No summary available.
ሰኔ 28 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አል ናይል ቢዝነስ ግሩኘ ኃ/የተ/የግል ማህበር ጠበቃ አቶ ዓለማየሁ ተፈሪ ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ መንገድች ባለስልጣን ነገረ ፈጅ ብርሃነ ደስታ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ በመዝገብ ያቀረበውን ክስና አመልካች በተጠሪ ላይ በመዝገብ ያቀረበውን ክስ በማጣመር በመዝገብ በማየት ሰኔ 12 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ውሣኔ ሰጥቷል።
በውለ ሁለተኛው ክፍል ተከሣሽ ከደገሀቡር እስከ ቀብራደሀር ከቀብራደሀር እስከ ሰላዩ ባለው ቦታ ጥልቀታቸው ሁለት መቶ ሀምሣ የሆኑ ስምንት ጉድጓድች ቆፍሮና አጠናቅቆ በመቶ ሰማኒያ ቀን ውስጥ ማለትም ግንቦት 29 ቀን 1999 ዓ.ም ለከሣሽ ለማስረከብ ተስማምቷል። ተከሣሽ ቆፍሮ ያጠናቀቀው ሁለት ጉድጓድ ሲሆን እነርሡም ቢሆኑ በውለ መሰረት የተሰሩ አይደለም። ተከሣሽ ያለከሣሽ ፈቃድ ሥራውን ለንዐስ ተቋራጭ በመስጠቱ ውለ ተቀርጧል። ስለሆነም ተከሣሽ በገባው የውሀ ጉድጓድ ቆፊሮ ሥራ ውል መሰረት ግዳታውን ያልፈፀመ በመሆኑ ከከሣሽ የወሰደውን ብር 1,838,592.27/አንድ ሚሉዮን ስምንት መቶ ሰላሣ ስምንት ሺ አምስት መቶ ዘጠና ሁለት ብር ከሃያ ሰባት ሣንቲም/ እንዱመልስ እንዱወሰንልኝ። ከዚህ በተጨማሪ የስራ ውለን በአግባቡ ባለመፈፀሙ ምክንያት ከሣሽ ጨረታ አውጥቶ ሥራውን ለላላ ተቋራጭ ሰጥቷል። ሥራው ለላላ ተቋራጭ ሲሰጥ ብር 2,7ዐ8,219/ሁለት ሚሉዮን ሰባት መቶ ስምንት ሺ ሁለት መቶ አሥራ ዘጠኝ ብር/ ከበፉተኛው ውል ብልጫ ያለው ገንዘብ ለመክፈል ተገድደናል።
ስለዚህ ተከሣሽ ይህንን በልዩነት የተጠየቅነውን ገንዘብ እንዱከፍል ይወሰንልን እንዱሁም ተከሣሽ በውለ በተገለፀው ጊዜ ውስጥ ሥራው ለዘገየበት አንድ ፏርሰንት በየቀኑ መቀጫ ለመክፈል የተስማማ በመሆኑ ብር 1,057,070.93/አንድ ሚሉዮን ሀምሣ ሰባት ሺህ ሰባ ብር ከዘጠና ሶስት ሣንቲም/ የመክፈል ከውል የመነጨ ግዳታ አለበት። ስለሆነም ተከሣሽ በድምሩ ብር 5,6ዐ3,532.52/አምስት ሚሉዮን ስድስት መቶ ሶስት ሺ አምስት መቶ ሰላሣ ሁለት ብር ከሀምሣ ሁለት ብር ከሀምሣ ሁለት ሣንቲም/ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል። ተጠሪ ተገቢ ናቸው የሚላቸውን ማስረጃዎች አቅርቧል።
አመልካች በተከሣሽነት ቀርቦ ከሣሽ ሥራውን በወቅቱ ያላስረከበና ሥራው እንዱጀመር ሁኔታዎችን ያላመቻቸ በመሆኑ ተከሣሽ መቀጫ እንዱከፍል ያቀረበው ጥያቄ ተገቢነት የለውም።
ተከሣሽ በውለ መሰረት በውለ ክፍል አንድ የተገለፁትን ሁለት ጉድጓድች በወቅቱ ቆፍሮ አጠናቅቋል። በውለ ሁለተኛው ክፍል ከተገለፁት ጉድጓድች አንድ ጉድጓድ ቆፍሯል። ሶስተኛው ጉድጓድ ሁለት መቶ ሃምሣ ሜትር ጥልቀት ተቆፍሯል። ውሃ ላይ ለመድረስ አስተላለፉ ቱቦ እንዱገባለት ተከሣሽ ለከሣሽ ሃሣብ ያቀረበለት ቢሆንም አልተቀበለውም። የዱዛይን ሥራ ለንዐስ ተቋራጭ የሰጠነው ከሣሽ አውቆትና ፈቃደኛ በመሆኑ ነው። ሰባት ጉድጓድች አልተሰሩም። ሰባት ጉድጓድች ያልተሰሩት በወቅቱ በአካባቢው የፀጥታ ችግር ስለነበረና ከሣሸ ሥራውን በቅርበት የሚከታተል ክፍያ የሚያፀድቅ መሀንዱስ ባለመመደቡ ነው። አመልካች ውለን ያፈረሰው በራሱ ምክንያትና ጥፊት በመሆኑ ለተጨማሪ ዋጋ ክፍያ እንዱሸፍን ያቀረበው ጥያቄ ተገቢነት የለውም በማለት የተከራከረ ሲሆን ተገቢ ነው የሚላቸውን ማስረጃዎች አቅርቧል።
ከሣሽ/አመልካች/ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ ከተከሣሽ ጋር በነበረኝ የውሀ ጉድጓድ ቁፊሮ ውል መሰረት በውለ ክፍል አንድ የተመለከቱትን ሁለት ጉድጓድች ሙለ በሙለ ቆፍሬ አጠናቅቄያለሁ። በውለ ሁለተኛ ክፍል ከተገለፁት ስምንት ጉድጓድች አንድ ጉድጓድ በውለ መሰረት ቆፍሬአለሁ። ተከሣሽ ለሰራሁት ሥራ ክፍያ ያልፈፀመልኝ ሲሆን በወቅቱ ኢንጅነር አልመደበም። ተከሣሽ የውለ ጊዜ ካለቀ ከስድስት ወር በኋላ የመደበው ኢንጅነር ሥራው በአግባቡ አልተሰራም በማለቱ ክፍያ ለመፈፀም ፈቃደኛ አልሆነም። ኢንጅነሩ ጋር እንድንነጋገር ያቀርብነውን ጥያቄ ተከሣሽ አልተቀበለውም። ስለሆነም ከሣሽ ለቆፈርኳቸው የሶስት ጉድጓድች ዋጋ ብር 2,776,728.22 /ሁለት ሚሉዮን ሰባት መቶ ሰባ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ ስምንት ብር ከሃያ ሁለት ሣንቲም/ ተከሣሽ እንዱከፍል ውሣኔ ይሰጥልኝ። ከዚህ ገንዘብ ውስጥ ከሣሽ ብር 1,838,298.12 ቅድሚያ ክፍያ ወስጃለሁ። ስለዚህ ተከሣሽ ብር 938,435.95/ዘጠኝ መቶ ስላሣ ስምንት ሺህ አራት መቶ ስላሣ አምስት ብር ከዘጠና አምስት ሣንቲም/ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል።
No topics extracted.
ተጠሪ በበኩለ በተከሣሽነት ቀርቦ ከሣሽ የሥራ ኘላንና ኘሮግራም ሣያወጣ ሥራውን ጀምሯል።
ከሣሽ ሁለት ጉድጓድ የቆፈረ ቢሆንም በውለ መሰረት በአግባቡ አልተሰሩም። ተከሣሽ ተቆጣጣሪ መሃንዱስ አለመመደቡ ከሣሽ ሥራውን በውለ መሰረት እንዲይሰራ የሚያደርግ ምክንያት አይደለም። ውለ የተቋረጠው በከሣሽ ጉድለት ነው ስለዚህ ከሣሽ ያቀረበው ክስ የህግ መሰረት የለውም በማለት መልስ አቅርቧል።
አመልካች የቆፈራቸው ሁለት ጉድጓድች በውለ መሰረት ያልተሰራ መሆኑን አሰሪው/ተጠሪ/ የገለፀ በመሆኑ ሥራ ተቋራጩ በቅድሚያ ከወሰደው ገንዘብ እንዱቀናነስለት ያቀረበው ክስ ተገቢነት የለውም። ስለዚህ አመልካች ከተጠሪ የወሰደውን ቅድመ ክፍያ ሙለ በሙለ ለተጠሪ የመመለስ ግዳታ አለበት። በአጠቃላይ አመልካች ብር 5,603,532.52/አምስት ሚሉዮን ስድስት መቶ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ስላሣ ሁለት ብር ከሃያ ሁለት ሣንቲም/ ለተጠሪ ይክፈል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍታብሓር ይግባኝ ሰሚ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ አመልካች በአካባቢው በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ነው ቀሪዎቹን ጉድጓድች ያልቆፈርኩት በማለት ያቀረበውን ክርክር ውድቅ አድርጎታል። በልላ በኩል ተጠሪ አመልካች በፅሐፍ ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ አለመስጠቱና ሥራውን የሚከታተል መሀንዱስ ባለመመደቡ ለውለ በአግባቡ አለመፈፀምና መቋረጥ አስተዋፅኦ እንዲበረከተ በመዘርዘር አመልካች ለመዘግየቱ ሉከፍል ከሚገባው የመቀጫ ገንዘብ ግማሹን ማለትም 528,520.47/አምስት መቶ ሃያ ስምንት ሺህ አምስት መቶ አስር ብር ከአርባ ሰባት ሣንቲም/ እንዱከፍል በማለት አሻሽል ወስኗል። ከዚህ በተጨማሪ ተጠሪ የሁለት ጉድጓድ ዋጋ በውለ መሰረት ለአመልካች የመክፈል ግዳታ አለበት በማለትም ወስኗል። በልላ በኩል ተጠሪ ሥራውን ለላላ የሥራ ተቋራጭ ሲሰጥ የተጠየቀውን የዋጋ ብልጫ ማለት ብር 2,7ዐ8,219 አመልካች ሙለ በሙለ ሉከፍል ይገባዋል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ተጠሪ በበኩለ ጥር 19 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተፃፈ መልስ በሥራው መዘግየት የሚከፈለው የመቀጫ ገንዘብ በሥራ ውለ ላይ በግልፅ የተወሰነና ተጠሪ ውለ ባለመፈፀሙ ለደረሰበት እርግጠኛ ጉዲት ከሚጠይቀው ገንዘብ የተለየ ነው። አመልካች የውል ግዳታውን ባለመፈፀሙ የተቋረጠው የቀሪ ጉድጓድ ሥራ ላላ ተጫራች እንዱያጠናቅቀው ተጠሪ የሰጠው አመልካች ጋር በተደረገው ውል ሣይሰሩ ለቀሩት 7/ሰባት/ ጉድጓድች ብቻ ነው። በአመልካች የተሰሩት በሁለተኛው ጨረታ አልተካተቱም በመሆኑም አመልካች ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰራሁትን ሥራ ግምት ውስጥ ሣያስገባ ካሣ እንዱከፍል ወስኖብኛል በማለት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተገቢነት የላለው ነው።
አመልካች መቀጫው ከተቀነሰ ጉዲቱንም እኔ ብቻ እንድከፍል መወሰኑ ስህተት ነው በማለት ያቀረቡት አቤቱታ የፍርድ ቤቱ ሥልጣንን ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ተከራክሯል። አመልካች የካቲት 4 ቀን 2ዐዐ3 ዓ/ም በተፃፈ የመልስ መልስ የዋጋ ልዩነት የታየው በወቅቱ ባለው የዋጋ ንረት ምክንያት በመሆኑ አመልካች ተጠያቂ ላሆን አይገባውም። የዋጋ ልዩነቱን አመልካች ይክፈል እንኳን ቢባል ተጠሪ ለውለ አለመፈፀም አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን ይግባኝ ሰሚው ችልት ያረጋገጠ በመሆኑ እንደሀላፉነቱ መጠን ኪሣራው ሉቀነስ ይገባዋል በማለት ተከራክሯል።
ከላይ የያዝነውን ጭብጥ በአግባቡ ለመወሰን በመጀመሪያ አመልካችና ተጠሪ ህዲር 15 ቀን 1999 ዓ.ም አድርገውት የነበረውን የውሃ ጉድጓድ ሥራ ውል አፈፃፀም ለማስረዲት ያቀረቡትን ክርክርና ማስረጃ በመመርመር ይግባኝ ሰሚው ችልት በፍሬ ጉዲይ ደረጃ የደረሰባቸውን መደምደሚያዎችና አመልካችና ተጠሪ በሰበር ደረጃ የማይካካደባቸውን ነጥቦች በዝርዝር ማየት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
6.1 የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች ከተጠሪ ጋር ያደረግኩትን የሥራ ውል በአግባቡ ያልፈፀምኩት በአካባቢው የፀጥታ ችግር የነበረ በመሆኑና ተጠሪ በውለ መሰረት ተቆጣጣሪ መሀንዱስ ባለመመደቡ ነው። ስለሆነም አመልካች ለውለ መዘግየትም ሆነ ቀሪው የውለ ክፍል አለመፈፀም ምንም አይነት ተጠያቂነት ስለላለብኝ የመቀጫ ገንዘብም ሆነ ኪሣራ ለተጠሪ የመክፈል ሀላፉነት የለብኝም በማለት ያቀረበውን ክርክር ሙለ በሙለ አልተቀበለውም። ይግባኝ ሰሚው ችልት ለሥራ ውለ አፈፃፀም መዘግየትና መቋረጥ የአመልካች ጥፊትና አስተዋፅኦ ያለበት መሆኑን ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣኑን በመጠቀም እንዲረጋገጠ በውሣኔው በግልፅ አስፍሮታል። በልላ በኩል ይግባኝ ሰሚው ችልት የሥራ ውለ በአግባቡ አለመፈፀምና ለውለ መቋረጥ አመልካች ብቻ ሣይሆን በተጠሪ በኩል የተፈፀመ ጥፊትና አስተዋፅኦ ያለ መሆኑን በተለይም አመልካች በሥራ ውለ መሰረት ተቆጣጣሪ መሃንዱስ እንዱመድብለት በተደጋጋሚ በፅሐፍ ላቀረበለት ጥያቄ ተጠሪ መልስ ያልሰጠ መሆኑን በማስረጃ እንዲረጋገጠ በውሣኔው ገልፆል።
በልላ አገላለፅ ይግባኝ ሰሚው ችልት በአመልካችና በተጠሪ መካከል ተደርጎ የነበረው የውሀ ጉድጓድ ሥራ ውል አፈፃፀም ለመዘግየቱም ሆነ ለውለ መቋረጥ አመልካችና ተጠሪ የየበኩላቸውን አስተዋፅኦ ያበረከቱ መሆኑን በግራ ቀኙ የቀረበውን ክርክርና ማስረጃ በመመዘን በውሣኔው አረጋግጧል። በዚህ ምክንያት ለውለ አፈፃፀም መዘግየት በሥራ ውለ መክፈል የሚገባውን የመቀጫ ገንዘብ ሙለውን ሣይሆን ግማሹን /ሃምሣ ፏርሰንቱን/ ብቻ የመክፈል ግዳታና ሀላፉነት አለበት በማለት የሥር ፍርድ ቤት አመልካች ለተጠሪ ብር 1,057,070.93 የመቀጫ ገንዘብ ይክፈል በማለት የሰጠውን ውሣኔ በማሻሻል አመልካች ግማሹን ብቻ ማለትም ብር 528,510.47 የመቀጫ ገንዘብ ለተጠሪ የመክፈል ግዳታና ሀላፉነት አለበት በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች የሚከራከረው ለውለ አለመፈፀምና መዘግየት የተጠሪ ጥፊትና አስተዋፅኦ እንዲለበት በፍሬ ጉዲይ ደረጃ ከተረጋገጠ፣ ውጤቱ የመቀጫ ገንዘብ በመቀነስ ብቻ የሚወሰን አይደለም በማለት ነው። ተጠሪ በበኩለ ሥልጣኑ የዳኞች በመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ችልት የመቀጫውን ገንዘብ በመቀነስ ብቻ መወሰኑ ተገቢ ነው የሚል መከራከሪያ አቅርቧል። በእኛ በኩል አመልካችና ተጠሪ የሚከራከሩበትን ይህንን መሰረታዊ ነጥብ የፍታብሓር ህጉ የመንግስት ሥራዎችን በተቋራጭ ስለማሥራት የተደነገጉትን ልዩ የህግ ድንጋጌዎችና ላልች አግባብነት ካላቸው የህግ ማዕቀፍች መሰረት በማድረግ መመርመሩ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
አንድን ሥራ ለሥራ ተቋራጭ የሰጠ የመንግስት መሥሪያ ቤት በራሱ ጥፊት ጉዲት አድርሶ እንደሆነ ወይም ተቋራጩ ውለን ለጊዜው እንዲይፈፅም አግድት እንደሆነ የሥራ ተቋራጩ ኪሣራ የማግኘት መብት ያለው መሆኑን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 3259 ንዐስ አንቀፅ 2 ይደነግጋል። ከሁለም በላይ የሥራው አሰሪ የሆነው የመንግስት መሥሪያ ቤት ጥፊት ወይም የመብት መተላለፍ ባያደርግም አድራጎቱ የሥራ ተቋራጩን ሥራ መደበኛ አፈፃፀም ከባድ ያደረገበት እንደሆነ ለሥራ ተቋራጩ ኪሣራ የመክፈል ሀላፉነት እንዲለበት በፍታብሓር ህግ ቁጥር 3259 ንዐስ አንቀፅ 3 በግልፅ ተደንግጓል። ተጠሪ በሥራ ውለ መሰረት ሥራውን የሚከታተል መሀንዱስ ባለመመደቡና አመልካች በፅሐፍ ለጠየቃቸው ጥያቄዎች ወቅታዊ ምላሽ ባለመስጠቱ ለሥራ ውለ መዘግየትና ለውለ አለመፈፀም የበኩለን አስተዋፅኦ እንዲበረከተ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ያረጋገጠው ፍሬ ጉዲይ ህጋዊ ዉጤትም በመቀጫ ገንዘብ ብቻ የሚወሰን እንዲልሆነና ተጠሪ ለአመልካች ካሣ የመክፈል ሀላፉነት ያለበት መሆኑን ከላይ የተጠቀሱትን ልዩ የህግ ድንጋጌዎች ይዘት መንፈስና ዓላማ በማገናዘብ ለመረዲት ይቻላል። በያዝነው ጉዲይ አመልካች ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ ተጠሪ ለውለ አፈፃፀም መዘግየትና ለውለ መቋረጠ የበኩለን አስተዋፅኦ ያበረከተ ስለሆነ ኪሣራ ወይም ካሣ ሉከፍለኝ ይገባል የሚል የዲኝነት ጥያቄ አላቀረበም። በልላ በኩል አመልካች በተጠሪ በኩል ተፈፅሟል የሚላቸውን ጥፊቶችና ጉድለቶች በመዘርዘር ተጠሪ ላቀረበው የኪሣራ ጥያቄ ሀላፉ ልሆን አይገባኝም በማለት የተከራከረ መሆኑን ከሥር ፍርድ ቤትና ከይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሣኔ ግልባጭ ተገንዝበናል።
ስለሆነም ይግባኝ ሰሚው ችልት ለውለ በአግባቡ አለመፈፀምና መዘግየት የተጠሪ ጥፊትና አስተዋፅኦ አለበት በማለት በፍሬ ጉዲይ ደረጃ ከደመደመ በኋላ የዚህን መደምደሚያውን የአመልካችን የመከላከያ መልስ ህጋዊ ውጤት የፍታብሓር ህግ ቁጥር 3259 ንዐስ አንቀፅ 2 እና ንዐስ አንቀፅ 3 ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ አለመመዘኑ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
አመልካች የሥራ ውለ በመዘግየቱና ባለመፈፀሙ የመቀጫ ገንዘብ እንዱከፍል ተወስኖብኛል። ይህ ከሆነ ለተጠሪ ኪሣራ የመክፈል ሀላፉነት የለብኝም በማለት የተከራከረ ሲሆን ተጠሪ በበኩለ አመልካች የመቀጫ ገንዘብ እንዱከፍል መወሰኑ ውለ ባለመፈፀሙ ተጠሪ የደረሰበትን ኪሣራ ከመክፈል ነፃ አያደርገውም በማለት ተከራክሯል። ይህም የአመልካችና የተጠሪ ክርክር የመንግስት ሥራዎችን ለመሥራት ስለመቋረጥ ከተደነገጉት ልዩ ድንጋጌዎችን አንፃርና መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። በተለይም የአመልካች ክርክር ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 3261 ድንጋጌዎችን አንፃር መሰረት በማድረግ መታየት ያለበት ሲሆን ከሥራ ውጭ የተደረገው ሥራ ተቀራጭ ሥራው ለአዱስ ተቋራጭ በጨረታ የተሰጠ ሲሆን አዱሱ የሥራ ውል በመሥሪያ ቤቱ የሚያስከትለውን ከባድ የሆነውን ወጭ መቻል እንዲለበት የፍታብሓር ህግ ቁጥር 3261 ንዐስ አንቀፅ 2 በግልፅና አስገዲጅነት ባለው ሁኔታ ይደነግጋል። ስለሆነም አመልካች ለሥራው መዘግየትና አለመፈፀም መቀጫ እንድከፍል የተወሰነ ስለሆነ ቀሪው ሥራው ለላላ ሥራ ተቋራጭ ሲሰጥ ተጠሪ የደረሰበትን ኪሣራ የመክፈል ግዳታ ያለብኝም በማለት ያቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀውን ድንጋጌ ያላገናዘብ በመሆኑ አልተቀበልነውም።
ከላይ በዝርዝር እንደገለፅነው ተጠሪ የሥራ ውለ ለመዘግየቱና ውለ በአግባቡ ላለመፈፀሙ ላደረገው አስተዋፅኦ የመቀጫ ገንዘብ በመቀነስ ብቻ የሚወሰን ሣይሆን ተጠሪን ተጨማሪ ሀላፉነት የሚያስከትልበት ስለመሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 3259 ንዐስ አንቀፅ 2 እና ንዐስ አንቀፅ 3 ተደንግጓል። በልላ በኩል ለውለ አለመፈፀምና መዘግየት ጥፊትና አስተዋፅኦ ያበረከተ መሆኑ የተረጋገጠበት አመልካች ተጠሪ ሥራውን ለላላ ተቋራጭ ሲሰጥ የወጣውን ወጭ የመጋራት ወይም መሸፈን ግዳታ እንዲለበት በፍታብሓር ህግ ቁጥር 3261 ንዐስ አንቀፅ 2 ተደንግጓል። አመልካች ተጠሪ ሥራውን ለላላ ሥራ ተቋራጭ ሲሰጥ የደረሰበትን ኪሣራ ሙለ በሙለ እንዱሸፍን በፍታብሓር ህግ ቁጥር 3261 ንዐስ አንቀፅ 2 መሰረት የሚገደደው ለሥራ ውለ መዘግየትና አለመፈፀም ተጠሪ ያበረከተው አስተዋፅኦ አለመኖሩ ሲረጋገጥ እንደሆነ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 3259 ንዐስ አንቀፅ 3 ድንጋጌ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 3261 ንዐስ አንቀፅ 2 ድንጋጌ የጣምራ ይዘት ተፈፃሚነትና ውጤትን በማገንዘብ ለመረዲት ይቻላል። አመልካች ለውለ አለመፈፀምና መዘገየት ብቸኛ ተጠያቂና ሀላፉ አለመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ችልት ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣኑን በመጠቀም ካረጋገጠ በኋላ በውለ አለመፈፀም ምክንያት በተጠሪ ላይ የደረሰውን ኪሣራ ሙለ በሙለ አመልካች እንዱሸፍን የተሰጠው ውሣኔ ከላይ የተገለፁትን የህግ ድንጋጌዎች ይዘትና ድንጋጌዎቹ በአንድ ላይ ሲፈፀሙ የሚያስከትለትን ውጤት ያገናዘበ ሆኖ አላገኘነውም።
ስለሆነም ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠውን ውሣኔ በማሻሻል አመልካች ሉከፍል የሚገባው ተጠሪ ቀሪውን ሥራ ለላላ ተቋራጭ ሲሰጥ የደረሰበትን ኪሣራ ማለትም ብር 2,7ዐ8,219/ሁለት ሚሉዮን ሰባት መቶ ስምንት ሺ ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ ብር / ሣይሆን የዚህን ግማሽ/ሀምሣ ፏርሰንት / በልላ አነጋገር ብር 1,354,1ዐ9.50 /አንድ ሚሉዮን ሶስት መቶ ሃምሣ አራት ሺ አንድ መቶ ዘጠኝ ብር ከሀምሣ ሣንቲም / ብቻ ነው በማለት ወስነናል።
6.2 አመልካች የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ኪሣራው ለተጠሪ እንዱከፈል የወሰነው አመልካች ምንም አይነት ሥራ እንዲልሰራ በመቁጠርና አመልካች ሰርቶ ለተጠሪ ያሥረከባቸውን የተወሰኑ ሥራዎች ከግንዛቤ ውስጥ ሣያስገባና ሑሳቡን ሣያቀናንስ ነው በማለት ክርክር በሰበር አቤቱታው አቅርቧል። ተጠሪ በበኩለ ለዚህ ሰበር ችልት ጥር 19 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በፅሐፍ በሰጠው መልስ ጨረታ ወጥቶ ለላላ የሥራ ተቋራጭ የተሰጡትን የውሀ ጉድጓድ ቁፊሮ ሥራ መጠን በተመለከተ በሥር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ካቀረበው ክርክር የተለየ መልሥ ሰጥቷል። ተጠሪ ለሰበር ችልት በሰጠው መልስ በተራ ቁጥር 3 ላይ ለላላ የሥራ ተቀራጭ በጨረታ የተሰጠው የሰባት /7/ ውሀ ጉድጓድ ቁፊሮ ሥራ መሆኑንና ይህም በአመልካች የቁፊሮ ሥራ የተሰራላቸውን የውሃ ጉድጓድች እንደማይጨምር በመግለፅ ተከራክሯል።
ይህም የተጠሪ ክርክር አመልካች በሥራ ውለ መሰረት ጥልቀታቸው ሁለት መቶ ሃምሣ ሜትር የሆነ የሶስት የውሀ ጉድጓድ ቁፊሮ ሥራ ሰርቻለሁ በማለት አመልካች ከሥር ጀምሮ ያቀረበውን ክርክር በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 235 ንዐስ አንቀፅ 2 መሰረት እንዲመነ የሚያስቆጥረው ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካች ሁለት የውሀ ጉድጓድ በመቆፈሩ እንጅ ሶስት የውሀ ጉድጓድ በውለ መሰረት የቆፈረ መሆኑን አላስረዲም በሚል ምክንያት ተጠሪ ለአመልካች ሁለት የውሀ ጉድጓድ የቆፈረበትን ዋጋ ይክፈል በማለት የሰጠውን ውሣኔ ተጠሪ በሰበር ካቀረበው ክርክር አንፃር በመመዘንና በማሻሻል ተጠሪ አመልካች ሶስት የውሃ ጉድጓድ የቆፈረበትን ዋጋ በውለ መሰረት የመክፈል ሀላፉነት አለበት በማለት ወስነናል።
6.3 በሥር ፍርድ ቤት በይግባኝና በሰበር በተሰጠው ውሣኔ መሰረት አመልካች ለተጠሪ ሉመልስ የሚገባው በቅድመ ክፍያ የወሰደውን ገንዘብ ያለመሆኑ ተረጋግጧል። ከዚህ በተጨማሪ ይግባኝ ሰሚው ችልት በሰጠው ውሣኔና በዚህ ሰበር ችልት በተሰጠው ውሣኔ መሰረት አመልካች ለተጠሪ መክፈል የሚገባው የመቀጫ ገንዘብና ኪሣራ /ካሣ/ እንዲለ በውሣኔው ተገልፆል። በልላ በኩል ተጠሪ አመልካች ለሰራው የሶስት ጉድጓድ ቁፊሮ ሥራ በውለ መሰረት ተገቢውን ዋጋ እንዱከፍል ይህ ሰበር ችልት ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠውን ውሣኔ በማሻሻል ውሣኔ ሰጥቷል።
በውሣኔው አመልካች ከተጠሪ እንደዚሁም ተጠሪ ከአመልካች የሚጠይቁት የገንዘብ ዕዲ ያለ መሆኑ ተረጋግጧል። ስለሆነም ዕዲውን በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 236 መሰረት በማቻቻል ተራፉ ገንዘብ የሚጠይቀውና በዚህ ፍርድ የፍርድ ባለመብት የሚሆነውን ወገን ለመለየት ፍርደ ለአፈፃፀም ምቹ በሚሆንበት መንገድ ለመስጠት ይቻል ዘንድ ጉዲዩን በዝርዝር ማየቱ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
ሀ/ አመልካች ለተጠሪ መክፈል ያለበት ገንዘብ አመልካች ከተጠሪ ብር 1,838,292.27 /አንድ ሚሉዮን ስምንት መቶ ሰላሣ ስምንት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ሁለት ብር ከሃያ ሰባት ሣንቲም/ በቅድሚያ ክፍያ የወሰደ መሆኑን ያልካደና በማመን የተከራከረ በመሆኑ ይህንን ገንዘብ አመልካች ለተጠሪ የመመለስ ግዳታና ሀላፉነት አለበት በማለት ወስነናል።
አመልካች ለሥራ ውለ መዘግየትና ለውለ አለመፈፀም በከፉል ሀላፉነት ያለበት መሆኑን በማረጋገጥ ለተጠሪ ብር 528,52ዐ.47 /አምስት መቶ ሃያ ስምንት ሺህ አምስት መቶ አስር ብር ከአርባ ሰባት ሣንቲም/ ለተጠሪ እንዱከፍል ይግባኝ ሰሚው ችልት በሰጠው ውሣኔ መሰረት የመክፈል ሀላፉነት አለበት።
ተጠሪ ለውለ መዘግየትና አለመፈፀም የበኩለን አስተዋፅኦ ያደረገ መሆኑ በፍሬ ጉዲይ ደረጃ ስለተረጋገጠ አመልካች በሥራ ውለ መሰረት ያልሰራውን ቀሪ ሰባት የውሃ ጉድጓድ ቁፊሮ ሥራ ተጠሪ ለላላ ተቋራጭ ሲሰጥ ከደረሰበት ኪሣራ ግማሹን ብቻ አመልካች የመሸፈን ሀላፉነት እንዲለበት ይኸ ሰበር ችልት የይግባኝ ሰሚውን ውሣኔ በማሻሻል ውሣኔ ሰጥቷል።
ስለሆነም አመልካች ብር 1,354,109.50/አንድ ሚሉዮን ሶስት መቶ ሃምሣ አራት ሺህ አንድ መቶ ዘጠኝ ብር ከሃምሣ ሣንቲም/ ለተጠሪ ካሣ ይክፈል በማለት ወስነናል። በአጠቃላይ አመልካች ብር 3,72ዐ,918.09 /ሶስት ሚሉዮን ሰባት መቶ ሃያ ሺህ ዘጠኝ መቶ አሥራ ስምንት ብር ከዜሮ ዘጠኝ ሣንቲም/ የመክፈል ሀላፉነት አለበት በማለት ወስነናል።
ለ/ ተጠሪ ለአመልካች የሚከፍለው ገንዘብ አመልካች ሶስት የውሃ ጉድጓድችን በውለ መሰረት የሰራ መሆኑን ተጠሪ በማረጋገጡ አመልካች የሶስት ውሃ ጉድጓድ ቁፊሮ ሥራ ዋጋ ለአመልካች የመክፈል ሃላፉነት እንዲለበት በዚህ ችልት በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሣኔ በማሻሻል ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች ሶስቱን ጉድጓድች ለሰራበት ተጠሪ በውለ መሰረት ሉከፍለው የሚገባው ብር 2,776,728.22/ሁለት ሚሉዮን ሰባት መቶ ሰባ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ ስምንት ብር ከሃያ ሁለት ሣንቲም/ እንደሆነ በሥር ፍርድ ቤት ተከራክሯል። ተጠሪ ዋጋው በውለ መሰረት ተሰልቶ የቀረበ አይደለም የሚል ክርክር አላቀረበም።
ስለሆነም ተጠሪ ከላይ መጠኑ የተገለፀውን ገንዘብ ለአመልካች የመክፈል ሃላፉነት አለበት በማለት ወስነናል።
በአጠቃላይ አመልካች ለተጠሪ ከሚከፍለው ብር 3,720,918.09 /ሶስት ሚሉዮን ሰባት መቶ ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ አሥራ ስምንት ብር ከዜሮ ዘጠኝ ሣንቲም/ ውስጥ ተጠሪ ለአመልካች የሚከፍለው ብር 2,776,728.22 /ሁለት ሚሉዮን ሰባት መቶ ሰባ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ ስምንት ብር ከሃያ ሁለት ሣንቲም/ ተቀንሶ ፣ /ተቻችል/ የሚቀረውን ብር 944,189.87/ዘጠኝ መቶ አርባ አራት ሺህ አንድ መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ብር ከሰማኒያ ሰባት ሣንቲም/ አመልካች ለተጠሪ ይክፈል በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ ተሻሽሎል።
ተጠሪ ለአመልካች መክፈል ያለበት ገንዘብ አመልካች ለተጠሪ ከሚከፍለው ገንዘብ ላይ ከላይ በውሣኔው በተገለፀው መሰረት ከተቀናንሶ የቀረውን ብር 944,189.89 /ዘጠኝ መቶ አርባ አራት ሺህ አንድ መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ብር ከሰማኒያ ሰባት ሣንቲም / አመልካች ለተጠሪ ይክፈል በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኑ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።