No summary available.
የካቲት 21 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ኮከብ ደቄትና ፒስታ ፊብሪካ - ጠበቃ ነቅዓጥበበ በየነ ቀረቡ ተጠሪ፡- ሙለ ዓለም የሥራ አመራር አማካሪዎች - ሙለሸዋ ወልደ ማርያም ሥራ አስኪያጅ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት የሰበር አቤቱታ በማቅረባቸው ነው። የክርክሩ መነሻ አመልካች ለሥር ፍርድ ቤት ያቀረበው የክስ ማመልከቻ ሲሆን ተጠሪም በበኩለ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በአመልካች ላይ አቅርቧል።
በሥር ፍርድ ቤት አመልካችና ተጠሪ የሚከራከሩበት መሰረታዊ ጉዲይ የሙያ ሥራ አገልግልት ውል አፈፃፀም የሚመለከት ነው። አመልካች ተጠሪ የድርጅቱን መዋቅር ለማስጠናት ያወጣሁትን ጨረታ አሸናፉ በመሆን የድርጅቱን መዋቅር በስልሣ ቀን ውስጥ ሰርቶ ለማስረከብ ታህሣሥ 4 ቀን 1999 ዓ.ም የውል ግዳታ ገብቷል። ተጠሪ በውለ መሰረት ብር 8‚625 /ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ሀያ አምስት ብር/ ከአመልካች የቅድሚያ ክፍያ ተቀብል ወስዶል። ሆኖም ተጠሪ ጥናቱን በወቅቱና በጥራት ሰርቶ ያላስረከበ ሲሆን ከአመልካች የተሰጠውን የማሻሻያ ሀሳብ በማካተት ሰርቶ አላስረክብም። ስለዚህ በቅድሚያ ክፍያነት የወሰደውን ገንዘብ ከነወለደ እንዱመልስ ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ መሰረቷል። ተጠሪ በተከሳሽነት ቀርቦ በውላችን መሰረት ጥናቱን ሰርተን ሁለት ጥራዝ ለአመልካች አስረክበናል። ስለዚህ የአመልካች/ከሳሽ/ ክስ ተገቢነት የለውም በማለት ተከራክሯል።
ተጠሪ በበኩለ በአመልካች ላይ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርቧል። የተጠሪ የተከሳሽነት ክስ ይዘት ከአመልካች/ከከሳሽ/ ጋር ባደረግነው ውል መሰረት ጥናቱን አጠቅቀን አስረክበናል።
ስለሆነም ያልከፈለን ቀሪ ክፍያ ብር 20‚125 /ሀያ ሺህ አንድ መቶ ሀያ አምስት ብር/ ለመልካም ሥራ አፈፃፃም ዋስትና ያስያዝነውን 2‚250 /ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሀምሣ ብር/ የጉዲት ካሣ በርትእ 10‚000/አስር ሺ ብር/ ከህጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍል ይወሰንልኝ የሚል የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርቧል። አመልካች በሥር በከሳሽ ተከሳሽነት ቀርቦ ተጠሪ ሥራውን በውለ በተገለፀው ጊዜ ውስጥ ያላጠናቀቀና ያጠናውም ጥናት በተሰጠው ቢጋር መሰረት ያልተሰራና ከድርጅቱ የተሰጠውን ማሻሻያ መሰረት በማድረግ አስተካክል ባለማቅረቡ ቀሪውን ክፍያ ለመፈፀም አልገደድም። አስር ሺህ ብር ተጠሪ የጠየቀው ከህግ ውጭ ነው የሚል ክርክር አቅርቧል።
የሥር ፍርድ ቤት በአመልካች በኩል ያቀረበውን ክስና ተጠሪ ያቀረበውን ክርክር እንደዚሁም በተጠሪ በኩል ያቀረበውን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስና አመልካች በከሳሽ ተከሳሽነት ያቀረበውን ክርክር እንደዚሁም ግራ ቀኙ የየበኩላቸውን ክርክር ለማስረዲት ያቀረቧቸውን ማስረጃዎች ከመረመረ በኃላ አመልካች ጥናቱ እስከ ሰኔ 7 ቀን 1999ዓ.ም ተጠሪ ጥናቱን አጠናቆ እንዱያቀርብ ደብዲቤ የፃፈ መሆኑንና ተጠሪ ሰኔ 11 ቀን 1999ዓ.ም ሁለት ጥራዝ ጥናት ለአመልካች መላኩ በማስረጃ ተረጋግጧል። ስለሆነም አመልካች የጥናቱን ማስረከቢያ ጊዜ ለማራዘም በፃፈው ደብዲቤ መሰረት ተጠሪ ጥናቱን ያሰረከበ በመሆኑ አመልካች በውለ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ተጠሪ ጥናቱን ሰርቶ አላስረከበም በማለት ያቀረበው ክርክር ተገቢ አይደለም። ተጠሪ ጥናቱን አጠናቅቆ ያስረከበ መሆኑ ተረጋግጧል። አመልካች ተጠሪ ያቀረበው ጥናት ጉድለት ያለበት ነው በማለት የሚከራከር ቢሆንም ጥናቱ ጉድለት ያለበት ስለመሆኑ በማስረጃ ስላላስረዲ አመልካች በቅድሚያ ክፍያ የከፈለው ገንዘብ እንዱመለስለት ያቀረበው ክስ ተገቢ አይደለም በማለት የወሰነ ሲሆን የተጠሪን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በተመለከተ የሙያ ግልጋልት ክፍያው ብር 29‚750 መሆኑ በውለ በግልፅ የተመለከተ በመሆኑና ተጠሪ ለመልካም ሥራ አፈፃፀም 2‚250 /ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሀምሣ ብር/ ያስያዘ መሆኑ ስለተረጋገጠ እንደዚሁም ተጠሪ ጥናቱን በውለ መሰረት ሰርቶ ያስረከበ ስለሆነ ቀሪ ያገልግልት ክፍያ 20‚125 /ሀያ ሺህ አንድ መቶ ሀያ አምስት ብር/ ለመልካም ሥራ አፈፃፀም የተያዘው ብር 2‚250 /ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሀምሣ ብር/ ከህጋዊ ወለድ ጋር አመልካች ለተጠሪ የመክፈል ሀላፉነት አለበት። ተጠሪ ጉዲት የደረሰበት መሆኑ ስላልተረጋገጠ ብር 10‚000 የጉዲት ካሣ እንዱከፈለው ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅረቧል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ የሚነቀፍበት የፍሬ ጉዲይ ወይም የህግ ስህተት የላለ መሆኑን በመግለጽ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች መስረከም 13 ቀን 2003 ዓ.ም ተጠሪ አመልካች በሰራው ቢጋር መሰረት ድርጅቱን ከኃላቀርነት ወደ ዘመናዊ አሰራር የሚያሸጋግር ጥናት ለማቅረብ የውል ግዳታ የገባ ቢሆንም የተጠሪ ጥናት አስራ ሁለት የሚደረሱ ጉድለቶች እንዲለበት በአመልካች የሥራ አመራር ቦርድ ያደረገውን ውይይት ቃለ ጉባኤ በማስረጃነት አቅርበን እያለ የሥር ፍርድ ጥናቱ ጉድለት ያለበት ስለመሆኑ አያስረዲም በማለት መወሰኑ መሰረታዊ ህግ ስህተት ያለበት ነው። ከተጠሪ ጋር ያደረግነውን የሙያ ግልጋልት ውል በማናቸውም ጊዜ በተናጠል የማፍረስ ሥልጣን በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2637 ንዐስ አንቀፅ 1 በግልፅ ተደንግጎ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች ይህንን ድንጋጌ በመተለለፍ ውለ የተፈፀመ በመሆኑ ቀሪ ክፍያ ለተጠሪ ይከፈለው በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልን በማለት የሰበር አቤቱታ አቅረቧል። ተጠሪ በበኩለ ጥናቱን ሙለ በሙለ አጠናቅቄ ለአመልከች ማስረከቤን የሥር ፍርድ ቤት በማስረጃ አረጋግጧል። አመልካች በጥናቱ ላይ ከሙያ አንፃር ጉድለት ያለ መሆኑን ያላስረዲ ሲሆን ቀሪውን የሙያ አገልግልት ክፍያ ላለመክፈል ያቀረበው መከራከሪያ የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ የሰበር አቤቱታው ውድቅ ይደረግልኝ የሚል ይዘት ያለው መልሰ አቅርቧል። አመልካች የመልስ መልስ ሰጥቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራቀኙ ያቀረቡት የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ በውለ መሰረት ግዳታውን ስለተወጣ አመልካች ቀሪውን የሙያ አገልግልት ክፍያ ይክፈል በማለት የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዘ ጉዲዩን መርምረናል። ይህንን መሰረታዊ ጭብጥ ለመወሰንና በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገውን ውል ልዩ ባህሪና ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎችን ይዘት መንፈስና ዓላማ ማገናዘብ አስፈላጊ ነው። አመልካች ከተጠሪ ጋር ያደረገውን የሙያ ግልጋልት ውል በማናቸውም ጊዜ በተናጥል የማፍረስ መብት አለኝ በማለት የሚከራከረው የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2637 ንዐስ አንቀጽ 1 በመጥቀስ ነው።
የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2637 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ ቃል በቃል ሲነበብ አሰሪው በማናቸውም ጊዜ ውለን ማፍረስ ይችላል የሚል ይዘት ያለው ነው። ሆኖም ይህ ድንጋጌ ተፈፃሚ የሚሆነው መቼ ነው የሚለው ነጥብ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። የዕውቀት ሥራ ለመስራት ከአሰሪው ጋር ውል የተዋዋለ ሰው የዕውቀት ሥራውን ሙለ ለሙለ አጠናቆ ለአሰሪው ካስረከበ በኃላ በአሰሪውና የዕውቀት የሥራ ውለን በሰራው ሰው መካከል የሚነሳው ክርክር የዕውቀት የሥራ ውለን የሰራው ሰው ፣ የሙያ ሥራውን በልምድና የሙያ ሥራ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ የአመልካችን ጥቅም በሚያረጋግጥ አኳኃን የሙያ ሥራውን ከልብ ስርቷል ወይስ አልሰራም; የሙያ ሥራውን የሰራው ሰው የዕውቀት ሥራውን የሙያውን ደንቦች በጠበቀና በሚያሟላ ሁኔታ ፈፅሟል ወይስ አልፈፀመም የሚለት ነጥቦች መሆናቸውን ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 2636 ንዐስ አንቀፅ 1 እና ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 2636 ንዐስ አንቀፅ 2 ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘት መንፈስና ዓላማ ለመገንዘብ ይችላል። ስለሆነም አሰሪው በተናጠል የዕውቀት ግልጋልት ውለን ለማቋረጥ የሚችለው የዕውቀት የሥራ ውለን የተዋዋለው ሰው የዕውቀት ሥራውን ሙለ በሙለ አጠናቅቆ ለአሰሪው ከማስረከቡ በፉት እንደሆነ ከላይ የተጠቀሱትን ድንጋጌዎችና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2637 ንዐስ አንቀፅ 2 ድንጋጌ በማገናዘብ ለመረዲት ይቻላል።
የሙያ ሥራ ለመሥራት የተዋዋለው ሰው የሙያ ሥራውን ሙለ በሙለ በማጠናቀቅ ለአሰሪው ካስረከበ በኃላ የኪነጥበብ ደንቦችን ማለትም የሙያውን ደንቦች በማፍረስ ጥፊት መፈፀሙ ካልተረጋገጠ በቀር በኃላፉነት እንደማይጠየቅ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2636 ንዐስ አንቀፅ 2 በግልጽ የተደነገገ ሲሆን የፍ/ህ/ቁ.2632 ንዐስ አንቀጽ 2 የእንግሉዘኛው ቅጅ ‛He shall not be liable to his client, unless he commits an error, having regard to the rules of his profession“ በሚል መንገድ ከአማርኛው ቅጅ በቀላልና ግልፅ በሆነ አገላለፅ ደንግጏታል። ተጠሪ ጥናቱን ሙለ በሙለ ለማጠናቀቅ ለአመልካች ሰኔ 11 ቀን 1999 ዓ.ም ሁለት ጥራዝ የጥናት ሰነድ ያስረከበ መሆኑ የሥር ፍርድ ቤት በማስረጃ ያረጋገጠው ፍሬ ጉዲይ ነው።
አመልካች በውለ መሰረት ቀሪውን የሙያ ግልጋልት ክፍያ የማይከፍልበት በቂ ምክንያት ያለው መሆኑን በተለይም ተጠሪ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2636 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት የውል ግዳታውን ያልተወጣና ተጠሪ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2636 ንዐስ አንቀፅ 2 በሚደነግገው መሰረት የሙያውን ደንብ ያልጠበቀና የዕውቀት ሥራው ስህተት ያለበት መሆኑን የማስረዲት ግዳታ (Burdon of proof) አለበት። በያዝነው ጉዲይ አመልካች ተጠሪ ያቀረበው የጥናት ሰነድ በድርጅቱ የሥራ አመራር ቦርድ ታይቶ ጉድለት የተገኘበት መሆኑን የሚያሣይ ቃለ ጉባኤ በማስረጃነት ለሥር ፍርድ ቤት ያቀረበ መሆኑን በመግለፅ የሚከራከር ቢሆንም ይህ ማስረጃ በተጠሪ ተጠንቶ የቀረበው ሁለት ጥራዝ የጥናት ሰነድ ሙያዊ ጉድለትና ስህተት ያለበት መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ እንዲልሆነ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባለው የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተረጋግጧል።
ስለሆነም አመልካች በተጠሪ ተሰርቶ በቀረበው የጥናት ሰነድ ላይ ተፈፅመዋል የሚላቸውን የሙያውን ደንብና አሰራር የሚጥሱ ጥፊቶች የማስረዲት ሸክሙን (Burdon of proof) ካልተወጣ ተጠሪ ለሰጠው ሙያዊ ግልጋልት መክፈል የሚገባውን ቀሪ ክፍያ እንዱከፍል የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2634 ንዐስ አንቀፅ 2ን መሰረት ያደረገና የህግ ስህተት የላለበት ነው። አመልካች በተጠሪ ተጠንቶ የቀረበው ሰነድ ሙያዊ ጉድለት ያለበት መሆኑን ይህ ሰበር ችልት በማጣራት እንዱወሰንላቸው ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ለሰበር ችልት በህገ መንግስቱ አንቀፅ 80 ንዐስ አንቀፅ 3/ሀ/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 10 የተሰጠውን ሥልጣን ያላገናዘበና የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም። ከላይ በዝርዝር በገለፅነው ምክንያት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
ቅ/መ
ቀን 19/9/2003 ዳኞች፣ ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ አሉ መሀመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች- የኢትዮጵያ መንገድች ባለስልጣን ነገረ ፈጅ አቶ ሳሙኤል ተገኔ፣ ቀረቡ ተጠሪ- ካንትሪ ትሬዱንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ፣ አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለው ፍርድ ሰጥቷል።
የሰበር አመልካች በስር የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ ነው።
ክሱም ለመንገድ ስራ የሚያገለግለትን የተለያዩ የአስፕልት ውጤቶችን እስከ ተከሳሽ ሳይቶች ድረስ ለማቅረብ ተከሳሽ መ/ቤት ያወጣውን ጨረታ ተወዲድሬ በማሸነፍ የሥራ አፈፃፀም ዋስትና (contractual security) የጠቅላላ ሥራ ዋጋ 10% ብር 9,559,525.37 ከወጋገን ባንክ የተሰጠ ዋስትና አስይዤ ስለእቃውም አቅርቦት ከተከሳሽ መ/ቤት ጋር እንደ አውሮፕ አቆጣጠር ሰፔቴምበር 20/2007 ውል የገባን ሲሆን ከሳሽ ከገባሁት ግዳታዎች የአስፕልት ውጤቶችን አቅርቤ Ac 60/70 ተብል ከሚታወቀው የአስፕልት አይነት ማቅረብ ከሚገባኝ 8.276 ሜትሪክ ቶን ውስጥ 3,829.5 ሜትሪክ ቶን ብቻ አላቀረብኩም። ምክንያቱም በውለ ይደርሳለ ተብል ያልተገመቱ ጉዲዮች ውለን በከፍተኛ ሁኔታ በማናወጣቸዉ ሲሆን ከተከሳሽ ጋር በመወያየት በቅድሚያ የተቀበልኩትን 10,224,989.13 ብር ተመላሽ በማድረግ ውለ ተቋርጧል። ሆኖም ተከሳሽ መ/ቤት ለመልካም አፈፃፀም ዋስትና ካስያዝኩት ፊይናንሻል ጋራንቲ ቦንድ ውስጥ ላላስረከብኩት የአስፕልት ውጤት መጠን ብር 3,557,729.34 በመቁረጥ ቀሪውን ገንዘብ እንደሚመልስልኝ ገልጿል። ስለሆነም ተሰካሽ ብር 3,557,729.34 ያስቀረብኝና ለተከሳሽ ባቀረብኳቸው የአስፕልት ውጤቶች ብር 497,735 ኪሣራ የደረሰብኝ በመሆኑ የተጠቀሰው ገንዘብ ወጪና ኪሳራ ተጨምሮ እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ የሚል ነው።
ለክሱ ተከሳሽ የሰጠው መልስ ከሳሽ ኪሳራ ገጥሞኛል ይበል እንጂ ደረሰብኝ የሚለው ኪሣራ አስቀድሞ ሉገመት የሚችል ነው። ተከሳሽ መ/ቤት ለሚሰራው እና ለሚያስጠግነው መንገድ በእቅድ የሚሰራ በመሆኑና ከሳሽም ማቅረብ የሚገባውቸውን የአስፕልት ውጤቶች በግዜ ካለማቅረቡ የተነሳ በተከሳሽ ላይ ከፍተኛ ጉዲት ደርሷል። Ac 60/70 ከተባለው የአስፒልት ውጤት ውስጥ 3829.5 ሜትሪክ ቶን እስካሁን ድረስ አላቀረበም። ተከሳሽም ለደረሰበት ጉዲት ከሳሽ ለመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ካስያዘው ገንዘብ ውስጥ ብር 3,557,927.34 መውሰደ አግባብነት አለው ይህ ለመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና የተያዘው ገንዘብ ለሚደርሰው ጉዲት እንደሚውል በውላችን የተስማማነው ጉዲይ ነው። በውለ ምክንያት ኪሳራ ብር 497,735 ደርሶብኛል በማለት እንዱከፈለው የጠየቀውም ቢሆንም ተቀባይነት የለውም። ምክንያቱም በውላችን በማናቸውም ሁኔታ የዋጋ ማስተካከያ እንደማይደረግ ተስማምተናል በማለት የከሳሽ ክስ ውድቅ እንዱደረግ ጠይቋል።
የግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው የሥር የፋ/ከ/ፍ/ቤትም ከሳሽ ለማቅረብ የውል ግዳታ ከገባው የአስፒልት ውጤት ውስጥ 3829.5 ሜትር አለማስረከቡን አምኗል፣ ውለም በግራ ቀኙ ስምምነት የተቋረጠ ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ የለም፣ ከሳሽ ከአቅም በላይ የሆኑ ምክንያቶች ናቸው በማለት የዘረዘራቸው ምክንያቶች በፍ/ህ/ቁ 1792/2/አንፃር ሲታዩ ከአቅም በላይ የሆኑ ምክንያቶች ናቸውየሚባለ አይደለም፣ተከሳሽ በደብዲቤ እንደገለፀው የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና ገንዘብ ቀንሶ ያስቀረው ከሳሽ ያስረከበውን እና ያላስረከበውን መጠን በማመጣጠን ሲሆን ይህን ተከሳሽ በራሱ መወሰኑ ተገቢነት ያለው አይደለም። የተከሳሽ መ/ቤት ኪሳራ ደርሶበታል ቢባል እንኳን በፍ/ቤት ክስ ቀርቦ ከሚያስወስን በስተቀር የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና ለደረሰበት ኪሣራ መቀነስ የለበትም ሲል ቀንሶ ያስቀረውን የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና ገንዘብ ብር 3,557,927.34 ለከሳሽ እንዱመልስ ሲወስን ከሳሽ በተጨማሪ ኪሣራ ገጥሞኛል ሲል የጠየቀውን የኪሳራ ገንዘብ ብር 497,735 ተከሳሽ ሉጋራ አይገባውም ብሎል።
የሥር ተከሳሽ በሥር የፋ/ከ/ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረበ ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ችልት የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ የሚነቀፍ አይደለም ሲል በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት አጽንቷል።
በሥር ፍ/ቤት ውሳኔ አመልካች መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈፅሟል በማለት የቅሬታ ነጥቦች ለዚህ ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን በዋናነት የጠቀሣቸውም ለዚህ ለተያዘው ጉዲይ አግባብነት ያለው የመንግስት የግዥ ስርአት ለመወሰን የወጣው የአዋጅ ቁጥር 430-97 ሆኖ እያለ ፍ/ቤቱ አግባብነት የላለውን የፍትሃብሓር ህግ ቁጥር 1790/1/ እና 1799 ለውሳኔው መሰረት ማድረጉ ተገቢነት የለውም፣ ለውሳኔው አግባብነት አለው እንኳን ቢባል የበሰለ የጉዲት ካሳ (liquidated Damages) በተመለከተ በውለ ጠቅላላ ክፍልና ልዩ ሁኔታ አንቀጽ 27 የተስማማንበት ጉዲይ ስለሆነ የፍትሐብሕር ህግ ቁ. 1894 እንደተደነገገው አመልካች ስምምነት በተደረሰበት ጉዲይ ላይ የጉዲቱን ልክ ሆነ መጠን የማስረዲት ሀላፉነት የለበትም፡- ስለሆነም ተጠሪው ካስያዘው የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ገንዘብ በስምምነቱ መሰረት ቆርጦ የመውሰድ መብት አለው።
ይህ ሆኖ ሳለ ይህንኑ ገንዘብ አመልካች በፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ማስወሰን አለበት የተባለው በፍ/ህ/ቁ 1731፤ በውለ አንቀፅ 18/2/ እና በመንግስት እቃ ግዢ መመሪያ አንቀፅ 11/14/2 መሰረት ተቀባይነት የለውም የሚለ ናቸው።
ለሰበር አቤቱታ ተጠሪው በሰጠው መልስ ከአመልካች ጋር የነበረው ውል በመቋረጡ ላስረከበው እቃ ለሚደርሰው ጉዲት ማካካሻ የሚከፈለውን ካሳ ስምምነት ያላደረገ በመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች ያልቀረበውን እቃ በተመለከተ የካሳ መጠን አመልካች ክስ አቅርቦ ከሚያስወስን በቀር ጉዲት መኖሩንም ሆነ የካሳውን ልክ ራሱ ወስኖ ሉወስድ እንደማይችል የሰጡት ውሳኔ በፍ/ህ/ቁ 3200 መሰረት ህጋዊ ነው፣ አመልካች ተጠሪ በውለ አንቀፅ 27 መሰረት የተስማሙትን ዘግይቶ ለቀረበ ዕቃ የሚከፈል መቀጫን እንጂ ውለ በመቋረጡ ላልቀረበ ዕቃ የሚደርስ ጉዲትን በተመለከተ አይደለም፣ ተጠሪ ላስረከበው ዕቃ የተረጋገጠ ጉዲትም ቢሆን ኪሳራ ሉከፍል አይገባም፣ አመልካች በውለ አንቀፅ 27 መሰረት ሉከፍለኝ የሚገባውን መቀጫ በውለ አንቀፅ 18 መሰረት ከዉል ማስከበሪያ ላይ የመቀነስ መብት አለኝ በማለት ያቀረበው ቅሬታ የህግ መሰረት የለውም በማለት የሥር ከፍ/ፍ/ቤትም ሆነ የፋ/ጠ/ፍ/ቤት አመልካች ከዘረዘራቸው የቅሬታ ነጥቦች አንፃር የፈፀሙት የህግ ስህተት የለም ሲል ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከዚህ በላይ የቀረበው ሲሆን እኛም ተጠሪው ለመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ካስያዘው ገንዘብ ውስጥ ባልፈፀመው የውል ግዳታ መጠን አመልካች ቀንሶ ማስቀረቱ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
ለዚህ ለተያዘው ጭብጥ ከአመልካች በኩል የቀረበው ክርክር በአዋጅ ቁጥር 430/97፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ሐምል 1997 ባወጣው የመንግስት ዕቃ ግዥ መመሪያ በአመልካችና ተጠሪ መካከል በተደረገው ውል መሰረት ተጠሪው ለመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና ካስያዘው ገንዘብ ውስጥ ባልተፈፀመው የውል ግዳታ መጠን የመቀነስ መብት አለኝ የሚል ነው።
ተጠሪው ግን አመልካች ለመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ከተያዘው ገንዘብ ውስጥ በራሱ ስልጣን ቀንሶ ለማስቀረት አይችልም ሲል ተከራክሯል። ተጠሪው ለዚህ ክርክር አግባብነት አለው በማለት በዋናነት የጠቀሰውም የፍ/ብ/ህ/ቁ 3200 ነው። የተጠቀሰው የፍ/ብ/ህ/ቁ 3200 ከአስተዲደር መ/ቤቶች ጋር የሚደረገውን ውል የሚመለከት ሲሆን ድንጋጌው በመርህ ደረጃ የቅድሚያ ልዩ መብት እንደማይኖር የሚናገር ነው። በዚሁ ህግ መሰረትም የአስተዲደር መ/ቤቱም ተዋዋዩ ውለን ባለመፀሙ የሚያስቀጣ ጥፊት አድርጓል በማለት በገዛ ራሱ አንድ ውሳኔ ለማድረግ ወይም በተዋዋዩ ግዳታ አለመፈፀም ወይም ለመፈፀም በመዘግየቱ ምክንያት የሚፈለግበትን ኪሣራ ልክ በገዛ ራሱ ለመወሰን አይችልም።
ይሁን እንጅ ለዚህ ለተያዘው ጉዲይ አግባብነት ያላቸው የመንግሰት የግዥ ሥርአትን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 430/97 እና የመንግስት የግዠ መመሪያ እንዱሁም ግራ ቀኙ የገቡት ውል እንጅ የተጠቀሰው የፍትሀብሓር ህግ ድንጋጌ አይደለም። ምክንያቱም በህግ አተረጓጎም ረገድ ለዚህ ለተያዘው ጉዲይ የፍ/ህጉ አጠቃላይ ህግ ሲሆን የመንግስት የግዥ ሥርአትን ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር 430/97 ልዩ ህግ በመሆኑ ከግዥ ጋር ተያይዞ ለሚነሳ ክርክር ተፈፃሚ የሚሆነው ይኸው አዋጅ ነው።
አዋጅ ቁጥር 430/97 አንቀፅ 43 ስለ ውል ማስከበሪያ (contract security) የሚደነግግ ሲሆን አቅራቢው በውለ መሰረት ባለመፀሙ በግዠ ፈፃሚው አካል ላይ ለሚደርሰው ጉዲት ማካካሻ የሚውል ማስከበሪያ ለግዥ ፈፃሚው አካል መስጠት አለበት ይላል። የግራ ቀኙ ተዋዋዮችም ይህንኑ አስገዲጅነት ያለውን የህግ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ በውላቸው የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ያካተቱ ሲሆን ተጠሪው በውለ መሰረት ማስረከብ የሚገባውን Ac 60/70 የተባለውን የአስፊልት ውጤት ቀንሶ በማስረከቡ በአመልካች ላይ ጉዲት መድረሱን ክርክሩ ያመለክታል። ይህ በመሆኑ አመልካች በውለ አንቀፅ 18/2/ እንደተጠቀሰው በውለ መሰረት ተጠሪው ግዳታውን ባለመፈፀሙ የተነሳ ለተፈጠረው ጉድለት መያዣ ከነበረው ከመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና ገንዘብ ቀንሷል። ሐምል1997 የገ/ኢ/ል/ሚኒስቴር ያወጣው የግዥ መመሪያ አንቀፅ 11/5/ም ቢሆን አቅራቢው ዕቃውን አጠናቅቆ ባለማስረከቡ ርክክቡ ባልተፈፀመበት ግዢ ላይ በየቀኑ 0.1 ወይም 1/1000 መቀጫ እንደሚከፍል ይናገራል።
መመሪያው መቀጫ የውለን ዋጋ 10% የሚበልጥ በሚሆንበት ጊዜ ግዥ ፈፃሚው ውለን የመሰረዝ መብት እንዲለው እና የውለ አፈፃፀም መዘግየት በግዠ ፈፃሚ ስራ ላይ ችግር የሚያስከትል ከሆነ ግዥ ፈፃሚው የመቀጫውን መጠን 10% ሳይጠብቅ ውለን መሰረዝ እንደሚችል ጭምር በቁጥር 11.7/5/ /ለ//ሐ/ ይገልፃል።
በመሆኑም ከአዋጁ አንቀፅ 43፣ ከመመሪያው ቁጥር 11.7/5/ /ሀ-ሐ/ እንዱሁም ከውለ አንቀፅ182፣27.1 ይዘት አንፃር ሲታይ አመልካች ለመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና ከተያዘው ገንዘብ ባልተፈፀመ ውል ግዳታ መጠን ቀንሶ መውሰደ አግባብነት አለው። የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና የሚያዘውም አቅራቢው በውለ መሰረት ግዳታውን ባለመፈፀም የተነሳ ግዥ ፈፃሚው ላይ ለሚደርሰው ጉዲት ተገቢውን መቀጫ አቅራቢው ከዚሁ ገንዘብ እንዱከፍልና ውለን አክብሮ በውለ በተገለፀው ጊዜ ውስጥ ግዳታውን እንዱፈፅም ታስቦ ነዉ። ስለሆነም አመልካች ለመልካም ስራ አፈፃፀም ተጠሪው ያስያዘውን ገንዘብ ራሱ ቀንሶ የአስፊልት ውጤቱ ባለመቅረቡ የተነሳ ለተፈፀመው ጉድለት ማስቀረት አይችልም በማለት በስር ፍ/ቤት የተወሰነዉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው።
ው ሣ ኔ
የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 30/4/2002 በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ እንዱሁም የፋ/ጠ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 24/1/2003 የሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሻሽለዋል።
ተጠሪው ለመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ካስያዘው ገንዘብ አመልካች ቀንሶ ያስቀረውን ብር 3,557,929.34 /ሶስት ሚሉዮን አምስት መቶ አምሳ ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ዘጠኝ ከሰላሳ አራት ሳንቲም /ለተጠሪው ሉመልስ አይገባም ብለናል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሳራ አመልካችና ተጠሪ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ የተዘጋ ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ተመላሽ ይሁን።
No topics extracted.