No summary available.
ሰኔ 28 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ራፑድ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭ ድርጅት - ጠበቃ አብደወሀብ ረቢ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ኦርቢስ ንግድና ቴክኒክ ክፍል ሉሚትድ - ጠበቃ ግርማ ስላሴ አርአያ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የመኪና ሽያጭ ውል ጋር ተያይዞ የተነሳውን መኪናና ሉብሬ ልረከብ እንዱሁም የተቋረጠ ጥቅም ይከፈለኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ ላይ በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም፡-አመልካች የሰላዲ ቁጥር 3-07539 እና 3-09190 የሆኑ ሁለት መርቸዱስ ከባድ የጭነት ገልባጭ መኪናዎችን በ15-10-1993 ዓ.ም በተፈረመ የሽያጭ ውል ከተጠሪ ላይ በብር 1,620,000.00 (አንድ ሚሉዮን ስድስት መቶ ሃያ ሺህ ብር) ገዝቶ አብዛኛውን ገንዘብ ከከፈለ በሁዋላ ቀሪውን ብር 486,000.00 በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ከፍል ለማጠናቀቅ ይችል ዘንድ ቀናቸው ወደፉት ተደርጎ የተፃፈ ሁለት ቼኮችን ለተጠሪ በመስጠት ሁለቱን መኪኖች የተረከበ መሆኑን ፣ አመልካች ገዝቶ የተረከባቸው መኪኖች 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) ኪል ሜትር ከመጓዛቸው ወይም አመልካች ከተረከባቸው ከአንድ አመት በፉት ቴክኒካል የሆነ ብልሽት ስለገጠማቸው ተጠሪ በውለ መሰረት መኪኖቹን ለመጠገን ባለበት ግዳታ መሰረት መኪኖቹን ለጥገና ከጋራዡ ገብተው ተገቢው ጥገናም የተደረገላቸው መሆኑን ፣ ተጠሪ ለጥገና ከተረከባቸው ሁለቱ መኪኖች ውስጥ የሰ.ቁጥር 3-09190 አ.አ የሆነውን መኪና ጠግኖ ለአመልካች ሲያስረክብ የሰላዲ ቁጥር 3-07539 የሆነውን መኪናና የሁለቱን መኪኖች ሉብሬ ለአመልካች መልሶ ለማስረከብ ፈቃደኛ ሆኖ አለመገኘቱንና ለዚህ ተግባሩም የሰጠው ምክንያት ቀናቸው ወደፉት ተደርጎ በአመልካች በኩል የተጻፈት ቼኮች የመክፉያ ጊዜ የደረሰ ስለሆነ በቼኮቹ ላይ የሰፈረውን ገንዘብ ሳይከፈለኝ ሉብሬዎቹንም ሆነ መኪናውን አላስረክብም የሚል መሆኑን ፣ ሉብሬዎቹና መኪናው እንዱመለስለት አመልካች ማስጠንቀቂያ የሰጠ ቢሆንም ተጠሪ ፈቃደኛ አለመሆኑን ፣ ተጠሪ በቼኮቹ ላይ የሰፈረው ገንዘብ እንዱከፈለው በፍርድ ቤት ክስ መስርቶም ያስወሰነ መሆኑን ፣ ተጠሪ አንደን መኪና ከእነ ሉብሬው እንዱሁም ላላኛውን መኪና ሉብሬ አላግባብ በመያዙ ምክንያት የሰ/ቁጥር 3-07539 አ.አ የሆነው ገልባጭ መኪና ለጥገና በተጠሪ ጋራዥ ከገባበት ከሚያዝያ 06 ቀን 1995 ዓ/ም ጀምሮ በስር ፍርድ ቤት ክስ እስከ ቀረበበት እስከ ታህሳስ 15 ቀን 1997 ዓ/ም ድረስ እንዱሁም የሰ/ቁጥር 3-09190 የሆነው መኪና ሉብሬ በተጠሪ በመያዙ ምክንያት ለስምሪት ከከተማው ለመውጣት የሚያስችለውን ፈቃድ አጥቶ ለዘጠኝ ወራት ያህል ስራ በማቆሙ ምክንያት በድምሩ ብር 1,402,741.00 (አንድ ሚሉዮን አራት መቶ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ አርባ አንድ ብር) ገቢ ያጣ መሆኑን ዘርዝሮ ሉብሬውንና የተያዘውን መኪና ለአመልካች እንዱያስረክቡ ፣ የተቋረጠውን ጥቅምም እንዱከፍል ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪም በተከሳሽነቱ ቀርቦ ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃሚያ ነጥቦችንና የፍሬ ነገር ክርክሮችን በማንሳት ተከራክሯል። ተጠሪ በመጀመሪያ ደረጃ ያነሳው ነጥብ አመልካች ክስ የመሰረተው ቀድሞ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ስለመሆኑ የሚገልፅ ሲሆን በፍሬ ነገር ደረጃ ደግሞ የመኪኖቹን ዋጋ ቀሪ ሂሳብ ለመክፈል የተጠሰው ቼክ ካልተከፈለ ተጠሪ መኪኖቹን ወዱያውኑ በእጁ አስገብቶ ለሕዝብ በሐራጅ ለመሸጥ ይችላል በሚል በግራ ቀኙ መካከል ውል መደረጉን ፣ ሉብሬውንም በመያዣነት ተይዞ አመልካች ክላውድ ለማስደረግ ሲፈልግ ሲሰጠው የነበረ በመሆኑ በገቢ መቋረጥ ላይ ተጠሪ የፈፀመው ድርጊት የላለ መሆኑንና ላልች ነጥቦችን በመዘርዘር ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለተከው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በተጠሪ በኩል በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት የቀረበውን መከራከሪያ ነጥብ ውድቅ አድርጎ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ተጠሪ መኪኖቹንና ሉብሬዎቹን በሕግ አግባብ በመያዣነት የያዛቸው መሆኑ ተረጋገጧል በሚል ምክንያት የአመልካችን ክስ ሙለ በሙለ ውድቅ አድርጓል። በዚህ ውሳኔ የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የስር ፍርድ ቤት ወሳኔ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ የካቲት 11 ቀን 2001 ዓ/ም በፃፈት ሦስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ፤ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ በሕግ አግባብ የተደረገ የመያዣ ውል በላለበት ሁኔታ የተሰጠ ፤ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2825 ፣ 2828 ፣ 2830 እና 2846 ድንጋጌዎችን ይዘትና መንፈስ ያላገናዘበ በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት የግራ ቀኙ የቃል ክርክር ጥቅምት 17 ቀን 2002 ዓ/ም በዋለው ችልት ተሰምቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ ሁኖ የተገኘው፡-በአመልካችና በተጠሪ መካከል በሕግ አግባብ የተደረገ የመኪኖች የመያዣ ውል አለ ወይስ የለም? የሚለው ሲሆን ላልች ነጥቦች ከዚሁ ነጥብ ጋር ተያይዘው ምላሽ ሉሰጣቸው የሚገባቸው ናቸው።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካችና ተጠሪ ሰኔ 15 ቀን 1993 ዓ/ም የሁለት መኪኖች ግዥ ውል ማድረጋቸውን ፣ የመኪኖቹ ዋጋ ብር 1,620,000.00 (አንድ ሚሉዮን ስድስት መቶ ሒያ ሺህ ብር) ሁኖ ገዥው ከዚሁ ገንዘብ ውስጥ አብዛኛውን ከፍል ብር 486,000.00 (አራት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺህ ብር) የቀረበትን ይህንኑ ገንዘብም በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ከፍል ለማጠናቀቅ ይችል ዘንድ ቀናቸው ወደፉት ተደርጎ የተፃፈ ሁለት ቼኮችን ለሻጭ በመስጠት መኪኖቹን ሰኔ 08 ቀን 1994 ዓ/ም ገዥው ተረክቦ የመኪኖቹን ሉብሬም በዚሁ ቀን መረከቡን ፣ መኪኖቹ በተጠሪው ጋራዥ ሚያዚያ 06 ቀን 1995 ዓ/ም መግባታቸውን ፣ ከዚህም በሁዋላ ለቀሪው እዲው መክፈያነት በአመልካች ለተጠሪ የተሰጡት ቼኮች ውስጥ 1ኛው የሚመነዘረው ሰኔ 02 ቀን 1995 ሲሆን ሁለተኛው ቼክ ደግሞ ሰኔ 30 ቀን 1995 ዓ/ም ሁኖ በእነዚህ ጊዜያት ለባንክ ቀርበው በቂ ስንቅ የላቸውም ተብል በመመለሳቸው ምክንያት ተጠሪ በአመልካች ላይ ቼኮቹን መሰረት አድርጎ ክስ መስርቶ የፍርድ ባለመብት መሆኑ መረጋገጡን ፣ ይህ ሁኖ እያለም ተጠሪ ለጥገና የገቡትንና ለአመልካች ከሸጣቸው መኪኖች ውስጥ የሰ/ቁጥር 3-0990 የሆነውን መኪና ሉብሬ ፣ የሰ/9 የሆነውን መኪና ደግሞ ሉብሬውንና መኪናውን በመያዝ ለአመልካች ላሰጥ ፈቃዲኛ ላሆን ያልቻለ መሆኑን ፣ ይህ መብት ከሽያጭ ውለ ያገኘው ስለመሆኑ ተጠሪ ጠቅሶ የሚከራከር ሲሆን አመልካች ደግሞ በሕግ አግባብ የተደረገ የመያዣ ውል የለውም በማለት የሚከራከር መሆኑን ነው።
በመሰረቱ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2825 ስር በግልጽ እንደተመለከተው የሚንቀሳቀስ ፣ ንብረት ፣ መያዣ ፣ (Pledge) መሰረተ ሐሳብ በዋናነት የአንድን ተንቀሳቃሽ ንብረት ይዞታ አሳልፍ በመስጠት ዋስ መሆን የሚቻልበት የግዳታ ዓይነት ነው። የዚህ አይነት ዋስትና (ፔላጅ) አንድ ሰው ለራሱ ወይም ላላ ሦስተኛ ወገን ለሚገባው ግዳታ ተፈጻሚነት ሉኖረው ይችላል። የዚህ አይነት ዋስትና ተፈጻሚነት ያለው በተንቀሳቃሽ ንብረት ላይ መሆኑ ከማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ (Mortgage) መለያ መንገደ መሆኑም የሚታወቅ ነው። በመሆኑም በመርህ ደረጃ ፔላጅ ሉመሰረት የሚችለው የሚንቀሳቀሰውን ንብረት በማስተላለፍ ስለመሆኑ በዚህ ረገድ የተደነገጉት ድንጋጌዎች በግልፅ የሚያሳዩን ነጥብ ነው። የድንጋጌዎቹ ቅርጽ ፣ ይዘትና መንፈስ የንብረቱ ይዞታ ካልተላለፈ ፔላጅ አልተቋቋመም ልባል ሁለ እንደሚችል ያስረዲል። የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2832 በሕጉ ላይ ተገልጾ ካልተፈቀደ በቀር በመያዣ ተሰጥቶ ተይዘዋል የተባለው ዕቃ ከባለዕዲው እጅ ሳይወጣ በመያዣ እንደ ተሰጠ ሆኖ ሉቆጠር እንደማይችል መደንገጉም ከላይ የተነሳውን ምክንያት የሚያጠናክር ነው። በሕግ ከተፈቀደው በቀር መያዣው በባለዕዲው እጅ ይሆናል ብለው ቢዋዋለ እንኳን ውለ እንደማይጸና ጨምሮ ሕጉ ደንግጓል። ሆኖም ሕጉ ሲፈቅድ በልዩ ሁኔታ /As an exception/ የንብረቱ ይዞታ ሳይተላለፍ ፔላጅ ሉመሰረት የሚችልበት የሕግ አግባብ አለ። ይህም በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2830 ላይ የተመለከተው ሲሆን ፣ በተለይ በዕቃው ለማዘዝ የሚያስችለት ሰነድች ከተሰጡት ባለገንዘቡ መያዣውን እጅ እንዲደረገ ያህል ይቆጠራል። እንደዚህ ዓይነት ንብረቶች ባለቤትነታቸው ያለምዝገባ ወረቀት (Title deed) ሉተላለፍ ስለማይችል የንብረት ይዞታ መተላለፍ ሳያስፈልግ ፔላጅ ሉፈጸም ይችላል። እነዚህ ዓይነት ዋስትና ሉሰራባቸው የሚችለት በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1186(2) የተጠቀሱት ፣ ልዩ ተንቀሳቃሽ ፣ ንብረቶች ፣ እንደ ፣ መኪናና ፣ የአክሲዮን ፣ የዕቃ ፣ ማከማቻ ፣ ደረሰኝ ፣ ዓይነት ፣ ንብረቶች ፣ ናቸው። ንብረቱን ለባለገንዘቡ ከማስተላለፍ (Dispossession) በተጨማሪ የሚንቀሳቀስ ንብረት መያዣ በሕጉ በተቀመጠው የአሰራር ሁኔታ ፍርም መሰረት ካልተፈጸመ በሕግ ፉት የጸና አይሆንም። ይህ የፍርም መስፈርት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2828 ላይ የተደነገገ ሲሆን ፣ ዋስትና የተሰጠበት ግዳታ ከፍተኛው ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን በግልጽና በጥንቃቄ በመያዣው ውል ውስጥ መመልከት ይገባዋል። ይህ ካልሆነ ግን ውለ ፈራሽ እንደሚሆን ሕጉ በግልጽ ደንግጓል። በተጨማሪም የመያዣው ውል ከብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በላይ የሆነ እንደሆነ ውለ በጽሐፍ ካልተደረገና ይኸውም እርግጠኛ ቀን ካገኘበት ዘመን ጀምሮ ካልሆነ በቀር አይጸናም። ስለዚህ ከብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በላይ የሆነ የሚንቀሳቀስ ንብረት መያዣ በጽሐፍ እንዱፈጸም ሕጉ በአስገዲጅ ሁኔታ ያስቀመጠው ጉዲይ ነው። ከዚህም በተጨማሪ እንዱህ ዓይነት የመያዣ ውል በጽሐፍ እንዱደረግ ሕጉ ግዳታ ካስቀመጠ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1727 መሰረት በውለ ፣ ግዳታ ፣ ያለባቸው ፣ አስያዡና ፣ መያዣ ፣ ተቀባዩ ፣ መፈረም ፣ እንዲለባቸውና ፣ ሁለት ፣ ምስክሮች ፣ ፉትም ፣ መረጋገጥን የግድ ይሎል ነው። ይህ ሁኔታ ካልተሟላ ውለ በሕግ ፉት የሚፀና አለመሆኑን ከላይ የተጠቀሱት ድንጋጌዎችን ፣ በአንድ ላይ ስናነብ የምንረዲው ጉዲይ ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ ተጠሪ የሚንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ውል( Pledge) አቋቁሜአለሁ በማለት ተከራክሮ የበታች ፍርድ ቤቶችም ውለ መያዣ ነው ከሚባል በስተቀር ላላ ምክንያት ሉሰጠው የሚችለው አይደለም በማለት ድምዲሜ ላይ ደርስዋል። ይሁን እንጂ ሰኔ 15 ቀን 1993 ዓ/ም በተደረገው ውል ለውለ መያዣነት የተያዙት የማይንቀሳቀሱት ንብረቶች አሁን ክርክር ያስነሱ ስለመሆኑ ፣ የዋስትናው መጠን ምን ያህል እንደሆነ በግልፅ ያልተመለከተ ሲሆን የበታች ፍርድ ቤቶች ውለ መያዣ ነው ወደሚለው ድምዲሜ የደረሱት "ገዥው ግዳታውን የማያከብር ሁኖ ሲገኝ ወይም ቼኩ ክፍያ ሳይፈጸምበት ከተመለሰ ያልተከፈለው ውዝፍ ሂሳብ በሙለ ወዱያውኑ ተገቢ ሂሳብና ተከፊይ ይሆናል። በዚህ ጊዜም ሻጩ ወዱያውኑ መኪናውን በእጁ አግብቶ ያላአንዲች ላላ አይነት አሰራር መኪናውን ለሕዝብ በሐራጅ የመሸጥ ስራውን ይቀጥላል።" በሚል በውለ ውስጥ የተቀመጠውን ዐረፍተ ነገር በመያዝ ነው። ሆኖም ከላይ እንደተጠቀሰው በሽያጭ ውለ ውስጥ የመያዣ ውለ በግልጽ የተጠቀሰና በሥርዓቱ መሰረት የተደረገ የመያዣ ውል አይደለም። ይልቁንም ተጠሪ ከመኪናዎቹ ውስጥ አንደን በውለ ባለው ግዳታ መሰረት ለጥገና ሲገባ የያዘው መሆኑ ሲታይ የሚንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ውል የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2828 እና 2930 ድንጋጌዎችን ባከበረ መልኩ ተደርጓል ለማለት የሚያስደፍር አይደለም። ተጠሪ በአንድ በኩል የሚንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ውል ያለው መሆኑን ጠቅሶ ከመኪኖቹ አንደንና የሁለቱን መኪኖች ሉብሬ በይዞታው ስር ያደረገ ሲሆን በልላ በኩል ደግሞ ለእዲው መክፍያ እንዱውል የተሰጠውን ቼክ መሰረት በማድረግ ክስ አቅርቦ የፍርድ ባለመብት መሆኑ ሲታይ የመኪናው ሽያጭ ውል ሰኔ 15 ቀን 1993 ዓ/ም ሲደረግ መያዣውን አስመልክቶ በግራ ቀኙ መካከል የነበረው ሐሳብ ግልፅነት የላለው መሆኑን የሚጠቁም ሲሆን በቼኩ ላይ በፍርድ ቤት ክስ መስርቶ መብቱን ከውለ መደረግ በሁዋላ ማስከበሩ ከፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1734 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ አንፃር ሲታይ የመያዣ ውል ሰኔ 15 ቀን 1993 ዓ/ም በተደረገው ውል መሰረት ያለመቋቋሙን የሚያሳይ ነው። አመልካች የመኪኖቹን ሉብሬ ለተጠሪ መስጠቱ ያልተካደ ፍሬ ነገር ሲሆን ይህ መሆኑ ተጠሪ መኪኖቹን በራሱ ስልጣን እንዱሸጥ መብት የሚሰጠው ሳይሆን መኪኖቹ እዲው ከመከፈለ በፉት ለሶስተኛ ወገን እንዲይተላለፈና የተጠሪን ቅድሚያ መብት የሚያስገኝ ይሆናል። በአጠቃላይ ተጠሪ የሚንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ ውል በመኪኖቹ አቋቋሜአሁ በማለት አንደን የአመልካች መኪና በቁጥጥር ስር ማዋለን ከውለ የመነጨና ሕጋዊ ጥበቃ ሉደርግለት የሚገባው እርምጃ አይደለም።
አመልካች ሉብሬውን ለመያዣነት መስጠቱን በክርክሩ ሂደት ያረጋገጠው ጉዲይ በመሆኑ ተጠሪ በመኪኖቹ ሉኖረው የሚችለው መብት ሉብሬውን በመያዝ የቅድሚያ መብት ማስከበር ነው።
በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ መኪናውን ይዞ ቁጥጥር ስር ያደረገው በመያዣ ውለ መሰረት ነው በማለት የደረሱበት ድምዲሜ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2825 ፣ 2828 እና 2830 እንዱሁም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1727 ድንጋጌዎችን ባገናዘበ መልኩ ሁኖ ስላላገኘን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈመበት ሁኖ አግኝተናል።
ላላው ተጠሪ የአመልካችን መኪኖች በራሱ ይዞ ቁጥጥር ስር ለማዋል የሚችልበት በሕግ አግባብ የተደረገና በሕጉ መሰረት ጥበቃ የሚደረግለት የሚንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ውል የለም ከተባለ መኪናውን ለጥገናው በቂና ተገቢ ጊዜ ነው ከሚባለው ምክንያታዊ ጊዜ በላይ ከሕግ ውጪ በመያዙ በአመልካች ላይ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉ የማይሆንበት ምክንያት የለም። በመሆኑም መኪኖቹ ወደ ተጠሪ ጋራዥ የገቡት ለጥገና ነው የሚለው ፍሬ ነገር የተረጋገጠ ቢሆንም ለጥገናው ጊዜ ያስፈልግ የነበረው ጊዜ ምን ያህል ነው ፣ ከሕግ ውጪ የተያዘው የሰላዲ ቁጥር 3-07539 የሆነውን መኪና በወቅቱ ተጠግኖ ለአመልካች ቢሰጥ ኑሮ ይገኝ የነበረው ሕጋዊ ገቢ ምን ያህል ነው የሚለው እና ላላ ከገቢ ጋር ተያይዞ የሚነሳ ክርክር በፍሬ ነገር ደረጃ በስር ፍርድ ቤት ያልነጠረ በመሆኑ በዚህ ችልት መቋጫ ሉሰጠው የሚችል አይደለም። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት ለመኪናው ጥገና የሚያስፈልገውን ምክንያታዊ ጊዜ በተገቢው መንገድ በማጣራት እንዱያረጋግጥና ከዚህ ጊዜ ውጪ ላለው የመኪና መያዝ ደግሞ ተጠሪ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2027 ፣ 2028 እና 2054 ኃላፉነት ያለበት መሆኑን በመገንዘብ አመልካች ሉያገኝ ይችል የነበረውን የገቢ መጠን በተመለከተ የግራ ቀኙኝ ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ሉወስነው የሚገባ ጉዲይ ሁኖ አግኝተናል። አመልካች የመኪኖቹን ሉብሬ ተጠሪ በመያዙ ምክንያት ጥቅም ተቋርጧል ለሚለው ክርክር የስር ፍርድ ቤት አመልካች በፈለገ ጊዜ ሉብሬውን እየፈረመ ወስድ ይመለስ የነበረ መሆኑን በፍሬ ነገር ደረጃ ያረጋገጠ ቢሆንም ሉብሬው በመያዙና የሰ/ቁጥር 3-09190 የሆነው መኪና ክላውድ ባለመደረጉ በአመልካች ላይ ደርሷል በማለት አመልካች በጠየቀው ዲኝነት ላይ ግልፅ ውሳኔ አልሰጠበትም።
ይህም ላሆን የቻለው በሕግ አግባብ የተቋቋመ የሚንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ውል አለ የሚል ድምዲሜ የስር ፍርድ ቤቱ በመድረሱ ምክንያት መሆኑን ተገንዝበናል። ነገር ግን ከላይ እንደተመለከተው በሕግ አግባብ የተቋቋመ የመያዣ ውል ባይኖርም ሉብሬዎቹን አመልካች ለተጠሪ አሳልፍ መስጠቱ ተጠሪ የቅድሚያ መብቱን ለማስከበር የሚያስችለው ይሆን የነበረ ሁኖ በየጊዜውም ሉብሬውን ለአመልካች አሳልፍ ይሰጥ የነበረ መሆኑን ተጠሪ በምስክሩ ማረጋገጡን ፣ አመልካች ሉብሬውን በየጊዜው እየፈረመ ያለመውሰደን ከመግለጽ ውጪ በተገቢው ማስረጃ በማስገደፍ ክርክሩን ያለማቅረቡን ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ጉዲይ ነው። እንዱህ ከሆነ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት የሰ/ቁጥር 3-09190 መኪና ሉብሬው በተጠሪ ለአመልካች በየጊዜው ይሰጥ የነበረ መሆኑን እንደተረጋገጠ ፍሬ ነገር በመውሰድ በሕግ አተገባበር ወይም አተረጓጎም ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ካለ ብቻ ማረም ስልጣኑ መሆኑን ከኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ))እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ድንጋጌ መገንዘብ የምንችለው ነው። በመሆኑም አመልካች የሰ/ቁጥር 3-09190 የሆነ መኪና ሉብሬ በተጠሪ በመያዙ ምክንያት ጥቅም ተቋርጦብኛል በማለት ያቀረበው ክርክር በተገቢው ማስረጃ የተደገፈ ባለመሆኑ ተቀባይነት ያለው ሁኖ አላገኘውም። እንዱሁም የመኪኖቹን ሉብሬ በተመለከተ አመልካች ለተጠሪ በራሱ ፈቃድ አሳልፍ መስጠቱ የተረጋገጠ ጉዲይ በመሆኑ አመልካች ቀሪ እዲውን ለተጠሪ እስካልከፈለው ድረስ ተጠሪ ሉብሬዎቹን በዚህ የክርክር ደረጃ እንዱመልስ የሚያስገደደው ሕጋዊ ምክንያት የላለ በመሆኑ በዚህ ረገድ የቀረበውን የአመልካች ጥያቄ የምንቀበለው ሁኖ አልተገኘም።
በአጠቃላይ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው የሽያጭ ውል ተጠሪ መኪኖቹ ላይ የቅድሚያ መብት እንዱኖረው ከሚያደርግ በስተቀር መኪኖቹን በራሱ ሥልጣን በመያዝና ቁጥጥር ስር በማዋል ራሱ እንዱሸጥ መብት የሚያጎናፅፍ አይደለም። በዚህም ምክንያት የሰላዲ ቁጥር 3- 07539 የሆነውን የአመልካች መኪና ለጥገና ከሚያስፈልገው ምክንያታዊ ጊዜ ውጪ በመያዙ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት ያለበት ሲሆን የጉዲት መጠኑ በስር ፍርድ ቤት ተጣርቶ ሉወሰን የሚገባ ሁኖ የሰ/ቁጥር 3-09190 የሆነውን መኪና ሉብሬ በመያዙ በአመልካች ላይ ጉዲት ደርሷል ፣ ሉብሬዎቹን ተጠሪ ሉመልስ ይገባል በማለት አመልካች ለአቀረበው የዲኝነት ጥያቄ ግን ተጠሪ ኃላፉ ላሆን የሚችልበት አግባብ የላለ ሁኖ ስለአገኘነው የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሉሻሻል የሚገባው ነው በማለት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 21 ቀን 1999 ዓ/ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ህዲር 15 ቀን 2001 ዓ/ም የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
በአመልካችና በተጠሪ መካከል ሰኔ 15 ቀን 1993 ዓ/ም የተደረገው የመኪኖች ሽያጭ ውል ተጠሪ መኪኖቹን በራሱ ሥልጣን በመያዝና ቁጥጥር ስር በማዋል ራሱ እንዱሸጥ መብት የሚያጎናፅፍ አይደለም ብለናል።
በዚህም ምክንያት የሰላዲ ቁጥር 3-07539 የሆነውን የአመልካች መኪና ለጥገና ከሚያስፈለገው ምክንያታዊ ጊዜ ውጪ በመያዙ ለደረሰው ጉዲት ተጠሪ ኃላፉነት ያለበት ሲሆን የጉዲት መጠኑ በስር ፍርድ ቤት ተጣርቶ ሉወሰን የሚገባው በመሆኑ ለመኪናው ጥገና የሚያስፈልገው ምክንያታዊ ጊዜ ምን ያህል እንደሆነ እና ለጥገናው ከሚያስፈለውገው ምክንያታዊ ጊዜ ውጪ መኪናው ሉያስገኝ ይችል የነበረው ገቢ መጠን ላይ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰምቶና በተገቢው መንገድ አጣርቶ ተገቢውን ሉወስንበት ይገባል በማለት በዚሁ ነጥብ ላይ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 343(1)መሰረት መልሰንለታል። ይፃፍ።
ተጠሪ የሰላዲ ቁጥር 3-07539 የሆነውን የአመልካች መኪና ለአመልካች ሉመልስና ሉያስረክብ ይገባል ብለናል።
የሰ/ቁጥር 3-09190 የሆነውን መኪና ሉብሬ በመያዙ በአመልካች ላይ ጉዲት ደርሷል በማለት አመልካች ያቀረበው የዲኝነት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
አመልካች ሉብሬውን ለክላውድ የሚያስፈልገው መሆኑን ሲያረጋግጥ ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጎ ከሚሰጥ በስተቀር እዲው እስከሚከፈለው ድረስ ሉብሬዎቹን ተጠሪ ለአመልካች እንዱያስረክብ አይገደደም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ውጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.