No summary available.
ኀዲር 15 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡-
አቶ አያላው ተሰማ ጠበቆች፡-
አቶ ጌታቸው አጎናፍር 1. ታምሩ ወንድምአገኘሁ ቀረቡ።
ዶ/ር መሐሪ መኮንን 2. ደሣለኝ ዓለሙ ቀረበ።
ገ/እግዚአብሓር ተስፊዬ ቀረበ።
ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዓቃቤ ሕግ
እሸቱ ወ/ሰማያት
ወንድወሰን ደሣለኝ ቀረቡ።
አውግቸው ክብረት **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሟል በሚል የቀረበውን ክስ ተከትል የተነሣውን የዋስትና ጥያቄ የሚመለከት ነው። በጉዲዩ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሣሽ የሆነው የተጠሪው ባለሥልጣን ዓቃቤ ሕግ በአመልካቾች ላይ ክስ መስርቷል። በአሁኑ 1ኛ አመልካች ላይ አስራ አንድ ክሶች በሁለተኛ አመልካች ላይ አምስት ክሶች በአራተኛ አመልካች ላይ ስድስት ክሶች መመስረታቸውን የሥር ፍርድ ቤት ብይን ይገልፃል። አመልካቾች የዋስትና ጥያቄ ያቀረቡት በክሶቹ የተመለከቱት የወንጀል ድርጊቶች የዋስትና መብት የሚያስነፍጉ አይደለም በማለት ሲሆን ዓቃቤ ሕግ ደግሞ ይህንኑ የአመልካቾችን ጥያቄ የተቃወመው በአመልካቾች ላይ የተመሰረተው ክስ ከአስራ አምስት ዓመታት በላይ ሉያስቀጣ ይችላል፤ አመልካቾች በዋስ ቢለቀቁ ግዳታቸውን አክብረው ፍርድ ቤት አይቀርቡም ላላ ወንጀል ሉፈጽሙ ይችላለ፤ ምስክሮችን በመግዛት ወይም በማባበል ወይም አስረጂ የሚሆኑበትን ያጠፊ ይሆናል በሚለ ምክንያቶችና የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 63፣ 67/ሀ/፣ /ለ/ እና /ሐ/ በዋቢነት በመጥቀስ ነው። ከዚህም በኋላ የሥር ፍርድ ቤት ከሁለቱም ወገኖች የቀረበውን ክርክር መርምሮ አመልካቾች የተከሰሱባቸው የወንጀል ክሶች ከባድ ተደራራቢ በመሆናቸው አመልካቾች የዋስትና መብታቸው ቢከበርላቸው ግዳታቸውን ሉያከብሩ ይችላለ የሚል እምነት ሉያሳድሩ የሚችለ አይደለም የሚል ምክንያት በመስጠትና የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 67/ሀ/ን ብቻ በዋቢነት በመጥቀስ የአመልካቾችን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አድርጓል። በዚህ ውሣኔ አመልካቾች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
እኛም የአመልካቾች ጠበቆች ሰኔ 3ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. ጽፈው ያቀረቡትን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን በጽሁፍ እንዱያደርጉ አድርገናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው የአመልካቾችን የዋስትና ጥያቄ የሥር ፍርድ ቤት ውድቅ ሲያደርግ በምክንያትነት የያዛቸው ነጥቦች በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 67/ሀ/ ሥር የተመለከተውን ነጥብ የማቋቋሚያ ነጥብ መሆን አለመሆናቸውን ለመመርመር ሲባል ነው። በመሆኑም በዚህ ረገድ የአመልካቾች ጠበቆች እና ዓቃቤ ሕግ ያቀረቡትን የጽሁፍ ክርክር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ ተመልክተናል።
የሥር ፍርድ ቤቶች በአመልካቾች ላይ የተጠቀሱባቸው ድንጋጌዎች በራሳቸው ዋስትና የሚከለክለ አለመሆናቸውን የተቀበለት ጉዲይ ነው። ይህ በመሆኑም አመልካቾች ዋስትና ይፈቀድ ዘንድ ክሱን ለሚያየው ፍርድ ቤት ጥያቄ /አቤቱታው/ አቅርበዋል።
በመሰረቱ የዋስትና መብት በሕገ መንግሥት ጥበቃ ከተደረጉለት የተያዙ ሰዎች መሰረታዊ መብቶች አንደ ነው። የኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 19/6/ ሥር የተያዙ ሰዎች በዋስትና የመፈታት መብት ያላቸው መሆኑን በመርህ ደረጃ ያስቀመጠ ሲሆን ይህ በሕገ መንግሥቱ የተከበረው ‛መሰረታዊ“ መብት ሉነፈግ፣ ሉገደብ ወይም በቂ የሆነ የዋስትና ማረጋገጫ እንዱቀርብ የሚደረገውም አግባብነት ባላቸው ላልች ዝርዝር ሕጎች መሰረት በልዩ ሁኔታ ስለመሆኑ ይኸው የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ በግልጽ ያሳያል። በመሆኑም የዋስትና መብት መሰረታዊ የሆነ ሕገ መንግሥታዊ መብት ቢሆንም ፍጹም መብት ሳይሆን በሕጉ አግባብ ሉነፈግ የሚችል ነው። ስለሆነም የዋስትናው ጥያቄ ተቀባይነት አለው? ወይስ የለውም? የሚለው ላይ ውሣኔ የሚሰጠው ፍርድ ቤት እንደመሆኑ መጠን በዚህ ረገድ አግባብነት ያለውን ልዩ ሕግ መሰረት አድርጎ ጉዲዩን ሉመዝነውና ተገቢውን ውሣኔ ላሰጥ እንደሚገባ ግልጽ ነው።
በያዝነው ጉዲይ አመልካቾች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ የተስተናገደው በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 67 መሰረት ነው። ይህ ድንጋጌ በዋስትና ወረቀት የመለቀቅ ማመልከቻ ለመቀበል የማይቻልባቸውን ሁኔታዎችን አስቀምጧል። የሥር ፍርድ ቤቶች የአመልካቾችን የዋስትና ጥያቄ ያልተቀበለት በተጠቀሰው ድንጋጌ ፉደል ‛ሀ“ ሥር የተመለከተውን ሁኔታ በመጥቀስ ነው። በእርግጥም ድንጋጌው በዋስትና ወረቀት የተመለከቱትን ግዳታዎች አመልካቾች የሚፈጽሙ የማይመስለ እንደሆነ ጥያቄውን ውድቅ ለማድረግ እንደሚቻል ያሳያል። እዚህ ላይ ሉስተዋል የሚገባው ዋናው ጉዲይ ግን ድንጋጌውን በመተግበር ረገድ ፍርድ ቤቱ ግንዛቤ ውስጥ ሉያስገባው የሚገባው ምክንያት ምንድነው? የሚለው ነው። ፍርድ ቤቱ ዋስትናውን ለመከልከል ግምቱን መነሻ የሚያደርግባቸው ሁኔታዎች በተጠቀሰው ድንጋጌ በግልጽ አልተመለከቱም። እንዱህ ከሆነ አንድ ተከሣሽ የዋስትና መብት ቢከበርለት ግዳታውን የሚፈጽም የማይመስል ነው ተብል ግምት የሚወስደው በቂና ሕጋዊ ሉባለ በሚችለ ምክንያቶች ላሆን ይገባል ተብል የሚታመን ሲሆን ምክንያቶች በቂና ሕጋዊ ናቸው የሚለው ጉዲይ ከተለያዩ ከባባዊ ሁኔታዎችና ከጉዲዩ ልዩ ባሕርይ አንፃር ፍርድ ቤቱ ሉገነዘበው የሚችለው ነጥብ ነው ተብል የሚታሰብ ነው።
የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 67 ድንጋጌ አቀራረጽና ይዘት በጠቅላላው ሲታይ ፍርድ ቤት የዋስትና መብትን የሚነፍግባቸውን ሁኔታዎች የሚያስገነዝብ ሲሆን ምክንያቶቹን ፍርድ ቤቶች ከተለያዩ ሁኔታዎች አንፃር እየተመለከቱ ሉመዝኗቸው የሚገባቸው ናቸው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካቾችን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ያደረጉት በዋስትና ቢወጡ የዋስትናውን ግዳታ አክብረው ይገኛለ ለማለት የሚቻል አይደለም በሚል ምክንያት ነው። ይህ ግምት መሰረቱ በአመልካቾች ላይ የተመሰረቱት የክሶች ብዛትና የወንጀልች ከባድነትና ሉያስከትለ የሚችለት ውጤት ነው። የሥር ፍርድ ቤት ወንጀልቹ ከባድና ተደራራቢ መሆናቸውን ለግምቱ መነሻ አድርጓል። ፍርድ ቤቱ በእነዚህ ምክንያቶች ላይ በመመስረት ዋስትናውን ነፍጎአል። ይህን ምክንያት ለግምቱ መነሻ እንዱያደርግ ደግሞ በሕጉ የተከለከለ ነው ለማለት አይቻልም። ሕጉ ለፍርድ ቤቱ ስልጣን የሰጠው ስለመሆኑ የሚታመን ከሆነ የሥር ፍርድ ቤት ሕጋዊ ምክንያት መሰረት ሳያደርግ ውሣኔ የሰጠ መሆኑ ሉረጋገጥ ይገባል። ይህ ሰበር ችልትም በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 8ዐ/3/ሀ/ እና አዋጅ ቁ
No topics extracted.