No summary available.
መጋቢት 23 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ዲዊት አሰፊ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ተሻለ ደስታ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለው ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ አመልካች የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ የሚጣራ ነጥብ ያለው መሆኑ ጭብጥ ተመሥርቶ ለሰበር የቀረበ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ነው። በፋደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሣሽ አመልካች ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ ፍሬ ጉዲይ የመኪና ሽያጭ ውልን የሚመለከት ነው። በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ በከሣሽነት ቀርበው ተከሣሽ /አመልካች/ ለከሣሽ /ተጠሪ/ና በሥር ፍርድ ቤት ጣልቃ ገብ ተከራካሪ ለነበሩት ወ/ሮ ደብሪቱ በየነ የሰላዲ ቁጥሩ 3-ዐ7999 ኦ.ሮ የሆነውን መኪና በብር 25ዐ,ዐዐዐ /ሁለት መቶ ሀምሣ ሺ ብር/ ሽጠዋል። ከመኪናው ዋጋ ውስጥ ገዥዎች ብር 2ዐዐ,ዐዐዐ /ሁለት መቶ ሺ ብር/ የከፈልን ሲሆን ሻጭ /አመልካች/ ውል ክፍል ቀርበው ውለን ባለመዋዋላቸው የመኪናው ባለሀብትነት ሉተላለፍልን አልቻለም። የመኪናው ባለሀብትነት ለገዥዎች ባለመዛወሩ መኪናውን ለማስመርመርና ቦል ማድረግ ስላልተቻለ ከመጋቢት 2ዐዐዐ ዓ.ም. ጀምሮ መኪናው ሥራ አልሰራም ስለሆነም ከሣሽና ጣልቃ ገብ በወር ብር 8ዐዐዐ /ስምንት ሺ ብር/ ገቢ ያጣን በመሆኑ ብር 2ዐዐዐዐ ጨምረው ተከሣሽ እንዱከፍለ በማለት ክስ አቅርበዋል። አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በተከሣሽነት ቀርበው ሻጭ የሽያጭ ውለን በአግባቡ ፈፅሜአለሁ። የመኪናውን ይዞታ ለገዥዎች አስተላልፈዋል።
የመኪናውን ባለቤትነት ለማስተላለፍ የሚያስፈልጉትን ሰነድች ለገዥዎች አስተላልፈዋል።
የመኪናውን ባለቤትነት ለማስተላለፍ የሚያስፈልጉትን ሰነድች ለገዥዎች ሰጥተዋል። የመኪናውን ስመሀብት የማዞር የእኔ የሻጭ ግዳታና ሀላፉነት አለመሆኑ እስከ ፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተከራክረን ውሣኔ ተሰጥቶበታል። ውለ እንዱፈርስ የቀረበው ክስ የህግ መሰረትም የለውም በማለት ተከራክረዋል።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ የመኪናውን ሻጭ የሆነው ተከሣሽ /አመልካች/ የመኪናውን ባለሀብትነት ለገዥዎች /ተጠሪ/ ለማስተላለፍ አስፈላጊ የሆነውን የመኪና ሽያጭ ውል በውል አዋዋይ ፉት ለመፈረም ፈቃደኛ አይደለም ስለዚህ ተከሣሽ ግዳታውን ያልፈፀመ በመሆኑ ውለ ሉፈርስ ይገባዋል። ተከሣሽ /አመልካች/ ከሣሽና /ለተጠሪና በሥር ጣልቃ ገብ ተከራካሪ ለሆኑት ለእያንዲንዲቸው ብር 112,5ዐዐ /አንድ መቶ አሥራ ሁለት ሺ አምስት መቶ ብር/ በድምሩ ብር 25ዐ,ዐዐዐ /ሁለት መቶ ሀምሣ ሺ ብር/ ይክፈል። ከሣሽ /ተጠሪና/ ጣልቃ ገብ መኪናውን ለተከሣሽ /ለአመልካች/ ያስረክቡ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች የሥር ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 28 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅረበዋል። የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ሻጭ /ይግባኝ ባይ/ መኪናውን የሚመለከቱ አስፈላጊ ሰነድችን ለገዥዎች /ለመልስ ሰጭዎች/ አስረክቧል። መኪናውን ለገዥዎች አስረክቧል የመኪናውን ባለሀብትነት ወደ ገዥዎቹ የማዛወር ኃላፉነት የሻጭ /ይግባኝ ባይ/ እንዲልሆነ ከዚህ በፉት ግራ ቀኙ እስከ ፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባደረጉት ክርክር የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ቁጥር 356ዐ1 ውሣኔ ሰጥቶበታል የመኪና ሽያጭ ውል በውል አዋዋይ ፉት እንዱደረግ የሚያስገድድ የህግ ድንጋጌ የለም። ሻጭ /ይግባኝ ባይ/ የመኪና ሽያጭ ውለን አሟልቶ የፈፀመ ስለሆነ ውለ የሚፈርስበት ምክንያት የለም በማለት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል።
ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙ ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል ይግባኝ ሰሚው ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል።
አመልካች ግንቦት 25 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር ማመልከቻ የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ቁጥር 4536ዐ ሚያዝያ 29 ቀን 2ዐዐ2 ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ የወሰነው ከዚህ በፉት ተጠሪ የመኪናውን ሽያጭ ውል እንዱፈፅም ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርበው ከፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እስከ ፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተከራክረን ይግባኝ ሰሚው ችልት በመዝገብ ቁጥር 356ዐ1 የሰጠውን ውሣኔ የሚሽርና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። አንድ ውል የማይፈፀመው ውለ ሣይፈፀም የቀረ ወይም ውለ ሉፈፀም የማይችል ሆኖ ሲገኝ ነው። አመልካች ከሶስት ዓመት በፉት የሽያጭ ውለን ፈፅሜአለሁ። ስለዚህ የመኪናው ባለሀብትነት ወደ ገዥዎች አላዛወርክም በማለት ውለ እንዱፈርስ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት። መኪናው የቆመው ለፍርድ ማስፈፀሚያነት ስለተያዘ ነው የመኪናው ዱኘሪሼሽን ዋጋና ገዥዎች በመኪናው በመጠቀም ሲሰበስቡት የነበረው ገቢ ሣይታሰብ መኪናውን በመውሰድ ገንዘባቸውን ይክፈላቸው በማለት የተሰጠው ውሣኔም መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪ በበኩላቸው ጥቅምት 19 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም. በተፃፈ መልስ እኔና አመልካች ከዚህ በፉት የተከራከርንበት ጭብጥ የሚያስነሳው የህግ ጥያቄ አሁን ከምንከራከርበት ጉዲይ የተለየ በመሆኑ አመልካች ጉዲዩ ከዚህ በፉት የተወሰነ ነው በማለት የሚያቀርቡት ክርክር የህግ መሰረት የለውም። የሽያጭ ውለ አልተፈፀመም። አመልካች በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2281 የተጣለባቸውን ግዳታ አልተወጡም። መኪናውን ያሣገደትም አመልካች ናቸው ስለዚህ ውለ ፈርሶ ወደ ነበርንበት እንድንመለስ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥተዋል።
አመልካች በቅንነት የሸጥኩት መኪና በገዥዎች ሥም እንዱዛወር የካቲት 12 ቀን 1999 ዓ.ም.
ከተጠሪ ጋር በመሆን በፅሐፍ ለምስራቅ ሸዋ ዞን ንግድ ኢንደስትሪና ትራንስፕርት ጽ/ቤት ማመልከቻ አቅርቤአለሁ። የመኪናውንም ክሉራንስ ለተጠሪ አስረክቤአለሁ። ስለዚህ በእኔ በኩል የሚፈፀም የሚገባኝን ማናቸውንም ግዳታ ተወጥቼ እያለ ውለ እንዱፈርስ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ተከራክረዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው የመኪና ሽያጭ ውል ፈርሶ ተዋዋዮቹ ወደነበሩበት ይመለሱ በማለት የሰጠው ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ይህንን ጭብጥ ለመመለስ በመጀመሪያ ተጠሪ ከዚህ በፉት ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ባቀረበው ክስ መነሻ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሰኔ 23 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠውን ውሣኔ በይግባኝ በማየት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ታህሣሥ 25 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሣኔ በይግባኝ በማየት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ የሰጠውን ውሣኔ ይዘት መመልከቱ አስፈላጊ በመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ መዝገብ ን በማስቀረብ ተመልክተናል።
ተጠሪና አመልካች በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመዝገብ የተከራከሩት ሻጭ አመልካች መኪናውን ከዕዲና እገዲ ነፃ በማድረግ ስም እንዱያዛውሩ በማለት ተጠሪ በመክሰሳቸውና አመልካች መኪናው ከዕዲና እገዲ ነፃ መሆኑን የካቲት 29 ቀን 1999 ከጉለላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 09/15 እና ከኢንሹራንስ ማስረጃ በማምጣት የሰጠ መሆኑን በማንሣት ተከራክሮ የአመልካች ማስረጃ ተዓማኒነት የለውም በማለት የሥር ፍርድ ቤት የወሰነ መሆኑን ተረድተናል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር ተሰኝተው ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበው ከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ሻጭ የሸጡትን መኪናና ሉብሬ ለገዥዎች አስተላልፈዋል ስሙ እንዱተላለፍላቸውም ለሚመለከተው አካል የተለያዩ ደብዲቤዎችን አቅርበዋል የመኪናው ዕዲ እስከ የካቲት 30 ቀን 1999 ዓ.ም የተከፈለ ለመሆኑም ማጣሪያ አቅርበዋል። የመኪና ሽያጭ ውል የተለየ ፍርም የለውም የመልስ ሰጭዎች ጠበቃ እንደገለፁት በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1723 መሰረት የመድረግ ግዳታ የለበትም የመኪና ሽያጭ ውል ከተደረገ በኋላ ስመሀብቱ የሚተላለፍበት ሁኔታ በህግ ማስታወቂያ ቁጥር 360/6/ ላይ በዝርዝር ተመልክቷል። በዚሁ መሰረት የሽያጭ ውለና ሉብሬው ሲቀርብለት የሚመለከተው የመንገድ ትራንስፕርት ስመሀብቱን በገዥው ስም ያዛውራል ሻጭ በህግ ለመንግስት መሥሪያ ቤት የተሰጠውን ስም የማዛወር ግዳታ ሉወስደ አይችለም የሚል ዝርዝር ምክንያት በመስጠት ተጠሪ አመልካች የመኪናውን ስም ያዛውርልኝ በማለት ያቀረቡት ክስ የክስ ምክንያት የላለውና ሻጭ (አመልካች) መኪናውን በማስረከብ ስም እንዱዛወርላቸው ደብዲቤ በማስገባት፣ የመኪናው ዕዲ መከፈለን ማረጋገጫ በማቅረብ ግደታቸውን የተወጡ መሆኑን በውሣኔው ውስጥ በግልፅ በማስፈር ውሣኔ የሰጠ መሆኑ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ መዝገብ ታህሳስ 25 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠውን ውሣኔ በማየት ለመረዲት ችለናል። ተጠሪ የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ አቅርበው ይግባኝ ሰሚው ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ይዘቱ ከላይ የተገለፀውን የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ያፀናው መሆኑን በይግባኝ መዝገብ ግንቦት 6 ቀን 2000 ዓ.ም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ከሰጠው ውሣኔ ተገንዝበናል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ የሰጠው ውሣኔና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ መዝገብ ያፀናው ውሣኔ መሰረታዊ ይዘት የመኪናው ሻጭ የሆኑት አመልካች በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2274 በተደነገገው መሰረት የሸጡትን መኪና ለገዥዎች ያስረከቡ መሆኑንና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2281 በተደነገገው መሰረት የተሸጠውን መኪና ባለሀብትነት ለገዥዎች (ለተጠሪና በሥር ጣልቃ ገብ ተከራካሪ ለነበሩት) ለማስተላለፍ አስፈላጊ የሆኑ ተግባሮችን የፈፀመ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። አመልካች በሽያጭ ውለ መሰረት በእሳቸው በኩል መፈፀም የሚገባቸውን ተግባራት ሙለ በሙለ የፈፀሙና ቀሪው ሥራ ሥልጣን ያለው የአስተዲደር ክፍል መሆኑን በማረጋገጥ የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ እና በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ውሣኔ ሰጥተውበታል።
ተጠሪ ከላይ ቁጥራቸው በተገለፀው መዛግብት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡትን ውሣኔ ግልባጭ የመኪናውን ስመሀብት ከሻጭ ወደገዥ የማዛወር ሥልጣን ላለው አካል በማቅረብ የመኪናው ስመሀብት እንዱዛወርላቸው መጠየቅና አስፈላጊም ከሆነ በሚመለከተው የመንግስት አካል ላይ ክስ በማቅረብ መብታቸውን ማስከበር ይገባቸዋል። ተጠሪ በሽያጭ ውለ መሰረት ግዳታቸውን ሙለ በሙለ አሟልተው የፈፀሙ መሆኑ በፍርድ የተረጋገጠላቸውን አመልካችን በሽያጭ ውለ መሰረት ግዳታውን አሟልቶ ያልፈፀመ ስለሆነ ውለ ፈርሶ ወደነበርንበት እንድንመለስ ይወሰንልን በማለት መክሰሳቸው የህግ መሰረት የለውም። ይህን ክስ በመቀበል የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ውለ እንዱፈርስ የሰጠው ውሣኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ መዝገብ የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔን በማፅናት የሰጠው ውሣኔ የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 5 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረታዊ ድንጋጌ የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል። ተጠሪ አሁን በቀረበው ክስና በፉት ከአመልካች ጋር ተከራክረው ውሣኔ ያገኘው ጉዲይ መካከል ግኑኝነት የላለው የተለያዩ ጭብጦች መሆናቸውን በማንሣት የተከራከሩ ቢሆንም አመልካች በሽያጭ ውለ መሰረት ግዳታቸውን አሟልተው ተወጥተዋል ወይስ አልተወጡም?
የሚለውን ነጥብ በመመርመር አመልካች በሽያጭ ውለ መሰረት ግዳታቸውን አሟልተው የተወጡ መሆኑን በመግለፅ የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ውሣኔ ሰጥተውበታል ስለሆነም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች በሽያጭ ውለ መሰረት ግዳታውን ስላልተወጣ ውለ ፈርሶ ተዋዋዮች ወደ ነበሩበት ይመለሱ በማለት በመዝገብ የሰጠው ውሣኔ ከዚህ በፉት የመጨረሻ ውሣኔ የተሰጠበትን ጭብጥ በድጋሜ በማየት የተሰጠው ከዚህ በፉት ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር የተሰጠ ውሣኔ በመሆኑ ተጠሪ ያቀረቡት ክርክር ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
በመሆኑም አመልካች በሽያጭ ውለና ስለ ሽያጭ ውል በተደነገጉት የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ግዳታቸውን አሟልተው የተወጡ መሆኑንና ቀሪው ሥራ ጉዲዩ የሚመለከተው የመንግስት አካል መሆኑን በማረጋገጥ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ የሰጠው ውሣኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ የሰጠው ውሣኔ በሰበር ታይቶ ሣይሻሻል ወይም ሣይሻር አመልካች በሽያጭ ውለ መሰረት ግዳታውን አሟልቶ ያልፈፀመ በመሆኑ የሽያጭ ውለ ሉፈርስ ይገባዋል በማለት ተጠሪ ያቀረበውን ክስ በመቀበል የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 5(1)ን የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 28 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠውን ውሣኔ በማፅናት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በሚያዝያ 29 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ መጋቢት 8 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
ጽ/ሽ የሰ.መ.
መጋቢት 22 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፣ ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች - ወ/ሮ መሰረት በቀለ ጠበቃ አቶ ታየ ገብረመድህን ቀረቡተጠሪ - ወ/ሮ ኤልዛ ሶሞኔላ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ የሚጣራ ነጥብ ያለው መሆኑ ተገልፆ ለሰበር ችልት ስለቀረበ ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሣሽ አመልካች ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል።ተጠሪ/ከሣሽ/ ተከሣሽ/አመልካች/ አውሉያቸውን ተለማምነው በጠና ታሞ የነበረውን ባለቤቴን እንደሚያድኑት ገልፀው የሽያጭ ውል የተደረገ በማስመሰል በድሬደዋ ከተማ በካርታ ቁጥር 1813 የተመዘገበውን ቤት በነፃ በስጦታ ወስደዋል ውለ ህገወጥ በመሆኑ እንዱፈርስ ይህ የሚታለፍ ቢሆን ውለ በአስገዲጅነት ማሟላት እንዲለባቸው በህግ የተደነገገውን መስፈርት የማያሟላ በመሆኑ እንዱፈርስልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል። አመልካች በተከሣሽነት ቀርበው ውለ በሙለ ፈቃድና ስምምነት ከሣሽ ቤታቸውን የሸጡልኝ በመሆኑ ውለ ለህግ ተቃራኒ አይደለም። በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት የተደረገ በመሆኑ አስገዲጅ መስፈርቶችን የሚያሟላ ውል በመሆኑ የሚፈርስበት ምክንያት የለም በማለት መልስ ሰጥተዋል። የሥር ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክር ከመረመረ በኃላ ከሣሽ /ተጠሪ/ እና ተከሣሽ /አመልካች/ ሰኔ 25 ቀን 1996 ዓ.ም ያደረጉት ውል ተዋዋዮቹ ብቻ የፈረሙበት ሰነድ ነው። በውልና ማስረጃ የተደረገ ቢሆንም በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1727 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት በሁለት ምስክሮች የተፈረመ አይደለም ስለዚህ ውለ እንደረቂቅ የሚታይና ፈራሽ ነው በማለት ከሣሽ /ተጠሪ/ ከተከሣሽ የወሰደትን ብር 23‚000 /ሃያ ሶስት ሺህ ብር/ ለተከሣሽ ይመልሱ ተከሣሽ /አመልካች/ በድሬዲዋ ከተማ በካርታ ቁጥር 4813 በ800 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈውን የድርጅት ቤት ተከሣሽ /ተጠሪ/ ያስረክቡ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ከርክር ከመረመረ በኃላ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል። አመልካች ሰኔ 15 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በድሬዲዋ ውልና ማስረጃ ጽ/ቤት ፉት የተደረገ ነው። ውለ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1723/1/ የተደነገገውን ፍርማሉቲ ያሟላል። ውለ በፅሐፍ የተደረገ በመሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2877 የተደነገገውን ፍርማሉቲ ያሟላል ውለ በሁለት ምስክሮች አለመፈረሙና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1727/2/ የተደነገገውን ፍርማሉቲ አላሟላም በማለት ውለ እንዱፈርስ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት። ቤቱን ከገዛሁ በኃላ ከብር 300‚000 /ሶስት መቶ ሺህ ብር በላይ ወጭ በማድረግ የማስፊፉያ ግንባታ አድርጌለሁ ስለዚህ ውለ ፈርሶ ወደነበራችሁበት ተመለሱ በማለት የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩላቸው ጥር 13 ቀን 2003 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት መልስ የውልና ማስረጃ ጽ/ቤት ባለሥልጣን ውለን ተቀብል ከመመዝገቡ ውጭ ውለን ስንፈራረም አላየም ውለን መንደር ውስጥ ነው የተፈራረምነው በውለ ላይ ምስክሮች እንዱኖሩ ያልተደረገው አመልካች እኔን በውለ ላይ ያስፈረሙኝ አውሉያው አዞሻል የሚልና ላልች የማስፈራሪያ ቃልችን በመጠቀም ያስፈረሙኝ በመሆኑ ነው። ውልና ማስረጃ መደረጉ የምስክሮችን ፊርማ አስፈላጊነት ቀሪ አያደርግም ስለዚህ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተገቢነት የለውም በማለት ተከራክረዋል አመልካች ጥር 30 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ የመልስ መልስ የተጠሪ ባለቤት ከዚህ ዓለም በሞት የተለያት ጥር 13 ቀን 1995 ዓ.ም በመሆኑና ተጠሪ ቤቱን የሸጡልኝ ሰኔ 25 ቀን 1996 ዓ.ም ተጠሪ አመልካች አሰፈራርታኝ ነው የፈረምኩት በማለት ያቀረቡት ክርክር ዕውነትነት የላለውና በክፈ ልቦና የቀረበ ነው በማለት ተከራክረዋል። ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራቀኙ ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው አመልካችና ተጠሪ ያደረጉት ውል በሁለት ምስክሮች ፊርማ ያልተረጋገጠ በመሆኑ ውለ ፈርሶ ተዋዋዬች ወደነበሩበት ይመለሱ በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
አንድን ውል የፀና ውል ለማድረግ ከሚያስፈልጉ ሶስት መሰረታዊ መስፈርቶች አንደኛው የውለ አፃፃፍ በህግ የታዘዘ በሆነ ጊዜ ውለ በህጉ የተመለከተውን ልዩ ፍርም በሚያሟላ ሁኔታ መደረጉ እንደሆነ በፍታብሐር ህግ ቁጥር 1678/ሐ/ በግልፅ ተደንግጓል። ተጠሪና አመልካች ያደረጉት የማይንቀሳቀሥ ንብረት ሽያጭ ውል ነው የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውለ በፅሐፍ ላደረግ የሚገባው መሆኑን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2877 ‛የውለ ፍርም“ በሚል ርዕስ ሥር ተደንግጓል። ህጉ በግልፅ የሚያስገድድ በሆነ ጊዜ ውለ በህጉ የታዘዘውን ልዩ ፍርም ማሟላት የሚገባው መሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1719 ንዐስ አንቀጽ 2 የተደነገገ ሲሆን ውለ በፅሐፍ እንዱደረግ በህግ የተደነገገ ግዳታ ሲኖር ልዩ በሆነ አሰራር ተገልፆ በውለ ግዳታ ያለባቸው ሰዎች ውለን መፈረም እንዲለባቸው የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1727 ንዐስ አንቀጽ 1 ይደነግጋል። ውለ በፅሐፍ እንዱሆን ህግ የሚያስገድድ በሆነ ጊዜ በፅሐፍ በተደረገው ውል ላይ ተዋዋዬች መፈረማቸው ብቻውን ህጉ የፀና ውል እንደማያደርገው በሁለት ምስክሮች ፉት ካልተረጋገጠ አይፀናም በማለት የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1727 ንዐስ አንቀጽ 2 በግልፅ ደንግጓል።
ከላይ ከተገለፀው በተጨማሪ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1727 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ውለ መደረጉን የሚያረጋግጡ ምስክሮች አካለመጠን ያልደረሱና ያልተከለከለ መሆን እንደሚገባቸው በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1729/1/ ተደንግጓል። በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1723/1/ መሰረት የማይንቀሳቀሥ ሽያጭ በውል አዋዋይ ወይም በፍርድ ቤት መዝገብ ሹም ፉት እንዲደረገ የተደነገገው በፍታብሐር ህግ ቁጥር 1727 ንዐስ አንቀጽ 2 እና በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1729 ንዐስ አንቀጽ 1 የተደነገገውን አስገዲጅ ፍርም ህግ አውጭው ለማስቀረት ወይም ለመተካት በማሰብ አይደለም። በአንፃሩ የማይንቀሳቀሥ ንብረት በውል አዋዋይ ፉት ወይም በፍርድ ቤት መዝገብ ሹም ፉት ሲደረግ ውለን የሚያዋውለው ባለሥልጣን በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1678 የተደነገጉት ሶስት መሰረታዊ ሁኔታዎች መሟላታቸውንና በተለይም በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1727 ንዐስ አንቀጽ 1 እና ንዐስ አንቀጽ 2 የተደነገጉት ፍርማሉቲዎች መሟላታቸውን በማረጋገጥ ተዋዋዩች ውለን እንዱፈራረሙ ያደርጋል የሚል ሀሳብ ስለነበረው ነው። በያዝነው ጉዲይ ተጠሪና አመልካች ሰኔ 25 ቀን 1996 ዓ.ም ያደረጉት የቤት ሽያጭ ውል በፍታብሐር ህግ ቁጥር 1678 /ሐ/ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2877 እና በፍታብሐር ህግ ቁጥር 1727 ንዐስ አንቀጽ 2 የተደነገገውን አስገዲጅና ልዩ የውል ፍርም የማያሟላ በመሆኑ ውለ ሉፈርስ ይገባዋል በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች ቤቱን ከገዙ በኃላ ከፍተኛ የሆነ የማስፊፉያ ግንባታ ሥራ እንደሰሩ በሰበር አቤቱታቸው በማንሳት ተከራክረዋል። ሆኖም አመልካች ይኸንን ለሰበር ችልት ያቀረቡትን መከራከሪያ ለሥር ፍርድ ቤት አንስተው ያልተከራከሩበትና በሰበር ደረጃ የቀረበ አዱስ የፍሬ ጉዲይ ክርክር መሆኑን ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ግልባጭ ተገንዝበናል በመሆኑም አመልካች ቤቱን ከገዙ በኃላ ተጨማሪ ግንባታ እንደገነቡ በማንሣት በሰበር ያቀረቡት ክርክር በሥር ፍርድ ቤት ያልተነሣና የፍታብሓር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 329 ንዐስ አንቀጽ 1ን በሚጥስ መንገድ ለሰበር ችልት የቀረበ አዱስ ክርክር በመሆኑ ህጋዊ መሰረትና ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
ስለሆነም ከላይ በዝርዝር የገለፅናቸውን መሰረታዊና አስገዲጅ የህግ ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተጠሪና አመልካች ያደረጉት የቤት ሽያጭ ውል እንዱፈርስ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ችልት መስከረም 26 ቀን 2003 ዓ.ም የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
ግራቀኙ በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ለየራሳቸው ይቻለ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.