No summary available.
ታህሳስ 26 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገብረሥላሴ ብርሀኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ጌቱ ብርሀኑ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- የፋዳራል ዐቃቤ ህግ - ወርቅነህ ዘነበ ቀርበዋል።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የበታች ፍርድ ቤት የሰጡት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ስላመለከቱ ነው። የክርክሩ መነሻ ተጠሪ አመልካች በወንጀል ህግ አንቀፅ 543 ንዐስ አንቀፅ 2 የተመለከተውን በመተላለፍ ግንቦት 22 ቀን 1998 ዓ.ም ከጧቱ ሁለት ሰዓት የንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀበላ 02/03 የሰላዲ ቁጥር 3-17408 አ.አ የጭነት መኪና ከአየር ጤና ወደ ቃሉቲ አቅጣጫ በማሽከርከር ላይ እንዲለ ገብሬል ቤተክርስቲያን ፉት ለፉት ሲደርስ ከመኪናው ላይ አሣፍሮት የነበረው ታምራት ሰማኸኝ ከመኪናው ወድቆ በመሞቱ በቸልተኝነት የሰው መግደል ወንጀል ፈፅሟል በማለት ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ነው። አመልካች ጥፊተኛ አይደለሁም ብል በመከራከሩ ተጠሪ ሁለት ምስክሮች አቅርቦ አሰምቷል።
የተጠሪ ምስክሮች ሟች አመልካች የቆመለት መስልት ለመውረድ ሲሞክር አመልካች መኪናውን በማሽከርከሩ ሟች ወድቆ የሞተ መሆኑንና አመልካች ከላይ የተጫነው ሰው ሁኔታ በስፕኬ ሣያይና ሣያረጋግጥ ማሽከርከሩ በሙያው ማድረግ የሚገባውን ጥንቃቄ ያላደረገ መሆኑን ያሳያል በማለት መስክረዋል። አመልካች የመከላከያ ማስረጃ የላለው መሆኑን ለሥር ፍርድ ቤት አረጋግጧል።
የሥር ፍርድ ቤት አመልካች የወንጀል ህግ አንቀፅ 543 ንዐስ አንቀፅ 2ን በመተላለፍ በቸልተኝነት የሰው መግደል ወንጀል የፈፀመ ጥፊተኛ ነው በማለት አመልካች በአንድ ዓመት ከሶስት ወር ቀላል እስራትና በብር 4500 መቀጮ እንዱቀጣ ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረበ ቢሆንም ይግባኝ ሰሚው ችልት የአመልካችን ይግባኝ አልተቀበለውም።
አመልካች ጥር 10 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የተጠሪ ምስክሮች ቃል በአይናቸው ያረጋገጡት ፍሬ ጉዲይን የመሰከሩ ሳይሆኑ የራሳቸውን ሀሳብ የገለፁ ናቸው። አመልካች ሟችን በሚያሽከረክረው መኪና ላይ አልጫነም ሀላፉነት ወስጄ ያልጫንኩትን ሰው ህይወት ደህንነት ጥንቃቄ ላደርግ አልችልም ስለዚህ የአመልካች ድርጊቱ በወንጀል ህግ አንቀፅ 543 ንዐስ አንቀፅ 2 የሚሸፈን አይደለም። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩለ ሟች ተጠሪ ሲያሽከረክረው ከነበረው መኪና ላይ ወድቆ የሞተ መሆኑን በማስረጃ አስረድተናል።
አመልካች ሟችን አለመጫኑን በመከላከያ ማስረጃ አላረጋገጠም። የአመልካች አድራጎት የትራንስፕርት ደንብ ቁጥር 279/56ን የሚጥስና በሙያው ማድረግ የሚገባውን ጥንቃቄ ባለማድረጉ የሟች ህይወት ለህልፈት የበቃ መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ ውሣኔው መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች በፈፀመው ጥፊት የሆነ ቸልተኝነት ከሚያሽከረከረው መኪና ላይ አሣፍሮት የነበረው ሟች ታምራት ሰማኸኝ የሞት አደጋ የደረሰበት መሆኑን ተጠሪ በቂ ማስረጃ በማቅረብ ያረጋገጠ መሆኑን ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው የከፍተኛው ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። አመልካች የተጠሪን ማስረጃ ለመከላከል ያቀረበው ማስረጃ የለም። በመሆኑም አመልካች የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ፍሬ ጉዲይ በማጣራትና ማስረጃ በመመዘን ሂደት ፈፅመውታል የሚለውን ስህተት ይህ ሰበር ችልት እንዱያርምላቸው ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ለሰበር ችልት በህገ መንግስቱ አንቀፅ 80 ንዐስ አንቀፅ 3(ሀ) እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 የተሰጠውን ሥልጣን ከግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ በመሆኑ አልተቀበልነውም። አመልካች ከመኪናው ላይ አሳፍሮት የነበረው ሟች ከመኪናው እየወረደ እያለ መኪናውን ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ በማሽከርከሩ ሟች ከመኪናው ላይ ወድቆ ለህልፈት የተዲረገ መሆኑን በሥር ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። ስለሆነም የአመልካች አድራጎት በወንጀል ህግ አንቀፅ 543 ንዐስ አንቀፅ 2 የተደነገገውን መሥፈርት የሚያሟላ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጡት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ በወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ 195(1/ለ-2) መሰረት ፀንቷል።
ውሣኔው የፀና መሆኑን አውቆ ተከታትል እንዱያስፈፅም ለአዱስ አበባ ማረሚያ ቤቶች አስተዲደር ይፃፍ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.