No summary available.
ህዲር 3ዐ ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገብረሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥለጣን - ግርማ ወልደማሪያም ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ እየሩሣላም ወንዳ ጠበቃ አቶ የሺጥላ አሰፊ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት አመልካች ስለጠየቁ ነው። አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ተከሣሽ ተጠሪ ከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል።ተጠሪ ከአሜሪካን አገር ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ 12,5ዐዐ የአሜሪካን ድላር ይዘው የመጡ መሆኑን በዳክራላሪስዮን ቁጥር ሲ-5-7119 ሐምል 29 ቀን 1999 ዓ.ም እንዲስመዘገቡ ገልፀው ጥቅምት 14 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ወደደባይ ሉሄደ ሲለ 25ዐዐ የአሜሪካን ድላር ብቻ የመለሱልኝ ሲሆን 1ዐ,ዐዐዐ የአሜሪካን ድላር አስቀርተዋል። ስለዚህ ድላሩን በአይነቱ ወይም በኢትዮጵያ ብር ምንዛሬ እንዱከፍል በማለት ክስ አቅርቧል። አመልካች አንድ ኢትዮጵያዊ ከ45 ቀናት በላይ የውጭ ገንዘብ መያዝ አይችልም ለጊዜያዊ ጉብኝት የመጣ ሰው ቢሆንም እንኳን ያመጣውን የውጭ ምንዛሬ ይዞ እንዱወጣ የሚፈቀድለት በአንድ መቶ ሰማኒያ ሶስት ቀናት ውስጥ ነው በማለት ተከራክሯል። የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ 1ዐ,ዐዐዐ የአሜሪካን ድላር ይዘው እንዲይወጡ መከልከለ ተገቢ ነው ሆኖም ድላሩን በኢትዮጵያ ብር መንዝሮ የማይከፍልበት ምክንያት የለም በማለት 1ዐ,ዐዐዐ የአሜሪካን ድላር የካቲት 18 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በነበረው የምንዛሬ ተመን መሰረት በኢትዮጵያ ብር መንዝሮ ከየካቲት 18 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ ፏርሰንት ወለድ ጋር ለተጠሪ እንዱከፍል ወስኗል። አመልካች የይግባኝ ቅሬታ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን የከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኙን በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ለኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣን ቦላ ቅርንጫፍ በላከው መመሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ በጊዜያዊነት ለጉብኝት የመጡ ወይም ለንግድ ወደ አገር ውስጥ የገቡ ሰዎች ለጊዜው በእጃቸው የያዙትን የውጭ ምንዛሬ ለጉምሩክ አስመዝግበው ማስረጃ ከያዙ ለአንድ መቶ ሰማኒያ ሶስት ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ይዘውት የመጡትን የውጭ ምንዛሬ ይዘው ለመውጣት ፈቃድ አያስፈልጋቸውም የሚል በመሆኑ የተጠሪ ድላር የተያዘው በዚህ መመሪያ መሰረት ነው። ስለዚህ የተያዘው ድላር በኢትዮጵያ ብር ተመንዝሮ እንዱከፈላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩላቸው 1ዐ,ዐዐዐ ድላሩን ጉምሩክ በሰጠኝ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ /Temporary Receipt for Deposit/ ገቢ ያደረግሁት በመያዣ ስም መሆኑንና ደረሰኙም ከአንድ መቶ ሰማኒያ ቀን በኋላ እንደማያገለግል ይገልፃል። ስለዚህ አመልካች በሕጋዊ መንገድ አሣውቀው ያስገቡትን ድላር እንዲይወጣ ከሚከለክል በስተቀር የሚወርስበት ሕጋዊ ምክንያት የላለ በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች ብሓራዊ ባንክ ያወጣውን መመሪያ በመጣስ ድላሩን ሉያወጡ ሲለ የተያዘ በመሆኑ የመውረስ ሥልጣን አለን በማለት መልስ ሰጥቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን ተጠሪ ከአሜሪካን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የግል ንብረታቸው የሆነውን 12,5ዐዐ /አሥራ ሁለት ሺህ አምስት መቶ/ የአሜሪካን ድላር አመልካች እንዱያውቀው በዱክራላሲዩን ያስመዘገቡ እና በጊዜያዊ የመያዣ ማስቀመጫ ያስያዙ መሆኑን በግራ ቀኙ ክርክር ተገልፆአል። ተጠሪ ከአሜሪካን አገር ይዘው የመጡትንና ለአመልካች በግልጽ ያሣወቁትን ድላር ከመቶ ሰማኒያ ቀን በኋላ ይዘው ለመውጣት የሞከሩ መሆኑንና አመልካች የብሓራዊ ባንክ ያወጣው መመሪያ ያለ ፈቃድ አንድ ሰው ለንግድ ወይም ለጉብኝት ወደ አገር ይዞት የገባውን ድላር ከመቶ ሰማኒያ ሶስት ቀን በኋላ ይዞ መውጣት የማይፈቀድለት መሆኑን በመግለጽ 1ዐ,ዐዐዐ የአሜሪካን ድላር ተጠሪ ይዘው እንዲይወጡ የከለከለና ድላሩን የያዘ መሆኑን ተገንዝበናል። አመልካች ተጠሪ ለመንግሥት አሣውቀው ይዘው የገቡትን 1ዐ,ዐዐዐ የአሜሪካን ድላር ከአንድ ዓመት ከአራት ወር በኋላ ያለ ብሓራዊ ባንክ ፈቃድ ይዘው መውጣት እንደማይችለ በመግለጽ መከልከለ ተገቢነት ያለው ተግባር ቢሆንም ተጠሪ የውጭ ምንዛሬውን ይዘው የመወጣት መብታቸውን ከሚያጡ በስተቀር ድላሩ በኢትዮጵያ ብር ተመንዝሮ እንዲይሰጣቸውና በሕጋዊ መንገድ ከአገራቸው ይዘውት የመጡትን ገንዘብ እንዲይጠቀሙ የሚያደርግ የወንጀል ተግባር ያልፈፀሙ በመሆኑ ገንዘቡን በኢትዮጵያ ብር ተመንዝሮ እንዱከፈላቸው በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ምንም አይነት የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሣቸው ይቻቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።