No summary available.
ጥቅምት 30 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ኢምራን ጉደሣ አብዱ ጠበቃ ገዛኸኝ ፍቅሬ ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል ዐቃቤ ሕግ አልቀረቡም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ፍርድ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው።
የክርክሩ መሰረታዊ ነጥቦች የፋዳራል ዐ/ሕግ በአመልካች ላይ ያቀረባቸው ሁለት የወንጀል ክሶች ናቸው። ዐቃቤሕግ አመልካች በወንጀል ህግ አንቀጽ 598(2) የተመለከተውን በመተላለፍ ሴቶችን ወደ ውጭ ለመላክ የሚያስችል ህጋዊ ፈቃድ ሣይኖረው ሰኔ 22 ቀን 2001 ዓ.ም በአዱስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ ቀበላ 03/02 ክልል ውስጥ ወ/ሮ መቅደስ ንጉሴን ኩዌት ከሚባል ሀገር በሰራተኝነት እልክሻለሁ ብል ብር 2000 /ሁለት ሺህ ብር/ ተቀብል ልኳት በሣምንት አንድ ቀን ጽዲት ትሰሪያለሽ ተብላ ከተቀጠረች በኋላ ሥራው በጣም ስለከበዲት ወደ አገሯ ለመመለስ ስትጠይቅ ሁለት ወር ከአስር ቀን የነፃነት መብቷ በአንድ ክፍል ውስጥ በመገደብ ሰብዓዊ ክብር አጥታ ለከፍተኛ እንግልት የተዲረገች በመሆኗ ዜጏችን ያለ ፈቃድ ወደ ውጭ የመላክ ወንጀል ፈጽሟል።
እንደዚሁም በሥር ፍርድ ቤት ሁለተኛ ተከሳሽ ከነበረው ሰው ጋር በመሆን በወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1)ሀ እና አንቀጽ 692(1) የተመለከተውን በመተላለፍ በአዱስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከከፈተው ጽ/ቤቱ ውስጥ እነ ሀያት መሐመድ የተባለትን አስራ ሁለት የግል ተበዲዮች ብር 6000 እስከ 6500 ብር ኩዌት ደባይና ሣውዱአርቢያ እልካችዋለሁ በማለት ሀሰተኛውን ነገር እውነት አስመስለው ገንዘብ ተቀብለው የወሰደና የግል ተበዲዮችን ያልላካቸው በመሆኑ የማታለል ወንጀል ፈጽመዋል በማለት ክስ አቀርቧል።
አመልካች የተለያዩ የክስ መቃወሚያዎችን አቅርቦ የሥር ፍርድ ቤት ውድቅ ያደረገበት ሲሆን በሁለቱም ክሶች ወንጀለን አልፈፀምኩም ጥፊተኛ አይደለሁም በማለት ተከራክሯል። ተጠሪ አንደኛውን ክስ ለማስረዲት የግል ተበዲይን ለምስክርነት አስቀርቦ ያስመሰከረ ሲሆን በክሱ የተጠቀሰውን ገንዘብ በመቀበል አመልካችን ወደ ኩዌት አገር እንደላካትና እና አመልካች ከነገሯት በላይ የከበደ ሥር እንድትሰራ ስለተደረገች ይህንኑ ለአመልካች መናገሯን በኋላም መሐመድ ሩሄን የሚባል ኤጀንሲ 475 ድላር ደመወዟን ቀምቶ ሁለት ወር ከአስር ቀን በአንድ ክፍል እንድትቆይ እንዲደረጋትና ነፃነቷን እንዱገደባት በመጨረሻ ቡታ ጋር አፈነዲለሁ ብላ ቢላ ይዛ በመጋበዟ ወደ አገሯ አሳፍረው እንደላኳት የመሰከረች ሲሆን ላልች ሁለት ምስክሮች የምስክሯን ቃል የሚያጠናክር የምስክርነት ቃል እንደሰጡ ከሥርፍርድ ቤት ውሳኔ ተገንዝበናል። ተጠሪ ሁለተኛውን ክስ ለማስረዲት አስራ አንድ ምስክሮችን አቅርቦ ያሰማ መሆኑንና ምስክሮቹም የግል ተበዲዩች እንደሆኑ አመልካችና በሥር ሁለተኛ ተከሳሽ የነበረው የማነ ወይም አሚር ገብረማርያም እያንዲንዲቸው ደባይ ሣውዱአረቢያ ኩዊት እንልካችኋለን በማለት ብር 6000 እስከ 6500 የተቀበላቸው መሆኑን መሥክረዋል። አመልካች የመከላከያ ማስረጃ እንዱያቀርብ የሥር ፍርድ ቤት በሰጠውብይን መሰረት አንደኛውን ክስ በተመለከተ በህግ በተሰጠኝ ፈቃድ ትኬት ቆርጬ ከመስጠት ውጪ የግል ተበዲይን ወደ ውጭ አልላኩም በሁለተኛው ክስ የተመለከተውን ተግባርም ያልፈፀምኩ ስለመሆኔ ያስረዲልኛል በማለት የመከላከያ ምስክሮችን አቅርቦ አሰምቷል።
የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማና ማስረጃቸውን ከመዘነ በኋላ ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበውን ሁለት ክሶች የተጠቀሰውን የወንጀል ተግባር አመልካች የፈፀመ መሆኑን በበቂ ማስረጃ አስረድቷል። የአመልካች የመከላከያ ማስረጃ ታዓማኒነት የላለውና የተጠሪን ክስ የሚያስተባብል አይደለም በማለት አመልካች የወንጀል ህግ አንቀጽ 598(2) እና አንቀጽ 692(1) የተመለከተውን በመተላለፍ ወንጀል የፈፀመ ጥፊተኛ ነው በማለት በአስራ ሁለት ዓመት ጽኑ እስራትና በብር 17,000 /አሥራ ሰባት ሺህ ብር/ እንዱቀጣ ፍርድ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ፍርድ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቧል። የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ ጉድለት የላለበት ነው በማለት ይግባኙን ሣይቀበለው ቀርቷል። አመልካች ሚያዚያ 1 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪ ላቀረበብኝ አንደኛ የወንጀል ክስ በአስር ዓመት ጽኑ እሥራት እንዱቀጣ ወስኖብኛል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት በወንጀል ህግ ቁጥር 598(2) የተመለከተውን በመተላለፍ ጥፊት ፈጽሟል በማለት የሰጠው የጥፊተኛነት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተተ አለበት።
ምክንያቱም የግል ተበዲይ በህይወት ወይም በአካሎ ላይ የደረሰባት ጉዲት ያለ ስለመሆኑ በሰጣቸው የምስክርነት ቃል አልገለፀችም አየር በማይገባበትም ቤት ተቆልፋ ነበር ያለችውም ስልክ እየደወለች ዘመድቿን ታገኝ የነበረ በመሆኑ በህጉ ድንጋጌ የተገለፀውን ፍሬ ጉዲይ ያልተሟላ መሆኑን ያሣያል። ስለዚህ በወንጀል ህግ አንቀጽ 598(1) ጥፊተኛ መባል ሲገባኝ በፍሬጉዲይ ደረጃ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ በወንጀል ህግ አንቀጽ 598(2) ጥፊተኛ ተብዬ የተጣለብኝ ቅጣት መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እነዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩለ የግል ተበዲይ ለሰባ ቀናት በውጪ አገር ሰብዓዊ ክብሯ ተጥሶ በአንድ ክፍል ውስጥ ተቆልፍባት የቆየች መሆኑን የመሰከረች በመሆኑ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 598(2) የተመለከተው ሁኔታ ተሟልቷል ስለዚህ የአመልካች ክርክር የህግ ድጋፍ የለውም በማለት መልስ ሰጥቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች የወንጀል ህግ አንቀጽ 598(2)ን የተላለፈ ጥፊተኛ ነው በማለት የሰጠው የጥፊተኛነት ውሳኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ነጥብ ለማጣራት መዝገቡ ለሰበር ችልት የቀረበ መሆኑን ተገንዝበናል። በፍሬ ጉዲይ ደረጃ አመልካች የተጠሪ አንደኛ ምስክርና የግል ተበዲይ የሆነችው ወ/ሮ መቅደስ ንጉሴ ፈቃድ ሣይኖረው ለቤት ሰራተኛነት ወደ ኩዌት የላከ መሆኑን የግል ተበዲይ ኩዌት ሄዲ ሥራ ከጀመረች በኋላ አሰሪዎቿ ከባድ ሥራ ያለእረፍት እንድትሰራ ያስገደዶት መሆኑን በመጨረሻም ሥራውን ለቅቃ ስትወጣ መሀመድ ሩሄን የሚባል ኤጀንሲ የወር ደመወዟን 475 ድላር በመውሰድ በቂ አየርና ምግብ ልታገኝ በማትችልበት ሁኔታ ለሁለት ወር ከአስር ቀን ነፃነትና መብቷን በመገደብ በአንድ ክፍል ውስጥ እንድትቀመጥ አስገድዶት መሆኑንና በመጨረሻም ከዚህ ክፍል እንድትወጣ የማይፈቀድላት ከሆነ ስሉንደር እንደምታፈነዲ ቢላ ይዛ ስትናገር ወደ አገሯ የላኳት መሆኑን በሥር ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። ይህ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ፍሬጉዲይ በየትኛው የወንጀል ህግ ድንጋጌ በሀላፉነት እንደሚያስጠይቅ ለመወሰን አግባብነት ያላቸውን የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎች ይዘት መመርመር ያስፈልጋል።
እኛም ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 598 ድንጋጌዎች መርምረናል።
ማንም ሰው ፈቃድ ሣይኖረው ወይም በማናቸውም ላላ ህግ ወጥ መንገድ ኢትዮጵጳያዊ ዜጋን ለሥራ ወደ ውጪ አገር የላከ እንደሆነ ከአምስት ዓመት እስከ አስር ዓመት ሉደረስ በሚችል ጽኑ እሥራት እና ከሀያ አምስት ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ እንደሚቀጣ“ የወንጀል ህግ አንቀጽ 598 ንዐስ አንቀጽ 1 ይደነግጋል። በዚህ ድንጋጌ አንድ ሰው ጥፊተኛነህ ተብል የሚቀጣው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 598 ንዐስ አንቀጽ 2 ከተዘረዘሩት የማክበጃ ምክንያት አንደኛው ያልተሟላ ሲሆን መሆኑን ከህጉ ድንጋጌ አንቀጽና ይዘት ለመረዲት ይቻላል።
ሆኖም አንድ ሰው ፈቃድ ሣይኖረው ወይም በማናቸውም ህገ ወጥ መንገድ ወደ ውጭ አገር የላካት ኢትዮጵያዊት ሰብአዊ መብቷ በህይወቷ ወይም በአካሎ ላይ ጉዲት የደረሰባት እንደሆነ ቅጣቱ ከአምስት ዓመት ጽኑ እሥራት እስከ ሀያ አመት የሚደርስ ጽኑ እሥራትና ከሀምሣ ሺ ብር የማይበልጥ መቀጮ እንደሚሆን የወንጀል ህጉ አንቀጽ 598 ንዐስ አንቀጽ 2 ይደነግጋል።
አመልካች የግል ተበዲይዋ በአካሎ ወይም በህይወቷ ላይ የደረሰባት ጉዲት ስለላለ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 598 ንዐስ አንቀጽ 2 ጥፊተኛ መባላ የህግ ስህተት አለበት በማለት ይከራከራል። ሆኖም የወንጀል ህግ አንቀጽ 598 ንዐስ አንቀጽ 2 የተላከችው ‛ኢትዮጵየዊት የሰብአዊ መብቷ በህይወቷ ወይም በአካሎ ላይ ጉዲት የደረሰባት እንደሆነ“ በሚል መንገድ የተደነገገ ሲሆን አጥፉው በዚህ የህግ ድንጋጌ ጥፊተኛ ነው ተብል ፍርድ የሚሰጠው የተላከችው ኢትዮጵያዊት በሰብአዊ መብቷ መደፈር ደርሶባት እንደሆነ ወይም በህይወቷ ላይ ጉዲት የማድረሥ መከራ ተደርጏ እንደሆነ ወይም በህይወቷ ላይ ጉዲት ደርሶባት እንደሆነ ወይም በአካሎ ላይ ጉዲት የማድረስ የሙከራ ወንጀል ተፈጽሞባት ወይም በአካሎ ላይ ጉዲት ደርሶባት እንደሆነ መሆኑን ከህጉ ድንጋጌ ይዘትና አቀራረጽ ለመገንዘብ ይቻላል።
በወንጀል ሕግ አንቀጽ 598 ንዐስ አንቀጽ 2 አንድ ሰው በሀላፉነት የሚጠይቀው ከላይ ከተዘረዘሩት አንደኛው ወደ ውጭ በላካት ኢትዮጵያዊት ላይ መፈፀሙ የተረጋገጠ እንደሆነ ነው።
ከዚህ አንፃር ስናየው የግል ተበዲይ የሆነችው አንደኛ የተጠሪ ምስክር መሐመድ ሩሄን በሚባል ኤጀንሲ በአንድ ክፍል ውስጥ ታግታና የነፃነትና የመንቀሣቀሥ መብቷ ተገድቦ ለሰባ ቀናት የቆየች መሆኑና በዚህም ወቅት ከፍተኛ የሆነ የሥነ ልቦናና የአካል መጎሳቆል ጉዲት ደርሶባት የነበረ መሆኑን ፍሬ ጉዲይ የማጣራት ሥልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። ስለሆነም የግል ተበዲይ በህይወቷ ወይም በአካሎ ላይ ጉዲት የማድረስ ሙከራ ያልተፈፀመባት ወይም ጉዲት ያልደረሰባት ቢሆንም በነፃነት የመንቀሣቀሥና ወደ አገር የመመለስ መብቷ በአንድ የንግድ ድርጅት ለሰባ ቀናት ያህል ተገድቦ በአንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ እንድትቆይ የተገደደችና ሰብአዊ መብቷ የተጣሰ መሆኑ ስለተረጋገጠ የከፍተኛው ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች ተጠሪ ባቀረበው አንደኛ ክስ የተጠቀሰውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 598 ንዐስ አንቀጽ 2 በመተላለፍ ወንጀል የፈፀመ ጥፊተኛ ነው በማለት የሰጡት ፍርድና የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195 (2(-2) መሰረት ፀንቷል።
ፍርድ የፀና መሆኑን በማወቅ ተከታትል እንዱየስፈጽም ለማረሚያ ቤት ይፃፍ።
No topics extracted.