No summary available.
የካቲት 07 ቀን 2003 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ሳህለ ሙለጌታ - ጠበቃ ወንድም ጌታሁን ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የከፍተኛው ፍ/ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። በሥር ፍ/ቤት ተጠሪዎች ከሣሽ አመልካች ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል። የክርክሩ መነሻ ተጠሪዎች አመልካች ታህሣስ 19 ቀን 1999 ዓ.ም. በተጻፈ የሽያጭ ውል በአዱስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ቀበላ 11/12 የሚገኙ ቁጥራቸው 595 እና 596 የሆነ ቤቶች በብር 1,330,000 /አንድ ሚሉዮን ሦስት መቶ ሰላሳ ሺህ ብር/ ለመሸጥ ተስማምቶ ብር 206,000 /ሁለት መቶ ስድስት ሺህ ብር/ ቀብድ ተቀብሎል። ተከሣሽ /አመልካች/ የቤት ሽያጭ ውለን መሰረዙን በደብዲቤ የገለፀ ሲሆን እኛም በሽያጭ ውለ መሰረት ቤቱን እንዱያስረክበን ማስጠንቀቂያ ሰጥተነዋል። ተከሣሽ/አመልካች/ ቤቱን ተገድድ እንዱያስረክበን እንዱወስንልን ይህ ቢታለፍ በውለ የተቀመጠውን የገደብ መቀጫና የቀብደን ገንዘብ አጠፋታ አድርጎ እንዱመልስ ይወሰንልን በማለት ያቀረቡት ክስ ነው። አመልካች በተከሣሽነት ቀርቦ ከከሣሾች/ተጠሪዎች/ ጋር በሕጉ አግባብ ያደረግሁት የቤት ሽያጭ ውል የለም።
ተጠሪዎች/ከሣሾች/ ያቀረቡት ውል በውል አዋዋይ ፉት ወይም በፍ/ቤት መዝገብ ሹም ፉት ያልተደረገ በመሆኑ ከረቂቅነት አልፍ ሕጋዊ አስገዲጅነት የላለው በመሆኑ የከሣሾች/ተጠሪዎች/ ክስ ውድቅ እንዱደረግልኝ በማለት መልስ ሰጥቷል። የሥር ፍ/ቤት የግራ ቀኙን የቃልና የጽሐፍ ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ በከሣሾች/ተጠሪዎች/ እና በአመልካች/ተከሣሽ/ መካከል የቤት ሽያጭ ውል አለ ወይስ የለውም? ተከሣሽ/አመልካች/ የቤት ሽያጭ ውለን ተገድድ መፈፀም አለበት ወይስ የለበትም? የሚለትን ጭብጦችና ላላ ሦስተኛ ጭብጥ ከመሰረተ በኋላ በከሣሾችና/በተጠሪዎች/ና በአመልካች/ተከሣሽ/ መካከል ሕጋዊ አስገዲጅነት ያለውና የፀና የቤት ሽያጭ አለ በማለት ስለ ቀብድ የተደነገጉ የፍታብሓር ሕግ ድንጋጌዎችና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት የሰበር መዝገብ መሰረት በማድረግ ውሣኔ ሰጥቷል።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ ተከሣሽ/አመልካች/ የቤት ሽያጭ ውለን በፍርድ ተገዲድ ይፈፅም ከሣሾች/ተጠሪዎች/ ቀሪውን የቤቱን ዋጋ ይክፈለ በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቀርቧል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል። አመልካች ግንቦት 16 ቀን 1992 ዓ.ም.
በተጻፈ የሰበር አቤቱታ የሥር ፍ/ቤትና ይግባኝ ሰሚ ችልት በውል አዋዋይ ወይም በፍ/ቤት መዝገብ ሹም ፉት ያልተረገ ውል ሕጋዊ አስገዲጅነትና የፀና ውል ነው በማለት የሰጡት ውሣኔ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1723/1/ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በመዝገብ የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የሚጥስና መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት።
ከተጠሪዎች ጋር ያደረግሁት የቤት ሽያጭ ውል የለም እንጅ አለ ቢባል እንኳን ተጠሪዎች በውለ አደራረግ ወቅት የተለያዩ ተፅዕኖ ያደረጉ በመሆናቸውና ጉድለት የላለ በመሆኑ አላግባብ የገደብ መቀጮና ቀብደ አጠፋታ ሆኖ እንዱከፈል ያቀረቡት ጥያቄ ተገቢ አይደለም። የሥር ፍ/ቤት ውለ እንዱፈፀም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪዎች በበኩላቸው ጥር 4 ቀን 2003 ዓ.ም. በተጻፈ መልስ አመልካች ቤቶቹን አልሸጥኩም የሚል ክርክር አላቀረቡም። አመልካች የሽያጭ ውለን መኖሩን አምኖ በሚከራከርበት ሁኔታ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1723/1/ በመጥቀሱ ብቻ የውለ አስገዲጅነት እንደማይቀር የበታች ፍ/ቤቶች የሰጡት የሕግ ትርጉም የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰበር መዝገብ የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉምና የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1883 ድንጋጌን መሰረት ያደረገ በመሆኑ የአመልካች አቤቱታ ተገቢነት የለውም። የሽያጭ ውለን አመልካች እንዱፈፅሙ የበታች ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔም የሕግ ስህተት የለበትም። በሥር ስለ ቀብድና መቀጮ የተሰጠ ውሣኔ በላለበት ሁኔታ አመልካች የሰበር አቤቱታ ማቅረባቸው ተገቢ አይደለም በማለት መልስ ሰጥቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የጽሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል የፀና የቤት ሽያጭ ውል አለ ወይስ የለም? በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል የፀና የቤት ሽያጭ ውል አለ የሚባል ቢሆን የአመልካች ግዳታና ኃላፉነት ምንድን ነው? የሚለትን ጭብጦች መመርመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ ተጠሪዎች ከአመልካች ጋር ታህሣስ 19 ቀን 1999 ዓ.ም. በተጻፈ የቤት ሽያጭ ውል በየካ ክፍለ ከተማ ቀበላ 11/12 የቤት ቁጥር 595 እና የቤት ቁጥር 596 በብር 1,330,000 /አንድ ሚሉዮን ሦስት መቶ ሰላሳ ሺህ ብር/ እንደገዙና አመልካች ከቤቶቹ ዋጋ ብር 206,000 /ሁለት መቶ ስድስት ሺህ ብር/ ቀብድ እንደወሰደ ለሥር ፍ/ቤት ባቀረቡት የክሥ ማመልከቻ ገልጸዋል። አመልካች ተጠሪዎች በቀብድ መልክ ወስደዋል በማለት የገለፁትን ብር 206,000 /ሁለት መቶ ስድስት ሺህ ብር/ አልወሰድኩም በማለት በግልፅ ክደው ያልተከራከሩ መሆኑን የሥር ፍ/ቤት ከሰጠው ውሣኔ ለመገንዘብ ችለናል። ይህም አመልካች ከተጠሪዎች የቤት ሽያጭ ቀብድ ገንዘብ የተቀበለ መሆኑን እንዲመኑ እንደሚቆጠር በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 234 ንዐስ አንቀጽ 1/ሰ/ እና በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 235 ንዐስ አንቀጽ 2 ተደንግጓል። አመልካች የቤት ሽያጭ ውለን መነሻ በማድረግ ብር 206,000 /ሁለት መቶ ስድስት ሺህ ብር/ መቀበላቸውን በግልፅ ክደው ያልተከራከሩና ይህም የቀብድ ገንዘብ መቀበላቸውን እንዲመኑ ከላይ በተገለፁት የሕግ ድንጋጌዎች መሰረት የሚቆጠር ነው። አንደ ወገን ለአንደ ወገን ቀብድ መስጠቱ በማያከራክር ሁኔታ ውለ መደረጉን እንደሚያረጋግጥ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1883 በግልጽ ተደንግጓል። በሥር ክርክሩን አይቶ የወሰነው የከፍተኛ ፍ/ቤት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በመዝገብ የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም በተዛባ መንገድ በመረዲት ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን ለዚህ ጉዲይ ተፈፃሚ አድርጓል በማለት አመልካች ሰፉ ክርክር አቅርበዋል። በእኛ በኩል የሥር ፍ/ቤት ጉዲዩን የወሰነው በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል በጽሐፍ የተደረገውን የሽያጭ ውል ብቻ መሰረት በማድረግ ሆኖ አላገኘነውም። የሥር ፍ/ቤት በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል የፀና የቤት ሽያጭ ውል አለ ከሚል መደምደሚያ ላይ የደረሰው በመካከላቸው ተደርጓል የተባለውንና ይህንኑ ፍርም አላሟላም የሚል ክርክር በቀረበበት የጽሐፍ ውል ላይ ብቻ በመመራት እና በመመልከት ሣይሆን ተጠሪዎች ለአመልካች የቀብድ ገንዘብ የከፈለ መሆኑንና አመልካችም የቀብድ ገንዘቡን ከተጠሪዎች የተቀበለ መሆናቸውን ማመናቸው በሕግ በኩል ያለውን ውጤት በመመዘን ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካች የቀብድ ገንዘብ መቀበላቸውን ያልካደና የቀብድ ገንዘብ እንደተቀበለ የሚቆጠር በመሆኑና ይህም የቤት ሽያጭ ውለ መደረጉን በማያከራክር ሁኔታ እንደሚያረጋግጥ ፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1883 በግልጽ የተደነገገ መሆኑን አመልካች ውለን በተናጥል ያፈረሰ መሆኑን በመግለጽ ማስጠንቀቂያ የጻፈ መሆኑን ክድ ያልተከራከረ መሆኑን በማገናዘብ የሥር ፍ/ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሣኔ በዚህ መዝገብ ያለውን ልዩ ሁኔታ የቀብድ ገንዘብ ክፍያ የሽያጭ ውለ መኖሩን በማረጋገጥ በኩል የሚኖረውን የአስረጅነት ዋጋ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1883 የተደነገገውን መሰረት ያደረገና የሕግ ስህተት የላለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ የሥር ፍ/ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካች የቤት ሽያጭ ውለን እንዱፈጽም የሰጡት ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ነጥብ ሲሆን ይህንንም ለመወሰን በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል የተደረገውን የቤት ሽያጭ ውል መሰረታዊ ባህሪና አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎች መመርመር ያስፈልጋል። አመልካችና ተጠሪዎች ታህሣስ 19 ቀን 1999 ዓ.ም. ያደረጉት የቤት ሽያጭ ውል የቤቱ ሻጭ የተባለት አመልካችና የቤቱ ገዥ የሆኑት ተጠሪዎች ቀብድ የተቀባበለበት ውል መሆኑ በሽያጭ ውለ በግልፅ የተመለከተ መሆኑን ከሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ለመገንዘብ ችለናል። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች ከተጠሪዎች የቀብድ ገንዘብ የተቀበለ መሆኑን በማመን ተጠሪዎች የውል ግዳታቸውን ስላልተወጡ ውለን በተናጠል ያፈረሱ መሆኑን በመግለፅ ጥቅምት 22 ቀን 2001 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዲቤ ለተጠሪዎች አሳውቀዋል። አመልካችና ተጠሪዎች ባደረጉት የቤት ሽያጭ ውል ተጠሪዎች የከፈለትን ቀብድ በመልቀቅ ውለን የማፍረስ መብታቸውን ቀሪ ያደረጉ መሆኑና በተመሣሣይ ሁኔታ አመልካች የተቀበለትን የቀብድ ገንዘብ አጠፋታ በመክፈል ውለን የማፍረስ መብታቸውን ቀሪ ያደረጉ ስለመሆኑ በአመልካችም ሆነ በተጠሪዎች የቀረበ ማስረጃ እንደላለ ከሥር ፍ/ቤትና በሰበር ከተደረገው ክርክር ለመገንዘብ ችለናል።
በውላቸው ላላ ስምምነት ከላለ በቀር ቀብድ የተቀበለው ወገን የተቀበለውን ቀብድ አጠፋታ በመክፈል ውለታውን ማፍረስ እንደሚችል በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1885 ንዐስ አንቀጽ 2 በግልፅ ተደንግጓል። አመልካች ይህን የሕግ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ውለን የማፍረስ መብታቸውን ቀሪ የሚያደርግ ተቃራኒ ስምምነት ያደረጉ መሆኑን ተጠሪዎች እስካላስረደ ድረስ አመልካች በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1885 ንዐስ አንቀጽ 2 የተደነገገውን በማሟላት የሽያጭ ውለን የማፍረስ መብት አላቸው። ተጠሪዎች አመልካች የሽያጭ ውለን ለመፈፀም ፈቃደኛ ካልሆኑ በአማራጭ የቀብደን ገንዘብ አጠፋታ አድርገው እንዱከፍለ እንዱዋሰንላቸው ያቀረቡት ክስ አመልካች ቀብደን አጠፋታ በመክፈል ውለን የማፍረስ መብታቸውን ቀሪ የሚያደርግ ተቃራኒ ስምምነት ያላደረጉ መሆኑን የማያመላክት ነው። ስለሆነም የሥር ፍ/ቤትና የጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል የቀብድ ገንዘብ የተከፈለበት ውል በመሆኑ ውለን በማፍረስ በኩል አመልካችም ሆነ ተጠሪዎች ያላቸውን መብትና ውለን ሲያፈርስ በሕግ የተጣለባቸውን ግዳታና ኃላፉነት ከግንዛቤ ውስጥ ሣያስገቡ አመልካች ቤቶቹን ለተጠሪዎች እንዱያስረክቡና የሽያጭ ውለን እንዱፈፅሙ የሰጡት ውሣኔ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1885 ንዐስ አንቀጽ 2 የተደነገገውን የሚጥስና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ስለሆነም የከፍተኛው ፍ/ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች የቤት ሽያጭ ውለን እንዱፈጽምና ቤቶቹን እንዱያስረክብ የሰጡትን ውሣኔ በፍታብሓር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት በማሻሻል አመልካች ከተጠሪዎች የተቀበለውን ቀብድ ብር 206,000 /ሁለት መቶ ስድስት ሺህ ብር/ አጠፋታ አድርጎ ብር 412,000 /አራት መቶ አሥራ ሁለት ሺህ ብር/ ለተጠሪዎች በመክፈል የሽያጭ ውለን ማፍረስ ይችላል በማለት በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1885 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ወስነናል።
ው ሣ ኔ 3. የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሻሽሎል።
አመልካች ከተጠሪዎች የተቀበለውን የቀብድ ገንዘብ አጠፋታ ማለትም ብር 412,000 /አራት መቶ አሥራ ሁለት ሺህ ብር/ ለተጠሪዎች ይክፈል በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.