No summary available.
ሰኔ 14 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ታደሰ ደሞሬ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ጌታሁን ለቻሞ - የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የገንዘብ ክርክር ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም የአሁኑ ተጠሪ ሕዲር 26 ቀን 1998 ዓ.ም ጽፊው ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ ሰኔ 05 ቀን 1997 ዓ/ም ለአመልካች ብር 180,000.00(አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ) ለጊዜው በአደራ አስቀማጭነት መኪና ተገዝቶ አብረው ለመጠቀም ተነጋግረው የሰጡ መሆኑን ገልፀውና በዚህ አጋጣሚ ወደ አመልካች እጅ ገንዘቡ ከገባ በሁዋላ ገንዘቡን ለመመለስ አመልካች ሲጠየቁ ሉመልሱ ያልቻለ መሆኑን ጠቅሰው ገንዘቡን ከእነ ወለደ እንዱመልሱላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸው የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስም ተጠሪ ለክሱ መሰረት የሆነውን ገንዘብ በአደራ ያልሰጧቸው መሆኑን ገልጸውና ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸው ማስረጃዎች በተጠሪ በኩል ያልቀረቡባቸው መሆኑን ጠቅሰው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ጉዲዩን በመመርመር አመልካችን ለክሱ ኃላፉ በማድረግ ለክሱ መሰረት የሆነውን ገንዘብ ከነሕጋዊ ወለደ(9%) ለተጠሪ ሉከፍለ ይገባል በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሙለ በሙለ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች መስከረም 04 ቀን 2003 ዓ.ም በፃፈት በ2/ሁለት/ገፅ የሰበር ማመልከቻ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡-ተጠሪ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ገንዘብ በአደራ የሰጡ መሆኑ እየተገለጸ ለጉዲዩ መቅረብ የሚገባው ማስረጃ ሳይቀርብ በሰው ምስክሮች ቃል ለክሱ ኃላፉ ተደርገው መወሰኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2782፣2472 እና በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2471 እስከ 2489 ድረስ የተደነገጉትን የማስረጃ አቀራረብ ሥርዓቶች ፣ እንዱሁም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 248 ስር ስለጭብጥ አመሰራረት የተደነገገውን ሥርዓት ባላገናዘበ መልኩ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው።
የሰበር አቤቱታው ተመርምሮም ተጠሪ ለአመልካች ብር 180,000.00(አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ብር) በአደራ መስጠታቸው ስለተረጋገጠ ይክፈለ ተብል መወሰኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2472 እና 2782 ድንጋጌዎች አንፃር ሕጋዊ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ ላቀርብ ይገባዋል በመባለ ነው። በዚህም መሰረት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ሕዲር 27 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ 2/ሁለት/ ገፅ ማመልከቻ፡- ገንዘቡ በአደራ ለአመልካች ተሰጠ ተብል ክሱ ሲመሰረት የተገለፀው የአገላለፅ ጉዲይ ካልሆነ በስተቀር አደራ ተብል አልተረጋገጠም ፣ ገንዘቡ ለአመልካች የተሰጣቸው መኪናውን በጋራ ገዝቶ ለመጠቀም በሚል ሃሳብ ሁኖ ይኸው ተረጋግጦ የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ ምንም አይነት የሕግ ግድፈት የላለበት በመሆኑ ሉጸና ይገባል ሲለ መልሳቸውን ሰጥተዋል። አመልካችም ታህሳስ 20 ቀን 2003 ዓ.ም በፃፈት 2/ሁለት/ገፅ ማመልከቻ የመልስ መልሣቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጹሁፍ እና የቃል ክርክር የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል እንደመረመውም አመልካች ለክርክሩ መነሻ ለሆነው ገንዘብ ኃላፉነት አለባቸው ተብል መወሰኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2472 እና 2782 ድንጋጌዎች አንፃር ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
በመሰረቱ የፍትሐብሕር ግዳታ ከውል ወይም ከህግ ከሚመነጭ ግንኙነት ላይ የተመሰረተ ነው። ክስ አቅራቢው ወገን ደግሞ ይህንኑ በአግባቡ በመለየትና በመግለጽ የሚጠይቀውን ዲኝነት በዝርዝር የማቅረብ እንዱሁም የማስረዲት ግዳታ አለበት። በተያዘው ጉዲይ በአመልካችና በተጠሪ መሀከል የተፈጠረው ግንኙነት ምን እንደነበረ ከላይ በተመለከተው መልኩ የጥሬ ገንዘብ አደራ ሲሆን አመልካች በክስ አቤቱታቸው በዝርዝር ለይተውና ገልፀው ለተጠሪ ገንዘቡን በአደራ የሰጡ መሆኑን በማሳየት ክሱን መስርተዋል ፣ ክርክርም አድርገዋል። ስለሆነም ተጠሪ ከአመልካች ጋር አለኝ የሚለትን ግንኙነት በሕጉ አግባብ ላቀርብ በሚገባው ማስረጃ የማስረዲት ግዳታ ይኖርባቸዋል። ለክርክሩ መነሻ የሆነው ገንዘብ አመልካች ከተጠሪ ወሰደ የተባለት በአደራ ሲሆን አመልካች ደግሞ ይኸው ግንኙት ከተጠሪ ጋር የለኝም በማለት ተከራክረዋል። ስለሆነም የተጠሪ ክርክር መሰረት ያደረገው አደራ ስለመሆኑ ተገንዝበናል።
No topics extracted.
እንግዱህ ግንኙነቱ አደራ ነው ከተባለ በዚህ ረገድ የቀረበው ክርክርም ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች በመመልከት ሉስተናገድ የሚገባው ይሆናል።
በመሰረቱ የፍትሐብሕር ግንኙነት ዓይነት የተለያየ ሲሆን እያንዲንደ ግንኙነት የሚቋቋምበት ፣ ግንኙነቱ ክርክር ቢያስነሣ ተከራካሪዎቹ የሚለያዩባቸውን ነጥቦችን ለማስረዲት መቅረብ ያለበት የማስረጃ ዓይነት በህጉ የተወሰነ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ግንኙነቱ ክርክር ሲያስነሣ ተከራካሪዎቹ የሚለያዩባቸውን ነጥቦች የማስረዲት ሸክም በተከራካሪ ወገኖች በሚቀርበው የክርክር ይዘት አግባብነት ባለው ህግ የተወሰነ ነው። በልላ አገላለፅ የፍትሐብሕር ግንኙነቶች ክርክር ሲያስነሱ በምስክር ወይም በተለየ ማስረጃ መረጋገጥ ያለባቸው መሆኑ በህግ ተለይተው ተመልክተዋል። በመሆኑም ለእያንዲንደ የፍታሐብሓር ግንኙነት የማስረዲት ሸክም ያለበት ወገን በቀጥታ አግባብነትና ተፈፃሚነት ባለው በፍትሐብሕር ህጉ በታዘዘው የማስረጃ ዓይነት ማረጋገጥ አለበት። አደራ የፍታሐብሓር ግንኙነት የሚቋቋምበት አንደ ተግባር ነው።ይህ ተግባር ክርክር ሲያስነሣ የግንኙነቱን መኖር ማስረዲት የሚቻልበትን መንገድ ህጉ ለይቶ ወስኗል። የአደራ ጉዲይን በተመለከተ አግባብነት ያላቸው የፍታሐብሓር ህግ ድንጋጌዎች ቁጥር 2779 እና ተከታዬቹ ናቸው። የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2782(1) ድንጋጌ የገንዘብ አደራ ሁኖ ሲገኝ ላቀርብ የሚገባውን የማስረጃ አይነት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2472"ን" በማጣቀስ ምላሽ ይሰጣል። በዚህም መሰረት ለአደራ ተቀባዩ የተሰጠው እቃ ጥሬ ገንዘብ የሆነ እንደሆነ አደራ ተቀባዩ እንዱገለገልበት ፣ ተፈቅድለት ከሆነ ስለእንደዚህ ያለው ጉዲይ የአላቂ ነገርን ብድር የሚመለከቱ ደንቦች ተፈጻሚ እንደሚሆኑ ይገልፃል።
በመሆኑም በአደራ የተሰጠው እቃ አደራ ተቀባዩ እንዱገለገልበት የተፈቀደለት ገንዘብ ከሆነ ይህ ግንኙት የሚገዛው የአላቂ ነገር ብድርን በሚመለከቱ ደንቦች ይሆናል ማለት ነው። አደራ ሰጪው አደራ ተቀባዩ በገንዘቡ እንዱገለገልበት በግልፅ ሉፈቅድለት የሚችል ሲሆን ግልፅ ስምምነት ባይኖርም ገንዘቡ ለአደራ ተቀባዩ የተሰጠው ሳይታሸግና ሳይዘጋበት ከሆነ ተቀባዩ እንዱገለገልበት እንደተሰጠው የሚቆጠር መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2782(2) ድንጋጌ ያሳያል። ተጠሪ ለአመልካቹ የሰጡት ጥሬ ገንዘብ ሲሆን ገንዘቡን ተጠሪ አሽገው ወይም ዘግተው ለአመልካች የሰጡ መሆኑንም የተነሳ ክርክር የላለ በመሆኑ አመልካቹ ገንዘቡን እንዱገለገለበት በተጠሪ እንደተፈቀደ የሚቆጠር ነው። እንዱሁም ተጠሪ ገንዘቡ ለመኪና መግዣ ተሰጠ ይበለ እንጂ በስር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር 180,000.00(አንድ መቶ ሰማኒያ ሽህ ብር) ቆጥረው ለአመልካች በአደራ የሰጡ ስለመሆኑ ማስረጃ አቅርቤ አሰማለሁ በማለት ባቀረቡት ክርክር ማስረጃዎቹን አቅርበው በአደራ የሰጡ ስለመሆኑ ማስመስከራቸውን የስር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ በግልፅ የሚያሳይ መሆኑን ተመልክተናል። እንዱህ ከሆነ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ያለው ግንኙነት የሚገዛው የአላቂ ነገር ብድርን በሚመለከቱ የፍትሐብሕር ሕግ ደንቦች መሆኑ ግልፅ ይሆናል።
ወደ ሕጉ ስንመጣም የፍ/ህ/ቁ 2472(1) በብድር የተሰጠ ገንዘብ ከብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ በላይ ሲሆን የብድሩን ውል በጽሁፍ ወይም በፍርድ ቤት በተደረገ የእምነት ቃል ወይም መሃላ ካልሆነ በቀር ለማስረዲት አይቻልም በማለት የሚደነግግ ሲሆን ለብድር ውለ ላላ ማናቸውም ዓይነት ማስረጃ ማቅረብ የማይቻል ስለመሆኑ ደግሞ የተጠቃሹ አንቀፅ ንዐስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ በአስገዲጅ ሁኔታ ደንግጓል። ስለሆነም ከብር 500.00 በላይ የሆነ የገንዘብ ብድር ውል ለማስረዲት ተቀባይነት ያለው ማስረጃ በጽሁፍ ወይም በፍርድ ቤት በተደረገ እምነት ቃል ወይም መሃላ ብቻ ነው። በመሆኑም ከእነዚህ ማስረጃዎች ውጪ ላልች የማስረጃ ዓይነቶች ተቀባይነት የላላቸው መሆኑ በህጉ ተለይቶ መቀመጡን መገንዘብ ይቻላል። በዚህ ጉዲይ የተጠሪ ክርክር ብር 180,000.00 ለአመልካች ለጊዜው በአደራ ሰጥቼው ነው የሚል ሆኖ ይህንኑ በተመለከተ በህጉ አግባብ ተቀባይነት ያለውን የማስረጃ ዓይነት የማቅረብ ግዳታ የተወጡ ሁነው አልተገኙም። ተጠሪ ጉዲዩን ለማስረዲት ያቀረቡት የሰው ማስረጃዎችን ሲሆን የሰው ማስረጃ ደግሞ ለጉዲዩ ተቀባይነት ያለው(Admissible) ማስረጃ አይደለም። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ለተጠሪ ለክሱ መሰረት የሆነውን ገንዘብ ሉመልሱ ይገባል ወደ ሚለው ድምዲሜ የደረሱት ተቀባይነት የላላቸው ማስረጃዎች የሰጡትን የምስክርነት ቃል በመያዝ በፍ/ህ/ቁ 2782 ፣ 2472(1) እና (2) ድንጋጌዎች ስር የተቀመጠውን ሁኔታ ባላገናዘበ መልኩ ነው። ሲጠቃለልም ተጠሪ ገንዘቡን ለአመልካች ሰጠሁ የሚለበትን ምክንያት ተቀባይነት ያለውን የማስረጃ ዓይነት /admissible evidence/ በማቅረብ ያላስረደ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት የሚከተለውን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ ግንቦት 21 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 04 ቀን 2002 ዓ/ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348 (1) መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ለተጠሪ ብር 180,000.00/አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ብር/ ሉከፍለ የሚችለበት ሕጋዊ ምክንያት የለም ብለናል።
በክርክሩ ሂደት የወጡትን ወጪዎችንና ኪሣራዎችን ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።