No summary available.
የካቲት 21 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ አሰገደች ዘርጋው ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አየለ ንዲኔ ጠበቃ አቶ ዘነበ አሰፊ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት የሰበር ማመልከቻ ስላቀረቡ ነው። የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረቡት የክስ ማመልከቻ ነው። ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት በከሳሽነት ቀርቦ ተከሳሽ /አመልካች/ መጋቢት 19 ቀን 2000 ዓ.ም በተደረገ የብድር ውል ስምምነት ብር 105‚000 /አንድ መቶ አምስት ሺህ ብር/ ወስደዋል። ተከሳሽ /አመልካች/ የተበደሩትን ገንዘብ እስከ ሰኔ 19 ቀን 2000 ዓ.ም ድረስ ሉከፍለ በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ቅጣት ብር 30‚000 /ሰላሣ ሺህ ብር/ ጨምረው ሉከፍለ ተስማምተዋል። ተከሳሽ የብድር ገንዘቡን በውለ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ያልከፈለ በመሆኑ ብር 135‚000 /አንድ መቶ ሰላሣ አምስት ሺህ ብር/ ከህጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍለ ይወሰንልኝ የሚል ክስ አቅርበዋል። አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በተከሳሽነት ቀረበው ከከሳሽ /ተጠሪ/ ጋር የብድር ውል ያደረግሁ መሆኑ አይካድም። ሆኖም ከሳሽ /ተጠሪ/ ውለን ካስፈረሙኝ በኃላ የውለን ኮፑ ላምጣ ብለው ገንዘቡን ሣይሰጡኝ በመሰወራቸው ጉዲዩን በሽምግልና ስከታተል ቆይቼ አሁን በወንጀል ከስሽ መያዣ ወጥቶባቸዋል። ስለሆነም ከሳሽ /ተጠሪ/ የብድር ውለ ገንዘቡን ተቀብያለሁ ብዬ ከፈረምኩ በኃላ ገንዘቡን ሣይሰጠኝ የተሰወረ በመሆኑ ውለ ፈራሽ ተደርጎ ክሱ ውድቅ እንዱደረግልኝ በማለት መልስ ሰጥተዋል። የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ ተከሳሽ /አመልካች/ ብር 105‚000 በብድር ከከሳሽ /ተጠሪ/ የወሰደ መሆኑን በመግለፅ መጋቢት 19 ቀን 2000 ዓ.ም በተደረገው የብድር ውል ላይ ፈርመዋል። ስለሆነም ተከሳሽ /አመልካች/ በውል ወስጃለሁ ብለው በፅሐፍ ያረጋገጡትን ገንዘብ ተጠሪ /ከሳሽ/ ያልሰጠኝ መሆኑን በሰው ምስክር ላስተባብል በማለት ያቀረቡት ክርክር የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2005/1/ እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2006 ድንጋጌዎችን የሚቃረን በመሆኑ የህግ መሰረት የለውም። ውለ በተንኮል የተደረገ አይደለም ውለ ለሞራልና ለህግ ተቃራኒ አይደለም። ስለሆነም ተከሳሽ /አመልካች/ የተበደሩትን ብር 105‚000 በውለ የተስማሙትን የቅጣት ገንዘብ ብር 30‚000 በድምሩ 135‚000 /አንድ መቶ ሰላሣ አምስት ሺህ ብር/ ከሰኔ 19 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ ፏርስንት ወለድ ጋር ይከፈለ በማለት ወሰኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል አመልካች ነሐሴ 17 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በእኔና በተጠሪ መካከል የተደረገው ውል በተንኮል ላይ የተመሰረተና ተጠሪ ግዳታቸውን ያልተወጡበት ውል ነው። በውለ የተገለፀውን ገንዘብ ያልሰጡኝ መሆኑን በምስክሮች ለማስረዲት ያቀረብኩት ጥያቄ የበታች ፍርድ ቤቶች ውድቅ ማድረጋቸው የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1704 እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2009/1/ን ያላገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩላቸው አመልካችና እኔ ያደረግነው የብድር ውል ገንዘቡን መውሰዲቸውን ያረጋግጣል። አመልካች ተዋዋይ እንጅ ሶስተኛ ወገን ባለመሆናቸው የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2009 በጉዲዩ አግባብነት የለውም። ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች የፍታብሓር ህግ አንቀፅ 2005 እና አንቀፅ 2006ን መሰረት በማድረግ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት በመሆኑ የሰበር አቤቱታው ውድቅ እንዱደረግልኝ በማለት ህዲር 29 ቀን 2003 ዓ.ም በፅሐፍ ባቀረቡት መልስ ተከራክረዋል። አመልካች ታህሣሥ 14 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ የመልስ መልስ ተጠሪ ውለ መፈረሙን እንጂ ውለ መፈፁሙን አላስረዲም። እኔ ውለ ከተፈረመ በኃላ የብድር ገንዘቡን ያለሰጠኝ መሆኑን በማስረጃ ለማስተባበል ያቀረብኩት ጥያቄ አላግባብ ተከልክያለሁ በማለት ተከራክረዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራ ቀኙ ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ብር 105‚000 /አንድ መቶ አምስት ሺህ ብር/ የብድር ገንዘብ ለተጠሪ እንዱከፍለ የሰጡት ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም; የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ብር 30‚000/ሰላሣ ሺህ ብር/ እና ወለድ ለተጠሪ እንዱከፍለ የሰጡት ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለት ጭብጦች መታየት ያለባቸው ሆነው አግኝተናቸዋል።
የአመልካች ክርክር በባህሪው የብድር ውል ስምምነት ሲደረግ ውለ ጉድለት አለበት የሚል ሣይሆን ተጠሪ በብድር ውለ መሰረት የብድር ገንዘቡን አልሰጠኝም በውለ የተገለፀውን ግዳታውን አልተወጣም የሚል ነው። ተጠሪ በበኩላቸው አመልካች የብድር ገንዘቡን የተቀበለ መሆኑን በነፃ ፈቃዲቸው አንብበው ተስማምተው በፊርማቸው ያረጋገጡ መሆኑን መጋቢት 19 ቀን 2000 የተደረገው የብድር ውል አስረጅ ነው። ስለዚህ አመልካች ገንዘብን አልተቀበልኩም በማለት የሚያቀረቡት ክርክር ተገቢ አይደለም በማለት ተከራክረዋል። አመልካችና ተጠሪ መጋቢት 19 ቀን 2000 ዓ.ም ያደረጉት ውል አመልካች በውለ ሰነድ የተገለፀውን ገንዘብ ከተጠሪ ተቀብለው የወሰደ ስለመሆኑ ሙለ እምነት የሚጣልበት በቂ መስረጃ እንደሆነ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2005 ንዐስ አንቀፅ 1 የተደነገገ በመሆኑና አመልካች በብድር ውለ ላይ ከተጠሪ ገንዘብ የተቀበለ መሆኑን የሚገልፀውን ህግ በሰው ምስክር ወይም በህሉና ግምት ማስረጃ በማቅረብ ለማስተባበል እንደማይፈቅድላቸው በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2006 ንዐስ አንቀፅ 2 አስገዲጅ ድንጋጌ የተደረነገገ በመሆኑ አመልካች ገንዘቡን ያልተቀበልኩ መሆኑን በምሰክር እንዲላስረዲ የበታች ፍርድ ቤቶች አላግባብ ከለከለኝ በማለት ያቀረቡት አቤቱታ የህግ መሰረትና ድጋፍ ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
አመልካች በብድር ውለ ገንዘብ እንደተቀበለ የሚገልፀውን ሀይለ ቃል ለመቃወም የሚችለት ተጠሪ ቃለ መሀላ እንዱፈፅም በመጠየቅ እንደሆነ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2006 ንዐስ አንቀፅ 1 ተደንግጓል። አመልካች ተጠሪ ቃለ መሀላ እንዱፈፅምላቸው ያቀረቡት ክርክር ያላለ መሆኑን ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ተገንዝበናል። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካችን ክርክር ውድቅ በማድረግ አመልካች የተበደሩትን ብር 105‚000 /መቶ አምስት ሺህ ብር / ለተጠሪ እንዱከፍለ የሰጡት ውሣኔ ከላይ የተገለፁትን የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገና የህግ ስህተት የላለበት በመሆኑ የአመልካችን አቤቱታ አልተቀበልነውም።
ከላይ ከተገለፀው በተጨማሪ አመልካች በብድር ውለ መሰረት ገንዘቡን በወቅቱ ባለመመለሳቸው መቀጫ ለተጠሪ ብር 30‚000 /ሰላሣ ሺህ ብር/ እንዱከፍለ በወሰኑት የበታች ፍርድ ቤቶች በተደራቢነት አመልካች የዋናውን ብድርና የመቀጫ ገንዘቡ ከሰኔ 19 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ የሚታሰብ ዘጠኝ ፏርሰንት ወለድ እንዱከፍለ የሰጡት ውሣኔ ህጋዊ መሰረት የላለውና የአመልካችና የተጠሪን የብድር ውል ስምምነት መሰረታዊ ይዘትና የሚያስከትለውን ህጋዊ ውጤት ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ለተጠሪ ብር 105‚000 /አንድ መቶ አምስት ሺህ ብር/ የሆነውን የብድር ገንዘብ ብድሩ መመለስ ካለበት ከሰኔ 19 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ ፏርስንት ወለድ ጋር እንዱከፍለ የሰጡት ውሣኔ የህግ ስህተት የለበትም። ሆኖም አመልካች ለተጠሪ መቀጫ ብር 30‚000 /ሰላሣ ሺህ ብር/ ከሰኔ 19 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ ፏርስንት ወለድ ጋር እንዱከፍለ የሰጡት ውሣኔ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2489 ንዐስ አንቀፅ 2 አስገዲጅ ድንጋጌን የሚጥስና መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ነው። በልላ በኩል አመልካች የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2009 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌን በመጥቀስ በብድር ውለ ላይ ገንዘብ ተቀብያለሁ በሚል አገላለፅ የተፃፈው ቃል ሀሰተኛ መሆኑን በምስክር ለማስተባበል ያቀረቡት ጥያቄ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2009 ንዐስ አንቀፅ 1 ይዘትና ተፈፃሚነት ያገናዘበ ሆኖ አላገኘነውም። በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2009 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት በውል ሰነድ የተፃፈን ቃል ሀሰተኛ መሆኑን በማናቸውም አይነት ማስረጃ ለማስተባበል ሰነደን የፃፈው ወይም የተቀበለው የመንግስት መሥሪያ ቤት ባለሥልጣን አለመሆኑን በውለ ላይ የተፃፈውን ቃል ለማስተባበል ጥያቄ ያቀረበው ሰው የውለ ተዋዋይ ሣይሆን ሶስተኛ ወገን ተከራካሪ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚገባ በግልፅ ይደነግጋል።
በያዝነው ጉዲዩ የአመልካችና የተጠሪ ውል በመንግስት መሥሪያ ቤት ባለስልጣን የፃፈው ወይም የተቀበለው ሰነድ አለመሆኑ የተረጋገጠ ቢሆንም በውለ ውስጥ ያለውን ቃል ሀሰተኛነት ለማስተባበል የጠየቁት አመልካች የብድር ውለ ተዋዋይ ወገን እንጂ ሶስተኛ ወገን ተከራካሪ አይደለም። ስለሆነም አመልካች የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2009 ድንጋጌዎችን በመጥቀስ የውለን ቃል ሀሰተኛነት በምስክር ለማስረዲት ያቀረቡት ጥያቄ የህግ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤት ብር 30‚000 /ሰላሣ ሺህ ብር/ መቀጮና ለዚህ የመቀጮ ገንዘብ ከሰኔ 19 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ የሚታሰብ ወለድ አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍለ የሰጡት የውሣኔ ክፍል ብቻ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበትና በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 348 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት ሉሻሻል የሚገባው ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤትና የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ ተሻሽሎል።
አመልካች ብር 105‚000 /መቶ አምስት ሺህ ብር/ ከሰኔ 19 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር ለተጠሪ ይክፈለ በማለት ወስነናል።
አመልካች የመቀጫ ገንዘብ ብር 30‚000 /ሰላሣ ሺህ ብር/ እና ይህ የመቀጫ ገንዘብ የሚወልደውን ወለድ ለተጠሪ የመክፈል ግዳታና ኃላፉነት የለባቸውም ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.