No summary available.
ሚያዝያ 19 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- እነ አቶ ተሾመ ካሣ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ቤዛ ኩለ አዲም የቀረበ የለም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በሽያጭ ምክንያት ተከፈለ የተባለ ገንዘብ ይመለስልኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካቶች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም፡- አመልካቾች ከመኖሪያ ቤታቸውና ከይዞታቸው በመቀነስ በግምት 270 ካ.ሜትር የሆነና ሁለት ክፍል ሰርቪስ ቤት ብር 40,000/ አርባ ሺህ/ ሽጠውላቸው ብር 10,000.00 /አስር ሺህ / በውለ እለት የከፈሎቸው መሆኑን ብር 20,000.00/ሃያ ሺህ ብር/ ደግሞ አመልካቾች ቤቱን አድሰው ለተጠሪ ሲያስረክቡ እንዱከፈላቸው የተሰማሙ ቢሆንም አመልካቾች ቤቱን ባለማደሳቸው ተጠሪ በራሳቸው ገንዘብ እንዱያድሱ ስምምነት ላይ በመደረሱ ምክንያት ተጠሪ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ/ ወጪ በማድረግ ቤቱን አድሰው የተረከቡ መሆኑን ከዚህም በተጨማሪ ተጠሪ ብር 51,000.00/ሃምሳ አንድ ሺህ ብር/ ወጪ በማድረግ ደረጃውን የጠበቀ አምስት ክፍል ቤት የሰሩ መሆኑን ተጠሪ በአመልካች ላይ የቤት ሽያጭ ውለን በውልና ማስረጃ ጽ/ቤት ቀርበው እንዱያስመዘግቡ በፍርድ ቤት ክስ መስርተው ክርክሩ ሲካሄድ ቆይቶ ፍርድ ቤት በሕግ ፉት የሚፀና ውል የለም በማለት ውሣኔ መስጠቱን በመዘርዘር በማይጸና ውል የተወሰደውና ለግንባታ የወጣው ወጪ በድምሩ ብር 81,000.00/ሰማንያ አንድ ሺህ ብር / እንዱከፍሎቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካቾች በበኩላቸው ተጠሪ ወደ ቤቱ የገቡት በኃይል መሆኑን በተጨማሪነት የገነቡት ግንባታም አለመኖሩን የሽያጭ ውለም የተጭበረበረ መሆኑን በውለ ደረሰኝነት ብር 10,000.00 ብቻ መቀበላቸውን ገልፀው ይኸው ገንዘብ ተከፍሎቸው ግራ ቀኙ ወደነበሩበት ቦታ እንዱመለሱ ላደረግ ይገባል ሲለ መልስ ሰጥተዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም አመልካቾች ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ገንዘብ ለተጠሪ ሉከፍለ ይገባል? ወይስ አይገባም?
የሚለውንና ተያያዥ ጭብጦችን በመያዝ የግራ ቀኙን ክርክርና ምስክሮችን ቃል መርምሮ አመልካቾች ለተጠሪ ብር 61,000.00 ውሣኔ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር ሉከፍለ ይገባል በማለት ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካቾች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ፀንቷል።
አመልካቾች ሐምል 22 ቀን 2002 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል።
ይዘቱም ባጭሩ፡- የቤት ሽያጭ ስለመኖሩ በሕግ መሰረት በጽሐፍ የተደረገና በሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ፉት የተፈረመ የቤት ሽያጭ ውለ በላለበት ሁኔታ ለቤቱ እድሳት የወጣ ገንዘብ ለተጠሪ ሉመለስላቸው ይገባል መባለ እንዱሁም ተጠሪ ተጨማሪ ግንባታ አከናወንኩ የሚል ክርክር ሳይኖራቸውና በማስረጃም ባልተደገፈበት መንገድ ለብር 61,000.00/ስልሳ አንድ ሺህ ብር / ሃላፉ ተደርገን ውሣኔ መሰጠቱ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም በማይፀና ረቂቅ ውል አመልካቾች የተቀበለትን ብር 10,000.00 እንዱመልሱ ከመደረጉ በተጨማሪ ተጠሪ የግንባታ ፈቃድ እንኳን ሳይኖራቸው ሰራሁት ለሚለት ቤት የምስክሮች ቃል ብቻ መሰረት ተደርጎ አመልካቾች ለተጠሪ የግንባታ ወጪ እንዱከፍለ የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጓል።
በዚህም መሰረት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በጽሐፍ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔና አግባብነት ከአላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው ጭብጥ፡- አመልካቾች ለተጠሪ ገንዘቡን እንዱመልሱ ተብል የተወሰነው በሕጉ ተቀባይነት ያለውን ማስረጃ መሰረት ባደረገ መንገድ ነው? ወይስ አይደለም? የሚል ነው።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ በአመልካቾች ላይ ክስ የመሰረቱት አመልካቾች ቤት ሽጠውልኝ የተወሰነ ገንዘብ ከፍዬአለሁ የተወሰነውንም የአመልካቾችን ግዳታ ለመወጣት ስል ወጪ አድርጌ ቤቱን በመረከብ ተጨማሪ ግንባታ አከናውኜ ባለበት ሁኔታ በፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር በሕግ ፉት የሚጸና ውል የለም ስለተባለ ገንዘቡ ሉመለስልኝ ይገባል በማለት መሆኑን በግራ ቀኙ መካከል የቤት ሽያጭ ውል አለ የለም የሚለው ክርክርም በፍርድ ቤት ታይቶ ሕጋዊ የሆነ የቤት ሽያጭ ውል የላለ መሆኑ መረጋገጡን ነው። የቤት ሽያጭ ውል የላለ መሆኑ የተረጋገጠው ተጠሪ አመለካቾች የቤት ሽያጭ ውለን ውል አዋዋይ ፉት ቀርበው ሉያስመዘግቡልኝ ይገባል በማለት በመሰረቱት ክስ አመልካቾች በሕግ ፉት የሚጸና ውል የለም በማለት በመከራከራቸው ምክንያት መሆኑንም ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ ችለናል። ተጠሪ ለአሁኑ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነውን ጉዲይ ያቀረቡትም የቤት ሽያጭ ውል የለም ተብል ውሣኔ ከተሰጠ በሁዋላ ሲሆን አመልካቾች ገንዘቡን ስለመቀበላቸው ያቀረቡትና ያሰሙት ማስረጃ የሰው ምስክሮችንና የሰነድ ማስረጃ ነው። አመልካቾችም የሰው ምስክሮችን አቅርበው ያሰሙ መሆኑን የስር ፍርድ ቤት የውሣኔ ግልባጭ ያሳያል። የስር ፍርድ ቤት አመልካቾችን ለክሱ ኃላፉ ያደረገው ገንዘቡን ከተጠሪ ስለመቀበላቸው ተጠሪ በተገቢው ማስረጃ አስረድተዋል አመልካች ግን በምስክሮቻቸው ሉያስተባብለ አልቻለም በሚል ምክንያት ነው። እንግዱህ ከላይ የተመለከቱት ነጥቦች በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጡት ሲሆን አመልካች የስር ፍርድ ቤት የስነ ሥርዓት ግድፈት ፈጽሟል በማለት የሚያቀርቡት አንደ ነጥብ ተጠሪ ሕጋዊ የሆነ ቤት ሽያጭ ውል አለ በማለት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት ሳያገኝ በቤት ሽያጭ ውል የተከፈለው ገንዘብ እንዱመለስ ተብል መወሰኑ ለጉዲዩ መቅረብ ከሚገባው ማስረጃ አይነት አንፃር ተገቢነት የላለው ነው በማለት ነው። ይሁን እንጂ የቤት ሽያጭ ውልን አስመልክቶ ክርክሩ የቀረበበት አግባብ በተጠሪ በኩል የቀረበው የቤት ሽያጭ ውል በውል አዋዋይ ፉት እንዱመዘገብ የሚል ክስ በመቅረቡ በመሆኑና በሕጉ አግባብ የተደረገ የቤት ሽያጭ ውል የለም ተብል ድምዲሜ የተደረሰ በመሆኑ ተጠሪ በሽያጩ ምክንያት ለአመልካቾች የሰጡትን ገንዘብ ሉመለስልኝ ይገባል በማለት ጥያቄ ከማቅረብና በማናቸውም ማስረጃ ከማስረዲት የማይከለክል መሆኑን ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1808/2/ ፣ 1815 ፣ 2001 እስከ 2019 እንዱሁም ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2162 እና 2164 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ የቀረበውን የማስረጃ አይነት መሰረት በማድረግ መቃወሚያ የሚቀርብበት ጉዲይ አይደለም።
No topics extracted.
በመሆኑም በዚህ ረገድ አመልካቾች ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት ያለው ሁኖ አላገኘነውም።
አመልካቾች አጥብቀው የሚከራከሩትና በዚህ ሰበር ችልት እንዱታይ የተያዘው ጭብጥ በጉዲዩ ላይ የቀረበው ማስረጃ በሕጉ ስላለው ተቀባይነት ነው። ተጠሪ ሕጋዊ አይደለም በተባለው የቤት ሽያጭ ውል መሰረት ለአመልካቾች ከፍያለሁ የሚለት የገንዘብ መጠን ብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር / ሲሆን ላላው ብር 51,000.00 ከቤቱ ርክክብ በሁዋላ ለተደረገ ግንባታ የወጣ ወጪ ነው። አመልካቾች ለጉዲዩ የቀረበው ማስረጃ ተቀባይነት የላለው ነው የሚለት ይህንኑ የገንዘብ መጠን በሰው ማስረጃ ሉረጋገጥ አይገባም ተጠሪ በማስረጃም ክርክራቸውን አላስደገፊም በማለት ነው። ይሁን እንጂ የአመልካችና የተጠሪ ግንኙነት የብድር ውል ሳይሆን ሕጋዊ ያልሆነ የቤት ሽያጭ ውል ስለመሆኑ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። በመሆኑም ጉዲዩ በሰው ምስክር ሉረጋገጥ አይገባም ተብል በአመልካቾች የቀረበው ክርክርም ሆነ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት በጭብጥነት የተያዘው ነጥብ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2472 ለጉዲዩ አግባብነት የላለው በመሆኑ ተቀባይነት የላለው ነው። ጉዲዩ መገዛት ያለበት ስለሽያጭ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በተለይ በመመልከት ወይም ስለጠቅላላው ውል የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በማየት ነው። በዚህም መሰረት ለጉዲዩ ቀጥተኛ ተፈጻሚነት ያላቸው ድንጋጌዎች በጠቅላላው የውል ሕግ ሲሆን በዚህ የውል ሕግ አንድን ነገር ለመግዛት ገንዘቡን የከፈለ ሰው ግዥው ሕጋዊ አይደለም ተብል ውሣኔ ከተሰጠው ገንዘቡ እንዱመለስለት ጥያቄ ቢያቀርብና ክሱን በሰው ምስክር ቢያስረዲ የሰው ምስክሮች ቃል ተቀባይነት የለውም ልባል እንደማይችል ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2001 እስከ 2019 ድረስ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ያስረዲለ። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ያቀረቧቸውን የሰው ምስክሮች ቃል በመቀበል ውሣኔ መስጠቱ ከላይ ከተመለከቱት የጠቅላላ ውል ሕግ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ አንፃር ሕጋዊ እንጂ የሚነቀፍ ሁኖ አልተገኘም። ተጠሪ በቦታው ላይ ግንባታውን ያከናወኑት በአመልካቾች በኩል ተቃውሞ እየቀረበ ባለበት ሁኔታ ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ያልተረጋገጠ ሲሆን የግንባታ ፈቃድ ሳያወጡ ግንባታው መከናወኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1178 እና 1179 ድንጋጌዎች አንፃር ሲታይ የተጠሪን የግንባታ ወጪ ይተካልኝ ጥያቄን ህጋዊ አይደለም ለማለት የሚያስችል አይሆንም። በአጠቃላይ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶቹ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የላለበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።