No summary available.
ሚያዚያ 06 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሤ አመልካች፡- አቶ ዮሐንስ ታደሰ - ቀረበ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አማረች መንገሻ ጠበቃ አቶ ምክሩ ወ/አረጋይ - ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የአሁኑ አመልካች ለሥር የመ/ደ/ፍ/ቤት ያቀረበው ክስ ፍሬ ቃለ ተከሳሽ /ያሁን ተጠሪ/ የአደረግነውን የወሰን ምልክት ስምምነት በመጣስና በውላችን በተስማማንበት መሰረት ባለመፈፀም ከፍ/ቤት የተሰጠ ትዕዛዝ ሳይኖር ሀሰተኛ የአጥር ፈቃድና ህገ ወጥ የይዞታ ማረጋገጫ በመያዝ አጥሬን በማፍረስ፣ የወሰን ምልክት በማጥፊትና ቀደም ሲል ከወ/ሮ ይርግደ ሳሙኤል ወራሾች ከነ ወልደየስ አምባዬ በግዥ ካገኘችው ቦታ አልፊ በንብረቶቼ ላይ ጉዲት ያደረሰችና አዱስ አጥር ስላጠረች በህገ ወጥ መንገድ ያጠረችውን አጥር አፍርሳና የራሴን ያፈረሰችውን አጥር መልሳ በመሣጠር ቀደም ሲል በገባነው ውል መሰረት እንደትፈጽም ይወሰንልኝ የሚል ነው።
የሥር ተከሳሽም በሰጠችው መልስ ይዞታው የከሳሽ ስለመሆኑ ማስረጃ ስለላለው ክስ የማቅረብ መብት የለውም፣ በዚህ ጉዲይ ለአምስት ተደጋጋሚ ጊዜያት በተለያዩ መዛግብት ክስ ሲያቀርብ የቆየ በመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5 መሰረት ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል፣ ከሳሽ እነደሚለው ሣይሆን ቦታውን ያጠርኩት ከአዱስ አበባ ከተማ መስተዲድርና ከሥራና ከተማ ልማት ጽ/ቤት በተሰጠኝ ፈቃድ ሲሆን ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ታጥሮ ያለ የግል ይዞታዬ ነው፣ በንብረቱም ላይ ያደረስኩት ጉዲት የለም። ነገር ግን ዛፍ ተቆረጠብኝ ለሚለው ዛፈ ጉዲት የሚያደርስ መሆኑ ታውቆ የደን ሚኒስቴር እና ፕሉስ ያስቆረጡ ስለሆነ አይመለከተኝም፣ ከዕርቅ ስምምነት ውጪ ስለመሥራቴም ከሳሽ ያቀረበው ማስረጃ ካለመኖሩም ላለ ከሳሽ የተከሳሽን ይዞታ 2x4 ሜትር የሆነውን አልፍ በመያዝ በጉልበት እየተጠቀመበት ስለመሆኑ የካርታ ቁጥሩ ጄ አይ ኤስ 5556 የሆነ ያረጋግጣል በማለት የከሳሽ ክስ ውድቅ ተደርጎ ኪሣራ ከፍል መዝገቡ እንዱዘጋ አመልክታለሁ ብላለች።
የሥር የመ/ደ/ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ በ24/10/2001 ዓ.ም በዋለው ችልት በሰጠው ፍርድ በአዋጅ ቁጥር 361/95 መሰረት ካርታ የመስጠትና የመሰረዝ ሥልጣን የክፍለ ከተሞች ነው። በመሆኑም ከሳሽ ካርታው የተሰጣት ያለአግባብ ነው የሚል ከሆነ ካርታውን የሰጠውን ክፍል እንዱሰርዝ ከሚጠይቅ ውጪ ጥያቄውን ለፍ/ቤት ማቅረብ የለበትም በማለት የከሳሽን ክስ ውድቅ አድርጏበታል። ከሳሽ አላአግባብ ተከሳሽን በመክሰሱ ምክንያት ለወጣው የጠበቃ አበል ብር 10‚000/አሥር ሺህ/ እንዱከፍል ወስኗል።
በዚሁ በሥር የመ/ደ/ፍ/ቤት ውሣኔ ቅር በመሰኘት የአሁኑ አመልካች ለሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን ከፍተኛው ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ወገን ካከራከረ በኋላ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348/1/ መሰረት የሥር ፍ/ቤት ውሣኔን በማጽናት ለሥር መ/ሰጪ የወጪና ኪሣራ የመጠየቅ መብት ጠብቆላታል። በዚሁ መሰረት የሥር መልስ ሰጪ የወጪ ዝርዝር ጥያቄ ለከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርባ በመዝገብ በቀን 24/12/2002 በተሰጠ ፍርድ ብር 6‚000/ስድስት ሺህ/ ይግባኝ ባይ /ያሁን አመልካች/ ለመልስ ሰጪ /ለአሁኗ ተጠሪ/ እንዱከፍል ተወስኗል።
የሰበር አመልካችም የሥር ፍ/ቤቶች በፍሬ ነገሩም ሆነ በወጪ ዝርዝር ላይ በሰጡት ውሣኔ ቅር በመሰኘት አቤቱታውን ለዚህ ችልት አቅርቧል። በዋነትም አመልካች የጠቀሳቸው የቅሬታ ነጥቦች፡እኔ ለሥር ፍ/ቤት ያቀረብኩት ክስ እንደውለ እንዱፈፀምልኝ ሆኖ ሳለና ካርታ ይሰረዝልኝ በሚል ተቀጥሮ ክሱ ውድቅ መደረጉ፣ እንዱሁም በሥር መ/ደ/ፍ/ቤት ብር 10‚000 የጠበቃ አበል እንድከፍል መወሰኑና ከፍተኛ ፍ/ቤትም ድጋሚ ኪሣራ እንድከፍል መወሰኑ ያለአግባብ ነው የሚለ ናቸው። ተጠሪዋ በጠበቃ አማካይነት በሰጠችው መልስ አመልካች የተጠሪው ይዞታ 500 ካ.ሜ ሲሆን 900 ካ.ሜ ካርታ ድንበሩን በመግፊት ያወጣችው ህገ ወጥ ካርታ ይሰረዝልኝ በማለት በተደጋጋሚ የሚከራከር ሲሆን ህገ ወጥም ሆነ ህጋዊ ካርታን ለማሰረዝ የሚቀርበው አቤቱታ በአዋጅ ቁጥር 361/95 ሥልጣኑ የክፍለ ከተማ በመሆኑ የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ የሚነቀፍ አይደለም፣ አመልካችና ተጠሪ ቦታን በሚመለከት ያደረግነው ስምምነት የለም፣ አለ ቢባል እንኳን ከ1985 ጀምሮ ክሱ እስከቀረበበት ድረስ በ10 ዓመት ይርጋ ቀሪ የሚሆን ነው። በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1727 መሰረት በምስክሮች ፉት ያልተረጋገጠ፣ በውል አዋዋይ ቀርቦ ያልተመዘገበና ተጠሪ ያልፈረምኩበት በአመልካች ብቻ የቀረበ ውል ተቀባይነት የለውም በማለት በሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ላይ የተፈፀመ የህግ ስህተት ባለመኖሩ ወጪና ኪሣራ የመጠየቅ መብት ተጠብቆ መዝገቡ እንዱዘጋ ጠይቃለች።
የግራ ቀኙ ክርክር ከዚህ በላይ በተገለፀው አኳኋን የቀረበ ሲሆን እኛም የሚከተለትን ጭብጦች በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
ተዋዋይ ወገኖች ሁለ የሚዋዋለበትን ጉዲይ እንደመሰላቸው የመወሰን መብት ያላቸው ሲሆን ሕግ የወሰናቸውንና የከለከላቸውን ነገሮች ግን ሉያከብሩ እንደሚገባ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1716 ይደነግጋል። ህግ የወሰናቸውንና የከለከላቸውን ነገሮች ባለመገንዘብ ወይም ባለማክበር የሚደረጉ ውልች የማይፀኑና የማይፈፀሙ ናቸው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካችና ተጠሪ የሚከራከሩት በከተማ መሬት ነው።
የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት ደግሞ የመንግስትና የሕዝብ ብቻ መሆኑ በኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 40/3/ ተደንግጓል። በመሆኑም በመንግሥትና በህዝብ መሬት ላይ ግለሰቦች አንደ ሰጪ ላላው ተቀባይ በመሆን የባለቤትነት መብት ሉመሰርቱ አይችለም።
በልላ በኩል የሚያከራክረው ቦታ የከተማ ቦታ እስከሆነ ድረስ በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 11/2//ሰ/ መሰረት ተጠሪዎች የአመልካችን ይዞታ አልፊ ስለመያዟ በከተማው ክልል ውስጥ የሚገኘውን መሬትና የተፈጥሮ ሀብት በሕግ መሰረት ለማስተዲደር ሥልጣን ለተሰጠው የከተማው አስተዲዲር ማመልከት ነበረበት። ይህን መብቱን ለመጠየቅ ደግሞ አመልካች ተጠሪዋ አልፊ ይዛብኛለች በሚለው ቦታ ላይ የባለይዞታነት መብት ያለው ስለመሆኑ የባለይዞታነት ማረጋገጫ ካርታ ሉኖረው ይገባል።
ተጠሪም በህገ ወጥ መንገድ የባለ ይዞታነት ማረጋገጫ ካርታ ተሰጥቷታል ለሚለውም ህገ ወጥ መሆኑንና አለመሆኑን መመርመርና ህገ ወጥነቱ ሲረጋገጥ መሰረዝ የሚችለው ይኽንኑ ማስረጃ ለመስጠት በህግ መብት የተሰጠው የከተማው አስተዲደር አካል መሆኑን ከዚህ በፉት ይህ ችልት በሰበር መ/ቁ. 22719 ጥቅምት 14 ቀን 2000 ዓ.ም በአመልካች የአ/አ ከተማ አስተዲደር ሥራና ከተማ ልማት ቢሮ ተተኪ የመሬት ልማትና አስተዲደር ባለሥልጣንና በተጠሪ አቶ ነጋሽ ደባለ መካከል በተደረገው ክርክር ከሰጠው የህግ ትርጉም መገንዘብ ይቻላል። የሰበር ችልቱም የሚሰጠው የህግ ትርጉም በተመሣሣይ ጉዲዮች ላይ በየትኛውም ፍ/ቤት የአስገዲጅነት ባሕሪ ያለው መሆኑን አዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2/1/ ስለሚደነግግ የሥር ፍ/ቤት ይኽንኑ የህግ ትርገም መሰረት በማድረግ ካርታ ማሰጠትም ሆነ ማሰረዝ የፍ/ቤት ሥልጣን አይደለም በሚል የወሰነው ከዚህ በላይ በተገለጹ ምክንያቶች የተነሣ አመልካች እንዱፈፀምለት ያቀረበው ውል የማይፈፀምና ካርታ የማሰጠትም ሆነ የማሰረዝ ሥልጣን የፍ/ቤት ሳይሆን የአስተዲደር መሥሪያ ቤት በመሆኑ በውሣኔው ላይ ይህን ጭብጥ በሚመለከት የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለም ብለናል።
2ኛው ጭብጥ የጠበቃ አበልን በሚመለከት የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ነው።
በመ/ደ/ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር አመልካች ለተጠሪ የጠበቃ አበል ብር 10‚000/አሥር ሺህ/ ፣ በከፍተኛ ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር ደግሞ ብር 6‚000.00 /ስድስት ሺህ/ እንዱከፍል ተወስኖበታል።
በጠቅላላው አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል የተወሰነበት ብር 16‚000/አሥራ ስድስት ሺህ ብር/ ነው።
ለሥር መ/ደ/ፍ/ቤት የሥር ከሳሽ /አመልካች/ ክሱን በ24/03/2001 ዓ.ም ያቀረበ ሲሆን ተጠሪዋም ፍ/ቤት ቀርባ ለክሱ መልስ የሰጠችው በ4/07/2001 ዓ.ም መሆኑንና ፍ/ቤቱም የሥረ ነገር ሥልጣን የለኝም በሚል የአመልካችን ክስ ውድቅ ያደረገው በ24/10/2001 መሆኑን የሥር ፍ/ቤት መዝገብ ያመለክታል። ተጠሪዋ ፍ/ቤት ቀርባ ክርክር ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በጉዲዩ ፍርድ እስከተሰጣት ጊዜ ተጠሪዋ ጠበቃዋ ፍ/ቤት የተመላለሡበት ጊዜ አጭር ነው። ፍርደም ብዙም ለውሣኔ የሚረደ ማስረጃዎችን መመርመር ሳያስፈልግ በሥር ነገር ሥልጣን መዝገቡ የተዘጋበት ነው።
ከፍተኛው ፍ/ቤትም ቢሆን ያስቀርባል በሚል ካከራከረ በኋላ በፍርም የፍትሐብሕር ሥ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348/1/ን በመጥቀሥ የሥር መ/ደ/ፍ/ቤት ውሣኔን አጽንቷል። ከዚህ አንፃር ሲታይ የተጠሪ ጠበቃ በፍ/ቤት ቀጠሮዎች በዚህ ጉዲይ ለብዙ ጊዜ በመመላለስ ተጉላላቷል የሚያሰኝ አይደለም።
በመሆኑም ጠበቃው ዕውቀቱን ሥራ ላይ ለማዋል ላበረከተው አስተዋጽኦ እንዱከፍለው የተወሰነው የጠበቃ አበል ከሰጠው አገልግልት አንፃር ሲታይ ከፍ ብል ተገኝቷል። በፍ/ብ/ህ/ቁ.
2635 ’ም’ ከመጠን በላይ የሚደረገውን የሥራ ዋጋ ዳኞች ሉቀንሱ እንደሚችለ የተደነገገውም ተዋዋይ ወገኖች ለሙያው ሥራና ተግባር እንዱሁም ክብር ተቃራኒ የሚሆን የሥራ ዋጋ ስምምነት እንዲያደርጉ ለመከልከል ታስቦ ነው።
የሥር ፍ/ቤቶችም ቢሆኑ የቀረበውን የወጪ ዝርዝር ጥያቄ በሚመረመሩበት ጊዜ የቀረበውን የወጪ ዝርዝር ከዚህ በላይ ከተጠቀሰው የፍትሃብሓር ሕግ ድንጋጌና ላልች አግባብነት ካላቸው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. ድንጋጌዎች አንጻር መርምረው መወሰን አለባቸው። ይህ ታልፍ አመልካች ከፍ ያለውን የጠበቃ አበል እንዱከፍል መወሰናቸው መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ነው።
የሥር የመ/ደ/ፍ/ቤት ኮ/መ/ቁ. 132135 በቀን 24/10/2001 ዓ.ም በዋለው ችልት አመልካች የጠበቃ አበል ብር 10‚000 /አሥር ሺህ/ እንዱከፍል የሰጠው ውሣኔና የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ኮ/መ/ቁ. 82975 በቀን 24/12/2002 አመልካች ብር 6‚000/ስድስት ሺህ/ እንዱከፍል የሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል አመልካች በሁለቱም ፍ/ቤቶች ለወጣው የጠበቃ አበል ብር 2‚000/ሁለት ሺህ/ ለተጠሪ እንዱከፈል ወስነናል።
አመልካች እንደውለ ይፈፀምልኝ በማለት ያቀረበው ውል ሉፈፀም የሚችል አይደለም ብለናል።
የሥር የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 132135 በቀን 24/10/2001 ዓ/ም በዋለው ችልት ካርታ የማሰረዝ ክስ የፍ/ቤት ሥልጣን አይደለም በማለት የሥር ከሳሽን ክስ ውድቅ ያደረገውና ከፍተኛው ፍ/ቤትም በመ/ቁ. 82975 በቀን 09/10/2002 ዓ.ም በዋለው ችልት የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348/1/ን በመጥቀስ ያፀናው በአግባቡ ስለሆነ አጽንተናል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ አመልካችና ተጠሪ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ የተዘጋ ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.