No summary available.
ሰኔ 28 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች- እነ ጠና ወ/ሰማያት - ከጠበቃ ሀይለ አግዘው ጋር - ቀረቡ ተጠሪ- ወ/ሮ አልማዝ አሰጋኽኝ - ከጠበቃ አሰፊ ንጉሴ ጋር - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በሽያጭ ምክንያት ተከፈለ የተባለ ገንዘብ ይመለስልኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካቾች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም፡- አመልካቾች የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል መመዘኛና መስፈርት ባላሟላ ሰነድ ቤት ሽያጭ ውል ተዋውለዋል በማለት ነሐሴ 20 ቀን 1997 ዓ/ም በተጻፈ ከተጠሪ ላይ ብር 80,000.00 (ሰማኒያ ሺህ ብር) መቀበላቸውን ፣ ይህ ረቂቅ ውል እንጂ የሚፀና ውል ባለመሆኑ ተጠሪ ያገኙት ቤት ወይም ጥቅም የላለ መሆኑንና ገንዘቡንም ሉመልሱላቸው ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገልጸው ያላግባብ የተወሰደባቸውን ገንዘብ ከወሰደበት ጊዜ ጀምሮ ከታሰበው ብር 24,300.00 ሕጋዊ ወለድ ጋር በድምሩ ብር 104,300.00 (አንድ መቶ አራት ሺህ ሶስት መቶ ብር) ገንዘቡ ተከፍል እስከሚያልቅ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍሎቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የአሁኑ አመልካቾች በበኩላቸው ተጠሪ በጉዲዩ ላይ ክስ አቅርበው የመጨረሻ ፍርድ በተሰጠበት ጉዲይ ላይ በድጋሚ ክስ ለማቅረብ የማይችለ መሆኑን ፣ ጉዲዩም ያላግባብ መበልፀግ ነው የሚል በመሆኑ በሁለት አመት ይርጋ ቀሪ ላሆን እንደሚገባ ገልፀው በእነዚህ የመጀመሪያ ደረጃ መቃሚያ ነጥቦች ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም አመልካቾች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያነሱትን የይርጋ ጊዜ የተጠሪ ዲኝነት ጥያቄ ያላግባብ የተወሰደ ገንዘብ ይመለስልኝ የሚል በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2143(1) መሰረት የሚገዛ ነው በማለት በሁለት አመት የይርጋ ጊዜ ቀሪ ነው በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካቾች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ጉዲዩ በሁለት አመት የይርጋ ጊዜ የማይታገድ መሆኑን በመግለፅ በዚህ ረገድ በስር ፍርድ ቤት የተያዘውን ምክንያት በመሻር ለጉዲዩ አግባብነት ያለው የአስር አመት የይርጋ ጊዜ ነው በማለትና ክሱ የቀረበውም ይኸው ጊዜ ሳይልፍ መሆኑን አረጋግጦ እንዱሁም አከራካሪውን ገንዘብ አመልካቾች ከተጠሪ መቀበላቸው በፍሬ ነገር ደረጃ በስር ፍርድ ቤት መረጋገጡን ጠቅሶ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን ሽሮ ብር 80,000.00 (ሰማኒያ ሺህ ብር) ከግንቦት 24 ቀን 2002 ዓ/ም ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ ጋር አመልካቾች ለተጠሪ እንዱከፍለ ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካቾች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካቾች ጥቅምት 29 ቀን 2003 ዓ/ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል።
ይዘቱም ባጭሩ፡- የይርጋው ጊዜ ወደ አስር አመት ተብል መተርጎሙም ሆነ ተጠሪ የቤት ሽያጭ ስለመኖሩ አለመኖሩ በነበረው ክርክር አጠቃልለው ማቅረብ ይችለ የነበረውን ክርክር ነጥለው በኋላ አቅርበው ተቀባይነት ማግኘታቸው ክስን ነጣጥል ማቅረብ የማይቻል መሆኑን የሚደነግገውን የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 216 ድንጋጌን ያላገናዘበ በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም ተጠሪ ቀደም ሲል ክስ አቅርቦ ባስወሰነበት መዝገብ አጠቃልለው ማቅረብ የነበረባቸውን ነጣጥለው አቅርበዋል በማለት አመልካቾች ያቀረቡት ተቃውሞ መታለፈ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጓል። በዚህም መሰረት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በጽሐፍ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔና አግባብነት ከአላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው ጭብጥ፡- አመልካቾች ለተጠሪ ገንዘቡን እንዱመልሱ ተብል የተወሰነው በሕጉ ተቀባይነት ያለውን ማስረጃ መሰረት ባደረገ መንገድ ነው? ወይስ አይደለም? የሚል ነው።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ በአመልካቾች ላይ መጀመሪያ ክስ የመሰረቱት ውል እንዱፈርስና ገንዘባቸው ተመልሶላቸው ወደ ነበሩበት እንዱመለሱ የሚል ሲሆን ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውለ ረቂቅ ስለሆነ የክስ ምክንያት የለውም በማለት መዝገቡን መዝጋቱን ፣ ለአሁኑ ክርክር መሰረት የሆነውን ክስ ተጠሪ የመሰረቱት በረቂቅ ውለ መሰረት የተከፈለ ገንዘብ እንዱመለስላቸው መሆኑን ፣ ቤቱ ከአመልካቾች እጅ ያልወጣና በተጠሪ እጅ ያልገባ መሆኑን ነው።
No topics extracted.
በመሆኑም ተጠሪ አመልካቾች ቤት ሽጠውልኝ ብር 80,000.00 ከፍዬአለሁ ፣ ውል ይፍረስልኝ፤ወደ ነበርንበት እንድንመለስ ይደረግ የሚል ጥያቄ አቅርበውም ውለ ረቂቅ በመሆኑ የክስ ምክንያት የለውም ተብል በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ በመሰጠቱ ምክንያት ሁለተኛ ክስ ሉያቀርቡ የቻለት በፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር በሕግ ፉት የሚጸና ውል የለም (ረቂቅ ነው) ስለተባለ ያላግባብ የተከፈለ ገንዘብ ሉመለስልኝ ይገባል በማለት መሆኑን ፣ በግራ ቀኙ መካከል የቤት ሽያጭ ውል አለ የለም የሚለው ክርክርም በፍርድ ቤት ታይቶ ሕጋዊ የሆነ የቤት ሽያጭ ውል የላለ መሆኑ መረጋገጡን ከክርክሩ ሂደት በግልጽ ተረድተናል። ተጠሪ ለአሁኑ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነውን ጉዲይ ያቀረቡትም የቤት ሽያጭ ውል የለም ተብል ውሳኔ ከተሰጠ በሁዋላ ሲሆን አመልካቾች ገንዘቡን ስለመቀበላቸው በፍሬ ነገር ደረጃ ተረጋግጧል። የስር ፍርድ ቤት አመልካቾችን ለክሱ ኃላፉ ያደረገው ገንዘቡን ከተጠሪ ስለመቀበላቸው ተጠሪ በተገቢው ማስረጃ አስረድተዋል ፣ አመልካቾች ግን አላስተባበለም በሚል ምክንያት ነው። እንግዱህ ከላይ የተመለከቱት ነጥቦች በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጡት ሲሆን አመልካቾች የስር ፍርድ ቤት የስነ ሥርዓት ግድፈት ፈጽሟል በማለት የሚያቀርቡት አንደ ነጥብ ተጠሪ ሕጋዊ ያልሆነ የቤት ሽያጭ ውል ይፍረስልኝ ፣ ወደ ነበርንበት እንድንመለስ ይወሰንልኝ በማለት ክስ ሲያቀርቡ ገንዘቡን ያላግባብ ለአመልካቾች የከፈለ መሆኑን ገልጸው ገንዘቡ እንዱመለስላቸው በአማራጭ ዲኝነት መጠየቅ ሲገባቸው እና ተጠሪ ቀደም ሲል በተመሳሳይ ጉዲይ ክስ ሲመሰርቱ ይህንኑ ክስ አጠቃልለው ሉከሱ ሲገባ ቀንሰው ባስቀሩት ገንዘብ ላይ ድጋሚ ክስ እንዲይመሰርቱ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 216 ይከለክላቸዋል የሚል መቃወሚያ አቅርበው መታለፈን ነው። በመሆኑም ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ በተያዘው መሰረት የተጠሪ ክስ በተጠቀሰው የሥነ ሥርዓት ድንጋጌ ውድቅ ላደረግ ይገባል ወይ? የሚለውን ጭብጥ ፍ/ቤቱ መርምሯል። ለዚህ ይረዲ ዘንድ ድንጋጌውን መመልከቱ ተገቢ ነው።
የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 216 በአጠቃላይ ስለ ክስ አቀራረብና አገላለፅ የሚመለከት ድንጋጌ ነው። በተለይ ከተያዘው ጉዲይ ጋር አግባብነት ያለው የድንጋጌው ንዐስ ቁጥር 2 እና 3 ነው። የንዐስ ቁጥር 2 የመጀመሪያው ዓረፍተ ነገር አንድ ከሳሽ ክስ ሲያቀርብ ለክሱ ምክንያት የሆኑትን ነገሮች በሙለ አጠቃል ማቅረብ እንደሚገባ የሚናገር ሲሆን ንዐስ ቁጥር 3 ደግሞ አንድ ከሳሽ ሉከስበት ሲችል ሆነ ብል በመቀነስ ባስቀረው ሃብት ምክንያት እንደገና ላላ ክስ ለማቅረብ እንደማይፈቀድለት ይገልፃል። በመሆኑም ከሳሽ ክስ ሲያቀርብ ክሱን ለማቅረብ ምክንያት የሆኑትን ነገሮች በሙለ አጠቃል ማቅረብ የሚጠበቅበት ሲሆን ማቅረብ ሲችል ሆነ ብል ቀንሶ ባስቀረው ሃብት ላይ ግን ድጋሚ ክስ ሉያቀርብ እንደማይችል ከድንጋጌዎቹ መረዲት ይቻላል።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመጣ የቤት ሽያጭ ውልን አስመልክቶ ክርክሩ የቀረበበት አግባብ በተጠሪ በኩል የቀረበው የቤት ሽያጭ ውል ይፍረስልኝ ፣ ወደነበርንበት እንድንመለስ ይደረግልኝ የሚል ክስ በመቅረቡ በመሆኑና በሕጉ አግባብ የተደረገ የቤት ሽያጭ ውል የለም ፣ ዉለ ረቂቅ ስለሆነ የክስ ምክንያት የለውም ተብል በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድምዲሜ ላይ የተደረሰ በመሆኑ ተጠሪ በሽያጩ ምክንያት ለአመልካቾች የሰጡትን ገንዘብ ሉመለስልኝ ይገባል በማለት ጥያቄ ከማቅረብና በማናቸውም ማስረጃ ከማስረዲት የማይከለክል መሆኑን ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1808(2) ፣ 1815 ፣ 2001 እስከ 2019 እንዱሁም ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2162 እና 2164 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ በመሆኑ በክስ አቀራረብ ሥርዓት ላይ መሰረታዊ የሆነ የሥነ ስርዓት ግድፈት ተፈጽሟል ለማለት የሚያስችል አይደለም። ተጠሪ ቀድሞ ከመሰረቱት የክስ ይዘትና ከጠየቁት ዲኝነት አንፃር ውለ ረቂቅ በመሆኑ የክስ ምክንያት የለውም ተብል በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከተሰጠው ውሳኔ አኳያ ሲታይ የሽያጭ ገንዘቡን ሆነ ብለው ትተዋል ፣ ወይም በክሱ ሉጠቃለል የሚችል ሀብት ቀንሰው አስቀርተው ላላ ጊዜ ክስ መስርተዋል ለማለት የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት የለም። በመሆኑም በዚህ ረገድ አመልካቾች ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት ያለው ሁኖ አላገኘነውም። በአጠቃላይ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶች መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የላለበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1)መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።