No summary available.
ጥቅምት 30 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የሐረሪ ክልል ዐቃቤ ሕግ - የቀረበ የለም።
ተጠሪ፡- ቦና አህመድ አሚን - የቀረበ የለም።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ እድሜአቸው አስራ ሦስት ዓመት በሆነና አስራ ስምንት ዓመት ባልሞላቸው ልጆች ላይ የሚፈፀም የግብረ ሥጋ ድፍረት በደል ወንጀልን የሚመለከት ነው። ጉዲዩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በሐረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- ተጠሪ ሕዲር 07 ቀን 2000 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 4፡00 ስዓት በሚሆንበት ጊዜ በሐረሪ ክልል በቀበላ 19 ልዩ ስሙ ንደ ጎቤ ተብል በሚጠራ ስፍራ የግል ተበዲይ የሆነችውን የ15 ዓመት ሕፃን ዘሙ አህመድን በመኖሪያ ቤት ውስጥ በር ዘግቶባት መብራት አጥፊቶ አፎንና አፍንጫዋን በማፈን እንዲትጮህ በማድረግ ለመከላከል በማትችልበት ሁኔታ ውስጥ ካደረገ በሁዋላ አስገድድ የግብረ ሥጋ ግንኙነት በመፈፀሙ በ1996 ዓ.ም በወጣው የኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 620 ስር የተመለከተውን ተላልፎል የሚል ነው። የአሁኑ ተጠሪም ክሱ ተነቦለት እንዱረዲው ከተደረገ በሁዋላ በክሱ ላይ ተቃውሞ የላለው መሆኑን ገልጾ ስለድርጊቱ አፈፃፀም ግን የክህደት ቃል ሰጥቷል። ከዚህም በኋላ አቃቤ ሕግ እንደክሱ ያስረደልኛል ያላቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅረቦ ከአሰማ በሁዋላ የስር ፍርድ ቤት አመልካች ከግል ተበዲይ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የፈጸመው በኃይል ተግባር ሳይሆን በግል ተበዲይ መልካም ፈቃድ ስለመሆኑ ተረጋግጧል በሚል ምክንያት ተጠሪን በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 141 መሰረት በነፃ አሰናብቶታል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ከአከራከረ በሁዋላ ተጠሪ የግል ተበዲይ ላይ የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀማቸው በአቃቤ ሕግ ማስረጃዎች መረጋገጡን እንደስር ፍርድ ቤት አባባል ተቀብል ድርጊቱ በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕግ አንቀጽ 620 ስር የሚሸፈን መሆን ያለመሆኑን በጭብጥነት በመያዝ ተጠሪ እድሜው 16 አመት የግል ተበዲይ ደግሞ እድሜዋ 15 አመት መሆኗንና እንደዚህ አይነት ሁኔታ ባጋጠመ ጊዜ ምን መሆን እንዲለበት የወንጀል ሕጉ ምንም የሚሰጠው ምላሽ የላለ መሆኑ በመጥቀስ እና በማመሳሰል ደግሞ ተጠያቂነትን ማስከተል እንደማይቻል ሕጉ በአንቀጽ 2(3) ስር ያስቀመጠው መርህ መሆኑን በዋቢነትይዞ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪን በነፃ በማሰናበት የሰጠውን ውሳኔ በውጤት ደረጃ ተገቢ መሆኑን በመቀበል አጽንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ ውሳኔ ባለመስማማት ነው።
አመልካች አቃቤ ሕግ ሚያዝያ 28 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈው ሦስት ገጽ የሰበር አቤተታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 2(3)፣ 56፣211 እና 626ን እንዱሁም የወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁጥር 113(2) ድንጋጌዎችን መንፈስና ይዘት ያላገናዘበ መሆኑን በመዘርዘር ተጠሪ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 626(1) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ መተላለፈ ተረጋግጧል ተብል እንዱከላከል ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል በመታመኑ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጏለት ቀርቦ መጋቢት 14 ቀን 2002 ዓ.ም በጠበቃው አመካኝነት በተጻፈ ማመልከቻ መልሱን ሰጥቷል። አመልካችም የመልስ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም ተጠሪው የወንጀል ተጠያቂነት የሚከተልበት አይደለም ተብል ከክሱ ነፃ መባለ ሕጋዊ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ እድሜዋ አስራ አምስት አመት ከሆናት ሕፃን ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈፀሙ መረጋገጡን ሁለቱም የስር ፍርድ ቤቶች የተቀበለት ጉዲይ መሆኑን ነው። የተጠሪ ጠበቃ በዚህ ችልት ባቀረቡት የፁሐፍ መልስ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የፈፀመ መሆኑ አልተረጋገጠም በሚል ተከራክረዋል። ሆኖም ይህ ችልት በዚህ ረገድ የበታች ፍርድ ቤቶች የደረሱበትን የማስረጃ ምዘና ድምዲሜ ለመመልከት በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕግ መንግሥት አንቀጽ 80(3)(ሀ) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት ስልጣን የላለው በመሆኑ የተጠሪ ጠበቃ ክርክር ተቀባይነት ያለው ሁኖ አልተገኘም።
ተጠሪ ከግል ተበዲይ ጋር ግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈፀመ በተባለበት ጊዜ እድሜው አስራ ስድስት አመት የነበረ መሆኑ ተረጋግጧል። ከወንጀለ ነፃ ነው የተባለውም የኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 626(1) የግል ተበዲይና የድርጊቱ ፈፃሚ እድሜው በአስራ ሶስት አመትና በአስራ ስምንት አመት ክልል ውስጥ ከሆኑ ሕጉ ምላሽ አይሰጥም በሚል ምክንያት ነው። ይሁን እንጂ የድንጋጌው አቀራረጽ ሲታይ ማንም ሰው ተቃራኒ ጾታ ካላትና እድሜዋ ከአስራ ሦስት ዓመት በላይ ሆኖ አስራ ስምንት ዓመት ካልሞላት ልጅ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የፈፀመ ወይም ይህችው ልጅ እንዱህ አይነቱን ድርጊት ከእርሱ ጋር እንድትፈጽም ያደረገ እንደሆነ በሚል የተቀመጠ ሲሆን ‛ማንም ሰው….የሚለው የሕጉ አገላለጽ የወንጀል ሐላፉነትን በተመለከተ የተደነገጉትን የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎችን ማለትም ከአንቀጽ 48 እስከ 56 ድረስ የተመለከቱትን ግንዛቤ ውሰጥ ባስገባ መልኩ መታየት ያለበት መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 56 ድንጋጌ በተለይም ሲታይም እድሜአቸው ከአስራ አምስት ዓመት በላይ ከ18 ዓመት በታች ያለ ወጣት ወንጀል አድራጊዎች ከተጠያቂነት የሚድኑ አለመሆኑን የሚያሳይ ሆኖ ይገኛል። በመሆኑም ተጠሪ እድሜው ሲታይ ከወንጀል ተጠያቂነት ነፃ የሚሆንበት ህጋዊ ምክንያት የለም በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 626(1) ስር የተቀመጠው ድንጋጌ ትኩረት የሚያደርገው የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም ወይም እንድትፈጽም ማድረግ የወንጀል ተጠያቂነትን ያስከትላል። አስራ ሶስት አመት በሆናትና አስራ ስምንት አመት ካልሞላት ልጅ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ያደረገ ወንድ እድሜው በዚሁ የእድሜ ክልል መገኘት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 211(1) መሰረት ታይቶ የግል ተበዲይን ተጠያቂነት ከማያመጣ በስተቀር ተጠሪን ከወንጀለ ነፃ የሚያደርገው አይደለም። የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽሙ ወንድና ሴት እድሜያቸው በአስራ ሶስት አመትና በአስራ ስምንት አመት መካከል መገኘት ሁለቱንም የወንጀል ተጠያቂነት ያስቀርላቸዋል ብል መደምደም የሕጉ አላማ አይደለም።
በዚህ እድሜ መካከል ያለት ሕፃናት ተገቢ ላልሆነ ድርጊት እንዲይጋለጡ መከላከል የሕጉ አላማ ነው ተብልም ይታመናል። በመሆኑም ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው ፍርድ ቤት የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 2(3)ን የጠቀሰው ያለቦታው ሆኖ አግኝተናል። ተጠሪ እድሜዋ አሥራ አምስት አመት ከሆናት ሕፃን ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀሙ ተረጋጋጧል ከተባለና ድርጊቱ በአቃቤ ሕጉ የክስ ማመልከቻ ስር ከተጠቀሰው ድንጋጌ ያነሰ ሁኖ ከተገኘ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 113(2) መሰረት ተጠሪ ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 56 እና 626(1) ድንጋጌ አንጻር እንዱከላከል መደረግ ነበረበት።
ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪን ሳይከላከል የወንጀል ተጠያቂነት የለበትም በማለት የሰጡት ውሳኔ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 56፣211 እና 626(1) ድንጋጌዎችን ይዘትና መንፈስ እንዱሁም የወንጀል ሕጉን ዓላማ ያላገናዘበ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 195(2)(ሀ) መሰረት ሙለ በሙለ ተሽሯል።
ተጠሪ በ1996ቱ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 626(1) ስር በተመለከተው ሁኔታ ድርጊቱን መፈጸሙን አቃቤ ሕጉ ያስረዲ መሆኑን የበታች ፍርድ ቤቶች የተቀበለት በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ መከላከያ ካለው እንዱያቀርብ አድርጏና ማስረጃዎቹን ሰምቶ ተገቢውን እንዱወሰን በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 195(2(ሀ) መሰረት መልሰንለታል። ይፃፍ።
No topics extracted.