No summary available.
ጥር 13 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ሰሚር ሱሩር - ጠበቃ በፀልት መኮንን ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው። የክርክሩ መነሻ አመልካች ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ነው። አመልካች በአዱስ አበባ በልደታ ክፍለ ከተማ ቀበላ 05/08 በቤት ቁጥር 441 በንግድ ፈቃድ ቁጥር 03/01/3/00/69/95 የሚያካሂደትን የንግድ ድርጅት በብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ተጠሪዎች ጥቅምት 28 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ የውል ሰነድ ሽጠውልኛል ተጠሪዎች ብር 40,000(አርባ ሺህ ብር) በቼክ ተቀብለው ወስደዋል። ቀሪውን ብር 160,000(መቶ ስልሳ ሺህ ብር) የንግድ ድርጅቱን ሽያጭ በውልና ማስረጃ ፈርመውና ባለሀብትነቱን ተጠሪዎች ሲያስተላልፈ ሉከፈላቸው ተስማምተናል። ሆኖም ተጠሪዎች (ተከሳሽ) በውለ መሰረት ለመፈፀም ፈቃደኛ ሣይሆኑ በመቅረታቸው ተከሳሾች (ተጠሪዎች) የሸጡት ድርጅት ከዕዲና ዕገዲ ነፃ አድርገውና ማናቸውም አስፈላጊ ፍርማሉቲ አጠናቀው እንዱያስረክቡና መቀጫውንም እንዱከፍለ ውሣኔ ይሰጥልን በማለት ክስ አቅርቧል።
ተጠሪዎች በሥር ፍርድ ቤት በተከሳሽነት ቀርበው ከሳሽ (አመልካች) በውለ ላይ አልፈረሙም ውለም ሲደረግ አልነበሩም። የቅድሚያ ክፍያው በወቅቱ አልተፈፀመም። ውለ በውል አዋዋይ ፉት ያልተደረገ በመሆኑ ህጋዊ ውጤት የለውም። ከሳሽ የበኩላቸውን ግዳታ እንዱወጡ በደብዲቤ ተጠይቀው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ውለ መፍረሡን አሣውቀናቸዋል። ከሳሽ ውለን በግድ የማሣወቅ ሀሳብ ያላቸው መሆኑን አስቀድመው ያላሣወቁን በመሆኑ ውለ በግዳታ ይፈፀምልኝ በማለት ክስ ማቅረብ አይችለም በማለት ተከራክረዋል። የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመዘነ በኋላ አመልካች በውለ ላይ በወኪላቸው በአቶ ሰብሀ ሱሩር አማካኝነት የፈረሙ ስለሆነ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ውል አለ። ሁለተኛ ተጠሪ አመልካች ፅፈው የሰጧቸውን ቼክ ባንክ ወስደው መንዝረዋል። ስለዚህ የንግድ ድርጅት ሽያጭ ውል ተዋዋዮች ስምምነታቸውን የሰጡበት ውል ነው። ውለ በፅሐፍ የተደረገ ስለሆነ በህጉ የተቀመጠውን ፍርም ያሟላ ነው። ሆኖም ከሳሽ አመልካች በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2331 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት ውለ በግዳታ እንዱፈፀምለት የሚያስገድድ ስለመሆኑ ለሻጭዎች (ተጠሪዎች) ያልገለፀ በመሆኑና ውለ የተለየ ጥቅም የሚያስገኝ መሆኑን ያላስረዲ በመሆኑ የንግድ ድርጅት ሽያጭ ውለ እንዱፈፀምለት ከሳሽ (አመልካች) የመጠየቅ መብት የለውም በማለት የአመልካችን ክስ ውድቅ አድርጎታል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ የህግ ወይም የፍሬ ጉዲይ ስህተት የለበትም በማለት በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ይግባኙን ሰርዞታል።
አመልካች መጋቢት 18 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪዎች የንግድ ድርጅቱን የሚያስረክቡት እስከ ህዲር 28 ቀን 2000 ዓ.ም ድረስ ነው፣ የአመልካች ወኪል ተጠሪዎች ገንዘቡን ተቀብለው የንግድ ድርጅቱን እንዱያስረክቡ በምስክሮች ፉት ጠይቀዋል።
ተጠሪዎች ታህሣሥ 10 ቀን 2000 ዓ.ም ውለን አፍርሰናል በማለት ደብዲቤ የፃፈት መጀመሪያም ያሰቡበት ጉዲይ ነው። የውለ መፈፀሚያ የጊዜ ገደብ ስለሚታወቅ ማስጠንቀቂያ መስጠት አስፈላጊ አልነበረም። የተከፈለው ብር 40,000 አላግባብ በዝምታ ታልፎል። ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች ውለን በግዳታ ለመፈፀም ለመጠየቅ አመልካች አይችልም በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ ይታረምልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪዎች በበኩላቸው በቃል ባቀረቡት ክርክር የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ውለ በግዳታ ለመፈፀም ልዩ ጥቅምና ፍላጎት ያላቸው መሆኑን አለማስረዲታቸውንና ውለ በግዳታ እንዱፈፀም ለመጠየቅ የሰጡት ማስጠንቀቂያ አለመኖሩን በማረጋገጥ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካች በቃል የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የፅሐፍና የቃል ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው የበታች ፍርድ ቤቶች የንግድ ድርጅት ሽያጭ ውል በግድ እንዱፈፀም አመልካች ለመጠየቅ አይችለም በማለት የሰጡት ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም ውለ በግዳታ አይፈፀምም ቢባል አመልካች ለተጠሪዎች የከፈለት ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) በተመለከተ ውሣኔ ሣይሰጡ ማለፊቸው ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለት ጭብጦች መፈታት ያለባቸው ሆነው አግኝተናቸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የንግድ መደብር ሽያጭ ውለ እስከ ህዲር 28 ቀን 2000 ዓ.ም የሚፈፀም ስለመሆኑ የአመልካችና ተጠሪዎች ባደረጉት ውል የተገለፀ ቢሆንም የሽያጭ ውለ በግዳታ እንዱፈፀምለት የሚፈልግ ገዥ ውለ በግዳታ እንዱፈፀምለት የማስገደድ ሀሳብ ያለው መሆኑን ለሻጭ ካልገለፀ ውለን በፍርድ ሀይል ተገድድ ሻጭ እንዱፈፅም ቢደረግ መብቱን እንደሚያጣ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2330 ንዐስ አንቀጽ 1 ይደነግጋል። አመልካች በዚህ ድንጋጌ መሰረት ማስጠንቀቂያ ያልሰጠ መሆኑንና ይልቁንም ተጠሪዎች ውለን አፍርሰናል በማለት ቀድመው ለአመልካች በፅሐፍ ያሣወቁ መሆኑ በሥር ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። ከዚህ በተጨማሪ በአመልካችና በተጠሪ ውል ላይ የተገለፀው የጊዜ ገደብ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2331 ንዐስ አንቀጽ 2 የተደነገገውን ጥብቅ መሥፈርት የሚያሟላ አይደለም። ይኸም በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች የንግድ ድርጅት ሽያጭ ውለ በግዳታ እንዱፈፀምላቸው አመልካች የመጠየቅ መብት የላቸውም በማለት የሰጡት ውሣኔና የደረሱበት መደምደሚያ የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል።
አመልካች ውለ በግዳታ የማይፈፀም ከሆነ በአማራጭ ውለ ባለመፈፀሙ የደረሰበትን የኪሣራ መጠን በመግለፅ ተጠሪዎች ኪሣራ እንዱከፍለት የቀረበው የዲኝነት ጥያቄ የለም። በዚህ በኩል አመልካች ያልጠየቁት ዲኝነት በመሆኑ በውለ መሰረት ባለመፈፀሙ ተጠሪዎች የሚከፍለት ካሣ የለም። ሆኖም ተጠሪዎች ከአመልካች በቼክ ተቀብለው የወሰደትን ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) ለአመልካች የመመለስ ግዳታ ያለባቸው መሆኑ ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 1815 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ የተደነገገ በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪዎች ከአመልካች የወሰደትን ብር 40,000(አርባ ሺህ ብር) እንዱከፍለ አለመወሰናቸው መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም ይህንን የውሣኔ ክፍል ብቻ በማሻሻል ተጠሪዎች ለአመልካች ብር 40,000(አርባ ሺህ ብር) የመክፈል ግዳታና ሀላፉነት አለባቸው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሻሽሎል።
ተጠሪዎች የንግድ ድርጅት ሽያጭ ውለን በግዳታ እንዱፈፅሙ አይገደደም በማለት ወስነናል።
ተጠሪዎች ለአመልካች ብር 40,000(አርባ ሺህ ብር) ይክፈለ በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.