No summary available.
የካቲት 21 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጉስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ አሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ዮርዲኖስ ሐጉስ አልቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሐይማኖት ተፈራ ጠበቃ አቶ ፊንታሁን አባተ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ ለሰበር የቀረበው ጉዲይ ተዋዋይ ወገኖች በውላቸው የወሰኑት መቀጫ/ገደብ/ እንዱፈፀም የሚያስገድድ ሆኔታ መኖር አለመኖሩን ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1889-1895 ካለት ድንጋጌዎች አንፃር መመርመርን የሚጠይቅ ነው።
ለክርክሩ መነሻ ሆኖ የተገኘው የካቲት 19 ቀን 2000 ዓ.ም የተደረገ የቤት ኪራይ ውል ነው። በዚህ ውል የአሁኗ አመልካች በአዱስ አበባ ከተማ ካልፋ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ቀበላ 06 ክልል ውስጥ የሚገኘ የቤት ቁጥሩ አዱስ የሆነ ቤት ለትምህርት ቤት አገልግልት ይውላል ተብል ለአሁኗ ተጠሪ በወር ብር 10‚000 የኪራይ ሂሣብ ለ5 ዓመት ለማከራየት ተስማምተዋል።
የቅድሚያ ክፍያ ብር 60‚000 ከተከራይዋ ወስደዋል። በኪራይ ውለ አከራይ ቤቱን አጥረው ነሐሴ 1 ቀን 2000 ዓ.ም ለተከራይዋ ለማስረከብ ግዳታ ገብትዋል። በውለ መሰረት ባይፈጽሙ መቀጮ/ገደብ/ ብር 50‚000 ለመክፈል ተስማምተዋል።
በኪራይ ውለ መሰረት ቤቱን አጥረው ሉያስረክቡኝ አልቻለም ማስጠንቀቂያም ተጽፍላቸው በውለ መሰረት ሣይፈጽሙ ቀርተዋል ቤቱንም ለታሰበለት አገልግልት ለማዋል ስላልተቻለ ውለን አፍርሰዋል ስለዚህ በቅድሚያ የተቀበለትን ብር 60‚000 ከወሰደበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር እንዱሁም ቤቱን ባለማስረከብ ውለን ስላፈረሱ በውለ ላይ የተወሰነውን መቀጫ/ገደብ/ ብር 50‚000 አከራይዋ የአሁኗ አመልካች ሉከፍለኝ ይገባል በሚል ወደ ፍርድ ቤት ክስ ያመሩት ተከራይ የሆኑት የአሆኗ ተጠሪ ናቸው። ተከሣሽዋ የአሁኗ አመልካች ክሱ ደርሷቸው በሰጡት መልስ የውል ግዳታዬን ለመወጣት በመንቀሳቀስ ላይ እያለሁ የቀበላ መስተዲድር ያጠርኩትን አጥር አፍርሶብኛል እንዲላጥርም ከልክልኛል ውለ ሣይፈፀም የቀረው በተከሣሽ ጥፊት አይደለም ቤቱም ለትምርት ቤት አገልግልት ሉውል አይችልም ተብሎል። ውለ በእኔ ጥፊት ስላልፈረሰ ገደብና ወለድ ሉከፍል አይገባም ኪሣራ በላለበት ገደብና ወለድ በክሱ የተጠየቀው ያለ አግባብ ነው። ውለ እንደማይፈፀም ከታወቀ በኃላ ከሣሽ ገንዘባቸውን እንዱወስደ ተጠይቀው ፈቃደኛ ስላልሆኑ ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል የሚለትን ክርክሮች አቅርበዋል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክሱን የግራቀኙን ክርክሮችና ማስረጃዎች መርምሮ በሰጠው ፍርድ አከራይዋ ቤቱን እንዲላጠሩ የቀበላ መስተዲድር ከልክልኛል የሚለውን ለማሰረዲት ያቀረቡት ቀበላው የፃፈው ደብዲቤ ከይዞታቸው ውጪ የያዙት የመንግሥት መሬት መኖሩን የሚያስረዲ ነው።
ከራሣቸው የካርታ ይዞታ ውጭ ያለ ቦታ አጥረው ለከሣሽ ለማስረከብ መንቀሳቀሳቸው ህጋዊ አይደለም በዚህ ምክንያት ለከሣሽ ማስረከብ የነበረባቸውን ቤት ሣያስረክቡ መቀረታቸው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በውለ መሰረት ሣይፈጽሙ ቀርተዋል ልባል አይችልም አንድ የትምህርት ቢሮ ተወካይ ማህተም በተደረገበት ደብዲቤ መፃፃፍ ሣይሆን በቃለ ቤትና ቦታው ለትምህርት ቤት አገልግልት ሉውል አይችልም ብለ ከልክሎል የተባለውም ተቀባይነት የለውም አከራይ የዉል ግዳታቸውን ባለመፈፀማቸው ምክንያት የኪራይ ውለ ፈርሷል። በቅድሚያ የተቀበለትን ብር 60‚000 ማስጠንቀቂያ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ /9%/ ጋር እና በኪራይ ውለ መሰረት ባለመፈፀማቸው በውለ ላይ የተስማሙበትን ብር 50‚000 ፍርደ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ተከፍል አለቀ ድረስ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር ለከሣሽዋ ለአሁኗ ተጠሪ ሉከፍል ይገባል በማለት ወስኗል።
የአሁኗ አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኙን አቅርበው ያስረቀርባል ተብል ግራቀኙ ቀርበው ክርክሩ ከተሰማ በኃላ ከፍተኛው ፍ/ቤትም መርምሮ በሰጠው ፍርድ በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ የሚነቀፍበት የፍሬ ነገርም ሆነ የሕግ ምክንያት አልተገኘም በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት አጽንቶታል።
የሰበር አቤቱታውም የአሁኗ አልካች በኪራይ ውለ ላይ የተመለከተውን መቀጫ ብር 50‚000 ፍርደ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር ለአሁኗ ተጠሪ እንዱከፍለ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል በሚል በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት የቀረበ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ቀርቦ እንዱታይ በመወሰኑ ማመልከቻው ለአሁኗ ተጠሪ ተልኮ ቀርበው መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
በዚህም መሰረት የተጠሪ ጠበቃ በጽሐፍ በሰጡት መልስ ውለ ሣይፈጽም የቀረው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ነው የሚያሰኝ ነገር አለመኖርን ውለ እንዲይፈፀም ያደረጉት አመልካች ራሣቸው እንደሆኑ ፣ በውለ ወለን አፍራሹ ወገን መቀጫ ብር 50‚000 ለመክፈል ግዳታ ስለመግባቱ እና አመልካችም በውለ መሰረት ሣይፈጽሙ መቅረታቸው በውለ የተወሰነውን መቀጫ በክሱ እንዱከፍለ ተጠይቆ የሥር ፍ/ቤት በሕጉ አግባብ አይቶ እንዱከፍለ ስለመወሰኑ በመዘርዘር ተከራክረዋል።
አመልካች በተጠሪ በኩል በተሰጠው መልስ ላይ የመልስ መልስ መስጠት አያስፈልገኝም ብለዋል።
ጉዲዩም እንደሚከተለው ተመርምሯል።
በአሁኗ አመልካችና ተጠሪ መካከል የካቲት 19 ቀን 2000 ዓ.ም በጽሐፍ የቤት ኪራይ ውለ ተደርጓል። አመልካች የቤቱ አከራይ ሲሆኑ ተጠሪ ደግሞ ተከራይ ናቸው። ተከራይ ቤቱ በውለ የተከራዩት ለትምርት ቤት አገልግልት ሉጠቀሙበት ነው። ተከራይ ለቤቱ ኪራይ በየወር ብር 10‚000 የሚከፍለ ሆኖ በቅድሚያ ብር 60‚000 ለአከራይ ከፍለዋል። ቤቱ በተከራይዋ በኩል ለተፈለገበት ለትምህርት ቤት አገልግልት እንዱውል ከነቦታ ይዞታው መታጠር ያለበት ስለመሆኑ በውለ አምነውበት አከራይዋ አጥረው ለማስረከብ ግዳታ ገብተዋል። ውለን የካቲት 19 ቀን 2000ዓ.ም ተፈራርመው ማስረከቢያው ከ5 ወር በኃላ ነሐሴ 1 ቀን 2000ዓ.ም እንዱሆን የተሰማሙትም በዚህ ጊዜ ውስጥ አከራይ የአጥሩን ሥራ ለማጠናቀቅ እንዱችለ ታስቦ ነው።
የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2900 አከራይ ያከራየውን የማይንቀሳቀስ ሀብት ከተጨማሪ ዕቃዎቹና በውለ መሰረት ወይም በሀብቱ ተፈጥሮ መሰረት ለተመደበበት ጉዲይ ሉያገለግል በሚችልበት ሁኔታ አሟልቶ ለተከራዩ ማስረከብ እንዲለበት ደንግጓል።
በዚህ ጉዲይ ቤት አከራይ የሆኑት የአሁኗ አመልካች ቤቱ በውለ ለተመደበበት ጉዲይ ሉያገለግል በሚችልበት ሁኔታ አጥረውና አሟልተው በውለ በተወሰነው የማስረከቢያ ግዜ ለተከራይዋ ለአሁኗ ተጠሪ ሣያስረክቡ ቀርተዋል።
አመልካች በኪራይ ውለ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ አሟልተው ቤቱን ለተከራይ የማስረከብ ግዳታቸውን ባለመፈፀማቸው በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1784 መሰረት ውለ ቀሪ እንዱሆን ተደርጓል።
አመልካች በውለ መሰረት ሉፈጽሙ ባለመቻላቸው ውለ ቀሪ መሆኑ ከተረጋገጠ በውለ ላይ የተወሰነውን መቀጫ /ገደብ/ ብር 50‚000 ለተከራይዋ ለአሁኗ ተጠሪ ለመክፈል ይገደዲለ ወይንስ አይገደደም; የሚለውን ዋናውን የክርክር ጭብጥ በተመለከተም አመልካች በውለ መሰረት ያልፈፀምኩት የቀበላ መስተዲዲር ቤቱን እንዲላጥር በመከልከለና ያጠርኩትንም በማፍረሱ ስለሆነ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ነው በማለት የሚከራከሩ ቢሆንም አመልካች ራሣቸው በጽሐፍ ማስረጃነት ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረቡት የቀበላ መስተዲድር የፃፈው ደብዲቤ እንዲያጥሩ የተደረገው ከይዞታቸው ውጭ የመንግሥት ቦታን ጨምረው በመከለል በመያዛቸው ምክንያት መሆኑን እንደሚያስረዲ በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ የሚያሣይ በመሆኑና አመልካችም በስር አቤቱታቸው ላይ ቀበላው ይህንን አላለም በሚል የገለጹት ነገር ስለላለ በሕጉ ከአቅም በላይ የሚል ትርጉም የሚሰጠው አይደለም። ሁለተኛውን ምክንያት በሚመለከት ቤትና ቦታው ለትምርት ቤት አገልግልት ሉውል የሚችል አይደለም ተብሎል የሚለውን የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከቀበላው የትምህርት ቢሮ በጽሐፍ ተገልጾ የቀረበ ማስረጃ አለመኖሩንና ተወካዩ በቃል ተናግሯል የተባለው በቂ አለመሆኑን በመግለጽ ሣይቀበለው ስለቀረ በሰበር ደረጃ የሚመረመር አይደለም። ስለዚህ የአሁኗ አመልካች በውለ መሰረት ያልፈፀምኩት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ነው በሚል ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። ለውለ መፍረስ ተጠያቂ የሚሆኑት አመልካች ናቸው።
የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1889 አንደኛው ወገን ግዳታውን ያልፈፀመ እንደሆነ ወይም አጓድል ወይም አዘግይቶ የፈፀመ እንደሆነ የሚከፈለውን መቀጮ ተዋዋዮች አስቀድመው በውላቸው ለመወሰን እንደሚችለ ያስረዲል።
በተያዘው ጉዲይም በዚሁ ሕግ መሰረት የአሁኗ አመልካች በውለ መሰረት ግዳታቸውን ካልፈፀሙ መቀጮ ብር 50‚000 ለመክፈል ተስማምተዋል።
የፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 1891 ባለገንዘቡ መቀጫ /ገድብ/ ሉቀበል የሚገባው ውለ ባለመፈፀሙ ኪሣራ ለመጠየቅ በሚችልበት ጊዜ ሁለ እንደሆነ ይገልፃል።
ከዚህ ላላ በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 1892/1/ ላይ የተመለከተውም ሲታይ ባለገንዘቡ ኪሣራ ባይደረስበትም የተዋዋለው መቀጫ/ገደብ/ ሉከፈለው የሚገባ ስለመሆኑ የሚደነግግ ነው።
አመልካች ተጠሪዋ በውለ አለመፈፀም ምክንያት የደረሰባቸው ኪሣራ ስለላለ መቀጫ ሉከፈላቸው አይገባም በሚል ያቀረቡት ክርክርም ከፍሲል በተጠቀሰው ድግጋጌ መሰረት ተቀባይነት የሚሰጠው አይደለም።
በሕጉም መቀጫውን ለመቀነስ የሚያስችል ምክንያት አልተገኘም።
በመሆኑም የአሁኗ አመልካች በውላቸው የተወሰነውን መቀጫ /ገደብ/ ብር 50‚000 ለአሁኗ ተጠሪ እንዱከፍለ በመወሰኑ የሚታይበት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም።
በልላ በኩል ግን እንደ ውለ ባለመፈፀሙ በተወሰነው የቅጣት ገንዘብ ላይ ህጋዊ ወለድ ታስቦ እንዱከፈልበት የተወሰነው በሕጉ የሚደገፍ ሆኖ አልተገኘም። ከፍርደ በኋላም ቢሆን በመቀጫ ገንዘብ ላይ ህጋዊ ወለድ /9%/ ታስቦ እንዱከፈል መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ መታረም የሚገባው ነው።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 14189‚ በ22/10/2001‚ በመቀጫው ብር 50‚000 ላይ ወለድ 9% እንዱከፈልበት የወሰነው እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 84660‚ በ28/10/2002 ይህንኑ ያፀናበት ፍርድ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሻሽል የአሁኗ አመልካች የመቀጫውን ገንዘብ ብር 50‚000 ያለ ወለድ ለአሁኗ ተጠሪ እንዱከፍለ ተወስኗል።
በዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የደረሰውን ወጪና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
No topics extracted.