No summary available.
ህዲር 28 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ሉዊዛ ፍርቤታ የቀረበ የለም።
ተጠሪ፡- ዓቃቤ ህግ የቀረበ የለም።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የዋስትና መብት ይከበርልኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ በአመልካችና በላልች ሦስት ግለሰቦች ላይ በመሰረተው የወንጀል ክስ ነው። ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ከቀጠለ በሁዋላም አመልካች የተከሰሱበት የወንጀል ጉዲይ የዋስትና መብት የማይከለክል በመሆኑ የዋስትና መብታቸው ተከብሮላቸው ቆይቷል። ከዚህ በሁዋላም ዓቃቤ ሕግ የተፈቀደውን የዋስትና መብት ሉያስነሳ የሚችል አዱስ ነገር መገኘቱን ገልጾ ለአመልካች የተከበረላቸው የዋስትና መብት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 74 መሰረት እንዱነሳ አመልክቷል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ሲመለከት የነበረው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ጉዲዩን ተመልክቶ ለአመልካች የተከበረላቸውን የዋስትና መብት የሚያስነሳ ፍሬ ነገር ተገኝቷል የሚል ምክንያት በመያዝ ቀድሞ የሰጠውን ትዕዛዝ በመቀየር የአመልካችንና የላልችን ተከሳሾች የዋስትና መብት ነፍጓል። ከዚህም በኋላ አመልካችና ላልች አብሯቸው የተከሰሱና የዋስትና መብት በማክበር የተሰጠው ትዕዛዝ የተነሳባቸው ሰዎች ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት በድጋሚ የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሮ የዋስትና መብት ተከብሮላቸዋል። ከዚህም በኋላ አቃቤ ሕግ አመልካችና ላልች አብሯቸው የተከሰሱ ሰዎች የዓቃቤ ህግ ምስክር የሆነውን ሰው ላላ ሰው ልከው አስፈራርተዋል፣ የዋስትና መብት በማክበር የተሰጠው ትዕዛዝ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 74 መሰረት ተነስቶ ጉዲያቸውን ማረሚያ ቤት ሁነው እንዱከታተለ ሲል ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቤቱታውን አቅርቧል። ፍርድ ቤቱም ተስፈራራ የተባለውን የዓቃቤ ህግ ምስክር በችልት አስቀርቦ በመስማትና ምስክሩ በጉዲዩ ላይ በተከሰሱ ሰዎች መስፈራራቱን መመስከሩን በማረጋገጥ ቀድሞ የአመልካችን የዋስትና መብት በማክበር የሰጠውን ትዕዛዝ በማንሳት ጉዲያቸውን በማረሚያ ቤት ሁነው እንዱከታተለ ሲል ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ነሐሴ 2ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በጻፈት ሁለት ገፅ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- ተስፈራራ የተባለው የአቃቤ ሕግ ምስክር አመልካች በላኩት ሰው የተስፈራራ ስለመሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የዋስትና መብቱ አዱስ ነገር ተገኝቷል ተብል መነሳቱ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው ነው ተብል በመታመኑ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ ሕዲር 13 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም. በተጻፈ ማመልከቻ መልሱን ሰጥቷል። በመልሱም ላይ የአመልካች የሰበር አቤቱታ የቀረበው ሥነ-ሥርዓቱን ጠብቆ ያለመሆኑንና የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ትእዛዝ በማስረጃ በተረጋገጠ ፍሬ ነገር ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልፆ የአመልካች አቤቱታ ውድቅ እንዱሆን ተከራክሯል። የአመልካች ጠበቃ በበኩላቸው ተስፈራራ የተባለው የዓቃቤ ሕግ ምስክር በዋናው ጉዲይ ላይ የምስክርነት ቃለን ሰጥቶ ያበቃ መሆኑን በመጨመር የሰበር አቤቱታቸውን አጠናክረው ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ሰበር ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ሥነ ሥርዓቱን ጨርሶ የቀረበ መሆን ያለመሆኑን ስንመለከተው የአመልካች የዋስትና መብት መጀመሪያ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከተሰጠ በኋላ አዱስ ነገር ተገኝቷል በሚል ምክንያት በአቃቤ ሕግ አቤቱታ አቅራቢነት በስር ፍርድ ቤት ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን በዚህ ትዕዛዝ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው የስር ፍርድ ቤት የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 74 ድንጋጌን መሰረት በማድረግ የሰጠውን ትዕዛዝ የተሻረ ቢሆንም አቃቤ ህጉ ለዚሁ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አዱስ ነገር ተገኝቷል በሚል በድጋሚ የአመልካች የዋስትና መብት እንዱነሳ አመልክቷል። ፍርድ ቤቱም ምስክር ሰምቶ በአቃቤ ሕግ በኩል የተገለጸው ፍሬ ጉዲይ በማስረጃ መረጋገጡን በመያዝ የአመልካችን የዋስትና መብት በማክበር የሰጠውን ትዕዛዝ አንስቶታል። ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው በውጤት ደረጃ ሁለቱም የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ትዕዛዝ ተመሳሳይ መሆኑን ነው።
በመሆኑም ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ መቅረቡ ሥነ ሥርዓቱን ሳይጠብቅ ነው ለማለት የሚያስችል ባለመሆኑ በዚህ ረገድ ተጠሪ ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት ያለው ሁኖ አለተገኘም።
አመልካች የተከሰሱበት የወንጀል ድርጊት የዋስትና መብት የማይከለከል ሲሆን የዋስትና መብታቸው ከተከበረላቸው በኋላ ሉከለከል የቻለው የዓቃቤ ሕግ ምስክርን በልላ ሰው አስፈራርተዋል በሚል ምክንያት ነው። ዋስትና የተፈቀደለት ሰው በዋስ ከወጣ በኋላ አዱስ ነገር ከተገኘ ፍርድ ቤቱ በማናቸውም ጊዜ ቢሆን በስልጣኑ ወይም በማናቸውም ባለጉዲይ አመልካችነት በዋስትና ወረቀት የተለቀቀው ሰው የተለቀቀበትን ሁኔታዎች (ግዳታዎች) እንደገና ተመልክቶ የተለቀቀው ሰው አዱስ ዋሶችን እንዱያመጣ ወይም በማረፉያ ቤት እንዱቆይ ለማዘዝ የሚቻል ስለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 74 ድንጋጌ በግልፅ ያሳያል። የአመልካችን የዋስትና መብት በማክበር የተሰጠው ትእዛዝ በስር ፍርድ ቤት እንደገና የታየውም በአቃቤ ሕግ ምስክር ላይ የማስፈራራት ተግባር ፈፅመዋል በሚል ምክንያት ነው። ምስክሩ የተስፈራራ ስለመሆኑ ደግሞ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አረጋግጧል። በዚህ ረገድ የአመልካች ጠበቃ አጥብቀው የሚከራከሩት ምስክሩ በአመልካች በቀጥታ ወይም አመልካች ራሳቸው በላኩት ሰው ስለመስፈራራቱ አልተረጋገጠም በሚል ነው። ይሁን እንጂ ይኸው የአመልካች ጠበቃ ክርክር የፍሬ ነገር ክርክር ሲሆን ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያለው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያረጋገጠው ሲሆን ይህ ሰበር ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕግ መንግስት አንቀፅ 8ዐ(3(ሀ)) እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 1ዐ መሰረት የተሰጠው ስልጣን ፍሬ ነገርን የማጣራት ወይም ማስረጃን መመዘን ባለመሆኑ በዚህ ችልት ላታይ የሚገባው አይደለም። በመሆኑም በዚህ ረገድ የአመልካች ጠበቃ ያቀረቡትን ክርክር አልተቀበልነውም። በዚህም መሰረት የአቃቤ ሕግ ምስክር መስፈራራቱ ከተረጋገጠ ምክንያቱ እንደአዱስ ነገር መገኘት የሚታይ ሲሆን የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 67(ለ) እና (ሐ) ድንጋጌዎች መንፈስ ጋር ተዲምሮ ሲታይ ለአመልካች የተከበረውን የዋስትና መብት እንደገና ለማንሳት የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት ነው። ስለሆነም በዚህ ረገድ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት የሚያስችል ምክንያት የለም።
ላላው የአመልካች ጠበቃ በዚህ ችልት በመልስ መልሳቸው ላይ ያነሱት ክርክር ተስፈራራ የተባለው ምስክር በጉዲዩ ላይ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተው ጉዲዩ አብቅቷል የሚለው ሲሆን ይህ ነጥብ በዚህ ችልት የተነሳ አዱስ ነጥብ ሲሆን ችልቱ መመርመር ያለበት የስር ፍርድ ቤቶችን የውሳኔ ግልባጭ መሰረት በማድረግ በሕግ አተረጓጎም ወይም አተገባበር ረገድ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት መኖሩ ሲረጋገጥ ከመሆኑ አኳያ ሲታይ የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት ለማለት የሚያስችል የክርክር ነጥብ አይደለም። የአመልካች ጠበቃ ተስፈራራ የተባለው ምስክር በጉዲዩ ላይ መስክሮ ጉዲዩ አብቅቷል የሚለ ከሆነም አዱስ ነገር መገኘቱን መሰረት በማድረግ የዋስትና መብቱን ለከለከለው ፍርድ ቤት ጥያቄአቸውን ከሚያቀርቡና በሚሰጠው ትእዛዝም ቅሬታ ካላቸውም ተዋረደን ጠብቀው የይግባኝ ቅሬታቸውን ወይም የሰበር አቤቱታቸውን ከሚያቀርቡ በስተቀር በዚህ ችልት ጉዲዩን ለማየት የሚያስችል ሁኖ አልተገኘም። በአጠቃላይ ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶች በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ትዕዛዝ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 72(2) መሰረት ፀንቷል።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.