No summary available.
ታህሳስ 25 ቀን 2003ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አበበ አበጋዝ ቀረበ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ጥሩነሽ ተክላ ቀረበች መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ ቀደም ሲል በቤት ላይ ተደርጎ የነበረው የሽያጭ ውል እንዱፈርስ በተወሰነው መሰረት ቤቱን ያስረክቡኝ፣ የአሁኑ አመልካችም ቤቱን ይዞ ስለሚገኝ እስኪያስረክበኝ ድረስ ኪራይ እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ተጠሪ በአሁኑ አመልካች እና ሃይለ ታደሰ በተባለ ግለሰብ ላይ ያቀረበችውን ክስ የሚመለከት ነው።
ክሱ የቀረበው ለፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ ፍ/ቤቱም የተከሳሾቹን መልስ ካየ እና ክርክሩን ከሰማ በኋላ በወቅቱ 1ኛ ተከሳሽ የነበረው የአሁኑ አመልካች ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤት ለቆ ለተጠሪ እንዱያስረክብ፤ በውለ መፍረስ ምክንያት ለደረሰበት ጉዲት 2ኛ ተከሳሽ የነበረውን ሃይለ ታደሰን ከሶ የመጠየቅ መብት አለው በማለት ወስኖአል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች ውሳኔውን በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ክርክሩ በድጋሚ ተሰምቶአል። ፍ/ቤቱም ቀደም ሲል ተሰጠ የተባለው ውሳኔ የስር ከሳሽ ቤቱን እንድትረከብ የሚያስችላት አይደለም የሚል ምክንያት በመስጠት በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ ሽሮአል። ከዚህ በኋላም ተጠሪ ለፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረብዋ በዚህ ደረጃም ክርክሩ የተሰማ ሲሆን፣ በመጨረሻም ፍ/ቤቱ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ ሽሮአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች የካቲት 3 ቀን 2001ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ከክርክሩ አነሳስ እና ቀደም ሲል ተሰጥቶ ነበር ከተባለው ውሳኔ አንፃር ሲታይ ያለው አግባብነት ሉመረመር ይገባል በመባለ ነው። በዚህ መሰረትም ግራ ቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
ከሥር ጀምሮ የተደረገውን ክርክር እና በየደረጃው የተሰጡትን ውሳኔዎች ይዘት በዝርዝር ተመልክተናል። ከዚህም በቅድሚያ መገንዘብ የቻልነው ተጠሪ በ2ኛ ተከሳሽነት ተመዝግቦ የነበረው ሃይለ ታደሰ የተባለው ሰው ሚስት እንደሆነች እና ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት ከኔ ፈቃድ ውጭ ነው የተሸጠውና የሽያጭ ውለ እንዱፈርስ ይወሰኝልኝ በማለት ተጠሪ ባልዋን ጨምራ መክሰስዋን ነው። ይህን የመሰለውን ክስ የቀረበለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ክርክሩን ከሰማ በኋላ፣ ውለ በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1723 የተመለከተውን መስፈርት አያሟላም፤ በሕግ ፉት የፀና አይደለም የሚለትን ምክንያቶች በመስጠት ክሱ የክስ ምክንያት የለውም የሚል ውሳኔ እንደሰጠም ተመልክተናል። ተጠሪ ቤቴን ልረከብ፤ ኪራይም ይከፈለኝ በማለት አዱስ ክስ የመሰረተችውም ከዚህ በኋላ ነው።
እንደምንመለከተው በአመልካች እና በተጠሪ ባለቤት መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል ይፍረስልኝ በማለት ተጠሪ ክስ ብትመሰርትም ክስዋ የክስ ምክንያት የለውም በሚል ትዕዛዝ ነው የተዘጋው። ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው ለክሱ መነሻ የሆነው ውል ሉፈርስ የሚገባው ነው ወይም አይደለም? በሚለው የሥረ ነገር ጭብጥ ላይ ክርክር ተደርጎ ውሳኔ አለመስጠቱን ነው። በእርግጥ ቀደም ሲል ቀርቦ በነበረው ክስ ውለ ፈራሽ ነው በማለት ተወስኖ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ አመልካች ይግባኝ ባይነት ጉዲዩ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርቦ ክርክር ከተካሄደበት በኋላ ተሽሮ ክርክሩ እንደገና ተሰምቶ ይወሰን ዘንድ ለፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተመልሶአል። ከዚህ በኋላም ነው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክሱ የክስ ምክንያት የለውም በማለት ክሱን ሳያስተናግድ መዝገቡን የዘጋው። በዚህ ላይም ማንኛውም ተከራካሪ ወገን ይግባኝ አላለም።
ቀደም ሲል እንዲየነው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እና የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት የክስ ምክንያት የለም በማለት የተሰጠው ትዕዛዝ ከጅምሩ የቤት ሽያጭ ውል የለም እንደማለት ነው በሚል እሳቤ ነው አመልካች ቤቱን ለተጠሪ ያስረክብ በማለት የወሰኑት። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ግን የክስ ምክንያት የለም በመባለ ተጠሪ ቤቱን ልትረከብ ችላለች ማለት አይቻልም የሚል አስተሳሰብ ነው የያዘው። በእርግጥ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተጠሪን የውል ይፍረስልኝ ክስ የክስ ምክንያት የለውም ለማለት የሰጠው ምክንያት ውለ በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1723 የተመለከተውን መስፈርት /ፍርም/ ያላሟላ እና ከጅምሩ ውል ሳይኖር የውል ይፍረስ ክስ ላቀርብ አይችልም የሚል ስለመሆኑ ከውሳኔው ይዘት ተገንዝበናል። የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤትም ይህን አካሄድ በመከተለ ነው በአመልካች እና በተጠሪ ባለቤት መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል ፈራሽ ላሆን የሚገባው ነው ወይም አይፈርስም? በሚለው የሥር ነገር ጭብጥ ላይ ክርክር ሳይሰማ ተጠሪ ቤቱን ትረከብ ዘንድ የወሰነው።
No topics extracted.
ለፍ/ቤት የቀረበ የፍትሐብሕር ክስ የክስ ምክንያት አለው ወይስ የለውም? ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት በጉዲዩ ላይ የዲኝነት ሥልጣን አለው ወይስ የለውም? የሚለት ጥያቄዎች መልስ የሚያገኙት ወይም የሚወሰኑት ፍ/ቤቱ ወደ ክሱ ሥረ ነገር ከመግባቱ በፉት ነው። ይህንንም የሚያደርገው ፍ/ቤት በራሱ አነሳሽነት እንደሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 33/2/ እና 231/1/ ከተቀመጡት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። እዚህ ላይ ልብ ልባል የሚገባው ዋነኛው ጉዲይ ከተጠቀሱት ድንጋጌዎች አግባብ የክስ መዝገብ ሲዘጋ ወይም ክስ አይስተናገድም ሲባል ፍ/ቤቱ በጉዲዩ ሥረ ነገር ላይ ጭብጥ ይዞ በማከራከር ያልወሰነ መሆኑን ነው። ይህ ሁኔታ ከያዝነው ጉዲይ ጋር አገናዝበን ስንመለከተው በአመልካች እና በተጠሪ ባለቤት መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል ይፈርሳል ወይስ አይፈርስም? የሚለው ነጥብ የክሱ ሥረ ነገር ጭብጥ ነው። ይህ የሥረ ነገር ጭብጥ በየትኛውም ደረጃ በተደረገው ክርክር ተይዞ በተከራካሪዎች መካከል ንጥጥር አልተደረገበትም።
በመሆኑም ምንም የተደረገ ውል የለም የሚለው የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት መደምደሚያ የሕግ መሰረት የላለው ነው። ተደጋግሞ እንደተገለፀው የቤት ሽያጭ ውል ስለመኖሩ አላከራከረም። ለዚህም ነው ተጠሪ የውል ይፍረስልኝ ክስ የመሰረተችው። "የግዳታዎች መቅረት "በሚለው በፍትሐብሕር ሕጉ አራተኛ መጽሐፍ አንቀጽ 12 በምዕራፍ 3 ሥር" ውልችን ስለመሰረዝና ስለማፍረስ" የሚል ክፍል አለ። በዚህ ክፍል ሥር ከተቀመጡት ድንጋጌዎች አንደ በሆነው በቁ.1808/2/ እንደተመለከተው ውለ የተደረገበት ጉዲይ ወይም ምክንያት ከሕግ ውጭ ነው ወይም ለሕሉና ተቃራኒ ነው ወይም ለውለ አጻጻፍ የተደነገገውን ፍርም አልጠበቀም የሚል መከራከሪያ /ምክንያት/ ያለው ተዋዋይ ወይም ማንኛውም ጥቅም ያለው ሰው ውለ እንዱሰረዝ ለመጠየቅ ይችላል።
ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስ ተጠሪ ውለ መፍረስ አለበት የሚል እምነት ስላላት የውል ይፍረስ ክስ መስርታለች። ውለ የሚፈርስበት የሕግና የፍሬ ነገር ምክንያት አለ ወይስ የለም የሚለው የሥረ ነገር ክርክር በዝርዝር የሚታየው ክሱ በቀረበለት ፍ/ቤት እንደሆነም ግልጽ ነው።
በእርግጥም ውለ የሕጉን ፍርም አልጠበቀም የሚል ክርክር የሚነሳ ቢሆን የሚታየው ከፍ ሲል ከጠቀሰነው ድንጋጌ አንፃር ነው። በዚህ አግባብ ውለ ፈራሽ ነው ካልተባለ ደግሞ ተጠሪ በቀጥታ ቤቱን ትረከብ ዘንድ መወሰን የሚቻልበት አካሄድ የለም። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ ቤቱ ተሽጦአል መባለን በመቋወም ክስ እስከ መሰረተች ድረስ ክርክሩ እስከመጨረሻው ድረስ ተኪድ ሳይታይ ከወዱሁ ልትሰናበት አይገባም። ነገሩን አጠቃለን ስንመለከተው የሥር ፍ/ቤቶች ወደ ድምዲሜ የደረሱት ክርክሩ መመራት ባለበት አግባብ ሳይመሩ ተገቢም ጭብጥ ሳይዙ ነው ለማለት ችለናል።
ይህ ደግሞ ከሕጉ አተገባበር አንፃር ሲታይ መሰረታዊ ስህተት ነው። ስለዚህም ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ. መጋቢት 20 ቀን 96ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፣ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ሐምል 22 ቀን 2000ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት በመ. ጥር 4 ቀን 2001ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክርክሩን በተከፈተው መዝገብ እንዱቀጥል በማድረግ በቅድሚያ ለተጠሪ የክስ መነሻ የሆነው ውል ይፈርሳል ወይስ አይፈርስም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ፤ ግራ ቀኝ ወገኖች በዚህ ረገድ የሚያቀርቡትን የሕግና የፍሬ ነገር ክርክር ከሰማ በኋላ ተገቢውን ውሳኔ ይሰጥ ዘንድ ጉዲዩ ይመለስለት ብለናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።