No summary available.
ግንቦት 15 ቀን 2003ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴአመልካች ፡- የኢት/ንግድ ባንክ አልቀረበምተጠሪዎች ፡- 1. አቶ መሐመድ ሙሳ 2. ወ/ሮ ሐሉማ ሃብቤ 3. ወ/ሮ ነኢማ ዩያ ተወካይ አቶ መሐመድ ሙሣ ቀረቡ 4. ወ/ሮ ሽኩር ዋቃዩ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ተጠሪዎች በስር ከፍተኛ ፍ/ቤት ከሳሾች ሲሆኑ አመልካች 2ኛ ተከሳሽ፣ እንዱሁም የኢት/ መንገድች ባለሥልጣን 1ኛ ተከሳሽ፣ የሚጨታ ከተማ አስተዲደር ደግሞ 3ኛ ተከሳሽ ነበሩ። ክሱም በሚጨታ ከተማ ቀበላ 01 ውስጥ በ1226 ካሬ ሜትር ላይ የሰፈረውን ግምቱ 250,000 ብር የሚያወጣውን የከሳሾች ቤት 1ኛ ተከሳሽ በብር 162,306 ብቻ በመገመት ይህንኑ ገንዘብ 1ኛ ተከሳሽ ለ2ኛ ተከሳሽ ሰጥቶ 2ኛ ተከሳሽም ከከሳሾች ጋር ምንም ዓይነት የዋስትናም ሆነ የብድር ውል ሳይኖር ገንዘባችንን የያዘብን ሲሆን 3ኛ ተከሳሽ ደግሞ የተለያዩ መብታችንን የሚጋፈ ደብዲቤዎች የሰጠ ስለሆነ ተከሳሾቹ የቤታችንን ግምት ብር 250,000 ከወጪና ኪሳራ ጭምር እንዱከፍለ ይወሰንልን የሚል ነው።
የሥር 1ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በስር ፍ/ቤት በተደረገ ክርክር ከክሱ የወጡ ሲሆን የ2ኛ ተከሳሽ መልስ 1ኛ ከሳሽ በ23/7/1986 ዓ.ም ከባንኩ ጋር በተደረገ ውል ብር 40,000 ተበድሮ ባለመክፈለ የተነሳ ወለድ ተጨምሮበት ብር 71,398.67 እዲ አለበት፣ እንዱሁም ወንድሙ ሶፍያን ሙሳ የተባለው ከባንኩ ጋር በተደረገ ውል ገንዘብ ሲበደር ከሳሽም የአንድነትና ነጠላ ዋስትና የገባ ሲሆን ከተበዲሪው የሚፈለገው ብር 19,583.53 በመሆኑ ከሳሽ ገንዘቡን የመክፈል ግዳታ ስላለበት በአጠቃላይ ከ1ኛ ከሳሽ ብር 90,583.59 የሚፈለግበት በመሆኑ ይህው ገንዘብ ተቀንሶ ቀሪውን ብር 71,727.27 ከሳሾች እንዱወስደ ቢነገራቸውም ለመውሰድ ፈቃደኞች አይደለም የሚል ሲሆን 1ኛ ከሳሽ የፈረመውን የብድር ውል እና የዋስትና ሰነድ አያይዞ አቅርቧል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የመረመረው የስር ከፍተኛ ፍ/ቤትም ባንኩ በብድር ውለ አንቀጽ 15 መሰረት በርሱ ዘንድ የተቀመጠውን ገንዘብ ለሚፈለገው የብድር እዲ እንዱቻቻል ከሚያደርግ ውጪ በሐዋላ አገልግልት የተላከውን በእንቅስቃሴ የሚገኘውን ገንዘብ ለእዲው ማቻቻል አይችልም በማለት 1ኛ ተከሳሽ ማለት የኢት/መንገድች ባለሥልጣን የላከውን የከሳሾች ገንዘብ ብር 162,306.90 ይመልስ በማለት ፈርዶል።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት በበኩለ ክርክሩ በይግባኝ ቀርቦለት ከመረመረ በኋላ ቤቱ በዋስትና የተያዘ ስለመሆኑ ውለ የሚያመለከት አይደለም። ይግባኝ ባይ /ያሁን አመልካች/ ውለን መሰረት አድርጏ ክስ አቅርቦ እዲውን ማስከፈል ከሚችል በቀር የመ/ሰጪዎችን ገንዘብ መያዙ አግባብነት የለውም። በስር ከፍተኛ ፍ/ቤትም ቢሆን ስለ ብድር ውል አንቀጽ 15 የሰጠው ትርጉም አግባብ ሆኖ አላገኘሁም በማለትና የውሳኔውን ድምዲሜ በመቀበል ይግባኝ ባይ ለመልስ ሰጪዎች የያዘውን ገንዘብ ይመልስ መባለ የሚነቀፍ አይደለም ተብሎል።
በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ቅር የተሰኘው የአሁን ሰበር አመልካችም ባቀረበው ቅሬታ አመልካች በግልጽ ከተጠሪዎች ጋር ባደረገው የብድር ውልና የአንድነትና የነጠላ ዋስትና ውል መሰረት ገንዘቡ ባለመከፈለ ዕዲውን ለማቻቻል በማንኛውም መልኩ በባንኩ ዘንድ በባለእዲዎች ስም የተቀመጠውን ገንዘብ መውሰድ የሚችል ሆኖ እያለ የስር ፍ/ቤቶች ለተጠሪዎች እዲ ገቢ የተደረገውን ገንዘብ አመልካች እንዱመልስ መወሰናቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው ብሎል።
ተጠሪዎች በበኩላቸው በሰጡት መልስ ከአመልካች ጋር የተፈራረምነው የብድርም ሆነ የአንድነትና የነጠላ ዋስትና ውል የለም፣ በፍትሐብሕር ህግ አንቀጽ 1832 እና 1833 መሰረትም የእዲ ማቻቻያ የሚያስደርጉ ምክንያቶች የለም በማለት የአመልካች የሰበር አቤቱታ ውድቅ ተደርጏ የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እንዱፀና ጠይቀዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከዚህ በላይ እንደተገለፀው የቀረበ ሲሆን እኛም አመልካች ለተጠሪዎች የቤት ግምት የተላከውን ገንዘብ ለእዲ ማቻቻያነት መያዙ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ ይዘን እንደሚከተለው መርምረናል።
በፍታብሓር ህጋችን እዲን ለማቻቻል የሚቻለው በሶስት መንገድች ሲሆን 1ኛው መንገድ በፍታብሓር ህግ አንቀጽ 1838/1/ እንደተጠቀሰው ባለእዲውን እንዱቻቻልለት መፈለጉን ለባለገንዘቡ ሲያስታውቅ ወይም ባለእዲው እዲው እንዱቻቻልለት ስምምነቱን ሲገልጽ ነው። 2ኛው የማቻቻያ መንገድ ደግሞ ሁለቱ ወገኖች በውል ፈቃዲቸውን ሲገልጹ መሆኑን የፍ/ህ/ቁ 1840 ያመለክታል።
3ኛው የእዲ ማቻቻያ መንገድ ደግሞ በፍ/ህ/ቁ 1841 መሰረት በፍ/ቤት የሚደረገው ማቻቻያ ነው።
ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት የማቻቻያ መንገድች አመልካች ጠቅሶ የሚከራከረው የእዲ ማቻቻያ መንገድ ማለትም የብድሩንና የዋስትና ውልች ሲሆን ውልቹም በፍ/ህ/ቁ 1731 መሰረት በመካከላቸው ህግ ሆነው ይገዛለ በሚል ነው። በዚህም መነሻ ለእዲው ማቻቻያነት ገንዘቡ የተያዘው ተገቢ ነው ይላል።
የአመልካች እና ተጠሪዎች የእዲ ማቻቻያ ክርክርን ለመወሰን የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት መሰረት ያደረገው ተያይዞ የቀረበለትን የብድር ውል አንቀጽ 15 ነው። ይህ የተጠቀሰው የውለ አንቀጽ ‛ተበዲሪው በዚህ ውል ላይ የተገለፀውን ማናቸውንም ግዳታ ያልፈፀመ እንደሆነ በባንኩ ዘንድ ያስቀመጠውን ገንዘብ ወጪ በማድረግ ለእዲው ለማቻቻል ባንኩ መብት አለው ይላል። ይህ የውል ድንጋጌ የሚናገረው በባንኩ ዘንድ ባለእዲው ያስቀመጠውን ገንዘብ ነው። አመልካች ግን 1ኛ ተጠሪ በአመልካች ባንኩ ያስቀመጠውን ገንዘብ ሳይሆን በስር 1ኛ ተከሳሽ የተላከለትን ገንዘብ ነው።
በተጠቀሰው የውል አንቀጽም በባንኩ ከተቀመጠ ገንዘብ ውጪ በላልች መንገድች የተገኙ የባለዲውን ገንዘቦች ለእዲው ማቻቻያነት የሚያዙ ወይም ገቢ የሚደረጉ ስለመሆናቸው አልተገለፀም።
በመሆኑም አመልካችና ተጠሪ የገባነው ውል በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1731 መሰረት አስገዲጅ ነው በሚል ብቻ በውለ ውስጥ ባልተካተተ ጉዲይ በክሱ የተጠቀሰውን ገንዘብ አመልካች ለእዲው ማቻቻያ ማድረጉ የህግ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘንም። በመሆኑም በስርፍ/ቤት አመልካች የያዘውን ገንዘብ ለተጠሪዎች ይመልስ በሚል በተሰጠ ውሳኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለም።
የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 25/10/2002 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔና የስር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 25/4/2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለባቸው ስለሆኑ ፀንተዋል።
ይህ ውሳኔ አመልካች ከተጠሪዎች የሚፈለግባቸው እዲ ካለ ስልጣን ባለው ፍ/ቤት ክስ አቅርቦ የማስወሰን መብቱን የሚያስቀርበት አይሆንም።
አመልካች የያዘውን የተጠሪዎች ገንዘብ እንዱመልስ ተወስኗል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሳራ የግራ ቀኙ ተከራካሪዎች የየራሳቸው ይችለ።
ከዚህ በፉት በዚህ ጉዲይ በመ/ ተጀምሮ የነበረው አፈፃፀም እንዱታገድ የተሰጠው ትዕዛዝ ተነስቷል።
መዝገቡ የተዘጋ ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ተመላሽ ይሁን።
No topics extracted.