No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዝያ 21 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ አሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ተድላ ማሞ ጌታቸው ጠበቃ አቶ ጌታቸው በለጠ - ቀረቡ ተጠሪ፡- 1- አቶ ፍስሐ ሱመር ቀረቡ 2- አቶ ስዩም ተክለማርያም አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ የሚጣራ ነጥብ ያለው መሆኑ ተገልፆ የቀረበ ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት አንድ በኩል አመልካች ከሣሽ ተጠሪዎች ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል።
በልላ በኩል ተጠሪዎች የተከሣሽ ከሣሾች አመልካች የከሣሽ ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል።
ስለሆነም ተጠሪዎች ከወሰደት ክፍያ ውስጥ ሥራ ላይ ያላዋለትን ብር 221,369.95 /ሁለት መቶ ሃያ አንድ ሺ ሶስት መቶ ስልሣ ዘጠኝ ብር ዘጠና አምስት ሣንቲም/ ከነወለደ ሉመልሱልኝ ይገባል። ከዚህ በተጨማሪ ግንባታው በወቅቱ ባለመጠናቀቁ ቤቱን ለመሥራት የሚጠይቀው ተጨማሪ ወጭ ብር 335,012.70 /ሶስት መቶ ሰላሣ አምስት ሺ አስራ ሁለት ብር ከሰባ ሣንቲም/ ሉከፍለ ይገባል። ግንባታው በመዘግየቱ ብር 71,562.50 መቀጫ የመክፈል ሀላፉነት አለባቸው። በአጠቃላይ ተከሣሾች /ተጠሪዎች / ብር 637,623.88 /ስድስት መቶ ስላሣ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሃያ ሶስት ብር ከሰማኒያ ስምንት ሣንቲም/ እንዱከፍለ ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል። ተጠሪዎች በተከሣሽነት ቀርበው ከሣሽ /አመልካች/ ያቀረበው ክስ ተገቢ አይደለም።
የግንባታ ሥራው በወቅቱ ያልተጠናቀቀው ከሣሽ የግንባታ ፈቃድ የላለው በመሆኑና ግንባታውን እንድናቆም የቀበላ አስተዲደር ስላስገደደን ነው። የዋጋ ጭማሪውም በዚህ ምክንያት የደረሰ ነው።
የግንባታውን ሰማኒያ አምስት ፏርሰንት አጠናቀናል። ከሣሽ ግምቱ ብር 100,000 የሆነ የግንባታ ዕቃ ወስዶል። ስለሆነም የከሣሽ ክስ ውድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክረዋል።
የአመልካችን ክስና የተጠሪዎችን የመከላከያ መልስ እንደዚሁም የተጠሪዎችን የተከሣሽ ከሣሽነት ክስና የአመልካችን የከሣሽ ተከሣሽነት ክርክርና ግራ ቀኙ ያቀረቡትን ማስረጃ በመስማትና በመመርመር የግንባታ ፈቃድ የማውጣት ኃላፉነት ያለባቸው ተከሣሾች /ተጠሪዎች/ በመሆናቸው ለግንባታው መዘግየት በሀላፉነት የሚጠየቁት ተከሣሾች /ተጠሪዎች/ ናቸው። ስለተሰራው የግንባታ ሥራ መጠን የተሻለ ማስረጃ ያቀረበው ከሣሽ /አመልካች/ በመሆኑ ተጠሪዎች/ ተከሣሾች/ በቅድሚያ ክፍያ ከወሰደት ገንዘብ ውስጥ ብር 221,369.95 ለከሣሽ /አመልካች/ ሉመልሱ ይገባል። የግንባታ ሥራው በወቅቱ ላለመጠናቀቁ ሀላፉነት ያለባቸው ተጠሪዎች ስለሆኑ በግንባታው መዘግየት ለተከሰተው የዋጋ ጭማሪ የተከሣሽ ከሣሾች ሉከፍለ ይገባል በማለት ተጠሪዎች ብር 556,382.65 / አምስት መቶ ሃምሣ ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ሰማኒያ ሁለት ብር ከስልሣ አምስት ሣንቲም/ ለአመልካች ከሣሽ ይክፈለ በማለት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ ሰጥቷል።
ተጠሪዎች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚ ችልቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የግንባታ ፈቃድ የማውጣትና ኘላኑን የማፅደቅ ሀላፉነት ያለበት ተዋዋይ ወገን ማንኛቸው እንደሆኑ አመልካች ተጠሪዎች ያደረጉት የግንባታ ሥራ ውል አይገልፅም። ተጠሪዎች የግንባታ ፈቃድ ለማውጣትና ኘላን ለማፀደቅ በውለ በግልፅ ሀላፉነት ያልወሰደ ከመሆኑና የግንባታ ፈቃድና ኘላን የሚሰጠው ለባለቤቱ ወይም ለህጋዊ ወኪል ብቻ እንደሆነ የየካ ክፍለ ከተማ የመሰረተ ልማትና ቤቶች ጉዲይ ጽ/ቤት የግንባታ ፈቃድ ክትትልና ቁጥጥር ደንብ ቁጥር 17 እና የመመሪያ ቁጥር 1/97ን በመጥቀስ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት በፅሐፍ ማብራሪያ ሰጥቷል። ተጠሪዎች የአመልካች ወኪል መሆናቸው አልተረጋገጠም ስለዚህ ግንባታ ፈቃድ የማውጣትና ኘላን የማፅደቅ የአመልካች ሀላፉነት ነው። አመልካች ለተጠሪዎች በኘላኑ መሰረት የተከናወነውን የግንባታ ሥራ በማረጋገጥ ክፍያ የመክፈል ሀላፉነት ያለበት መሆኑ አመልካችና ተጠሪዎች መስከረም 27 ቀን 1996 ዓ.ም ባደረጉት ውል አንቀፅ 3 በግልፅ ተመልክቷል። አመልካች ለተጠሪዎች የከፈለው የመጀመሪያ ክፍያ የግንባታ ሥራውን ለማስጀመር ሁለተኛው ክፍያ ደግሞ ሥራው የተሰራ መሆኑ ተረጋግጦ የተከፈለ መሆኑ ተጠሪዎች ባቀረቡት የሰነድ ማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ ተጠሪዎች ለአመልካች ብር 221,369.95 የመመለስ ግዳታ የለባቸውም። አመልካች የግንባታ ፈቃድ ባለማውጣቱና ኘላን ባለማፀደቁ ምክንያት የግንባታ ሥራው በመዘግየቱ ምክንያት የመጣን የግንባታ ዕቃ ዋጋ ጭማሪ ተጠሪዎች ለአመልካች የመክፈል ግዳታ ያለባቸውም በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል። የተጠሪዎችን የከሣሽነት ክስ በተመለከተ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን አከራክሮ ይወስን በማለት በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 341/1/ መሰረት ለከፍተኛው ፍርድ ቤት መልሶለታል።
አመልካች ሚያዝያ 18 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪዎች አመልካች ጋር የቤት ግንባታ ውል የተዋዋለት የግንባታ ፈቃድ አውጥተውና ኘላኑን አፀድቀው በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ግንባታውን ጨርሰው ለአመልካች ለማስረከብ ነው ተጠሪዎች የግንባታ ፈቃድ ሣይኖርና ኘላን ሣይፀድቅ ቤቱ ሉገነባ እንደማይችል ያውቃለ። የግንባታ ፈቃድ ሣይወጣና ኘላኑ ሣይፀድቅ ሥራ መጀመራቸው ጥፊት ነው። ስለዚህ ለግንባታው መዘግየት ተጠሪዎች ሀላፉነት ያለባቸውም በማለት ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠው ውሣኔ የህግ ስህተት ያለበት ነው።
ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተጠሪዎች የወሰደትን ገንዘብ የሚመጥን የግንባታ ሥራ ሰርተዋል ወይስ አልሰሩም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ የግራ ቀኞችን ክርክርና ማስረጃ በመመዘንና በማጣራት መወሰን ሲገባው በገለልተኛ ባለሙያ ተገምቶ የቀረበውን ማስረጃ ውድቅ በማድረግ ክፍያው የተፈፀመው ለተሰራው ሥራ መጠን ነው በማለት መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ለውለ መዘግየት ሀላፉ መሆናቸውንና የግንባታ ዕቃ ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት የመጣውን ልዩነት መክፈል ሀላፉነት ወስኖ እያለ የተጠሪዎችን የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ ውሣኔ አልሰጠበትም በማለት ጉዲዩን መመለሱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪዎች ታህሣሥ 1 ቀን 2003 ዓ.ም በሰጡት መልስ ስለግንባታ ፈቃድ ማመልከቻ አቀራረብ አሰጣጥና ቁጥጥር በወጣው አዋጅ ቁጥር 316/79 ግንባታ ፈቃድ የሚጠየቀው ሲፈቀድም የሚሰጠው ለባለቤቱ ወይም ለወኪለ ስለመሆኑ በግልፅ ተደንግጓል። ይህንኑ ነጥብ በተመለከተ ማብራሪያ እንዱሰጠው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቶ የሚመለከተው አካል ግልፅ ምላሽ በፅሐፍ ሰጥቶ እያለ ይህንን በማለፍ የከፍተኛው ፍርድ ቤት መወሰኑ ተገቢ ባለመሆኑ በይግባኝ ሰሚው ችልት መሻሩ ተገቢ ነው። አመልካች የግንባታ ፈቃድ ያወጡት ከአንድ ዓመት በኋላ በመሆኑ ግንባታው በመዘግየቱ ምክንያት ለደረሰው የግንባታ ወጭ ጭማሪ ተጠሪዎች የመካስ ሀላፉነት የለብንም። የግንባታ ሥራውን ዋጋ ክፍያ የወሰድነው የተሰራው ሥራ መጠንን በተመለከተ አሰሪው /አመልካች/ እና የሥራ ተቋራጮች የሆኑት ተጠሪዎች ጥር 28 ቀን 1996 ዓ.ም በተፃፈ መተማመኛ ተፈራርመው በመሆኑ የምንመልሰው ገንዘብ የለም። ተጠሪዎች 85% እንደሰራንና አመልካች ለሰራነው ሥራ ክፍያ ያልፈፀመ በመሆኑን ገልፀን ያቀረብነው የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ ሣያጣራና ሣይወሰን የከፍተኛው ፍርድ ቤት ያለፈው በመሆኑ ጉዲዩን ይግባኝ ሰሚው ችልት መመለሱ ተገቢ ነው በማለት ተከራክረዋል። አመልካች ጥር 27 ቀን 2003 ዓ.ም የተፃፈ ሁለት ገፅ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራ ቀኙ ያቀረቡት የፅሐፍ ክርክር ይዘት በአጭሩ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩ ለሰበር ሲቀርብ የተያዘውን ጭብጥ ማለትም የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተጠሪዎች የግንባታ ፈቃድ የማውጣትና ኘላን የማስፀደቅ ሀላፉነት የላለባቸው በመሆኑ ግንባታው በመዘግየቱ ምክንያት የግንባታ ዕቃ ዋጋ በመጨመሩ የደረሰውን የዋጋ ጭማሪ ለመክፈል ሀላፉነት የለባቸውም በማለት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም?
የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ከላይ የተገለፀውን ጭብጥ ለመወሰን በመጀመሪያ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ያላቸው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተለያየ መደምደሚያ ላይ የደረሱበትን ምክንያት መመልከት አስፈላጊ ነው። የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ግንባታ ፈቃድ የማውጣትና ኘላን የማስፀደቅ ሀላፉነት አለባቸው ከሚለው መደምደሚያ ላይ የደረሰው አመልካችና ተጠሪዎች የግንባታ ሥራ ውል ለመዋዋል ሲነጋገሩ ተጠሪዎች የግንባታውን ፈቃድ ከሚመለከተው የመንግስት አካል በማውጣትና ኘላኑን በማስፀደቅ ግንባታውን በስድስት ወር ውስጥ አጠናቅቀው ለማስረከብ ለአመልካች ገልፀውላቸዋል በማለት የአመልካች ምስክሮች ቃል ለሰጡት የምስክርነት ቃል ታዓማኒነትና ክብደት ያለው ማስረጃ መሆኑን በመግለፅና ተጠሪዎች የግንባታ ፈቃድ ሣይኖር ሥራ መጀመራቸው ከሙያቸው አንፃር ሲታይ ጥፊታቸው ነው በማለት መሆኑን በውሣኔው በግልፅ አስፍሮታል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በበኩለ አመልካችና ተጠሪዎች መስከረም 27 ቀን 1996 ዓ.ም የተዋዋለት የግንባታ ሥራ ውል ተጠሪዎች የግንባታ ፈቃድ የማውጣትና ኘላን የማስፀደቅ ሀላፉነት ያለባቸው መሆኑን አይገልፅም። ከዚህ በተጨማሪ የግንባታ ሥራ ፍቃድ የሚሰጠው ለንብረቱ ባለቤት ወይም ለህጋዊ ወኪለ ብቻ መሆኑ አግባብነት ባላቸው የህግ ማዕቀፍችና የአሰራር መመሪያዎች ተመልክቷል። ተጠሪዎች የአመልካች ወኪልች ስለመሆናቸው የቀረበ ማስረጃ የላለ በመሆኑ ተጠሪዎች የግንባታ ሥራ ፈቃድ ለማውጣት የሚችለ አይደለም። ስለሆነም የግንባታ ሥራ ፈቃድ ባለመውጣቱ ምክንያት የግንባታ ሥራ ለመዘግየቱም ሆነ በዚህ ምክንያት ለተከሰተው የዋጋ ለውጥ ተጠሪዎች በሀላፉነት አይጠየቁም በማለት ነው።
ከዚህም የምንረዲው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካችና ተጠሪዎች መስከረም 27 ቀን 1996 ዓ.ም በፅሐፍ ያደረጉትን የግንባታ ሥራ ውል ይዘትና አግባብነት ባላቸው የህግ ማዕቀፍች መሰረት የግንባታ ሥራ ፈቃድ ማውጣት የሚችለው ማንኛው ወገን ነው የሚለውን ነጥብ መሰረት ማድረግ ውሣኔ የሰጠ መሆኑን ነው። የአንድ ሰው ግዳታ ሀላፉነት ከውል ወይም ከህግ የሚመነጭ መሆኑ ግልፅ ነው። ተጠሪዎች ከአመልካች ጋር ሲደራደሩ የግንባታ ፈቃድ ለማውጣትና ኘላኑን ለማስፀደቅ እንደሚችለ እንደገለፀ በአመልካች ምስክሮች የተገለፀ ሲሆን አመልካችና ተጠሪዎች ያደረጉት የግንባታ ሥራ ውል ስምምነት ውስጥ ተጠሪዎች የግንባታ ሥራ ፈቃድ ለማውጣትና ኘላኑን አፅድቀው ሥራ ለመጀመር በግልፅ ያልተዋዋለም መሆኑን ፍሬ ጉዲይ በማጣራትና ማስረጃ በመመዘዘን የሥር ፍርድ ቤት የፈፀመውን ስህተት በይግባኝ አይቶ የማረም ሥልጣን ባለው ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተረጋግጧል።
ከዚህ በተጨማሪ የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች የግንባታ ሥራ ከመጀመራቸው በፉት የግንባታ ሥራ ፈቃድ የተሰጠ መሆኑን የማረጋገጥና የፀደቀ ኘላን መኖሩን የማረጋገጥ ሙያዊ ሀላፉነት አለባቸው በማለት የወሰነው ውሣኔ የግንባታ ፈቃድ አሰጣጥ ክትትልና ቁጥጥር ደንብ ቁጥር 17 እና ከመመሪያ ቁጥር 1/97 አንፃር ሲታይ ተገቢነት የላለው መሆኑን፣ የግንባታ ሥራ ፈቃድ የሚሰጠው ለባለቤቱ ወይም ለወኪለ ብቻ መሆኑን በማረጋገጥ ይግባኝ ሰሚው ችልት የከፍተኛ ፍርድ ቤት በህግ አተረጓጎም ረገድ የፈፀመውን ግድፈት እንዲረመ ለመገንዘብ ችለናል።
የግንባታ ሥራ ፈቃድ የማውጣት ሀላፉነት ያለበት ማን ነው? የሚለው መሰረታዊ ጥያቄ መፍታት ያስፈለገው የግንባታ ሥራ ፈቃድ ባለመውጣቱ ምክንያት ለግንባታ ሥራው መዘግየትና የግንባታ ዕቃዎች ባሣዩት የዋጋ ጭማሪ ምክንያት የወጣውን ተጨማሪ ወጭ የመሸፈን ሀላፉነት ያለበት አመልካች ነው ወይስ ተጠሪ ነው የሚለውን ጭብጥ ለመወሰን ነው። ስለሆነም አመልካች በግንባታ ሥራ ውለ በግልፅ ተጠሪዎች ግዳታ ያልገቡበትንና ከላይ በተገለፁት አግባብነት ባላቸው የህግ ማዕቀፍችና የአሰራር መመሪያዎች የአመልካች ወይም የአመልካች ህጋዊ ወኪልች ተግባርና ሀላፉነት መሆኑ የተደነገገውን ግዳታቸውን ባለመወጣታቸው ምክንያት የግንባታ ሥራው የዘገየ መሆኑ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባለው ይግባኝ ሰሚ ችልት ተረጋግጧል።
ተጠሪዎች ከውል ወይም ከህግ የመነጨ የግንባታ ሥራ ፈቃድ የማውጣትና ኘላን የማስፀደቅ ሀላፉነት የላላባቸው በመሆኑ የግንባታ ሥራው የግንባታ ሥራ ፈቃድ ባለመወጣቱ ምክንያት ለመዘግየቱና የግንባታ ሥራው በመዘግየቱና ምክንያት ለተከሰተው የግንባታ ዕቃ ዋጋ ጭማሪ ተጠያቂ የሚሆኑበት ምክንያት የለም። በመሆኑም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያላለበት በመሆኑ በዚህ በኩል አመልካች ያቀረበውን ክርክር አልተቀበልነውም።
አመልካች ይግባኝ ሰሚው ችልት ተጠሪዎች የሰሩት የግንባታ ሥራ መጠንና ከአመልካች የወሰደትን የገነዘብ መጠን ተመጣጣኝ መሆኑን በማጣራት መወሰን ሲገባው ተጠሪዎች ለአመልካች የሚመልሱት ገንዘብ የለም በማለት መወሰኑ የህግ ስህተት አለበት በማለት ያቀረቡት አቤቱታ በሰበር በጭብጥነት የተያዘ አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ የፍደራል ጠቅለይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ለአመልካች ብር 221,369.95 እንዱመልሱ በማለት የሰጠውን ውሣኔ የሻረው ተጠሪዎች ለገነቡት የግንባታ ሥራ አመልካች ክፍያ ስለሚፈፅምበት ሁኔታ በግንባታ ሥራ ውለ የተስማሙበትን የውል ሀይለ ቃልና አመልካች ተጠሪዎች ጥር 25 ቀን 1996 ዓ.ም በመተማመን የተፈራረሙበትን ሰነድ ይዘት ታዓማኒነትና ክብደት በመመዘን እንደሆነ ተገንዝበናል። ስለሆነም ይግባኝ ሰሚው ችልት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ በመመዘን ውሣኔ የተሰጠበት በመሆኑና የሰበር ችልት ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን የላለው መሆኑ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 80 ንዐስ አንቀፅ 3/ሀ/ እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 10 የተደነገገ በመሆኑ በዚህ በኩል አመልካች ያቀረቡት ክርክር የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም።
አመልካች የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የተጠሪዎችን የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ አጣርቶ እንዱወስን ጉዲዩን መመለሱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት መሆኑን በመግልፅ አመልካች የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የከሣሽን ክስና ማስረጃ በመቀበል ተጠሪዎች በሀላፉነት ይጠየቃለ ብል ስለወሰነ የተጠሪዎችን የተከሣሽ ከሣሽነት ጥያቄ በጥቅለ ውድቅ አድርጎባቸው የነበረ መሆኑን ውሣኔው ያሣያል። ይግባኝ ሰሚው ችልት ተጠሪዎች ለአመልካች ክስ ተጠያቂ አይደለም በማለት ወስኖ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል። ይህም በመሆኑ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ከዚህ በፉት በዝርዝር አጣርቶ ያልወሰነውን የተጠሪዎች የተከሣሽ ከሣሽነት ጥያቄ አጣርቶ እንዱወስን ጉዲዩን መልሶታል። ይህ ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ከመሆኑም በላይ ገና በሂደት ላይ ያለና የመጨረሻ ውሣኔ ያልተሰጠበት በመሆኑ አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን አጣርቶ እንዱወሰን ይግባኝ ሰሚው ችልት መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ያቀረበውን አቤቱታ አልተቀበልነውም።
ከላይ በዘረዘርናቸው ምክንያቶች የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.