No summary available.
ሐምል 12 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሪት ፍሬወይኒ ቴዎድሮስ የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ተርካንፋ ፔሮሞሽን የማስታወቂያ ስራ ድርጅት - ጠበቃ ነፃነት ጌታሁን ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የውል ይፈፅምልኝ ጥያቄን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ ላይ በአዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መደበኛ ጉዲይ ችልት ሚያዚያ 07 ቀን 2002 ዓ/ም በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ተጠሪ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የደቡብ ክልል ሁለም ዞኖችና ልዩ ወረዲዎች የሚሳተፈበትን የደቡብ ሚስስ ቱሪዝም የቁንጅና ውድድር በኮንሶ ልዩ ወረዲ ካራት ከተማ መስከረም 09 ቀን 2001 ዓ/ም እንደሚያዘጋጅና ተወዲዲሪዎች እንዱመዘገቡ ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት መመዝገባቸውን ፣ በማስታወቂያውም ላይ በውድድሩ አሸናፉ ለሆነች ወጣት በክልለ ርዕሰ ከተማ ሐዋሳ መኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ፣ በክልለ በሚገኙ ታላላቅ ኮላጆች ውስጥ ነፃ የትምህርት እድል እና የብር 5000.00(አምስት ሺህ) የገንዘብ ስጦታ ለመስጠት አመልካች በሚኖሩበት የዲውሮ ዞን በፊክስ የማስታወቂያ ደብዲቤ ቃል መግባቱን ፣ በውድድሩም አመልካች ተወዲድረው አንደኛ በመውጣት የደቡብ ሚስስ ቱሪዝም ማዕረግ ያገኙ መሆኑን ፣ ተጠሪ በገባው ቃል መሰረት በኮላጅ የነፃ የትምህርት እድለን እና ብር 5000.00 ለአመልካች የሰጣቸውና አመልካችም የተቀበለ ሁኖ የቤት መስሪያ ቦታ ግን በገባው ቃል መሰረት ያልፈፀመላቸው መሆኑን ዘርዝረው ተጠሪ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንዱሰጣቸው ፣ ቦታውን መስጠት የማይችል ከሆነ ደግሞ በወቅቱ በነበረው የከተማው የሉዝ ዋጋ ተመን መሰረት የሁለት መቶ ካሬ ሜትር ዋጋ ብር 360,000.00 (ሶስት መቶ ስልሻ ሺህ ብር) እንዱከፍል ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም በማስታወቂያው ላይ የተገለፀው እድል የሚለው ቃል የሚያመላክተው የሥጦታ ተስፊ ቃል እንጂ ሽልማት ባለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥ 2435 መሰረት ግዳታ የሚጥል አይደለም ፣ የስጦታ ተስፊ ቃል በሕግ ፉት ተቀባይነት የላለው ከመሆኑም በላይ ፍርማሉቲውንም የጠበቀ አይደለም ፣ የውለ ጉዲዩ በግልፅ ያልተመለከተና የሚቻል ውል ባለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1714 መሰረት ሕጋዊነት የለውም ፣ እንዱሁም መሬት የመንግስትና የሕዝብ በመሆኑ ልገደድበት አይገባም በማለት ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ማስታወቂያው የሚያሳየው የስጦታ ተስፊ ቃል መሆኑን ፣ ይህ ደግሞ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2435 መሰረት ግዳታ የሚጥል አለመሆኑን ፣ የውለ ጉዲይም በሕዝብና በመንግስት መሬት ላይ የተደረገ በመሆኑ ተጠሪ ሉፈፀመው የሚችለው አይደለም ፣ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1689(1) ለጉዲዩ አግባብነት የለውም የሚለትን ምክንያቶችን በመያዝ የአመልካችን ክስ ሙለ በሙለ ውድቅ አድርጎ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ተጠሪ በማስታወቂያው ላይ ከገለፃቸው ሽልማቶች መካከል ሁለቱን ፈጽሞ እያለ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ለመሸለም ቃል አልገባሁም በማለት ያቀረበው ክርክር በበታች ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ማግኘቱ የውል አተረጓጏም ደንቦችን ስለውል አፈፃጸም የተደነገጉትን ድንጋጌዎችን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው መሆኑ ታምኖበት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ በይዘቱ በስር ፍርድ ቤት ከአቀረበው መከራከሪያ ነጥብ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ክርክር ያቀረበ ሲሆን አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም አመልካች ያቀረቡት ክስ ውድቅ መደረጉ ባግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ነው።
ከላይ እንደተገለፀለው አመልካች በተጠሪ በተደረገው ጥሪ መሰረት ተወዲድረው የደቡብ ሚስስ ቱሪዝም ማዕረግ ማግኘታቸው ፣ በጥሪው ጊዜም ለአሸናፉ ሉሰጡ የሚገባቸው ሽልማቶች መገልፃቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከሽልማቶች መካከል በክልለ በሚገኙ ታላላቅ ኮላጆች መካከል የነጻ ትምህርት እድልና ብር 5000.00 (አምስት ሺህ ብር) ተጠሪ ለአመልካች የፈጸመላቸው ሽልማቶች መሆናቸው ተረጋግጠዋል። አሁን ግራ ቀኙን እያከራከሩ ያለው የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ከሽልማቶች መካከል የሚገኝ መሆን ያለመሆኑ ነው። ተጠሪ በዚህ ረገድ አጥብቆ የሚከራከረው በማስታወቂያው ላይ "በሐዋሳ ከተማ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እና በክልል የሚገኙት ታላላቅ ኮላጆች ውስጥ ነጻ የትምህርት እድል---"በሚል ከተቀመጠው አረፍተ ነገር ውስጥ እድል የሚለው ቃል የስጦታ የተስፊ ቃል እንጂ ሽልማት አይደለም ፣ የስጦታ የተስፊ ቃል ደግሞ አስገዲጅ ግዳታ የማይጥል ነው በማለት ሲሆን የስር ፍርድ ቤቶችም ይህንኑ የተጠሪን ክርክር ተቀብለዋል። ይህን የስር ፍርድ ቤቶችን ድምዲሜ በፍ/ሕ/ቁጥር 2427 ስር ከተመለከተው የስጦታ ትርጓሜ አንፃር ማየቱ ተገቢ ነው። በዚህ ድንጋጌ ስጦታ ማለት አንድ ወገን ተዋዋይ ማለት ሰጪ ተቀባይ ተብል ለሚጠራው ለላላ ሰው ችሮታ በማድረግ አሳብ ከንብረቶቹ አንደን የሚለቅበት ወይም ግዳታ የሚገባበት ውል ስለመሆኑ የተመለከተ ሲሆን በተቀባዩ በኩል የሚገባ ግዳታ የለም። በልላ አነጋገር ስጦታ በስጦታ ሰጪ ለስጦታ ተቀባዩ በችሮታ(gratuitously) የሚደረግ ውል ነው። አመልካች እና ተጠሪ ያደረጉት ውል ግን አመልካች የቁንጅና ውድድሩ አሸንፈው የደቡብ ሚስስ ቱሪዝም ማዕረግ ከአገኙ ሽልማቱን ተጠሪ የሚሰጣቸው መሆኑን የሚገልፅ በመሆኑ የውለ ጉዲይ ሲታይ አንደ ተዋዋይ ለላላኛው አንድ ነገር ለማድረግ ወይም ለመስጠት የተስማማበትና በሕጉ አግባብ የተቋቋመ መሆኑን የሚስገነዝብ ነው። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች ከመነሻው ጉዲዩ በስጦታ ውል የሚሸፈን መሆን ያለመሆኑን ግራ ቀኙ ከአቋቋሙት ውል የግራ ቀኙን ግዳታ በመለየት ስጦታ መሆን ያለመሆኑን ሳይለዩ ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2435 ድንጋጌን ለውሳኔአቸው ዋቢ ማድረጋቸው አግባብነት ያለውን ሕግ በመለየት ረገድ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት መፈፀማቸውን የሚያሳይ ነው። ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ሕግ ፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1689 ሲሆን በዚህ አንቀፅ ንዐስ አንቀጽ አንድ ድንጋጌ መሰረት የጠፊ እቃ ላገኘ ወይም ላላ ነገር ለፈጸመ ሰው ሽልማት ይሰጠዋል ተብል በተለጠፈ ማስታወቂያ ወይም በአደባባይ ሉታወቅ በሚችል ላላ ዐይነት ማስታወቂያ ወጥቶ ቃል ከተሰጠ በኋላ የጠፊውን ዕቃ አግኝቶ ቢያመጣ ወይም እንዱፈጽም የተባለውን ስራ ፈጽሞ ቢገኝ ይህን ያደረገው ሰው የወጣውን ማስታወቂያ ሳይውቅ ቢቀርም የተሰጠውን የተስፊ ቃል እንደተቀበለ እንደሚቆጠር የተደነገገ ሲሆን በአንቀፁ ንዐስ ቁጥር ሁለት ደግሞ ቃል ሰጪውም በበኩለ የሰጠውን የተስፊ ቃል የመፈጸም ግዳታ እንዲለበት በኃይለ ቃል ተደንግጓል። ከዚህ ድንጋጌ ላላ ነገር መፈፀም በሚል ከተቀመጠው ሐረግ መረዲት የሚቻለው የውድድር አሽናፉንም የሚያካተት መሆኑን ሲሆን ለጉዲዩ ቀጥተኛ አግባብነት ያለው ድንጋጌ ይኸው ድንጋጌ እንጂ የስጦታ ውልን በሚመለከት የተቀመጡት የፍትሐብሕር ሕግ ድንጋጌዎች አይደለም።
ላላው የበታች ፍርድ ቤቶች ለውሳኔው መሰረት ያደረጉት የግራ ቀኙ ሐሳብን የሚመለከት ነው። በመሰረቱ በውል ውስጥ የተጠቀሱት ቃላትና ድንጋጌዎች ግልጽ ባልሆኑ ጊዜ ከፍ/ሕ/ቁጥር 1732 ፣ 1735-1738 ድረስ ባለት ድንጋጌዎች ስር በሰፈሩት ደንቦች መሰረት መተርጏም የተፈቀደ ነው። በዚህም መሰረት ለተያዘው ጉዲይ አግባብነት ያላቸው ደንቦች የፍ/ሕ/ቁጥር 1734 እና 1736 ሲሆኑ ተዋዋዮች ውላቸውን ከመዋዋላቸው አስቀድሞ ወይም ከተዋዋለ በኋላ የነበሩበትን ሁኔታዎች ፣ የፈጸሙትን ተግባር በማመዛዘንና ሐሣባቸው ምን እንደነበር ለማወቅ መሞከር እና የውልችን ቃልች አንደን ከአንደ ጋር እያዛመደ በመመልከት ለውለ ጉዲይ አግባብ ያለውን ትርጉም በመስጠት አዎንታዊ ውጤት እንዱኖረው ማድረግ ተገቢ ስለመሆኑ ተጠቃሽ ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ። በያዝነው ጉዲይ አመልካች በተጠሪ በኩል የቀረበው የውል አቀባበል ማስታወቂያ በ19/12/2000 ዓ/ም የተጻፈ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ተጠሪም ይህንኑ ደብዲቤ ስለመኖሩ ሳይክድ አጥብቆ የሚከራከረው በይዘቱና መንፈሱ ላይ ነው። ለክርክሩ መሰረት የሆነው የደብዲቤው ክፍል " ….አሽናፉ የሆነች ወጣት በክልለ ርዕስ ከተማ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እና በክልለ የሚገኙት ታላላቅ ኮላጆች ውስጥ ነጻ የትምህርት እድል ሲኖራት የብር 5000.00 (አምስት ሺህ ብር) ገንዘብ ሽልማትም ታገኛለች" በሚል የተቀመጠ ስለመሆኑ የስር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ በግልጽ ያሳያል። ከዚሁ የደብዲቤ ይዘት የነፃ ትምህርት እድልና የብር 5000.00 ሽልማት ለአመልካች በተጠሪ የተፈጸሙ ግዳታዎች ናቸው። ተጠሪ በደብዲቤው ….እድል ሲኖራት… የሚለው ሐረግ አመልካች የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ሽልማት ይሰጣታል ወይም ታገኛለች የሚል ግልጽ የሆነ የተስፊ ቃል የለም ፣ ቃለ መኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ልታገኝ የምትችልበት ሁኔታ መኖሩን ከሚያመላክት አልፍ በእርግጠኝነት ይህ ቦታ በሽልማት የሚሰጥ መሆኑን አያሳይም በማለት ተከራክሮ የስር ፍርድ ቤቶችንም ይሕንኑ የተጠሪን ክርክር ተቀብለዋል። ይሁን እንጂ ከላይ እንደተመለከተው የውል ቃልች ግልፅነት የሚጎድላቸው ከሆነ ሕጉ የአተረጎጎም ደንቦችን ያስቀመጠ ሲሆን ዲኞቹም ይህንኑ የአተረጎጎም ደንብ ሉከተለ እንደሚገባ የግድ ይላል። ተጠሪ ለአመልካች የነጻ ትምህርቱን የሰጠውና ብር 5000.00 የከፈለው ከውለ በሁዋላ ሲሆን ይህን ግራ ቀኙ ከውለ በሁዋላ የፈጸሙትን ተግባር በማመዛዘንና ሐሣባቸውን ምን እንደነበር ለማወቅ ሲሞከር ተጠሪ ለአመልካች የመኖሪያ ቤት መስሪያ ለመሸለም የተስፊ ቃል መስጠቱን የሚገልፅ ነው። ስለሆነም ተጠሪ ለአመልካች የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ለመሸለም የገባው ግዳታ የለም በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የደረሱበት ድምዲሜ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1734 እና 1736 ድንጌጋዎችን መሰረት ያላደረገ ነው። የበታች ፍርድ ቤቶች በግራ ቀኙ መካከል የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ሽልማት ቃል አልተገባም ለማለት በምክንያትነት የያዙት ጉዲይ የውለን ጉዲይና ሉፈፀም የሚችል መሆን ያለመሆኑን የሚመለከታው ነጥብ ነው። እንደሚታወቀው የውል ጉዲይ የሚያሳየው ተዋዋይ ወገኖች ለመፈጸም የገቡትን ግዳታ ሲሆን ይህ የሚቋቋመው ግዳታም አንደ ተዋዋይ ለላላኛው አንድ ነገር ለማድረግ ወይም ለመስጠት አለበለዚያ አንድን ማድረግ ይችል የነበረውን ከማድረግ ለመቆጠብ የሚስማማበት ነው። ይህ የተባለው ነገር እንዱደረግለት የሚፈልገው ላላኛው ወገንም በበኩለ ላላ ግዳታ ይገባል። ይህ ግዳታ የሚያሳየው የውለን ጉዲይ ሲሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1711 ላይ እንደተመለከተው ሕግ ከከለከለው በስተቀር ተዋዋዮቹ ሁለ የሚዋዋለትን ጉዲይ እንደመሰላቸው የመወሰን መብት አላቸው። የውል ጉዲይ አወሳሰን ከመዋዋል ነጻነት(Freedom of Contract)ጋር በእጅጉ በቀጥታ የተገናኘና ለተዋዋዮች ግላዊ ምርጫ የተተወ ስለመሆኑ የጠቅላላ ውል ፅንሰ ሐሳቦች የሚያስገነዝቡን ጉዲይ ነው። በዚህም መሰረት ተዋዋይ ወገኖች የራሳቸውን መብትና ግዳታ ገልፀው የሚፈልጉትን ባግባቡ ለይተው ካመለከቱ በመካከላቸው በሕግ ጥበቃ ላደረግለት የሚገባ ውል ተመስርቷል ለማለት የሚቻል መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1715 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የሚሳየን ጉዲይ ሲሆን ግዳታዎቹ በትክክልና በሚበቃ ሁኔታ ሉገለፁ እንዱሚገባም የዚሁ ድንጋጌ ይዘት ያስረዲል። እንዱሁም የአንደኛው ተዋዋይ ወገን ግዳታ ሉፈፅሙት ፍጹም የማይቻልና የማይሞከር ጠባይ ያለው ሆኖ ከተገኘ ፈራሽ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1714 የተመለከተው ድንጋጌ የሚያስገነዝብ ሲሆን ይኸው ድንጋጌ ፍፁም የማይቻልና የማይሞከር ጠባይ ያለው ግዳታ ሲባል ተዋዋይ ወገን ብቻ ሳይሆን ማንም ሰው ሉፈፅመው የማይችለው ግዳታ መሆን እንዱሚኖርበት የሚያስረዲ ሲሆን ሉፈጸም እስከቻለ ድረስ አስቸጋሪነቱ ግዳታውን ሉያፈርሰው እንደማይችል የተጠቃሹ ድንጋጌ መንፈስና ይዘት በግልጽ ያሳያል። ውል ሕጋዊ ውጤት ያለው ተግባር እንደመሆኑ መጠንም እያንዲንደ ተዋዋይ ወገን በውለ የተጣለበትን ግዳታ መፈፀም የሚገባው ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1740 እስከ 1762 ድረስ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ያሳያለ።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም የበታች ፍርድ ቤቶች የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ በእርግጠኝነት በተጠሪ እጅ የሚገኝ መሆኑ ፣ ስፊቱ እና አቀመማጡ የተለየ እና የታወቀ መሆኑ በትክክል እና በግልጽ በሚበቃ መልኩ አልተመለከተም በማለት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1714(1)ን በመጥቀስና ተጠሪ የከተማ ቦታን በስጦታም ሆነ በሽልማት የመስጠት ስልጣንም ሆነ ችልታ የለውም በማለት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1715 ድንጋጌ ጋር በማዛመድ ውለ በሕግ ግዳታን የሚፈጥር አይደለም በማለት የደረሱበት ድምዲሜ ሲታይ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታዎች በከተሞች ለሰዎች የሚሰጡበትን ስርዓት ፤ የማዘጋጃ ቤትን ስልጣንና የሉዝ ሕጎችን ፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1711፣1713፣1714 እና 1715 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ያላገናዘበ ነው።
መሬት የመንግስትና የሕዝብ መሆኑ በፋዳራልም ሆነ በክልል ሕግጋተ መንግስታት የተደነገገ ሲሆን በከተማ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታዎች ለሰዎች የሚሰጡበትና ስራው የሚያከናውነው የክፍለ ማዘጋጃ ቤት መሆኑን ስራ ላይ ያለት ሕጎች የሚሳዩን ሲሆን መጠኑን በተመለከተም ሕግና ሥርዓት የተዘረጋለት ጉዲይ ነው።የከተማ ቦታን የመስጠት ስልጣን የከተማው ማዘጋጃ ቤት ስልጣን መሆኑ በሕጉ በተደነገገበት ሁኔታ ተጠሪ ቦታ ለአመልካች እሸልማለሁ ብል የገባው ቃል ስልጣኑ ሲኖረው የሚፈጽመው ግዳታ መሆኑን አውቆ ያደረገው ሳይሆን ቦታ የሚገኝበትን ሥርዓት ተከትል ለአመልካች ለማስረከብ ግዳታ መግባቱን የሚያሳይ ነው። የከተማ ቦታ ከሚገኝባቸው መንገድች አንደ ደግሞ የሉዝ ስርዓት ነው። ቦታ በሉዝ የሚገዛው ደግሞ በሕጉ ፣ ደንቡና በመመሪያው መሰረት ተመንና የውለ ጊዜ ወጥቶለት ነው። ተጠሪ የቦታ ሽልማት ውለን በወቅቱ በነበረው የሉዝ ተመንና በሕጉ አግባብ በሉዝ ገዝቶ የሚፈጸመው ጉዲይ እንጂ ፍጹም የማይቻልና የማይሞከር ጉዲይ አይደለም። የሥር ፍርድ ቤት የመሬቱን አቀማመጥና ተይዞ የሚገኝበትን ሁኔታ እንዱሁም ቦታ በሽልማት የመስጠት ስልጣንን በምክንያትነት በመያዝ በሕግ ጥበቃ ላደረግለት የሚችል ውል የለም ብል መደምደሙ ከፍ/ሕ/ቁጥር 1715 ድንጋጌ አንፃር ሲታይ ሕጋዊ መሰረት የላለው ነው። በመሆኑም ተጠሪ በከተማ የመኖሪያ መስሪያ ቦታ የሚገኝበትን የሕግ ስርዓት እያወቀ ያደረገው ውል መሆኑ እየታወቀ በሕግ ጥበቃ ላደረግለት አይችልም በማለት መደምደም በተዋዋዮች መካከል ሉኖር የሚገባውን የቅንነትንና የመተማማን ግንኙነት መሰረት በማድረግና በጉዲዮቹ ውስጥ ያለውን ልማዲዊ ሥርዓት በመከተል ውልች በቅን ልቦና ሉተረጎሙ ይገባል ተብል በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1732 ስር የተደነገገውን ድንጋጌ ውጤት አልባ የሚያደርግ ነው።
በአጠቃላይ የበታች ፍርድ ቤቶች ለጉዲዩ አግባብነት ያለው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1689(1) ድንጋጌ ሁኖ እያለ አግባብነት የላለውን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2435 ድንጋጌ መሰረት በማድረግ የደረሱበት ድምዲሜ የውል አተረጎጎም ደንቦችንና የውል ውጤትን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.