No summary available.
መጋቢት 9 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ አመልካች፡- ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ - ይሁንልኝ ቡል ቀረበ ተጠሪዎች፡-
በዚህ ሰበር መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ ለትምህርት (ለስልጠና) የተደረገው ወጪ በውለ መሰረት ይመለስልኝ በማለት አመልካች የመሰረተውን ክስ የሚመለከት ነው። ከመዝገቡ እንደሚታየው 1ኛ ተጠሪ በውሃ (ወተር) ኢንጂነሪንግ የማስትሬት ዱግሪ ትምህርቱን በአመልካች ድጋፍ እና ትብብር ፈቃድ ወደ ቤልጂየም ሀገር ሄድ እንዱማር እና ተምሮ ሲመለስም ለተማረበት ሁለት ዓመት ሦስት እጥፍ ማለትም ስድስት ዓመት አመልካችን ለማገልገል፣ ይህን ማድረግ ካልቻለ ደግሞ ለትምህርት የወጣውን እና ለቤተሰቡ የተከፈለውን ደመወዝ በጠቅላላው ብር 190,470.00 ለአመልካች እንዱከፍል ስምምነት ተደርጎአል። 2ኛ ተጠሪም 1ኛ ተጠሪ ግዳታውን ባይወጣ ባልተነጣጠለ ኃላፉነት ገንዘቡን ለመክፈል ግዳታ ገብታለች። ሆኖም 1ኛ ተጠሪ በገባው ግዳታ መሰረት ተመልሶ ለማገልገል ፈቃደኛ አልሆነም። ስለዚህም ሁለቱም ተጠሪዎች ገንዘቡን ይከፍለ ዘንድ ይወሰንልኝ በማለት ነው አመልካች ክሱን የመሰረተው። ክሱ የቀረበለት የሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት መደበኛ ችልት ተጠሪዎች የሰጡትን መልስ ካየ በኋላ፣ 1ኛ ተጠሪ በአሁኑ ጊዜ በመማር ላይ እንደሆነ ማስረጃ ቀርቦልኛል የሚል ምክንያት በመስጠት ክሱን ሰርዞአል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች የተሰጠውን ትዕዛዝ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ክርክሩ የተሰማ ሲሆን፣ በመጨረሻም ፍ/ቤቱ ይግባኝ የተባለበትን ትዕዛዝ አፅንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች ሰኔ 4 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ በሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞአል የሚልበትን ምክንያት በመግለጽ ስህተቱ ይታረምለት ዘንድ ጠይቆአል።
በበኩላችንም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በግራ ቀኝ ወገኖች የተገባውን ውል መሰረት ያደረገ ነው ወይ? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው። በመሆኑም ጭብጡን ግራቀኝ ወገኖች ካሰሙት ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ካቀረቡት ክርክር መገንዘብ እንደቻልነው ለክሱ መነሻ የሆነው ውል በግራቀኙ መካከል ስለመደረጉ እና 1ኛ ተጠሪም ወደቤልጅየም ሃገር ሄድ የማስተርስ ዱግሪውን ስለማግኘቱ አልተካደም ወይም አከራካሪ አልሆነም። ተጠሪዎች ክሱን የተቃወሙት 1ኛ ተጠሪ የማስተርስ ዱግሪውን ካገኘ በኋላ ወደ አሜሪካን ሃገር በመሄድ ለፑ.ኤች. ዱግሪ ትምህርት በመቀጠል ላይ ስለሆነ በውለ መሰረት ተመልሶ አመልካችን ሉያገለግል አልቻለም በሚል ገንዘቡን እንዱከፍል አይገደድም የሚል ምክንያት በመስጠት ነው። የሥር ፍ/ቤቶችም ይህን በተጠሪዎች የቀረበውን የመከራከሪያ ነጥብ እንዲለ በመቀበል ነው ክሱን ውድቅ ያደረጉት። አመልካች 1ኛ ተጠሪ የቀጠለውን ትምህርት ጨርሶ ሲመለስ ክሱን ማንቀሳቀስ ይችላል በማለትም ነው ክሱን የሰረዙት።
አመልካች በዚህ መልኩ የተሰጠውን ውሳኔ የተቃወመው በመሃከላችን የተደረገውን ውል እና ሕጉን መሰረት ያደረገ አይደለም በማለት ነው።
በበኩላችን እንደምናየው እና እንደምንገነዘበው ክርክሩ ሉወሰን የሚገባው በግራቀኝ ወገኖች የተደረገውን ውል እና አግባብነት ያለውን ሕግ መሰረት በማድረግ ነው። በመሆኑም ከሁለ በፉት የውለን ይዘት እንደዚሁም ውለ ለተዋዋይ ወገኖች የሰጠውን መብት እና የጣለውን ግዳታ መመርመር ተገቢ ይሆናል። በክርክሩ እንደተገለጸው አመልካች 1ኛ ተጠሪን በማስተርስ ዱግሪ ለማስተማር ግዳታ የገባ ሲሆን፣ ተጠሪዎች ደግሞ በውለ ለተመለከቱት ዓመታት አመልካችን ለማገልገል፤ ይህ ካልተፈጸመ ደግሞ ለትምህርቱ የወጣውን ወጪ ለአመልካች ለመተካት ግዳታ ገብተዋል። 1ኛ ተጠሪ በውለ መሰረት ትምህርቱን ጨርሶ የማስተርስ ዱግሪውን ያገኘ ቢሆንም፤
ወደ አገሩ በመመለስ ለአመልካች አገልግልት አልሰጠም ወይም ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።
ይህም ማለት ውለ በሰጠው መብት የተጠቀመ (ትምህርቱን የተማረ) ሲሆን፣ ግዳታውን ግን አልፈጸመም። የፑ.ኤች ዱግሪ ትምህርት እንዱቀጥል የሚያስችለው ተጨማሪ ስምምነትም ከአመልካች አላገኘም።
No topics extracted.
በሕጉ አግባብ የተቋቋሙ ውልች ባቋቋሙዋቸው ሰዎች ላይ ሕግ ስለመሆናቸው በፍትሐብሕር ሕግ ቁ.1731 በተቀመጠው ድንጋጌ ተመልክቶአል። ውለታዎች ግልጽ በሆኑ ጊዜ ግልጽ ሆኖ ከሚሰማው በመራቅ ወይም ከዚሁ በመውጣት በፍ/ቤት ሉተረጎሙ እንደማይችለ በፍ/ብ/ሕግ ቁ.1733 ተደንግጎአል። በያዝነው ጉዲይ ለክርክሩ መሰረት የሆነው ውል ግልጽ ነው።
1ኛ ተጠሪ ተመልሶ አመልካችን ለማገልገል ግዳታ የገባው የማስተርስ ዱግሪውን ካገኘ በኋላ ነው።
በዚህ መሰረትም ትምህርቱን ጨርሶ ዱግሪውን እንዲገኘ ተረጋግጠኦል። በመሆኑም የማገልገል ግዳታውን መወጣት የሚችለው በኋላ የጀመረውን የፑ.ኤችዱ ድግሪ ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ ነው ለማለት የሚቻልበት የውልም ሆነ የሕግ አግባብ የለም። የሥር ፍ/ቤቶች ወደላላኛው ጫፍ (ትምህርቱን ጨርሶ ከተመለሰ በኋላ ክሱ ይቀጥል ወደሚለው) የሄደት ግልጽ የሆነውን ውል ግልጽ ሆኖ ከሚታየው በመውጣት እንደሆነ ነው መገንዘብ የቻልነው። ከዚህ የተነሣም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ በሕጉ አተረጓጎም ረገድ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል። በዚህ መሰረትም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ