኘው የኢትዮጵያ ብር እንዱወረስ አስተያየት መስጠቱን በማንሣት የተከራከረ ሲሆን ተጠሪ በበኩላቸው አመልካች የኢትዮጵያ ገንዘብ እንዱወርስ በሥር ፍርድ ቤት አልተከራከረም። አመልካች የመወረስ ትዕዛዝ የኢትዮጵያን ብር እንዱጨምር እንደማይፈልግ በመግለፅ ነው አስተያየት የሰጠው የሚል ክርክር አቅርበዋል። ግራቀኙ አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በሰጠው የቅጣት አስተያየት በተለይም በተጠሪ ሱቅ ውስጥ ስለተያዘው የኢትዮጵያ ገንዘብ አመልካች ባቀረበው ክርክር ይዘት ላይ ሰፉ ልዩነት ያላቸው በመሆኑ ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ሶስተኛ የወንጀል ችልት የአመልካችንና የተጠሪን ክርክር ከመቅረፀ ድምፅ ያቀረቡትን ካሴት እንዱልክ ችልቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል። የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካችና ተጠሪ በመዝገብ ያደረጉት ክርክር የተቀረፀን ካሴት በፕስታ በማሸግ ህዲር 8 ቀን 2003 በተፃፈ መሸኛ ልኳል። ይህ የሰበር ችልትም አመልካችና ተጠሪ ያቀረቡትን የቅጣት አሰተያየትና ክርክር የተቀረፀበትን ካሴት ግንቦት 3 ቀን 2003 ዓ.ም በቴፔ ሪከርደር ሰምቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በተጠሪ ሱቅ ውስጥ የተያዘው የኢትዮጵያ ብር እንዱወረስ ትዕዛዝ ሣይሰጡ ማለፈ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ይህንን ጭብጥ ለመወሰን አመልካች የተጠሪ ሱቅ ውስጥ ስለተያዘው የኢትዮጵያ ገንዘብ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረበውን አስተያየትና የውሣኔ ሃሣብ ትክክለኛ ይዘት መመርመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትና ለሰበር ችልት የሥር ፍርድ ቤት በተጠሪ ሱቅ ውስጥ የተገኘው የኢትዮጵያ ገንዘብ እንዱወረስ ትዕዛዝ ሣይሰጥ በዝምታ ማለፈ የወንጀል ህግ አንቀጽ 346 እና የወንጀል ህግ አንቀጽ 98ን የሚጥስ መሆኑን በመጥቀስ በሰፉው የሚያቀርበውን ክርክር በሥር ፍርድ ቤት ባቀረበው የቅጣት አስተያየትና የውሣኔ ሃሣብ በማንሣት እንዲልተከራከረ በመቅረፀ ድምፅ ከተቀዲው የአመልካች የቅጣት አስተያየትና የውሣኔ ሃሣብ ለመገንዘብ ችለናል።
የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ላይ የጥፊተኝነት ውሣኔ ከሰጠ በኃላ አመልካች የቅጣት አስተያየትና የውሣኔ ሃሣቡን እንዱያቀርብ እድል ሲሰጠው ፍርድ ቤቱ ተጠሪን ሉያርምና ሉያስተምር የሚችል የቅጣት ውሣኔ እንዱሰጥለት የጠየቁ መሆኑንና በተጠሪ ሱቅ ውስጥ የተገኙ የውጭ ገንዘቦች እንዱወረሱ ውሣኔ እንዱሰጥለት የጠየቁ መሆኑን በተጠሪ ሱቅ ውስጥ የተያዘው የኢትዮጵያ ገንዘብ እንዱወረስ ያቀረበው የቅጣት አስተያየትና የውሣኔ ሃሣብ እንደላለ ተገንዘበናል። በተቃራኒው አመልካችን በመወከል ለችልቱ የቅጣት አስተያየትና የውሣኔ ሃሣብ ያቀረቡት ዐቃቤ ሕግ በተጠሪ ሱቅ ውስጥ የተያዙት የውጭ ገንዘቦች እንዱወረሱ ያቀረቡት የውሣኔ ሃሣብ እንደተጠበቀ ሆኖ የመወረስ ትዕዛዙ በተጠሪ ሱቅ የተያዘውን የኢትዮጵያ ገንዘብን የማይጨምር መሆን እንዲለበት በግልፅ አስተያየትና የውሣኔ ሃሣብ ያቀረበ መሆኑን ችልቱ በትዕዛዝ አስቀርቦ ከሰማውና በመቅረፀ ድምፅ የተቀረፀው የቅጣት አስተያየትና ይህንን አሰተያየት በፅሐፍ በመገልበጥ በሥር ፍርድ ቤት መዝገብ ጋር ከተያያዘው ሰነድ ተገንዝበናል።
አመልካች በወንጀል ክሱ በኤግዚቢትነት ዘርዝሮ ያቀረበውና ከተጠሪ የንግድ ሱቅ ውስጥ የተገኘው 1‚275‚159 /አንድ ሚሉዩን ሁለት መቶ ሰባ አምስት ሺህ አንድ መቶ ሃምሣ ዘጠኝ ብር/ ተጠሪ ጥፊተኛ ከተባለበት የወንጀል ድርጊት ጋር ግንኙነት አለው የሚልበትን ምክንያት በመግለፅ ይህ የኢትዮጵያ ገንዘብ እንዱወረስ የውሣኔ ሃሣብና ክርክር በሥር ፍርድ ቤት አላቀረበም።
አመልካች ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው የመውረስ ትዕዛዝ በተጠሪ ሱቅ ውስጥ የተያዘውን የኢትዮጵያ ገንዘብ እንዱጨምር ክርክር የማያቀርብ መሆኑን የውሣኔ ሃሳቡን በግልፅ አስመዝግቧል አመልካች የተጠሪ ሱቅ ውስጥ የተያዙት የውጭ ገንዘቦች እንዱወረሱና የኢትዮጵያ ገንዘብ እንዲይወረስ በግልፅ የቅጣት አስተያየትና የውሣኔ ሃሣብ ከቀረበ በኃላ የሥር ፍርድ ቤት በተጠሪ ሱቅ ውስጥ የተያዘው የኢትዮጵያ ገንዘብ እንዱወረስ ውሣኔ ሣይሰጥ አልፍብኛል በማለት ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትና ለሰበር ችልት ያቀረበው ክርክር ምንም አይነት የህግ መሰረት የላለውና በሙግት ሂደት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ አሰጣጥ ሂደት ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን ነፃና ገለልተኛ ሆነው የመምራት የመመርመርና የመመዘንና ውሣኔ የመስጠት ህገመንግስታዊ ሃላፉነት ያለባቸው መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ክርክር ባለመሆኑ አልተቀበልነውም።
የአገሪቱን ህዝብና የፋዳራለን መንግስት በመወከል በጉዲዩ ተከራካሪ ሆኖ የቀረበው አመልካች በክስ መከፈትና በመሰማት ሂደት ያለበት ግዳታና ሃላፉነት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 136 ንዐስ አንቀጽ 1 የተደነገገ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የጥፊተኝነት ውሣኔ ከመስጠቱ በፉት ሉፈፅመው ስለሚገባው ተግባር በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 148 ንዐስ አንቀጽ 1 ተደንግጓል። በተመሳሳይ ሁኔታ ፍርድ ቤቱ የጥፊተኝነት ውሣኔ ከሰጠ በኃላ አመልካች ፍርድ ቤቱ ቅጣት ከመወሰኑ በፉት ሉመረምራቸው አስፈላጊም ከሆነ በማስረጃ አረጋግጦ ውሣኔ ላሰጥባቸው የሚገቡ ነጥቦችና ክርክሩን ሉያስረደለት የሚችለ ማስረጃዎችን በመዘርዘር የቅጣት አስተያየትና የውሣኔ ሃሣብ የማቅረብ ሃላፉነት እንዲለበት በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 149 ንዐስ አንቀጽ 3 ተደንግጓል።
የሥር ፍርድ ቤት አመልካች በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 149 ንዐስ አንቀጽ 3 መሰረት ያቀረበውን የቅጣት አሰተያየትና የውሣኔ ሃሣብ ከተቀበለና ተጠሪም የአመልካችን የቅጣት አሰተያየት የውሣኔ ሃሣብ መሰረት በማድረግ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 149 ንዐስ አንቀጽ 4 ያቀረበውን ክርክር ከተቀበለ በኃላ ጉዲዩን ነፃና ገለልተኛ ሆኖ በመመዘን በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 149 ንዐስ አንቀጽ 5 መሰረት ውሣኔ ሰጥቷል። በመሆኑም አመልካች በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 149 ንዐስ አንቀጽ 3 መሰረት ግልፅ ክርክርና የውሣኔ ሃሣብ ያላቀረበበትን በተቃራኒው በተጠሪ ሱቅ ውስጥ የተያዘው የኢትዮጵያ ገንዘብ እንዱወረስ ክርክር የማያቀርብ መሆኑን በግልፅ አስተያየቱን ያስመዝገበበትን ጉዲይ የኢትዮጵያ ገንዘብ እንዱወረስ የሥር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በዝምታ አልፍብኛል በማለት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ከላይ የተደነገጉትን የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ያላደረገና አመልካች ለሥር ፍርድ ቤት በተጠሪ ሱቅ ውስጥ ስለተገኘው የኢትዮጵያ ገንዘብ ያቀረበውን የውሣኔ ሃሣብ ትክክለኛ ይዘት የማያንፀባርቅ ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪ ሱቅ ውስጥ የተያዙት የውጭ አገር ገንዘቦች ብቻ እንዱወረሱ የሰጠው ውሣኔ በወንጀለኛ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 149 ንዐስ አንቀጽ 3 መሰረት አመልካች ያቀረበውን የቅጣት አስተያየትና የውሣኔ ሃሣብ መሰረት ያደረገና ምንም አይነት የህግ ስህተት ያልተፈፀመበት ነው።
ስለሆነም ይግባኝ ሰሚው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ሀምላ 24 ቀን 2001 ዓ.ም የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል ይፃፍ።
ከበታች ፍርድ ቤቶች የመጡትን መዝገቦችና ከሥር ፍርድ ቤት የመጣው ካሴት ይመለስ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.