No summary available.
የካቲት ዐ9 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመሬት ልማትና አስተዲደር ቦርድ ጽ/ቤት ነ/ፈጅ ተስፊዬ ዘውዳ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ላቀች መንግሥቴ - ጠበቃ ዶ/ር ንዋይ ዘርጌ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡
**
ጉዲዩ ከሉዝ ውል አፈፃፀም ጋር የተያያዘ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ ተጠሪ በአሁኑ አመልካችና በላልች ሁለት የመንግሥት ተቋማት ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፤ በንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀበላ 13 ክልል ውስጥ የሚገኙ ቁጥራቸው 1ዐ55 እና 1ዐ56 የሆኑ ቤቶች ያረፈበትንና ስፊቱ 3139 ካ.ሜትር የሆነ ቦታ ከአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የካቲት 2ዐ ቀን 1992 ዓ.ም በተፈረመ የሉዝ ውል ቦታውን ወስደው በእለቱ የቦታ ይዞታ ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸው ቦታው በከፉልም ቢሆን በእጃቸው እንዲለ የሉዝ ውለ እንዱሰረዝ አቤቱታ ቀርቦበት ሉሰረዝ አይገባም ተብል ጥቅምት 18 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በሉዝ ቦርደ ውሣኔ ከተሰጠ በሁዋላ በመንግሥት ቤቶች እና በፍትህ ሚኒስቴር አመልካችነት የሉዝ ውለ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል እንዱሰረዝ ጥያቄው ለሉዝ ቦርድ ቀርቦ የካቲት ዐ5 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሉዝ ውለ እንዱሰረዝ ከሕግ ውጪ ቦርደ መወሰኑን ገልፀው በሉዝ ውለ የመጠቀም መብታቸው እንዱጠበቅላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው።
የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም የሉዝ ውለ ሉሰረዝ የቻለው በአዋጅ ቁጥር 2ዐ/1997፣ 34/2ዐዐዐ እና 272/1994 መሰረት መሆኑን ጠቅሶ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የማየት ስልጣን እንደላለው እና የዲኝነት ጥያቄውም ተቀባይነት የላለው መሆኑን ገልፆ ተከራክሯል። በስር ፍርድ ቤት እንደየቅደም ተከተላቸው ሁለተኛ እና ሶስተኛ ተከሣሽ የነበሩት የፍትህ ሚኒስቴርና የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ የሉዝ ውለ እንዱሰረዝ አቤቱታ ለማቅረብ በሕጉ አግባብ ሥልጣንና መብት ያላቸው መሆኑን ጠቅሰው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ የሉዝ ውለ ሉሰረዝ አይገባም ተብል ከተወሰነ በሁዋላ እንደገና ታይቶ መሰረዙ ከአዋጅ ቁጥር 2ዐ/1997 አንቀጽ 5/11/ ድንጋጌ ውጪ ነው፣ ተጠሪ በቦታው ላይ ግንባታውን ያላከናወኑት ቦታው ሙለ በሙለ ነፃ ሁኖ ሣይረከቡት በመቅረታቸው ከመሆኑም በላይ የሉዝ ውለ ሉፈፀም ይገባል ተብል በፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሣኔ አግኝቶ ባለበት ሁኔታ የሉዝ ውለ እንዱሰረዝ መደረጉ ያላግባብ መሆኑን በአዋጅ ቁጥር 272/1994 አንቀጽ 15/ለ/ መሰረትም የሉዝ ውለን ለመሰረዝ የሚያስችል የሕዝብ ጥቅም ስለመኖሩ ተረጋግጧል ለማለት አይቻልም የሚለትን ምክንያቶች በመያዝ ተጠሪ በሉዝ ውለ የመጠቀም መብታቸው ሉጠበቅላቸው ይገባል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሣኔ የአሁኑ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ሙለ በሙለ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነገረፈጅ መጋቢት 28 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በፃፈት ስምንት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። የሰበር አቤቱታው መሰረታዊ ይዘትም ባጭሩ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ የአዋጅ ቁጥር 34/2ዐዐዐ፣ 272/1994፣ 455/97፣ 555/2ዐዐዐ ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎችን ይዘትና መንፈስ እንዱሁም ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁጥር 276ዐ4 እና 46ዐ52 የሰጣቸውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉሞችን ያላገናዘበ በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም የሉዝ ውለ እንዱሰረዝ አመልካች መወሰኑ ተገቢነት የለውም ተብል በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰጠቱ ከአዋጅ ቁጥር 272/1994 እንዱሁም ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁጥር 276ዐ4 ከሰጠው የሕግ ትርጉም ጋር ተገቢነቱን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎአል። በዚህም መሰረት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ጥር ዐ5 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተፃፈ ሰባት ገጽ ማመልከቻ መልሣቸውን ሰጥተዋል። የመልሣቸው መሰረታዊ ይዘትም በጉዲዩ ላይ የተለያዩ ክርክሮች ቀርበውበት በፍርድ ቤት ውሣኔ ተጠሪ የሉዝ ውል መብት የተረጋገጠላቸው ከመሆኑም በላይ በዚህ በውለ ጊዜ ግንባታውን ያላከናወኑትም ቦታው ሙለ በሙለ ነፃ ሁኖ ባለመረከባቸው መክንያት በመሆኑና ይህም በፍርድ ቤት ውሣኔ ጭምር የተረጋገጠ መሆኑን፣ እንዱሁም አዋጅ ቁጥር 34/2ዐዐዐ ተብል የሚጠቀሰው ሕግም በሕግ አግባብ የታወጀ ስለመሆኑ የሚያመላክት ነገር በላለበት ሁኔታ የአመልካች እርምጃ በዚሁ አዋጅ መሰረት የተከናወነ ነው በማለት ክርክር መቅረቡ እውነት የላለው መሆኑን ጠቅሰው የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለውም ተብል ሉፀና ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው። የአመልካች ነገረፈጅም ጥር 23 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በፃፈት አራት ገጽ የመልስ መልስ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን አጠናክረው ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ ለበርካታ ጊዜያት በጉዲዩ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሥልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች በተሰጠው ውሣኔ የፍርድ ባለመብት የሆኑ ከመሆኑም በላይ የሉዝ ቦርደም ጉዲዩን ተመልክቶ የሉዝ ውለ ሉሰረዝ እንደማይገባ በቃለ ጉባዔ ቁጥር 6/2ዐዐዐ አረጋግጦ ከወሰነ በሁዋላ የካቲት ዐ5 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ የሉዝ ውለን ለሕዝብ ጥቅም ሲባል መሰረዙ አግባብ መሆኑን ገልፆ የቀድሞውን ውሣኔ ሽሮ ቦታው ለመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ እንዱሸጥ የወሰነ መሆኑን ነው። የአመልካች ነገረ ፈጅ የሉዝ ቦርደ የካቲት ዐ5 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠውን ውሣኔ ሕጋዊ ነው በማለት የሚከራከሩት አዋጅ ቁጥር 34/2ዐዐ0 ‛ን“ መሰረት ያደረገ ነው በማለት ነው። ይህ አዋጅ በሕጉ አግባብ የታወጀ አይደለም በማለት ተጠሪ ለአቀረቡት ክርክርም አዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ያልታወጀ መሆኑን በመልስ መልሣቸው ላይ የአመልካች ነገረፈጅ አምነው አዋጅ አለ ለማለት ይቻላል በማለት የሚከራከሩት ተፈፃሚነት ያለው ስለመሆኑ በአስተዲደሩ አፈ-ጉባዔ ጽ/ቤት ለሚመለከታቸው አካላት በደብዲቤ ተልኳል፤ ተገልጿል የአስተዲደሩ የሕግ አወጣጥ ስርዓትም ለየት ያለ ነው በማለት ነው። ይህ ችልትም አለ የተባለውን አዋጅ ኮፑውን አስቀርቦ የተመለከተ ሲሆን የአመልካች ነገረ ፈጅ እንደአረጋገጡት በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ የወጣ ስለመሆኑ የሚያሣይ ነገር የላለው መሆኑን ተገንዝቧል። በአዋጅ ቁጥር 2ዐ/1997 አንቀጽ 5/11/ መሰረት ቦርደ በሉዝ ውል ጉዲይ ላይ በሚሰጠው ውሣኔ የሚነሣ ቅሬታን መርምሮ ተገቢነት ካለው ውሣኔውን ለአንድ ጊዜ ብቻ ማሻሻል እንደሚችል በግልጽ የተደነገገ ሲሆን በተያዘው ጉዲይ በቃለ ጉባዔ ቁጥር 6/2ዐዐዐ በቀድሞው ውሣኔ ላይ የቀረበውን ቅሬታ መርምሮ የቀድሞውን ውሣኔ መሻሻል እንደላለበት የወሰነ ሲሆን የካቲት ዐ5 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ተሰጠ የተባለው የሉዝ ውልን የሚሰርዝ ውሣኔ አዋጅ ቁጥር 2ዐ/1997 አንቀጽ 5/11/ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ የሚሰርዝ በሕጉ የወጣ አዋጅ በላለበት ሁኔታ ነው። አዋጁ ቁጥር 34/2ዐዐዐ ተብል የሚጠቀሰው ሰነድ በሕጉ አግባብ የወጣና ተፈፃሚነት ያለው ስለመሆኑ ያልተረጋገጠ ሲሆን አዋጁ በስራ ላይ ውሎል ቢባል እንኳ የሉዝ ውለ ሉሰረዝ አይገባም ተብል ውሣኔ ከተሰጠ በሁዋላ በድጋሚ የሉዝ ውለ ይሰረዝልኝ ጥያቄ ቀርቦ ውለ እንዱሰረዝ የተሰጠው ውሣኔ አዋጁ ተፈፃሚነት አለው ከተባለበት ከአንድ ቀን በሁዋላ መሆኑ ከውለ አፈፃፀም ሁኔታ ጋር ያለው ተገቢነቱ ላታይ የሚገባው ነው። ተጠሪ በሉዝ ውለ መሰረት ቦታውን ሙለ በሙለ እንዱረከቡ ይወሰንላቸው ዘንድ ጥያቄ አቅርበው ከስር ፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እስከ ፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቦታውን እንዱረከቡ ውሣኔ ተሰጥቷቸው በጉዲዩ ላይ የፍርድ ባለመብት በመሆን በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ የአፈፃፀም ጥያቄው አቅርበው ያልተፈፀመላቸው መሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መረጋገጡ ተጠሪ በሉዝ ውለ መሰረት በአንድ ዓመት ከስድስት ወር የጊዜ ገደብ ሕንፃውን የመገንባት ግዳታቸውን ያልተወጡት በራሣቸው ችግር ነው ለማለት የሚያስችል ምክንያት አለመኖሩን የሚያሣይ ነው። ላላው የአመልካች ነገረፈጅ አጥብቆ የሚከራከሩት የሉዝ ውለ በአዋጅ ቁጥር 272/1994 አንቀጽ 15 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት የሉዝ ውለን የመሰረዝ ስልጣን የአስተደደር አካል የሆነው የሉዝ ቦርድ ነው፣ ፍርድ ቤቶች ሉመለከቱ አይገባም በማለት ነው። በመሰረቱ ማንኛውም ሰው በፍርድ ሉወስን የሚገባውን ጉዲይ ለፍርድ ቤት ወይም ለላላ በሕግ የዲኝነት ሥልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሣኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ የኢ.ፋዱ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 37/1/ ድንጋጌ በግልጽ የሚያሣየው ጉዲይ ነው፡ ከዚሁ የሕገ መንግሥት ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው ደግሞ ፍርድ ቤቶች አንድ ጉዲይ /አቤቱታ/ ተቀብለው ውሣኔ መስጠት የሚችለት ዲኝነት የተጠየቀበት ጉዲይ በሕግ ለላላ አካል ያልተሰጠ ጉዲይ /አቤቱታ/ ተቀብለው ውሣኔ መስጠት የሚችለት ዲኝነት የተጠየቀበት ጉዲይ በሕግ ለላላ አካል ያልተሰጠ ጉዲይ በሚሆንበት ጊዜ እንደሆነ መሆኑን ነው።
በሕግ ተለይተው በአስተዲደራዊ ውሣኔ እንዱቋጩ በተባለ ጉዲዮች ላይ መደበኛ ፍርድ ቤት የመዲኘት የስረ ነገር ሥልጣን ስለላለው በሕጉ መሰረት ለአንድ አስተዲደር አካል ቀርቦ አስተዲደራዊ ውሣኔ የተሰጠበትን ጉዲይ ወይም ለአስተዲደር መቅረብ የሚገባውን ጉዲይ ፍርድ ቤት ሉያስተናግደውም ሆነ አከራክሮ ውሣኔ ላሰጥበት አይችልም። ለአንድ የመንግሥት አካል በተወሰኑ ጉዲዮች ላይ የመወሰን ስልጣን የሚሰጡት ሕጎች መጠበቅና መከበር ያለባቸው ሲሆን የዲኝነት አካል ስልጣንም በሕግ የተወሰነ ስለሆነ ሕግ የተመርጎም ስራው በሕጉ በተመለከተው አድማስ የሚመራ ይሆናል። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 4 ድንጋጌ የሚያሣየውም ፍርድ ቤቶች በልላ ሕግ በግለጽ በታገደ ጉዲዮች ላይ አከራክሮ የመወሰን ስልጣን የላላቸው መሆኑን ነው። በመሆኑም በአስተዲደራዊ ውሣኔ የመጨረሻ እልባት እንዱያገኙ በሕግ ተለየተው የተቀመጡ ጉዲዮችን ፍርድ ቤቶች የመዲኘት ስልጣን የላላቸው መሆኑ ሉስተዋል የሚገባው ጉዲይ ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ /ክርክር/ መሰረት ያደረገው ከአመልካች ጋር ባደረጉት የሉዝ ውል የተሰጠውን ቦታ የሉዝ ውለ ከውለ አፈፃፀም መሰረታዊ ባህርያትና ከሕግ ውጪ ተሰርዞ ቦታው ለመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ እንዱሰጥ መደረጉ ያላግባብ ነው የሚል ነው። አዋጅ ቁጥር 272/1994 የሉዝ ቦታ የሚሰጥበትና ውለ የሚቋረጥበትን አግባብ ዘርግቷል። የአዋጁ አንቀጽ 15፣16 እና 17 ድንጋጌዎች ሲታዩ የሉዝ ውል የሚቋረጥበትንና ካሣ የሚከፈልበትን አግባብ፣ ጉዲዩን ሉመለከቱ የሚችለ ወገኖችንና የይግባኝ አቀራረብን ሥርዓት ደንግገው እናገኛለን።
በተያዘው ጉዲይ የሉዝ ውል እንዱቋረጥ ተደርጓል የሚባለው ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ነው በሚል ምክንያት በመሆኑ ለጉዲዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት ያላቸው የአዋጅ ቁጥር 272/94 ድንጋጌዎች አንቀጽ 15/1/ለ/ እና 16 ናቸው። የአንቀጽ 15/1ለ/ ድንጋጌ የከተማ ቦታ የሉዝ ይዞታ ቦታው ለሕዝብ ጥቅም ተብል ለላላ ስራ ወይም አገልግልት እንዱውል ሲወሰን ሉቋረጥ እንደሚችል የተመለከተ ሲሆን በአንቀጽ 16/1/ ደግሞ አግባብ ያለው አካል ለሕዝብ ጥቅም ይውላል ተብል በሚወስነው መሰረት ለሚመለከተው አካል የማስለቀቂያ ትእዛዝ ወይም ማስጠንቀቂያ በጽሐፍ በመስጠት የሚገለገለውን የከተማ ቦታ ማስለቀቅና መረከብ እንደሚችል አስቀምጧል። የአዋጁ አንቀጽ 17/1/ ድንጋጌ ሲታይም በአንቀጽ 16 መሰረት የማስለቀቅ ትእዛዝ የደረሰው ወይም ትእዛዝ በተሰጠበት ንብረት ላይ መብት ወይም ጥቅም አለኝ የሚል ወገን የካሣም ሆነ ማንኛውንም ለፍርድ ላቀርብ የሚገባው ላላ አቤቱታ ከዝርዝር ምክንያቱ እና ማስረጃው ጋር ትእዛዙን ለሰጠው አካል የማቅረብ መብት አንዲለው ያስገነዝባል። በዚህ መልኩ ቀርቦ የታየ ጉዲይም በአንቀጽ ንዐስ ቁጥር ሁለት ስር የተመለከተውን ተገቢ ዲኝነት የሚሰጥበት ሲሆን በውሣኔው የማይስማማ ሰው ለጉባዔው ይግባኙን ማቅረብ እንደሚችል በአንቀጽ 18/1/ ስር ተደንግጎ ያለ ከመሆኑም በላይ ይህ አካል የሚሰጠው ውሣኔ ካሣ አነሰኝ ወይም ካሣ በዛብኝ ወይም ካሣ ተከለከልኩ በሚል ክርክሮች ላይ ካልሆነ በስተቀር በሕግም ሆነ በፍሬ ነገሮች ላይ የመጨረሻ ውሣኔ ስለመሆኑ የጠቀሰው አንቀጽ ንዐስ ቁጥር ሦስት ድንጋጌ ያሣያል። ከዚህ ሁለ መገንዘብ የሚቻለው በሉዝ የተሰጠ ቦታን የሚመለከተው አካል ማስለቀቅ የሚችለውና ጉዲዩ ላይ ጉባዔው የሚሰጠው ውሣኔ የመጨረሻ እና በፍርድ ቤት ላቀርብ የማይገባው ቀድሞ የቦታ ማስለቀቁ እርምጃ የተወሰደው ለሕዝብ ጥቅም ተብል ሲረጋገጥ ስለመሆኑ ነው። አዋጅ ቁጥር 272/94 አንቀጽ 2/7/ ስለሕዝብ ጥቅም ትርጉም አስቀምጧል። በዚህም መሰረት የሕዝብ ጥቅም ማለት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ሕዝቦች በመሬት ላይ ያላቸውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና የከተማ ልማትን በቀጣይነት ለማጎልበት አግባብ ያለው አካል በመሪ ፔላን ወይም በልማት እቅድ የሕዝብ ጥቅም ብል የሚወስነው ነው በሚል ትርጓሜ የተቀመጠ ሲሆን አዋጅ ቁጥር 455/97ም ተመሣሣይ ይዘት ያለውን ትርጉም በአንቀጽ 2/5/ ስር ይዞ እናገኛለን።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች ጉዲዩ ከሕዝብ ጥቅም ጋር የተገናኘ ነው በሚል ያቀረበው ክርክር በበታች ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ያላገኘው የሉዝ ውለ የተሰረዘበት መንገድ ሕጉ ከደነገገው ስርዓት ውጪ ነው ከሚል ምክንያት በተጨማሪ ቀድሞውንም ቢሆን የሉዝ ውለ የሚሰርዝበት ምክንያት የለውም ተብል በመወሰኑ፣ በአዋጅ ቁጥር 555/2ዐዐ0 ስር ለመንግሥት ቤቶች የተሰጠው ስልጣንም ጉዲዩን የማይማለከተው መሆኑን፣ በአዋጅ ቁጥር 471/1998 መሰረት ለፍትህ ሚ/ር የተሰጠው ስልጣንም ለሕዝብ ጥቅም ሲባል አቤቱታ ማቅረብ የሚችል መሆኑን ቢያሣይም በተያዘው ጉዲይ ግን ከሕግ የበላይነት መርህ ጋር በሚጋጭ መልኩ የፍርድ ቤትን ውሣኔ ውጤት ሉያሣጣ የሚችል ሁኖ ተገኝቷል በሚለት ምክንያቶች መሆኑን ከመዝገቡ ተመልክተናል። ከላይ እንደተመለከተውም ተጠሪ በተለያዩ የክርክር መስመሮችና ደረጃዎች በሕጉ አግባብ በተቋቋመ የሉዝ ውል የቦታው ሕጋዊ ባለይዞታ መሆናቸው ተረጋግጦላቸዋል። ስለሆነም የፍርድ ቤት ውሣኔ ስለአለ ብቻ ለሕዝብ ጥቅም ተብል ንብረት አይወስድም ለማለት የማይቻል ቢሆንም ከተያዘው ጉዲይ ልዩ ባሕርይ አንፃር ሲታይ ግን የአመልካች እርምጃ ለሕዝብ ጥቅም ተብል የተወሰደ ነው ለማለት የሚያስችል ምክንያት የላለው ሁኖ አግኝተናል።
ላላው የአመልካች ነገረፈጅ አጥብቀው የሚከራከሩትና ሰበር ችልቱ እንዱመለከተው የተያዘው ጭብጥ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ይህ ሰበር ችልት በመ/ቁጥር 276ዐ4 ከሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ጋር ስላለው ተገቢነት የሚመለከት ነው። በሰ/መ/ቁጥር 276ዐ4 የተሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የቦታ ምስክር ወረቀት ይሰጠኝ ጥያቄን በሚመለከት የተነሣን ክርክር መሰረት ያደረገ ሲሆን በችልቱ የተሰጠው ትርጉምም እንዱህ አይነት የቦታ ወይም ይዞታ ይሰጠኝ ጥያቄዎችን በመቀበል እየመረመረ ለቦታ ጥያቄዎች ቦታ የመመደብ፣ የይዞታ ምስክር ወረቀት የመስጠት የከተማው አስተዲደር ተግባርና ኃላፉነት እንጂ በፍርድ የሚያልቅ ጉዲይ አይደለም የሚል ነው። በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ ክስ የመሰረቱት ከሉዝ ውል አፈፃፀም ጋር የተያያዘ እንጂ የቦታ ወይም የይዞታ ይሰጠኝ ጥያቄ አይደለም። ስለሆነም የተጠሪ የዲኝነት ጥያቄና የአመልካች ክርክር በመ/ቁጥር 276ዐ4 በተያዘው ጉዲይ ካለው ፍሬ ነገር እና የሕግ ክርክር ሙለ በሙለ ግንኙነት አለው ልባል የሚችል አይደለም። ምክንያቱም የተጠሪ ክስ መሰረቱ የሉዝ ውል ሆኖ ውለ ተጥሷል በሚል ዲኝነት የጠየቁ ስለመሆኑ የሚያሣይ ነውና። ላላው የአመልካች ነገረፈጅ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁጥር 46ዐ52 የሰጠው የሕግ ትርጉም ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር ሲታይም የሉዝ ውለን ከከተማው አስተዲደር ጋር አደረጉ የተባለት ግለሰብ ቦታውን ሙለ በሙለ ተረክበው በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ግንባታውን ባለማከናወናቸው የሉዝ ውለ የተሰረዘ ስለመሆኑ ስለሚያሣይ ሲሆን አሁን በእጃችን ባለው ጉዲይ ግን መሰረታዊ ክርክሩ የሉዝ ውለ ያላግባብ ተሰርዟል የሚል ቢሆንም ቦታውን ተጠሪ በከፉል በመረከባቸው ምክንያት በገቡት ግዳታ መሰረት ግንባታውን ሉያከናውኑ ያልቻለ መሆኑ በፍርድ ቤት ውሣኔ ጭምር የተረጋገጠ በመሆኑ በመ/ቁጥር 46ዐ52 ከተያዘውና የሉዝ ውለን ከከተማው አስተዲደር ጋር አደረጉ የተባለት ግለሰብ ቦታውን ሙለ በሙለ ተረክበው በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ግንባታውን ባለማከናወናቸው የሉዝ ውለ የተሰረዘ ስለመሆኑ ከሚያሣይ ውሣኔ ጋር በፍሬ ነገር ደረጃ ጉልሕ ልዩነት ያለበት በመሆኑ የመ/ቁጥር 46ዐ52 አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ነው ተብል ለዚህ ጉዲይ በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2/4/ መሰረት የሚጠቀስበት አግባብ የለም። በመሆኑም በዚህ ረገድ የቀረበው የአመልካች ክርክር ተቀባይነት ያለው ሁኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለልም የተጠሪ ጥያቄ የአዱስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዲደር ቦርድ ጽ/ቤት በሉዝ የተወሰደ ቦታን ከሕግ ውጪ የሉዝ የምስክር ወረቀትን በመሰረዝ ሕገ ወጥ እርምጃ ወስዶል በማለት በዚህ ውል ያገኙት የንብረት መብታቸው /የኢ.ፋ.ዱሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 4ዐ/6 ይመለከቷል/ በፍርድ እንዱጠበቅላቸው የሚጠይቅ በመሆኑ በፍርድ ቤት ሉስተናገድ የሚገባው እና ውሣኔ የሚሰጥበት ጉዲይ ሁኖ ክርክሩ ሲጀመር የክርክሩ ተሣታፉ ከነበሩት አካላት ማንነት አንፃር ጉዲዩ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች መቅረቡም ሆኖ የአመልካች ክርክር ውድቅ ሁኖ ተጠሪ በሉዝ ውለ የመጠቀም መብታቸው እንዱጠበቅ በማለት የተሰጠው ውሣኔ ከአዋጅ ቁጥር 272/94፣ 2ዐ/1997፣ 555/2ዐዐዐ፣ ከአዋጅ ቁጥር 471/1998 ድንጋጌዎች እንዱሁም ከውል አፈፃፀም መሰረታዊ መርሆዎች ጋር ተዛምድ ሲታይ ሕጋዊ ሁኖ አግኝተናል። በዚህ ምክንያት በውሣኔው ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ባለመኖሩ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ 1/ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 66717 ጥር 27 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር ዐ7 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
2/ በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.