No summary available.
ጥቅምት 2ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ አመልካች፡- አቶ ሣልህ ሁሴን ቀረቡ ተጠሪ፡- ደግፋ ደርቤ ከጠበቃ ጣሰው ማሞ ጋር ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሣሽ የአሁኑ ተጠሪ ደግሞ ተከሣሽ ነበሩ።
አመልካች ግንቦት ዐ5 ቀን 1997 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ ተጠሪ በስማቸው ተመዝግቦ የሚታወቀውንና በቀድሞው አጠራር ከፍተኛ ዐ9 ቀበላ ዐ7፣ በአሁኑ አጠራር በአራዲ ክፍለ ከተማ ቀበላ ዐ6 የሚገኘውን ቁጥሩ 2ዐ7 እና 2ዐ6 የሆነ ቤት በመያዣነት አስይዘው ብር 12ዐዐዐ.00 /አስራ ሁለት ሺህ/ ተበድረው ቤቱን እንዲስረከቧቸው፤ በስምምነቱ ወቅት የማይንቀሳቀስ ንብረት መሸጥና መለወጥ ችግር ስለነበር ገንዘቡ የ1ዐ ዓመት መክፈያ ጊዜ ተወስኖለት ኀዲር 2ዐ ቀን 199ዐ ዓ.ም. ማብቃቱን፤ ኀዲር 2ዐ ቀን 198ዐ ዓ.ም. በተፃፈ የብድርና የዋስትና ውል ቤትን መሸጥና መለወጥ በመንግሥት ሲፈቀድ አመልካች ብር 5ዐዐዐ.00 /አምስት ሺህ/ ለተጠሪ በመጨመር ከወሰደት ብር 12ዐዐዐ.00 ጋር ተደምሮ በብር 17ዐዐዐ.00 /አስራ ሰባት ሺህ ብር/ ቤቱን በሽያጭ ለማስተላለፍ ተጠሪ ውል መፈረማቸውን፤ የቤቱን የእድሣት ወጪዎችም አመልካች እንዱሸፍኑ ተጠሪ ፈቃዲቸውን በውለ የገለጹላቸው ሆኖ ተጠሪ ከወሰደት የቤቱ መያዣ ብድር ጋር የእድሣት ወጪ ሲደመር ድምሩ .90 /አስራ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ ሰማኒያ ሰባት ብር ከዘጠና ሣንቲም/ መሆኑን፤ የቤት ሽያጭም ከ1982 ዓ.ም. ጀምሮ በመንግሥት መፈቀደን ዘርዝረው ተጠሪ በስምምነቱ መሰረት የብድሩን ገንዘብ በወቅቱ ካለመመለሣቸውም በላይ የቤቱን ስመ ንብረት በሽያጭ ለማስተላለፍ በአማራጭ የገቡትን ግዳታ ስላልፈፀሙላቸው አመልካች ብር 5ዐዐዐ.00 /አምስት ሺህ/ ለተጠሪ ጨምረውላቸው የቤቱ ስም በአመልካች እንዱዛወር ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። ለማስረጃነትም የጽሐፍና የሰው ምስክሮችን ዘርዝረው አቅርበዋል።
የአሁኑ አመልካች የክስ ማመልከቻና ማስረጃ ለተጠሪ እንዱደርስ ተደርጎም ተጠሪ በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል። ፍ/ቤቱም የአመልካችን ክስና ማስረጃ መርምሮ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገ ውል የመያዣ ውል ሣይሆን የወለድ አገድ ውል ነው፤ ውለ በተደረገበት ወቅት የወለድ አገድ ግንኙነት የሚገዛው በአዋጅ ቁጥር 47/67 ስለነበር ይኸው አዋጅ የወለድ አገድ ውልን የሚከለክል በመሆኑ ውለ ሕገወጥ ስለሆነ ፈራሽ ነው፤ ተዋዋዮች ወደ ነበሩበት ይመለሱ፤ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤት አመልካች ያስረክቡ፤ ተጠሪ ከአመልካች የወሰደትን ገንዘብና የቤት ማደሻ ብር በገቡት ውል መሰረት ለከሣሽ ይክፈለ በማለት ወስኗል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት ፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ አጽንቶታል። የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍ/ቤቶችን ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች የበታች ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት የሚለባቸውን ምክንያቶች ኀዲር 16 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ ዘርዝረው አቅርበዋል።
ይዘቱም በአጭሩ የበታች ፍ/ቤቶች ተጠሪ ቀርበው ባልተከራከሩበት እና የተጠየቀ ዲኝነት በላለበት ሁኔታ ቤት እንዱረከቡ መወሰናቸው ያላግባብ በመሆኑ ውሣኔው ተሽሮ ኀዲር 2ዐ ቀን 198ዐ ዓ.ም.
በውል ያገኙት መብት ተጠብቆ እንዱወሰንላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም በጉዲዩ ከተጠየቀው ዲኝነት በተለየ ሁኔታ የተሰጠውን ውሣኔ የሕግ አግባብነት ለማጣራት ተጠሪ እንዱቀርብ ተደርጎ ጥር 29 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ መልሣቸውን አቅርበዋል። ይዘቱም በአጭሩ የበታች ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የላለበት፣ የፍ/ሕ/ቁ. 1815 ድንጋጌን ያገናዘበ፣ የአመልካች ጥያቄ ግን በፍ/ሕ/ቁ 2851 ድንጋጌ ተቀባይነት የላለው መሆኑን ዘርዝረው የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ ሉፀና ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው። አመልካች የካቲት 14 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት የመልስ መልስ ማመልከቻ ተጠሪ ወደ ዋናው ጉዲይ ገብተው ለመከራከር ሥነ ሥርዓቱ የማይፈቅድላቸው መሆኑን ገልፀውና የሰበር አቤቱታቸውን አጠናክረው ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ይህንኑ አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
No topics extracted.
እንደመረመረውም የችልቱ ምላሽ የሚያስፈልጋቸው ጭብጦች፡- 1ኛ/ የበታች ፍ/ቤቶች አመልካች ከጠየቁት ዲኝነት በተለየ ሁኔታ የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? እና 2ኛ/ የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ የክስ ምክንያት አለው ወይስ የለውም? የሚለት ሁነው ተገኝተዋል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ፡- አመልካች ከተጠሪ ጋር ተደርጓል በሚለት ስምምነት አከራካሪውን ቤት ተረክበው በይዞታቸው ሥር አድርገው እየተጠቀሙበት የሚገኙ መሆኑን ገልፀው የሚከራከሩ ሲሆን የጠየቁት ዲኝነትም ቀሪውን ብር ለተጠሪ ጨምረው የቤቱ ስመንብረት እንዱዛወርላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ነው። ይህንኑ የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ የአሁኑ ተጠሪ ፍ/ቤት ቀርበው ከስር ያልተከራከሩበት ሆኖ የስር ፍ/ቤት ግን የውለን ሕጋዊነት በራሱ ጊዜ በማንሣት ሕገ ወጥ ነው ወደሚለው ድምዲሜ ደርሶ ውለ ፈራሽ ነው በማለት ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤት አመልካች ለተጠሪ ሉያስረክቡ ይገባል ሲል ወስኗል። ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው የስር ፍ/ቤት ውሣኔ የሰጠው የአሁኑ አመልካች በግልጽ ባላመለከቱት እና ባልጠየቁት ዲኝነት ላይ መሆኑን ነው። ይህ ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 182/2/ ድንጋጌ ሥር የተመለከተውን የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የዲኝነት አሰጣጥ የስልጣን አድማስ በግልጽ የሚፃረር ነው። የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤትም በይግባኝ ሰሚነቱ ስልጣን የስር ፍ/ቤትን የውሣኔ አሰጣጥ ማረም ሲገባው በተመሣሣይ ምክንያት ተቀብል ማጽናቱ የዲኝነት አሰጣጥ ሥርዓቱን ያላገናዘበ ነው። የስር ፍ/ቤት ስለውለ ሕጋዊነት ክርክር ባልተነሣበት ሁኔታ በራሱ ጊዜ ማንሣቱም የክርክር አመራር ስርዓቱ በሚፈቅድለት ሁኔታ አይደለም። ተጠሪ በስር ፍ/ቤት ሣይቀርቡ ጉዲዩ በላለበት ታይቶ ከተወሰነ በኋላ አሁን በሰበር ችልት ያቀረቡት ክርክር ሥነ ሥርዓታዊ አይደለም። ተጠሪ በስር ፍ/ቤት ሣይቀርቡ ታይቶ በተሰጠው ውሣኔ ለበላይ ፍ/ቤት ሉያቀርቡ የሚችለት ክርክር ከስር ክስ ተያይዘው የቀረቡትን የከሣሽን ማስረጃዎች አግባብነት፣ ተቀባይነት እና ጥንካሬ ያገናዘብ መሆን ያለመሆኑን መሰረት በማድረግ ብቻ የተወሰነ ነው። ስለሆነም ተጠሪ በዚሁ የክርክር ደረጃ ያነሱት ክርክር ተቀባይነት የላለው በመሆኑ አልፈነዋል። በዚህም መሰረት የስር ፍ/ቤት የውሣኔ አሰጣጥ ከተጠየቀው ዲኝነት በተለየ ሁኔታ መሆኑ ከላይ የተጠቀሰውን የሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌ ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ፡- በመጀመሪያው ጭብጥ እንደተገለፀው የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ ስመ ንብረቱ እንዱዞርላቸው ይወሰን ዘንድ ነበር። የስር ፍ/ቤትም የዚህኑ ጥያቄ አግባብነት በመመርመር ውሣኔ መስጠት እየተገባው ከተጠየቀው ዲኝነት በተለየ ሁኔታ ውሣኔ ሰጥቷል። የአመልካች ጥያቄ ተገቢነት ያለው መሆን ያለመሆኑን የስር ፍ/ቤት በጭብጥነት ይዞ በሕጉ አግባብ የሰጠው ውሣኔ ባይኖርም ከተጠየቀው ዲኝነት ይዘት በሰበር ችልቱ ከዚህ በፉት በተመሣሣይ ጉዲይ ከተሰጠው የሕግ ትርጓሜና ከፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ዓላማ አኳያ ሲታይ በዚህ ችልት ለጉዲዩ እልባት መስጠቱ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ የሚያስከስስ ላሆን ይችላል አይችልም? የሚለው ነጥብ ምላሽ የሚያስፈልገው ሆኖ ተገኝቷል።
ከአመልካች ክስና ክርክር ማረጋገጥ የተቻለው ከተጠሪ ጋር በተደረገው ስምምነት ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤት አመልካች ተረክበው ለረጅም ጊዜያት በይዞታቸው ስር አድርገው የሚገኙ መሆኑን፣ ቤቱን የሚመለከቱ አስፈላጊ ሰነድችም በተጠሪ እጅ ይገኛለ ተብል በክሱ አለመገለጹንና የዲኝነት ጥያቄ ያልቀረበበት መሆኑን በተጠሪ በኩል መፈፀም አለበት የተባለው የቤቱ ስመ ንብረት ማዞር ብቻ መሆኑን ነው። የስም ዝውውር ተግባር የሚፈፀመው በመንግሥት አስተዲደር ክፍል ፉት እንጂ ሻጭ ነው የተባለው ወገን ሉፈጽም ይገባል ተብል ከሕግ ወይም ከውል ያመነጫል ልባል የማይችል ግዳታ ነው። የስም ዝውውር ጥያቄ የሚስተናገደው የባለ ሀብትነት የምስክር ወረቀት በሚሰጥ የመንግሥት አስተዲደር አካል ገዢው ውልና አስፈላጊ ሰነድችን ይዞ ሲቀርብ እንጂ በፍ/ቤት ክስ ቀርቦ ዲኝነት የሚሰጥበት አይደለም። አንድ ክስ ላቀርብ የሚገባው የክስ ምክንያት ሲኖረው ሲሆን የክስ ምክንያትም ተከሣሽ ለከሣሽ ሉፈጽመው የሚገባው ግዳታ መኖሩ ጋር ተያይዞ ሉነሣ የሚችለውን ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ መስጠት የሚቻልበት ሁኔታ ስለመኖሩ ሲረጋገጥ የሚታወቅ ነው። በዚህም መሰረት አመልካች ተጠሪ የስም ዝውውሩን እንዱፈጽሙ ይወስንልኝ ብለው ዲኝነት መጠየቃቸው በተጠሪ በኩል ሉፈፀም የሚገባ የሕግ ወይም የውል ግዳታ የላለ መሆኑን ስለሚያሣይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 231/1/ሀ/ መሰረት ፍሬ ነገሩ የማያስከስስ ነው ተብል መወሰን ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 13295 ጥቅምት 16 ቀን 1999 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 511ዐ7 ኀዲር ዐ3 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች የስም ዝውውር ጥያቄ ታይቶ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀው እያለ ከተጠየቀው ዲኝነት በተለየ ሁኔታ ውለ ሕገወጥ ነው ተብል ቤቱን እንዱያስረክቡ መባለ የዲኝነት አሰጣጥ ሥርዓትን የተከተለ አይደለም ብለናል።
የአመልካች የስም ይዛወርልኝ ጥያቄ የሚያስከስስ ምክንያት የለውም ብለናል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መ/ቤት ይመለስ።